የግጥም ጥግ
770 subscribers
56 photos
2 videos
7 files
39 links
ያ ዶሮዬ ጮኈ መንጋቱን ነገረኝ፥
ሲነጋጋ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ።

የተለያዩ ምርጥ ግጥሞችን እዚህ

ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት

@Esamif
@amen1995 መጠየቅና መስጠት ይችላሉ።
Download Telegram

ከእለታት ባንዱ ሀሳብ
‎ያልመንህ ነገር ውጦት
ምስኪን ልቡን ያሸፈተ
‎እንደ ተራ ቀላል ነገር
‎እልህ መንገድ ሲጠርግለት
‎ የጥል በሩን የከፈተ

ወይም ወይም ........
‎ከእለታት ሌላው ሲያዝን
‎ግድየለቱን በሳቅ ሞልቶ
በንቀቱ የተመካ
‎ከራስ በላይ ንፋስ ባዩ
‎ያልሞላለት ባዶነቱን
አለኝ በሚል ቃል የለካ

‎ንፉግ ሆኖ እንደ ለጋስ
‎ጥሩ መስሎ ግፍ የሆነ
‎ለሰው ቀርቶ ለሱነቱ
‎ታምኖም እንኳን ያልታመነ

‎የጭልምቱን ጓዳ ሲሞቅ
‎በድን ገላን ተሸክሞ
የቁም ሞቱን የሚያፋጥን
‎አጉል ጥጋብ ልቡን አንቆት
‎ የጠፋበት የሀቅ ውጥን

‎ደረት ነፍቶ የሚያቅራራ
በአጉል አልህ የተኳለ
‎ስድ አመሉን ተከናንቦ
‎መሀላችን ድንገት ካለ

‎የወጠረው ተንፍሶለት
‎በልብነት አደብ ገዝቶ
ቅን እሳቤን እስኪቀበል
‎መንገድ ሁሉ ጨርቅ ሆኖለት
‎በእንቅፋት ሳይናጋ
በመጣበት ጥርግ ይበል!

Mekdi
@getmtg
@getmtg
4👍2💯1
😁(18+)

።።።።አንቀፀ ንሰሐ።።።።

ይኸው ልናዘዘው የክፋት ልፋፌን፣
ከፊትሽ ልቅደደው የበደል እራፌን፣
ኑዛዜ ቢያጠዳው የክህደት እድፌን፣

አንቺን የቀረብሁሽ ለአልጋ መአዱ፣
በሰው ስለቀናሁ ከሴት ጋር ....

ልጠቀምብሽ ነው ጎጆ የምወጣ፣
ብዙ ጥሪት አለሽ 'ካባትሽ የመጣ፣

ልሞላብሽ አሰብሁ ባዶ ጉሮሮዬን፣
ልከብርብሽ ነበር ላስውበው ጓሮዬን፣

ከሰው ላለማነስ አንቺን አገባሁሽ፣
'ካምሮቴ እንዳልጎል አንቺን አረከስሁሽ፣

እርግጥ ነው አልክድም ሌላም ሴት አምሮኛል፣
ልክስክስ አመሌ ለእህትሽ ድሮኛል፣

ይሄ ሁሉ ሲሆን ይህ ሁሉ ሲወድም፣
ያንቺ ቀና ልብሽ እኔኑ ቢወድም፣

ሌላ ባያሰኝሽ ክፋቴ ባይገፋሽ ፣
ልቀጥል አልችልም በደሌን በጭራሽ፣

እናም አሰናብቺኝ ከማዕሰረ ግፌ፣
ይቅርታሽን ላንባ በሬን ተደግፌ።

✍️Zemed

@getmtg
@getmtg
3😭2🔥1👏1

ለእግዜር የተላከ ደብዳቤ
(አሌክስ አብርሃም)

እንደምነህ እግዜር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው
እኛማ ......
ለእልፍ አእላፍ ጠበቃ
ማመልከቻ ፅፈን
ለወፈ ሰማይ ህዝብ
መድረክ ላይ ለፍፈን
ፀሎት ቤታችንን እኛው ላይ ቆልፈን
የምድር አተካራ ህግጋቱን አልፈን
ደብዳቤ ላክንልህ .......

