፡
ያማል!
(በሰለሞን ሳህለ)
እና እንደነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ
የነፍሰጡርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ
ባልታሰበ ናዳ ተመቶ እንደመድቀቅ
ከተስፋ ጉልላት ተከፍቶ እንደመውደቅ
ተአምር በበዛባት በዚች ቧልተኛ አለም
ከዚህ የበለጠ ምንም ህመም የለም
አውቶቢሱ ያማል
ሚኒባሱ ያማል
ላዳ ታክሲው ያማል
የማይጎል የሰው ጎርፍ ደራሽ ማዕበሉ
የእንባ ቅጥልጥሉ
ምን ብዬ ልንገርሽ ያማል ይሄ ሁሉ(2)
እና እንደነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥረው ካረፈደ
የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥረው ካረፈደ
ነገር ተበላሸ
ህመም ተወለደ ጨጓራ በገነ
እሳት በእንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ሁሉም ተቀይሮ ተተካ በሲቃ
ምን ብዬ ልንገርሽ ይሄም ያማል በቃ
ወጪ ተራማጁ
አስመሳይ ሰጋጁ
ፀሀዩ ዝናቡ
የለምን ምክንያት የለምን ሰበቡ
ተቆራጭ አበባ ሊቆረጥ ማበቡ
ውል የለሽ ደመና ተራራን መክበቡ
እልፍ አእላፍ ኮከብ ጨረቃን ማጀቡ
ደግሞ ለእሷ ግጥም እናቷን ጨረቃ
ምን ብዬ ልንገርሽ ይሄም ያማል በቃ
.... እናቷን ጨረቃ ....
እና እንደነገርኩሽ
ጉንጭ የማትሞላ ኬክ 10 ብር የሸጠ
የካፌ አሳላፊ ወደኔ አፈጠጠ
ዘይት የነካውን መንታ እጁን አጣምሮ
ምን ልታዘዝ ይላል ቁልቁል አቀርቅሮ
ምን ልታዘዝ ይላል(2)
እንዴት ቅጥሉ ሰው ቅጥሉን ሰው ያዛል
ማኪያቶ ልዘዝ?
ካፕቺኑ ልዘዝ?
ጥቁር ቡና ልዘዝ?
ለምን ሰው አላዝም?
መታዘዝ መናዘዝ ርግማን የሆነው
ካፌውን ሲያሳልፍ
እራሱ ግን የሚያልፍ
ቁልቁል አቀርቅሮ
ሞቱን በአንገት ቀብሮ
ምን ልታዘዝ ይላል
አንድ ካፕቺኖ ከአንድ እሷ ጋር ልበል?
አንድ ጥቁር ቡና ከአንድ እሷ ጋር ልበል?
ከማኪያቶ ጋር እሷን አምጣ ልበል?
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
እና እንደነገርኩሽ
የላስቲክ አበባ የአርቲ ቡርቲ ስዕል
የጭቃ እሾህ ወግቶት እዥ ያወጣ ቁስል
ትልቁ ነቀዝ ሰው የማንቀዙን ያህል
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
እና እነንደነገርኩሽ ......
የሚወዱትን ሰው ቀጥረው ካረፈደ
የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
ነገር ተበላሸ
ህመም ተወለደ ጨጓራ በገነ
እሳት እንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ሁሉም ተቀድሮ ተተካ በሲቃ
ምን ብዬ ልነንገርሽ ይሄም ያማል በቃ
እና እንደነገርኩሽ .......
ላንቺ የያዝኩት አበባ መጠውለግ አመጣ
ፀሀይ ገባ ወጣ
ዝናብ ቀረት መጣ
ጨረቃም የለችም
እናቷን ስላልኳት
ደግሜ ሰድቤ ሺ አመት እንዳይገርማት
እናቷን
እናቷን ጨረቃ
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄም ያማል በቃ
እናቷ ግን ማነች
እናቷን ጨረቃ
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄም ያልፋል በቃ
ግን ......
እኔ አንቺን ስወድሽ
ይሄን ሁሉ ችዬ ነው የምጠብቅሽ
ቢሆንም ግን ያማል!
@getmtg
@getmtg
ያማል!
