የግጥም ጥግ
770 subscribers
56 photos
2 videos
7 files
39 links
ያ ዶሮዬ ጮኈ መንጋቱን ነገረኝ፥
ሲነጋጋ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ።

የተለያዩ ምርጥ ግጥሞችን እዚህ

ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት

@Esamif
@amen1995 መጠየቅና መስጠት ይችላሉ።
Download Telegram

ላየኝማ ......
‎ስፈግግ ደልቶኝ ይመስላል
‎                     ሳቀና ያልጎደለብኝ
‎ለቃኘኝ ለአይን ሞልቼ
‎እንደፈካሁኝ ታይቼ
‎               ለእኔ ግን መች አማረብኝ

‎ባዶ ነው ሁለ ድባቡ
‎ተማምነውበት አለልኝ
‎                   ያሉት ሰው ሲታጣ ከጎን
‎ምን አለ ልብ የሚያጨልም
‎ሙሉነት እየናፈቁ
ሰው ከቦት ብቻ እንደመሆን

‎        ተጓዝኩኝ በቀናው መንገድ
‎ወና ቤት መሆኔን ሳ'ቅ ነው
‎                        ተስቶኝ የምንገዳገድ
‎        እረገጥኩ የእግዜር ደጁን
‎ዝምታው ቢበረታ እንኳ
‎                    አይተውምና ወዳጁን
‎፡
‎ከራስ ጋር መኗኗር ይዞት
‎ብቻነት ዙሯን ስታጦፍ ለፀና እየታገለ
‎ምንጊዜም ከርሞ እንዳዲስ
‎          ሰው መቅረብ ያስፈራስ የለ?

‎ቀን ደርሶ ስኬት ሲለግስ
‎               "ታድሎ" ሲሉ ሰማሁኝ
‎ለራሴ ከሰው ጎድዬ
‎በናቀኝ ባከበረኝ አፍ
‎                ስመጥር ሆኜ ታማሁኝ

‎መች አዩትና የውስጤን
‎ወዳጁ በራቀው ቁጥር
‎                            ተዛዝኖ እንደጠቆረ
‎አብሮነት ትርጉሙን ሲያጣ
‎ያኔ ነው እንደ ልማዱ
‎               ............ ባዶነት ጓዙን ያቆረ፡፡

‎(ሀሳቡን በግጥም እንድፅፍለት ለጠየቀኝ ሰው ይድረስልኝ😊)

Mekdi
@getmtg
@getmtg
👏6👍21😭1

"እኔ ከእኔ እንደተረዳሁት የፍቅር ወግ እምንም ውስጥ የማይገባ እንቶ ፈንቶ ነው፡፡ ግን ከየትኛውም ወሬ በላይ በስሜት የተሞላ፡፡"

‎ "ኩርቢት"
@getmtg
@getmtg
👍4

በዜሮ ...
(አሌክስ አብርሃም)

አንድ ጓደኛየ መንጃ ፈቃድ አውጥቶ መኪና መንዳት በጀመረ በመጀመሪያው ቀን በሰላም በእግሬ ከምሄድበት ጠራኝና
"ና ግባ አደባባዮን ላሻግርህ" አለኝ
"ግዴለም በእግሬ እሻገራለሁ" አልኩ። ነዝንዞ  አስገባኝና ጋቢና አስቀመጠኝ። መንግስትና ህዝብ ንዳ ብሎ ፈቃድ ከሰጠው እኔ ማነኝ ችሎታውን የምጠራጠር ብየ ተመቻቸሁ። ገና በሩን ከመዝጋቴ  ስለመኪና ባህሪና ስለአነዳድ ቴክኒክ ልቤ እስኪደክም ያስረዳኝ ጀመር። ያለምንም ዓላማ ከተማችንን አንድ ጊዜ አዞረኝ። እስከዚህ ደህና ነበር።