አይንህን ካየነው
ሁለት ሺህ ዘመን እንደቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ዘመን
እየኮሰመነ መቅረትህ ገዘፈ
እንደውም እንደውም
በእመጣለሁ ተስፋ
ሁለት ሺህ ዘመን ገትሮን ከጠፋ
በቀጠሮ ሰአት መምጣት ከተሳነው
....... እግዜር ሀበሻ ነው
እያሉ ያሙሃል

እኔ ምን አውቃለሁ ....
አመስግነው ሲሉኝ እልልታ የማቀልጥ
ቃሉን ስማ ሱሉኝ
ሰባኪው እግር ስር በደስታ 'ምቀመጥ
እግዚኦ በል ሲሉኝ እንባዮን የማፈስ
ሃሌሉያ ሲሉኝ በሳቅ ልቤ 'ሚፈስ
ምናምንቴ እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ
እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ
.... እኔ ምን አውቃለሁ ....

ግን አንተ ደህና ነህ .....
ከምር እንደሚያሙት ምፅአት ቀረ እንዴ
የስናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ
አትከፋም አንዳንዴ?

ከሆነስ ሆነና
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
አብረሃም ሰላም ነው?
እዛስ ቤት ገነባ
ዛሬስ በድንኳን ነው?

እኛማ ይኸውልህ
በቤት ኪራይ ችንካር እየተሰቀልን
ኤሎሄ እንላለን ዳቦ እንድትጥልልን
ወደ ላይ ገነባን
ወደ ጎን አሰፋን
ወደላይም ከላይ ወደ ግንም ከጎን
እንደ ጉድ ተገፋን
ቤት ለእንግዳ ማለት ጭራሹኑ ጠፋን

አባታችን ሙሴ እንዴት ነው ለክብሩ
ውቅያኖስ መግፊያው ደህና ናት በትሩ
እኛማ ይኸውልህ
እንጀራ ፍለጋ ባህር ስናቋስጥ
የተስፋዋን ምድር አሸዋ ሳንረግጥ
የትም ውሃ በላን የትም አሳ ላሰን
ንገርልንና በትሩን ያውሰን

እናልህ እግዜር ሆይ
ከተስፋዋ ምድር
ወደሌላ ተስፋ አለን እየኳተን
መሄጃው ሲገርመን
መመለሻው መንገድ መቆሚያ ቦታ አጥተን

ለአባታችን ሙሴ እንደምትልልን
የመሄድ ዘመን ነው
ባህር የመሻገር ዱላህን ላክልን
....... ብሎሃል በልልኝ

ሰማይ ቤት እንዴት ነው
ዳዊትስ ደህና ነው?
ዛሬም ይዘምራል
ዛሬም ይፎክራል
ሰላም ነው ጠጠሩ ሰላም ናት ወንጭፉ
እዛስ አቅል ገዛ
ጎልያድ ተራራው ጎልያድ ግዙፉ

እልፍ አእላፍ ጎልያድ
ከቦን ሲደነፋ
ወንጭፉን ጠቅልሎ
ምነው ዳዊት ጠፋ

ብሎሃል በልልኝ
ለረከሰ ጠጠር ለሞላ ወርዋሪ
ወንጭፍህን ስጠው
ለዚህ ታሪክ አውሪ
ብለህ እዘዝልን

እንዴት ነህ ጌታ ሆይ
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
የሙሴ አልጋ ወራሽ
እያሱስ ሰላም ነው?
ያቆማትን ፀሀይ ግቢ ቢላት ምነው
አንተ እንደምታውቀው
እስራ ሶስት ወራት ነው
ፀሀይ የምንሞቀው