(በሰለሞን ሳህለ)
እና እንደነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ
የነፍሰጡርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ
ባልታሰበ ናዳ ተመቶ እንደመድቀቅ
ከተስፋ ጉልላት ተከፍቶ እንደመውደቅ
ተአምር በበዛባት በዚች ቧልተኛ አለም
ከዚህ የበለጠ ምንም ህመም የለም
አውቶቢሱ ያማል
ሚኒባሱ ያማል
ላዳ ታክሲው ያማል
የማይጎል የሰው ጎርፍ ደራሽ ማዕበሉ
የእንባ ቅጥልጥሉ
ምን ብዬ ልንገርሽ ያማል ይሄ ሁሉ(2)
እና እንደነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥረው ካረፈደ
የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥረው ካረፈደ
ነገር ተበላሸ
ህመም ተወለደ ጨጓራ በገነ
እሳት በእንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ሁሉም ተቀይሮ ተተካ በሲቃ
ምን ብዬ ልንገርሽ ይሄም ያማል በቃ
ወጪ ተራማጁ
አስመሳይ ሰጋጁ
ፀሀዩ ዝናቡ
የለምን ምክንያት የለምን ሰበቡ
ተቆራጭ አበባ ሊቆረጥ ማበቡ
ውል የለሽ ደመና ተራራን መክበቡ
እልፍ አእላፍ ኮከብ ጨረቃን ማጀቡ
ደግሞ ለእሷ ግጥም እናቷን ጨረቃ
ምን ብዬ ልንገርሽ ይሄም ያማል በቃ
.... እናቷን ጨረቃ ....
እና እንደነገርኩሽ
ጉንጭ የማትሞላ ኬክ 10 ብር የሸጠ
የካፌ አሳላፊ ወደኔ አፈጠጠ
ዘይት የነካውን መንታ እጁን አጣምሮ
ምን ልታዘዝ ይላል ቁልቁል አቀርቅሮ
ምን ልታዘዝ ይላል(2)
እንዴት ቅጥሉ ሰው ቅጥሉን ሰው ያዛል
ማኪያቶ ልዘዝ?
ካፕቺኑ ልዘዝ?
ጥቁር ቡና ልዘዝ?
ለምን ሰው አላዝም?
መታዘዝ መናዘዝ ርግማን የሆነው
ካፌውን ሲያሳልፍ
እራሱ ግን የሚያልፍ
ቁልቁል አቀርቅሮ
ሞቱን በአንገት ቀብሮ
ምን ልታዘዝ ይላል
አንድ ካፕቺኖ ከአንድ እሷ ጋር ልበል?
አንድ ጥቁር ቡና ከአንድ እሷ ጋር ልበል?
ከማኪያቶ ጋር እሷን አምጣ ልበል?
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
እና እንደነገርኩሽ
የላስቲክ አበባ የአርቲ ቡርቲ ስዕል
የጭቃ እሾህ ወግቶት እዥ ያወጣ ቁስል
ትልቁ ነቀዝ ሰው የማንቀዙን ያህል
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
እና እነንደነገርኩሽ ......
የሚወዱትን ሰው ቀጥረው ካረፈደ
የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
ነገር ተበላሸ
ህመም ተወለደ ጨጓራ በገነ
እሳት እንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ሁሉም ተቀድሮ ተተካ በሲቃ
ምን ብዬ ልነንገርሽ ይሄም ያማል በቃ
እና እንደነገርኩሽ .......
ላንቺ የያዝኩት አበባ መጠውለግ አመጣ
ፀሀይ ገባ ወጣ
ዝናብ ቀረት መጣ
ጨረቃም የለችም
እናቷን ስላልኳት
ደግሜ ሰድቤ ሺ አመት እንዳይገርማት
እናቷን
እናቷን ጨረቃ
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄም ያማል በቃ
እናቷ ግን ማነች
እናቷን ጨረቃ
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄም ያልፋል በቃ
ግን ......
እኔ አንቺን ስወድሽ
ይሄን ሁሉ ችዬ ነው የምጠብቅሽ
ቢሆንም ግን ያማል!
@getmtg
@getmtg
❤7👏5
.........ዘ-ተቃራኒ........