  "ይሄ ፍሬን ይባላል፣ ድንገተኛ ነገር ...ለምሳሌ ሰው ፣ አህያ ወይም  የተናኘ  ባል የሚነዳው መኪና ቢገቡብህ ማቆሚያ ነው"  አለና አጎንብሶ ፍሬኑንን ይፈልግ ጀመረ...(ተናኘ ሹፌር ያገባች የቀድሞ  ፍቅረኛው ናት፤ከነቂሙ ነው መንጃ ፈቃድ የያዘው?) "ፍሬኑን እስክትፈልግ ግን ....ከማለቴ  ፍሬኑን አግኝቶ ባለ በሌለ ሀይሉ ረገጠው። ወደፊት ተወርውሬ የሆነ ነገር ጋር ተጋጭቸ ተመለስኩ። ዘና ብሎ "አሁን የገጨኸው ዳሽ ቦርድ ይባላል የትም አገር የሚያጋጥም ነገር ነው" አለና ቀጠለ። ደረቴን ደግፌ  እያሳልኩ ዝም አልኩ።

ብቻ እንዲህ አሰቃይቶኝ በመጨረሻ "አንዲት ብዙ ሹፌሮች ያልባነኑባት ቴክኒክ ላሳይህ ወደፊት ይጠቅምህ ይሆናል" አለኝ። ወይ እዳየ። ከዚህ ሁሉ ለዓመታት የነዳ ሹፌር ተደብቆ  ገና በአንድ ቀን ምን ተገልጦለት ይሆን እያልኩ ሳስብ በከተማችን አለ ወደሚባለው ቁልቁለት መንገድ ወሰደኝና "አሁን እዚህ ቁልቁለት ላይ ሞተሩን ታጠፋውና በዜሮ ትሄዳለህ ...መሪዋ ላይ ብቻ መጫወት ነው...ነዳጅ አተረፍክ ማለት ነው አባቴ" ብሎ ትልቅ ግኝት እንደነገረኝ አይነት በኩራት ሀሀሀሀሀ ብሎ ሳቀ። እኔ ግን ነፍሴ ተጨነቀች።  መኪናው ወደታች ፍጥነት እየጨመረ  መምዘግዘግ ጀመረ ። ወገኖቸ ባጭሩ ፍሬን ቢረግጥ ምን ቢረግጥ (እኔን ሁሉ እግሬን ቢረግጥ) መኪናው አልቆምም አለ። አታምኑኝም ዞር ስል የሹፌሩ በር ተከፍቶ አጅሬው ሲዘል ተገጣጠምን። ለደይቃወች ራሱን በሚነዳ መኪና ከተጓዝኩ በኋላ .... መኪናዋና እኔ ለግንባታ ፒራሚድ መስሎ  የተከመረ አሸዋና ጠጠር ክምር ጫፍ ላይ ጉብ አልን። እዚህ  ቴውድሮስ አደባባይ ያለውን የአፄ ቴውድሮስን የመድፍ ሀውልት ነበር የምንመስለው።

አሁን ያለንበትን የኑሮ ሁኔታ ሳየው፣  የሆነ ቴክኒክ ላሳያችሁ ብሎ ያሳፈረን ሹፌር ዘሎ የወረደ እስኪመስለኝ ቀላል እየተምዘገዘግን ነው?! ብቻ ማረፊያችንን ያሳምረው። ለእኔ በነጠላው  የደረሰ አምላክ በጅምላ ይድረስልን።

@getmtg
@getmtg
😁7👏32

አለሽ ወይ
(በዕውቀቱ ስዩም)

አለሽ ወይ አለሽ ወይ
አለሽ ወይ በጤና
ይመስገን ደመና

በገበሬው አጥንት መሬቴን እያረስኩ
እንጀራ ሲጠፋ ገበሬ እየጎረስኩ
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ደመና

ሰው ሲያፈርስ እያየሁ ሰው ሆኖ ቡልዶዘር
አንዱ ጭቃ ነገድ ሌላው የብረት ዘር
በፈረሰ ሰው ላይ በቆመ ሰገነት
ሲዖል አናቱ ላይ በታነፀ ገነት
ይኽን ኑሮ ብለው ጥቂቶች ሲኖሩ
ያለምንም ፀፀት ያለምንም ሃፍረት
ይህንን እያየሁ በታላቅ ፅሞና
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ዳመና

በምቾት መዲና የምንዱባን ትዝብት
እንደ ሀሩር ልፎኝ
በጠዳው ጎዳና
ለማኝ ብላቴና
እንደ ጉቶ አናቅፎኝ
ሃፍረት እንደ ዝናር ከፊት ከኋላ ኣቅፎኝ
ልክ እንደ ገባሮች ለመኖር እያቀድሁ
በጌቶች መሶብም እጄን እየሰደድሁ
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ደመና