አረ ፀሀይ በዛ
አረ ፀሀይ በዛ
የመጣው ወር ሁሉ ፀሀይ እየዘለ
የተሾመው ሁሉ ፀሀይ ነኝ እያለ
የአስራ ሶስት ወር የእግዜር ፀሀይ
የአስራ ስስት ወር የእግዜር ጀንበር
ባቃጠላት ምድጃ ሀገር
ምን ተአምር ሊኖር ይችላል
ፀሀይ ሆኖ እንደመፈጠር

አረ እግዜር በእናትህ በጭንቅ አማላጇ
ባዘለ ጀርባዋ ባቀፉት እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሆነህ ና
...... ሙቀት ገደለና

እናልህ ጌታ ሆይ ማጣፊያው አጥሮናል
ስም ያለው ሞኝ ነው ሁሉም ይጠራናል
ጳውሎስ ሲሉን አቤት
ጴጥሮስ ሲሉን ወዬ
ይሁዳ ሲሉንም አቤት እንላለን
ስማችንን ሸጠን
ሰላሳ ጭብጨባ እንቀበላለን

ተወው የእኛን ነገር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
ሄዋንስ ደህና ናት?
ያው የልጅ ልጆቿ በእግሯ ተተክተው
የፍሬው ሲገርመን ግንዱንም አንክተው
ለፍጥረተ አዳም ባይኑ ይገምጡታል
ሴጣንም ደህና ነው ኑሮ ተስማምቶታል
ሰውን ለማሳሳት ላይ ታች ማለት ትቷል
ሳይጠራው የሚጎርፍ ህዝብ በዝቶለታል

አረ እግዜር በእናትህ በጭንቅ አማላጇ
ባዘለ ጀርባዋ ባቀፉት እጆቿ   
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሆነህ ና
               ...... ሙቀት ገደለና

@getmtg
@getmtg
8👏1

ያምር ነበር እሱነቱ
‎ቅን እሳቤው ያኖር ነበር
‎ ቀን መሻቱን ባያላላው
‎ደረስኩኝ ሲል ስኬት ደጃፍ
‎አለፍኩ ሲል ኑሮ ክሱን
‎ የድንገቱን ውሃ በላው

‎ወትሮ ጎኑ የነበረ
‎እንደልቡ እየተራጨ
‎ ክንዱን ሰዶ ያደገበት
‎የዛሬን ግን ምነው ከዳው?
‎ና ልንገርህ ብሎ ጠርቶ
‎ ነፍሱን ስቦ ወሰደበት

‎ሂድ እንዳለው ታቹን ሄደ
‎ ላዩን ሰማይ እየራቀው
‎ትጉ አይኖቹ ደርቀው ቀሩ
‎ ከመንገዱ ሞት አነቀው

‎(መታሰቢያነቱ ለማላውቀው በድንገት ለተለየን ወንድማችን ይሁንልኝ፡፡)

Mekdi
@getmtg
@getmtg
😭62👏1
. 👆👆👆👆👆👆
ሁላችንም ማንበብ ያለብን መፅሀፍ!

@getmtg
@getmtg
💯32

ስታየኝ
ስታየኝ!
      ሰውነቴ ትርክክ
      ጉልበቴ ብርክ ብርክ
      ልቤ ድንብርብርብር
      ሆዴ ሽብር ሽብር
      አይኔ መሬት ስብር
      ሀሞቴ ፍስስስ
      ሀሳቤም ትርምስምስ
      ቆዳዬ ልውጥውጥ
      እሷን እያሰብኩ ከፍቅር አለም ጭልጥ።
ስታየኝ!
       እኔነቴን እርስት
       አዲስ ሆኜ ክስት
       በአዲስ አለም ውስጥ
       ያለመጠን ምስጥ
       ክንፍ አውጥቼ ብርር
       ሳይገድበኝ ድንበር
       አድማስን ስሻገር
       ከአድማስ በስተጀርባ
       ሰማይ ቤት ስገባ
       ከሰማይ ከፍ ስል
       ሰማየ ሰማያት ወስዶ የሚከተኝ
       በነዛ ውብ አይኖች ያቺ ልጅ ስታየኝ።
አይኖቿ ተአምር
ልብን የሚሰውር
ራስን የሚያስረሳ
ቀልብን የሚነሳ
ፍቅርን አስይዞ
ወደ ሰማይ ጉዞ
ወደ አዲስ አለም
ሳይተኙ በማለም።
                  