እኔ የምወዳት ቁመት የምበልጣት፣
እኔ የምወዳት ገንዘብ የማልሰጣት፣
እኔ የምወዳት ምርጥ ባለሙያ የኪቺኗ እመቤት፣
እኔ የምወዳት መልኳ ስዕል አድን፣
ሲያዩአት የምታክም የምትፈውስ በድን ፣
እኔ የምወዳት በኔ የምትረጋ፣
ትቶኝ ይሄድ ይሆን? ብላ የምትሰጋ፣
................
እኔን የምትወደኝ ወርቅ ቆፋሪዋ (gold digger)፣
እኔን የምትወደኝ ዋሌት ፈርፋሪዋ፣
እኔን የምትወደኝ ቁመቷ ቀጀላ፣
ከኔጋ ተጋድማ ተጨማሪ ሚያምራት የሌላ .....
እኔን የምትወደኝ ወጡን አገንፍታ እንጀራ የምትከትፍ፣
በወጣሁ በገባሁ በነገር የምትለክፍ፣
እኔን የምትወደኝ መልኳ ፎጣ መሳይ፣
እንኳን ለጀለሶች ለናቴም አላሳይ።
ምነው ጌታዬ?
✍️Zemed
@getmtg
@getmtg
እኔ የምወዳት ቁመት የምበልጣት፣
እኔ የምወዳት ገንዘብ የማልሰጣት፣
እኔ የምወዳት ምርጥ ባለሙያ የኪቺኗ እመቤት፣
እኔ የምወዳት መልኳ ስዕል አድን፣
ሲያዩአት የምታክም የምትፈውስ በድን ፣
እኔ የምወዳት በኔ የምትረጋ፣
ትቶኝ ይሄድ ይሆን? ብላ የምትሰጋ፣
................
እኔን የምትወደኝ ወርቅ ቆፋሪዋ (gold digger)፣
እኔን የምትወደኝ ዋሌት ፈርፋሪዋ፣
እኔን የምትወደኝ ቁመቷ ቀጀላ፣
ከኔጋ ተጋድማ ተጨማሪ ሚያምራት የሌላ .....
እኔን የምትወደኝ ወጡን አገንፍታ እንጀራ የምትከትፍ፣
በወጣሁ በገባሁ በነገር የምትለክፍ፣
እኔን የምትወደኝ መልኳ ፎጣ መሳይ፣
እንኳን ለጀለሶች ለናቴም አላሳይ።
ምነው ጌታዬ?
✍️Zemed
@getmtg
@getmtg
😁6❤5😭2👍1👏1
፡
አንቺን ፍቅሬን አገኝ መስሎኝ
ሰርክ ደከምኩ ደጅ ጠናሁ
ጥንዶች ሲያልፉ በጎዳና
ተቃቅፈው ሳይ ይባስ ቀናሁ
አትመጪም ወይ .....
በእናትና ባባትሽ ቤት
ሰው ማስጠየቅ መማለዴ
እንድትይዢኝ አልነበር ወይ
እንድይዝሽ አይደል እንዴ
ትመጭ መስሎኝ በተስፋ አለም
ከልቤ ውስጥ የቀጠርኩሽ
አፌ ፍቅርን ሲፈታበት
አይኔ አይንሽን እየፈራ
የልቤን ቃል ፍቅሬ ያልኩሽ
አንቺን አይደል? .......
የዋልንበት ጫካ ሜዳው
ትዝታሽን የሚያውሰኝ
ውበትና ሳቅ ጨዋታሽ
ዘወትር ቀልቤን እየገዛ
እኔነቴን የሚወረሰኝ
ፍቅርሽ አይደል? ........
የክት ሆነሽ 'ምታሳሺ
ሁሌ እንዳሻት የማትገኝ
ከአበባም የአደይ አበባ
በናፍቆትሽ ስመነምን
የክረምቱን ብትጨክኚ
መስከረም እንኳ ሲጠባ
አትመጪም ወይ .....
@getmtg
@getmtg
አንቺን ፍቅሬን አገኝ መስሎኝ
ሰርክ ደከምኩ ደጅ ጠናሁ
ጥንዶች ሲያልፉ በጎዳና
ተቃቅፈው ሳይ ይባስ ቀናሁ
አትመጪም ወይ .....