ወይ በሩን አሳዪን ወይ ጠቁሚን መላ
ማዕበል ሲቃረብ ያመልጣል ሺመላ
በነፋስ ገፅ ፊት ይሸሻል ደመና
የኔ አዚም ያለበት ያ’ገሬ ሰው ግና
በስጋ ደም አጥንት የተሰራ አይመስል
እንደ ኮንሶ ሃውልት የመቃብር ምስል
አይሸሽ አያባርር ወይ አይተነፍስ ቃል
እንጨት ሆኖ ቆሞ ሰደድ ይጠብቃል

ይህንን እያየሁ
ሁኘ በጥሞና
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ደመና

አንቺ ግን አለሽ ወይ እኔ አለሁ በደህና
አለሁ ግርምት ወሮኝ
ምላሱን በምላጭ እንደተሰለበ
ምናገረው ኖሮኝ
የምለው ቸግሮኝ።

@getmtg
@getmtg
3👏2
ምርኩዜ ወደቀ ቀጥ ብዬ ቆምሁኝ
እንባዬም ደረቀ መሀረቤን ጣልሁኝ

ከት ብዬ ሳቅሁኝ ጠላቴ በሸቀ
አበራሁኝ ሻማ ጎጆዬ ደመቀ

አመስግኜ ተኛሁ ሀዘኔም አለቀ
ልቤ አንቺን ስላየ አንቺን ስላወቀ።

✍️Zemed

@getmtg
@getmtg
👏83👍2🥰1

‎ክረምቱ ህመም ለጫረ
‎ቀናቱ ላጎደለብን ዝናቡ ለምን ይወቀስ
‎ ... ከእውነታው እርቅ ከሌለ ...
‎ደመና በረከቱ ስር
‎ ያነባል ቁስል ቀስ በቀስ

@getmtg
@getmtg
4🔥2

ከእለታት ባንዱ ሀሳብ
‎ያልመንህ ነገር ውጦት
ምስኪን ልቡን ያሸፈተ
‎እንደ ተራ ቀላል ነገር
‎እልህ መንገድ ሲጠርግለት
‎ የጥል በሩን የከፈተ

ወይም ወይም ........
‎ከእለታት ሌላው ሲያዝን
‎ግድየለቱን በሳቅ ሞልቶ
በንቀቱ የተመካ
‎ከራስ በላይ ንፋስ ባዩ
‎ያልሞላለት ባዶነቱን
አለኝ በሚል ቃል የለካ

‎ንፉግ ሆኖ እንደ ለጋስ
‎ጥሩ መስሎ ግፍ የሆነ
‎ለሰው ቀርቶ ለሱነቱ
‎ታምኖም እንኳን ያልታመነ

‎የጭልምቱን ጓዳ ሲሞቅ
‎በድን ገላን ተሸክሞ
የቁም ሞቱን የሚያፋጥን
‎አጉል ጥጋብ ልቡን አንቆት
‎ የጠፋበት የሀቅ ውጥን

‎ደረት ነፍቶ የሚያቅራራ
በአጉል አልህ የተኳለ
‎ስድ አመሉን ተከናንቦ
‎መሀላችን ድንገት ካለ

‎የወጠረው ተንፍሶለት
‎በልብነት አደብ ገዝቶ
ቅን እሳቤን እስኪቀበል
‎መንገድ ሁሉ ጨርቅ ሆኖለት
‎በእንቅፋት ሳይናጋ
በመጣበት ጥርግ ይበል!

Mekdi
@getmtg
@getmtg
4👍2💯1
😁(18+)

።።።።አንቀፀ ንሰሐ።።።።

ይኸው ልናዘዘው የክፋት ልፋፌን፣
ከፊትሽ ልቅደደው የበደል እራፌን፣
ኑዛዜ ቢያጠዳው የክህደት እድፌን፣

አንቺን የቀረብሁሽ ለአልጋ መአዱ፣
በሰው ስለቀናሁ ከሴት ጋር ....