Abosina
@getmtg
@getmtg
👏73

‎"እንደው አንቺን ሳጣ
‎ሰላሜ ተለየኝ ልልሽ አሰብኩና
‎ ደግሞም ትዝ ሲለኝ
‎አልተለየሽኝም
‎ከእኔው ጋር ነው ያለሽ
‎ እንዲህም አልኩና
‎ ሀሳቤን ቀየርኩኝ ........
‎፡
‎ልክ እንደ ውሃ ጥም
‎ደግሞ ናፍቀሽኛል ለማለት አስቤ
‎ተውኩት 'ረሳሁት
‎ጥሜን ልቆርጥበት ውሃውን አቅርቤ
‎፡
‎እንዲህ ብዬ ነበር
‎ደግሞ ካንቺ ሌላ የቱንስ ሀብት አለኝ
‎ ( ያው እንደ ልማዴ)
‎ዛሬም አላጣሁሽ
‎ምን ምክንያት ሊኖር
‎ እንዲህ የሚያስብለኝ
‎፡
‎ደግሞም አንድ 'ለታ
‎ሳስብሽ ደስ አለኝ ከድሮ ሳቄ አለሽ
‎ያው እንደነገሩ
‎ አሁን ሕይወቴ ነሽ
‎........ ብዬ እንዳላሞገስኩ
‎ካንቺው ላንቺው ሆኖ
‎ ይህን አልኩ የምለው
‎የውስጤን ልነግርሽ
‎ እንዲህ የምሆነው

‎ ለምን ይሆን?"

‎ (የሚልም ሰው አለ😊)

Mekdi
@getmtg
@getmtg
4😁3

ኬሬዳሽ

እኔ ስለ እሷ
እኔ ስለ እሷ
ሁሌም አስባለሁ ሁሌ እጨነቃለሁ
በነጋ በጠባ
ውሎና አዳሯን አረጋግጣለሁ

     ምን በላች ምን ጠጣች
         በምን ተደሰተች
በምንስ ተከፋች

   በምን ተቸገረች
ምን እጅስ አጠራት
   እጆቼን ቆርጬ እንድተባበራት

አሁን አሁንማ ከሷም አለፍ ብዬ
ስለቤተሰቧ
ስለእህት ወንድሟ ስለእማ አባብዬ
እጠይቃታለሁ እንዴት ሆኑ ብዬ

እሷ ግን ስለእኔ
እሷ ግን ስለእኔ ከቶ ግድ የላትም
ታሟል እንኳን ቢሏት
ምንም አይመስላትም

           አይሞቃት አይበርዳት
እኔን ችላ ማለት በፍጹም አይከብዳት

በቃ በጥቅሉ ሆናለች ኬሬዳሽ
ማፍቀሬ ማይገባት
የመውደድ ግዴለሽ፡፡

Abosina
@getmtg
@getmtg
👏43👍1

ከ80 በላይ
አለም ባዶ ሆና እኔና አንቺ ብቻ
ማንም በሌለበት ቀርበን ለጋብቻ
ሱፍ ቬሎ ሳናደርግ ሰርግም ሳይሰረግ
ሚዜ አጃቢ ሳይኖር
ቀለበት ሳንገዛ ምንም ሳይደረግ
                                   