በእናትና ባባትሽ ቤት
ሰው ማስጠየቅ መማለዴ
እንድትይዢኝ አልነበር ወይ
እንድይዝሽ አይደል እንዴ
ትመጭ መስሎኝ በተስፋ አለም
ከልቤ ውስጥ የቀጠርኩሽ
አፌ ፍቅርን ሲፈታበት
አይኔ አይንሽን እየፈራ
የልቤን ቃል ፍቅሬ ያልኩሽ
አንቺን አይደል? .......
የዋልንበት ጫካ ሜዳው
ትዝታሽን የሚያውሰኝ
ውበትና ሳቅ ጨዋታሽ
ዘወትር ቀልቤን እየገዛ
እኔነቴን የሚወረሰኝ
ፍቅርሽ አይደል? ........
የክት ሆነሽ 'ምታሳሺ
ሁሌ እንዳሻት የማትገኝ
ከአበባም የአደይ አበባ
በናፍቆትሽ ስመነምን
የክረምቱን ብትጨክኚ
መስከረም እንኳ ሲጠባ
አትመጪም ወይ .....
@getmtg
@getmtg
❤6👍2
😍😍ሴቶች ተጣሉብኝ🥰
ገነት ተናገረች
.... አዳም ሆይ አትክዳኝ ይልሀል የኔ ልብ፣
ባለበስኩህ ስጋ በሰጠሁህ ምግብ ፣
ጥንተ ተፈጥሮዬ ያንተም አንድ ናቸው፣
ህጋህና ምድሬ ያው ነው ዝምድናቸው ፣
እኔኮ ካንተ ጋር ከሁሉ አስቀድመን የተወዳጀን ነን ፣
አሁን በሌላ ሴት ትላንት በመጣች እንዴት ተለያየን ፣
ወደቀድሞ ፍቅርህ ተመለሰ አትራቀኝ፣
ሁሉ ነገሬ ነህ አገልጋይህ አርገኝ፣
ሄዋን ቀበል አርጋ ይሄንን መለሰች ፣
..........ምን ቆሞ እንዲራመድ አፈር ብታውሽው ፣
ግራ ጎኑ እኔ ነኝ ይሄንን አትርሽው፣
ባለቤቴ እሱ ነው የሁለንተናዬ፣
ደራሲዬም እርሱ የዛሬ የነገ የትናንትናዬ፣
ስለዚህ የኔ ነው እርሱም የብቻዬ፣
ክሱ ሲበረታ በመካከላቸው፣
ፈጣሪን ጠሩና እንዲፈርድላቸው ፣
ነገሩን ቢያዋዩት ከስር መሰረቱ ፣
ስለ አደም አወራ ስለወንድነቱ፣
ወንድልጅ እንዲህ ነዉ አይኖርም በሎጂክ፣
ምን አሪፍ ብትሆኚ ሲሰጥ ታይዋለሽ ልቡን ለሌላ ቺክ፣
እና ፍርዴ ይህ ነው እንደ ፍላጎቱ ከሄዋን እንዲኖር፣
በኑሮውም መሀል ምድር እንዳትመግበው እንዲለፋ እንዲጥር ፣
ካለፈም በኋላ የገነትን ንብረት እንዲመልስ አፈር፣
.....ይሄንን ስትሰማ ገነት እሪ አለች ጠየቀች ለይግባኝ፣
አፈሬ ይቅርብኝ እሱ ብቻ ያግባኝ፣
ጌታም ጠጋ ብሎ ...
....ግዜው አልደረሰም ግን ይስተካከላል፦
ከሷጋ መኖሩ አንገፍግፎት ገርፎት፣
ካንቺጋ ሊመለስ ንሰሀ ይገባል ይሳልሻል ስለት፣
ገነትን ፍለጋ በኔ ሽምግልና በመስቀል እርቃችሁ፣
አምስት ሺህ ተኩል ግዜው ሲጠናቀቅ ትመለሳላችሁ!