ልጠቀምብሽ ነው ጎጆ የምወጣ፣
ብዙ ጥሪት አለሽ 'ካባትሽ የመጣ፣

ልሞላብሽ አሰብሁ ባዶ ጉሮሮዬን፣
ልከብርብሽ ነበር ላስውበው ጓሮዬን፣

ከሰው ላለማነስ አንቺን አገባሁሽ፣
'ካምሮቴ እንዳልጎል አንቺን አረከስሁሽ፣

እርግጥ ነው አልክድም ሌላም ሴት አምሮኛል፣
ልክስክስ አመሌ ለእህትሽ ድሮኛል፣

ይሄ ሁሉ ሲሆን ይህ ሁሉ ሲወድም፣
ያንቺ ቀና ልብሽ እኔኑ ቢወድም፣

ሌላ ባያሰኝሽ ክፋቴ ባይገፋሽ ፣
ልቀጥል አልችልም በደሌን በጭራሽ፣

እናም አሰናብቺኝ ከማዕሰረ ግፌ፣
ይቅርታሽን ላንባ በሬን ተደግፌ።

✍️Zemed

@getmtg
@getmtg
3😭2🔥1👏1

ለእግዜር የተላከ ደብዳቤ
(አሌክስ አብርሃም)

እንደምነህ እግዜር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው
እኛማ ......
ለእልፍ አእላፍ ጠበቃ
ማመልከቻ ፅፈን
ለወፈ ሰማይ ህዝብ
መድረክ ላይ ለፍፈን
ፀሎት ቤታችንን እኛው ላይ ቆልፈን
የምድር አተካራ ህግጋቱን አልፈን
ደብዳቤ ላክንልህ .......

አይንህን ካየነው
ሁለት ሺህ ዘመን እንደቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ዘመን
እየኮሰመነ መቅረትህ ገዘፈ
እንደውም እንደውም
በእመጣለሁ ተስፋ
ሁለት ሺህ ዘመን ገትሮን ከጠፋ
በቀጠሮ ሰአት መምጣት ከተሳነው
....... እግዜር ሀበሻ ነው
እያሉ ያሙሃል

እኔ ምን አውቃለሁ ....
አመስግነው ሲሉኝ እልልታ የማቀልጥ
ቃሉን ስማ ሱሉኝ
ሰባኪው እግር ስር በደስታ 'ምቀመጥ
እግዚኦ በል ሲሉኝ እንባዮን የማፈስ
ሃሌሉያ ሲሉኝ በሳቅ ልቤ 'ሚፈስ
ምናምንቴ እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ
እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ
.... እኔ ምን አውቃለሁ ....

ግን አንተ ደህና ነህ .....
ከምር እንደሚያሙት ምፅአት ቀረ እንዴ
የስናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ
አትከፋም አንዳንዴ?

ከሆነስ ሆነና
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
አብረሃም ሰላም ነው?
እዛስ ቤት ገነባ
ዛሬስ በድንኳን ነው?

እኛማ ይኸውልህ
በቤት ኪራይ ችንካር እየተሰቀልን
ኤሎሄ እንላለን ዳቦ እንድትጥልልን
ወደ ላይ ገነባን
ወደ ጎን አሰፋን
ወደላይም ከላይ ወደ ግንም ከጎን
እንደ ጉድ ተገፋን
ቤት ለእንግዳ ማለት ጭራሹኑ ጠፋን

አባታችን ሙሴ እንዴት ነው ለክብሩ
ውቅያኖስ መግፊያው ደህና ናት በትሩ
እኛማ ይኸውልህ
እንጀራ ፍለጋ ባህር ስናቋስጥ
የተስፋዋን ምድር አሸዋ ሳንረግጥ
የትም ውሃ በላን የትም አሳ ላሰን
ንገርልንና በትሩን ያውሰን

እናልህ እግዜር ሆይ
ከተስፋዋ ምድር
ወደሌላ ተስፋ አለን እየኳተን
መሄጃው ሲገርመን
መመለሻው መንገድ መቆሚያ ቦታ አጥተን

ለአባታችን ሙሴ እንደምትልልን
የመሄድ ዘመን ነው
ባህር የመሻገር ዱላህን ላክልን
....... ብሎሃል በልልኝ

ሰማይ ቤት እንዴት ነው
ዳዊትስ ደህና ነው?
ዛሬም ይዘምራል
ዛሬም ይፎክራል
ሰላም ነው ጠጠሩ ሰላም ናት ወንጭፉ
እዛስ አቅል ገዛ
ጎልያድ ተራራው ጎልያድ ግዙፉ