ሱፌ ያንቺ ፍቅር ቬሎሽ ፍቅሬ ሆኖ
ሰርጋችን ዘላለም ማይኖር ተወስኖ                                 
                                
አጃቢ ከዋክብት
ሚዜዎች ብርሃናት ፀሐይም ጨረቃ
ሰማይ ድንኳናችን ለሁሉ የሚበቃ                                             
                                        
እንግዶች ፍጥረታት ሰው ያልተገኘበት
ሰው እኔና አንቺ ብቻ ሆነን ያለንበት።

ፍቅር ቀለበት ነው በልብ የሚታሰር
ወልቆ የማይጠፋ ወድቆ የማይሰበር
እግዜር የነገር አባት እኛን ያጣመረን
ሁለት አርጎ ፈጥሮ
አንድ አርጎ የሚያኖረን
                                       
ውል የሌለው ትዳር 80 ያልወሰነው
እንዲህ ያለ ፍቅር  
ከየት ነው የሚገኘው።

Abosina
@getmtg
@getmtg
6👍2

"ለማንኛውም ተንኮል ሁለት መፍትሄዎች አሉት፡ ጊዜና ዝምታ!"
‎ "እፎይታ"
@getmtg
@getmtg
👏5

ቀኑ ነግቶ ውሎ እስኪመሽ
‎            ደግሞም መሽቶ እስኪነጋ
‎ስንታችን ነን የምንኳትን
‎              ....... ያልጠፋብንን ፍለጋ

@getmtg
@getmtg
👏4
።።።።። ብዕሲት ወዳጄ ።።።።።

አይና'ፋር ሳቂታ ደሞም ሸራፋ ነች ፣
በለዛ በምክር ማስተርሷን የያዘች፣
አንዲት ሴት ወዳጄ ፍቅርን የታደለች፣

አይጎልባት - ስምረት ችላ አትል -ነርስ ናት ፣
ሁሌ ለመታወስ ግዜ 'ማይወስናት፣

ሚስት ማድረግማ በ'ውነት እሷን ነበር፣
ምላሳም ባትሆን በነፋስ ባትበር ። (በረሮ)

✍️Zemed

@getmtg
@getmtg
👏3😁21

እንዲፃፍላችሁ የምትፈልጉት ሀሳብ ካለ
👇
@amen1995
@Zemeduu
share አድርጉን፡፡

@getmtg
@getmtg
2👍2

እኔ ማን ነኝ?

ማንነቴን ስብዕናዬን ብዙ እንዳውቀው
"እኔ ማን ነኝ?" ስል እራሴን ብጠይቀው
“እኔ ማለት ........ ” ሲል ጀምሮ
 ክፉነቴን አስታወሰኝ ሁሉን ነግሮ

"እኔ ማለት
ንግግሬ ያላማረ
ለዛ ቃናው ያልሰመረ
በንጭንጭ የተሞላ
ለአድማጭ ጆሮ አሜኬላ
ቅስም ሰባሪ ሰቅጣጭ ቃላት
ርካሽ ሆሄ ረባሽ ድምፀት
ለአፍ ወለምታ ማልፀፀት
 
ለፈጣሪ ማልገዛ
ማማረርን የማበዛ
ችግሮቼን
በአምላኬ ላይ የማሳብብ
የእምነት ካባን የማልደርብ
ባለኝ ነገር የምኮራ
ለመጀነን የማልፈራ
ምንቀባረር ምመፃደቅ
በሄድኩበት ራሴን ማደንቅ
 
የሰው ችግር የማይገኝ
ቅንጣት ታክል ርህራሄ ማይሰማኝ
መልካም ስራን የማልሰራ
የህይወት ፍሬን ማላፈራ
ፅድቅ የራቀኝ
እሱም ቀርቶ በቅጡ እንኳን ማይኮንነኝ
እኔ ማለት ክፉ ሰው ነኝ"

ብሎ አለኝ፡፡

Abosina
@getmtg
@getmtg
7👍4👏1
የግጥም ጥግ pinned «፡ እንዲፃፍላችሁ የምትፈልጉት ሀሳብ ካለ 👇 @amen1995 @Zemeduu share አድርጉን፡፡ @getmtg @getmtg»

ውበትሽ አይንን ሰራቂ
‎                ፀባይሽ ልብን ነጣቂ
‎ደምቆልኝ ይውላል ቀኑ
‎             ሁልጊዜ ባይሽ ስትስቂ