✍️Zemed
@getmtg
@getmtg
ገነት ተናገረች
.... አዳም ሆይ አትክዳኝ ይልሀል የኔ ልብ፣
ባለበስኩህ ስጋ በሰጠሁህ ምግብ ፣
ጥንተ ተፈጥሮዬ ያንተም አንድ ናቸው፣
ህጋህና ምድሬ ያው ነው ዝምድናቸው ፣
እኔኮ ካንተ ጋር ከሁሉ አስቀድመን የተወዳጀን ነን ፣
አሁን በሌላ ሴት ትላንት በመጣች እንዴት ተለያየን ፣
ወደቀድሞ ፍቅርህ ተመለሰ አትራቀኝ፣
ሁሉ ነገሬ ነህ አገልጋይህ አርገኝ፣
ሄዋን ቀበል አርጋ ይሄንን መለሰች ፣
..........ምን ቆሞ እንዲራመድ አፈር ብታውሽው ፣
ግራ ጎኑ እኔ ነኝ ይሄንን አትርሽው፣
ባለቤቴ እሱ ነው የሁለንተናዬ፣
ደራሲዬም እርሱ የዛሬ የነገ የትናንትናዬ፣
ስለዚህ የኔ ነው እርሱም የብቻዬ፣
ክሱ ሲበረታ በመካከላቸው፣
ፈጣሪን ጠሩና እንዲፈርድላቸው ፣
ነገሩን ቢያዋዩት ከስር መሰረቱ ፣
ስለ አደም አወራ ስለወንድነቱ፣
ወንድልጅ እንዲህ ነዉ አይኖርም በሎጂክ፣
ምን አሪፍ ብትሆኚ ሲሰጥ ታይዋለሽ ልቡን ለሌላ ቺክ፣
እና ፍርዴ ይህ ነው እንደ ፍላጎቱ ከሄዋን እንዲኖር፣
በኑሮውም መሀል ምድር እንዳትመግበው እንዲለፋ እንዲጥር ፣
ካለፈም በኋላ የገነትን ንብረት እንዲመልስ አፈር፣
.....ይሄንን ስትሰማ ገነት እሪ አለች ጠየቀች ለይግባኝ፣
አፈሬ ይቅርብኝ እሱ ብቻ ያግባኝ፣
ጌታም ጠጋ ብሎ ...
....ግዜው አልደረሰም ግን ይስተካከላል፦
ከሷጋ መኖሩ አንገፍግፎት ገርፎት፣
ካንቺጋ ሊመለስ ንሰሀ ይገባል ይሳልሻል ስለት፣
ገነትን ፍለጋ በኔ ሽምግልና በመስቀል እርቃችሁ፣
አምስት ሺህ ተኩል ግዜው ሲጠናቀቅ ትመለሳላችሁ!
✍️Zemed
@getmtg
@getmtg
❤9👏3😁2🔥1
፡
አንቺ ስትቀሪ
ሽፋን ታቅፊያለው
ሲያይዋት የምታምር ልብ የምትሰረስር
አበባ ይዣለው
የሚያምር አበባ ከሽፋኑዋ ሆድ ስር
ትመጣለች ይሆን!
እያልኩኝ ጠበኩዋት
ጠበኩዋት
ጠበኩዋት
እንዳትቀር ያሰበች ልቤን አስጨነኩዋት
ኮቴሽን ናፍቄ መምጫሽን ናፍቄ
ጠብቂያት እላለው
እንዳትከፋብኝ አበባዬን ስቄ
ገፁዋ ጠወለገ ሟሸሸ ቅጠሏ
ብትቀሪ ጊዜ ነው ባንቺ መቃጠሏ
እያልኩኝ ….....
እያልኩኝ .......
በሳምሺው መዳፌ ውብ ፊቴን ከለልኩኝ
አይኔ የሚያየው አጣ እንባ ከለከለኝ
..... ልቤ ደነገጠ ቀርተሻል መሰለኝ
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ከራሱ የራቀ ወደማን ይሸሻል!?
ታዲያ ስትቀሪ
የያዝኩት አበባ ደርቆ ጠወለገ
ፀሀይ ወቶ ሳለ
የሚያስጠላ ሆኖ ቀኑ ጨፈገገ
ይህው አበባዬ
ሲጠብቅሽ ዉሎ አዘነ ተከፋ
ፀአዳው ፀዳሉ
ጠረኑን ለውጦ እጅጉን ከረፋ
አንቺ ስትቀሪ ……
ሽፋን ውስጥ ያለውን
ውዱን ስጦታዬን የሚከፍተው አጣ
የዘላለሙ ቤት
መቃብር ሆነበት አዘነ ተቆጣ
ተቆጥቶ እንዲህ አለኝ ምስኪን አበባዬ
ናፍቆት የደፈነው
ምን ጆሮ አለውና ሰማሁት በእንባዬ
"አስተውል ወዳጄ!!