እልፍ አእላፍ ጎልያድ
ከቦን ሲደነፋ
ወንጭፉን ጠቅልሎ
ምነው ዳዊት ጠፋ

ብሎሃል በልልኝ
ለረከሰ ጠጠር ለሞላ ወርዋሪ
ወንጭፍህን ስጠው
ለዚህ ታሪክ አውሪ
ብለህ እዘዝልን

እንዴት ነህ ጌታ ሆይ
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
የሙሴ አልጋ ወራሽ
እያሱስ ሰላም ነው?
ያቆማትን ፀሀይ ግቢ ቢላት ምነው
አንተ እንደምታውቀው
እስራ ሶስት ወራት ነው
ፀሀይ የምንሞቀው

አረ ፀሀይ በዛ
አረ ፀሀይ በዛ
የመጣው ወር ሁሉ ፀሀይ እየዘለ
የተሾመው ሁሉ ፀሀይ ነኝ እያለ
የአስራ ሶስት ወር የእግዜር ፀሀይ
የአስራ ስስት ወር የእግዜር ጀንበር
ባቃጠላት ምድጃ ሀገር
ምን ተአምር ሊኖር ይችላል
ፀሀይ ሆኖ እንደመፈጠር

አረ እግዜር በእናትህ በጭንቅ አማላጇ
ባዘለ ጀርባዋ ባቀፉት እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሆነህ ና
...... ሙቀት ገደለና

እናልህ ጌታ ሆይ ማጣፊያው አጥሮናል
ስም ያለው ሞኝ ነው ሁሉም ይጠራናል
ጳውሎስ ሲሉን አቤት
ጴጥሮስ ሲሉን ወዬ
ይሁዳ ሲሉንም አቤት እንላለን
ስማችንን ሸጠን
ሰላሳ ጭብጨባ እንቀበላለን

ተወው የእኛን ነገር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
ሄዋንስ ደህና ናት?
ያው የልጅ ልጆቿ በእግሯ ተተክተው
የፍሬው ሲገርመን ግንዱንም አንክተው
ለፍጥረተ አዳም ባይኑ ይገምጡታል
ሴጣንም ደህና ነው ኑሮ ተስማምቶታል
ሰውን ለማሳሳት ላይ ታች ማለት ትቷል
ሳይጠራው የሚጎርፍ ህዝብ በዝቶለታል

አረ እግዜር በእናትህ በጭንቅ አማላጇ
ባዘለ ጀርባዋ ባቀፉት እጆቿ   
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሆነህ ና
               ...... ሙቀት ገደለና

@getmtg
@getmtg
8👏1

ያምር ነበር እሱነቱ
‎ቅን እሳቤው ያኖር ነበር
‎ ቀን መሻቱን ባያላላው
‎ደረስኩኝ ሲል ስኬት ደጃፍ
‎አለፍኩ ሲል ኑሮ ክሱን
‎ የድንገቱን ውሃ በላው

‎ወትሮ ጎኑ የነበረ
‎እንደልቡ እየተራጨ
‎ ክንዱን ሰዶ ያደገበት
‎የዛሬን ግን ምነው ከዳው?
‎ና ልንገርህ ብሎ ጠርቶ
‎ ነፍሱን ስቦ ወሰደበት

‎ሂድ እንዳለው ታቹን ሄደ
‎ ላዩን ሰማይ እየራቀው
‎ትጉ አይኖቹ ደርቀው ቀሩ
‎ ከመንገዱ ሞት አነቀው

‎(መታሰቢያነቱ ለማላውቀው በድንገት ለተለየን ወንድማችን ይሁንልኝ፡፡)

Mekdi
@getmtg
@getmtg
😭62👏1
. 👆👆👆👆👆👆
ሁላችንም ማንበብ ያለብን መፅሀፍ!