‎ልነግርሽ ብዬ መውደዴን
‎          አልቻልኩም ድፍረት እራቀኝ
‎የውስጤን የምታውቂበት
‎                   ማረፊያ ልብሽ ናፈቀኝ

‎ደፍሬ ፍቅሬን ላሰማሽ
‎            መጥቼ ደጅሽ ላይ ስደርስ
‎ቆርጦለት ሊያዋይሽ ያለ
‎                   አቅሜ ነው የሚደፈርስ      
‎     
‎ ፍቅርሽን በልቤ ይዤ             
‎                 ምን በጀኝ መንከራተቱ
‎ እወቂው ከአይኔ ላይ ሰርቀሽ
‎                    መላ በይኝ ባክሽ እቱ

@getmtg
@getmtg
👏3🥰2👍1
።።።ደቀ ማዕምር።።።።

ግፉ እጅግ ብዙ
ሰላሳ ቤሳ እርዙ

ሸክሙ ክርፍፍ ጓዙ
አባርሩት ከቅየው አስምጡት ከወንዙ

ነውና

አፍቅሮ የከዳ
     ትንሹ ይሁዳ

✍️Zemed

@getmtg
@getmtg
👏32😍1

ሳምንሽ የከዳሽኝ

‎በፈለግሽኝ ሰአት
‎ከጎንሽ ለመቆም የቋመጠ ነፍሴ
‎ና ባልሽበት ሁሉ
‎በጠራሽኝ ጊዜ አቤት ነበር መልሴ

‎ለምን ይሆን ታዲያ
‎ማጠፍ የቀለለሽ የሰጠሽኝን ቃል
‎መታመኔን አይተሽ
‎ያጎደፍሽው ልቤ      
‎መሄድሽን አይቶ ዘውትር ይማቅቃል

‎ላትኖሪልኝ ነገር
‎አለሁልህ ማለት እንዴትስ አስቻለሽ
‎ላንቺ ቀላል ነወይ
‎ክዶ ርቆ መሄድ
‎ የታመነልሽን አፍቃሪ ሰው ጥለሽ

@getmtg
@getmtg
5👏2

ያልፋል እያልን ቀን ስንጠብቅ
‎የእለት ጓዙን እየገፋን
‎ካለመኖር ተጠላልፈን
‎እኛው ከእኛው ተጠፋፋን

@getmtg
@getmtg
💯6👏4😍1

"ያልፋል ይለኛል ሰው"
     
ያልፋል .... ያልፋል .... ያልፋል

ያለወቅቱ መሽቶ ጨልሞበት ቀኑ
ለልቤ ምኑ ነው ተስፋ ማቀንቀኑ

አስማት የለኝ ፀጋ
                 ጥበብ የለኝ መክሊት
እንዴት ልሸውደው ይህን ክፉ ለሊት

"ያልፋል .... ያልፋል .... ያልፋል"

ሁሉም ጦሩን ስሎ  ጋሻውን አንግቦ
ቁርስ ምሳ ራቱን ንዴት ተመግቦ
ሲሸልል ለግዳይ ሲፎክር ለበቀል
አይመክተው ሼሁ
                አይበግረው መስቀል

ከቀን እስካመሻሽ ከሌት እስከ ንጋት
እሰከመቼ ልግፋው ኑሮዬን በስጋት

ያልፋል .... ያልፋል .... ያልፋል

"የሞተው ወንድምሽ
    የገደለው ባልሽ"
የሚባለው ተረት
መች ቀረ በወርት

ምን ጆሮ ተገኝቶ ምክር የሚሰማ
ዘወትር ለጦርነት ነጋሪት ጉሰማ
በለው ነው .....
ግፋው ነው .....
ግዝቱ ስብከቱ ልብ አያልፈሰፍስ
ያልፋል ያላችሁት
               ይህ ዘመን ባያልፍስ!?

(አስታወሰኝ ረጋሳ)
@getmtg
@getmtg
😭5