@getmtg
@getmtg
💯32

ስታየኝ
ስታየኝ!
      ሰውነቴ ትርክክ
      ጉልበቴ ብርክ ብርክ
      ልቤ ድንብርብርብር
      ሆዴ ሽብር ሽብር
      አይኔ መሬት ስብር
      ሀሞቴ ፍስስስ
      ሀሳቤም ትርምስምስ
      ቆዳዬ ልውጥውጥ
      እሷን እያሰብኩ ከፍቅር አለም ጭልጥ።
ስታየኝ!
       እኔነቴን እርስት
       አዲስ ሆኜ ክስት
       በአዲስ አለም ውስጥ
       ያለመጠን ምስጥ
       ክንፍ አውጥቼ ብርር
       ሳይገድበኝ ድንበር
       አድማስን ስሻገር
       ከአድማስ በስተጀርባ
       ሰማይ ቤት ስገባ
       ከሰማይ ከፍ ስል
       ሰማየ ሰማያት ወስዶ የሚከተኝ
       በነዛ ውብ አይኖች ያቺ ልጅ ስታየኝ።
አይኖቿ ተአምር
ልብን የሚሰውር
ራስን የሚያስረሳ
ቀልብን የሚነሳ
ፍቅርን አስይዞ
ወደ ሰማይ ጉዞ
ወደ አዲስ አለም
ሳይተኙ በማለም።
                  
Abosina
@getmtg
@getmtg
👏73

‎"እንደው አንቺን ሳጣ
‎ሰላሜ ተለየኝ ልልሽ አሰብኩና
‎ ደግሞም ትዝ ሲለኝ
‎አልተለየሽኝም
‎ከእኔው ጋር ነው ያለሽ
‎ እንዲህም አልኩና
‎ ሀሳቤን ቀየርኩኝ ........
‎፡
‎ልክ እንደ ውሃ ጥም
‎ደግሞ ናፍቀሽኛል ለማለት አስቤ
‎ተውኩት 'ረሳሁት
‎ጥሜን ልቆርጥበት ውሃውን አቅርቤ
‎፡
‎እንዲህ ብዬ ነበር
‎ደግሞ ካንቺ ሌላ የቱንስ ሀብት አለኝ
‎ ( ያው እንደ ልማዴ)
‎ዛሬም አላጣሁሽ
‎ምን ምክንያት ሊኖር
‎ እንዲህ የሚያስብለኝ
‎፡
‎ደግሞም አንድ 'ለታ
‎ሳስብሽ ደስ አለኝ ከድሮ ሳቄ አለሽ
‎ያው እንደነገሩ
‎ አሁን ሕይወቴ ነሽ
‎........ ብዬ እንዳላሞገስኩ
‎ካንቺው ላንቺው ሆኖ
‎ ይህን አልኩ የምለው
‎የውስጤን ልነግርሽ
‎ እንዲህ የምሆነው

‎ ለምን ይሆን?"

‎ (የሚልም ሰው አለ😊)

Mekdi
@getmtg
@getmtg
4😁3

ኬሬዳሽ

እኔ ስለ እሷ
እኔ ስለ እሷ
ሁሌም አስባለሁ ሁሌ እጨነቃለሁ
በነጋ በጠባ
ውሎና አዳሯን አረጋግጣለሁ

     ምን በላች ምን ጠጣች
         በምን ተደሰተች
በምንስ ተከፋች

   በምን ተቸገረች
ምን እጅስ አጠራት
   እጆቼን ቆርጬ እንድተባበራት

አሁን አሁንማ ከሷም አለፍ ብዬ
ስለቤተሰቧ
ስለእህት ወንድሟ ስለእማ አባብዬ
እጠይቃታለሁ እንዴት ሆኑ ብዬ

እሷ ግን ስለእኔ
እሷ ግን ስለእኔ ከቶ ግድ የላትም
ታሟል እንኳን ቢሏት
ምንም አይመስላትም

           አይሞቃት አይበርዳት
እኔን ችላ ማለት በፍጹም አይከብዳት

በቃ በጥቅሉ ሆናለች ኬሬዳሽ
ማፍቀሬ ማይገባት
የመውደድ ግዴለሽ፡፡

Abosina
@getmtg
@getmtg
👏43👍1

ከ80 በላይ
አለም ባዶ ሆና እኔና አንቺ ብቻ
ማንም በሌለበት ቀርበን ለጋብቻ
ሱፍ ቬሎ ሳናደርግ ሰርግም ሳይሰረግ
ሚዜ አጃቢ ሳይኖር
ቀለበት ሳንገዛ ምንም ሳይደረግ
                                   
ሱፌ ያንቺ ፍቅር ቬሎሽ ፍቅሬ ሆኖ
ሰርጋችን ዘላለም ማይኖር ተወስኖ                                 
                                
አጃቢ ከዋክብት
ሚዜዎች ብርሃናት ፀሐይም ጨረቃ
ሰማይ ድንኳናችን ለሁሉ የሚበቃ                                             
                                        
እንግዶች ፍጥረታት ሰው ያልተገኘበት
ሰው እኔና አንቺ ብቻ ሆነን ያለንበት።

ፍቅር ቀለበት ነው በልብ የሚታሰር
ወልቆ የማይጠፋ ወድቆ የማይሰበር
እግዜር የነገር አባት እኛን ያጣመረን
ሁለት አርጎ ፈጥሮ
አንድ አርጎ የሚያኖረን
                                       
ውል የሌለው ትዳር 80 ያልወሰነው
እንዲህ ያለ ፍቅር  
ከየት ነው የሚገኘው።

Abosina
@getmtg
@getmtg
6👍2

"ለማንኛውም ተንኮል ሁለት መፍትሄዎች አሉት፡ ጊዜና ዝምታ!"
‎ "እፎይታ"
@getmtg
@getmtg
👏5

ቀኑ ነግቶ ውሎ እስኪመሽ
‎            ደግሞም መሽቶ እስኪነጋ
‎ስንታችን ነን የምንኳትን
‎              ....... ያልጠፋብንን ፍለጋ

@getmtg
@getmtg
👏4
።።።።። ብዕሲት ወዳጄ ።።።።።

አይና'ፋር ሳቂታ ደሞም ሸራፋ ነች ፣
በለዛ በምክር ማስተርሷን የያዘች፣
አንዲት ሴት ወዳጄ ፍቅርን የታደለች፣

አይጎልባት - ስምረት ችላ አትል -ነርስ ናት ፣
ሁሌ ለመታወስ ግዜ 'ማይወስናት፣

ሚስት ማድረግማ በ'ውነት እሷን ነበር፣
ምላሳም ባትሆን በነፋስ ባትበር ። (በረሮ)

✍️Zemed

@getmtg
@getmtg
👏3😁21

እንዲፃፍላችሁ የምትፈልጉት ሀሳብ ካለ
👇
@amen1995
@Zemeduu
share አድርጉን፡፡

@getmtg
@getmtg
2👍2

እኔ ማን ነኝ?

ማንነቴን ስብዕናዬን ብዙ እንዳውቀው
"እኔ ማን ነኝ?" ስል እራሴን ብጠይቀው
“እኔ ማለት ........ ” ሲል ጀምሮ
 ክፉነቴን አስታወሰኝ ሁሉን ነግሮ

"እኔ ማለት
ንግግሬ ያላማረ
ለዛ ቃናው ያልሰመረ
በንጭንጭ የተሞላ
ለአድማጭ ጆሮ አሜኬላ
ቅስም ሰባሪ ሰቅጣጭ ቃላት
ርካሽ ሆሄ ረባሽ ድምፀት
ለአፍ ወለምታ ማልፀፀት
 
ለፈጣሪ ማልገዛ
ማማረርን የማበዛ
ችግሮቼን
በአምላኬ ላይ የማሳብብ
የእምነት ካባን የማልደርብ
ባለኝ ነገር የምኮራ
ለመጀነን የማልፈራ
ምንቀባረር ምመፃደቅ
በሄድኩበት ራሴን ማደንቅ
 
የሰው ችግር የማይገኝ
ቅንጣት ታክል ርህራሄ ማይሰማኝ
መልካም ስራን የማልሰራ
የህይወት ፍሬን ማላፈራ
ፅድቅ የራቀኝ
እሱም ቀርቶ በቅጡ እንኳን ማይኮንነኝ
እኔ ማለት ክፉ ሰው ነኝ"

ብሎ አለኝ፡፡

Abosina
@getmtg
@getmtg
7👍4👏1