ለወደድካት እንስት ላፈቀርካት ወጣት
አበባህን እንጂ ልብህን አትስጣት
ምክንያቱም .......
እኔ ብጠወልግ ብዙ አበቦች አሉ
ለወደድከው ሁሉ መሆን የሚችሉ"
አሊያ ግን ለዛች ሴት
ከአበባህ ቀድመህ ልብህን ካቀናህ
ድንገት የቀረች'ለት
ከ አበባህ ቀድመህ ትሞታለህና
ለወደድካት እንስት ላፈቀርካት ወጣት
አበባህን እንጂ ልብህን አትስጣት።"
(አስታወሰኝ ረጋሳ)
አንቺ ስትቀሪ
ሽፋን ታቅፊያለው
ሲያይዋት የምታምር ልብ የምትሰረስር
አበባ ይዣለው
የሚያምር አበባ ከሽፋኑዋ ሆድ ስር
ትመጣለች ይሆን!
እያልኩኝ ጠበኩዋት
ጠበኩዋት
ጠበኩዋት
እንዳትቀር ያሰበች ልቤን አስጨነኩዋት
ኮቴሽን ናፍቄ መምጫሽን ናፍቄ
ጠብቂያት እላለው
እንዳትከፋብኝ አበባዬን ስቄ
ገፁዋ ጠወለገ ሟሸሸ ቅጠሏ
ብትቀሪ ጊዜ ነው ባንቺ መቃጠሏ
እያልኩኝ ….....
እያልኩኝ .......
በሳምሺው መዳፌ ውብ ፊቴን ከለልኩኝ
አይኔ የሚያየው አጣ እንባ ከለከለኝ
..... ልቤ ደነገጠ ቀርተሻል መሰለኝ
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ቀርተሻል
ከራሱ የራቀ ወደማን ይሸሻል!?
ታዲያ ስትቀሪ
የያዝኩት አበባ ደርቆ ጠወለገ
ፀሀይ ወቶ ሳለ
የሚያስጠላ ሆኖ ቀኑ ጨፈገገ
ይህው አበባዬ
ሲጠብቅሽ ዉሎ አዘነ ተከፋ
ፀአዳው ፀዳሉ
ጠረኑን ለውጦ እጅጉን ከረፋ
አንቺ ስትቀሪ ……
ሽፋን ውስጥ ያለውን
ውዱን ስጦታዬን የሚከፍተው አጣ
የዘላለሙ ቤት
መቃብር ሆነበት አዘነ ተቆጣ
ተቆጥቶ እንዲህ አለኝ ምስኪን አበባዬ
ናፍቆት የደፈነው
ምን ጆሮ አለውና ሰማሁት በእንባዬ
"አስተውል ወዳጄ!!
ለወደድካት እንስት ላፈቀርካት ወጣት
አበባህን እንጂ ልብህን አትስጣት
ምክንያቱም .......
እኔ ብጠወልግ ብዙ አበቦች አሉ
ለወደድከው ሁሉ መሆን የሚችሉ"
አሊያ ግን ለዛች ሴት
ከአበባህ ቀድመህ ልብህን ካቀናህ
ድንገት የቀረች'ለት
ከ አበባህ ቀድመህ ትሞታለህና
ለወደድካት እንስት ላፈቀርካት ወጣት
አበባህን እንጂ ልብህን አትስጣት።"
(አስታወሰኝ ረጋሳ)
👍16❤1
፡
አስደግማብኝ ነው ......
(ሰለሞን ሳህለ)
ለሰባት ጠንቋይ ልጅ ለደብተራ ምርኩዝ
ጠጠር ገበጣ አርጋ ላኬር እጣው እርኩዝ
"ይቺን ያየ" አስብላ
መሬት ልታስገባ ደቼ ልታስበላ
የስር ማሽ እንጉዳይ የኮከብ ቆጣሪ
የነ መገን ቦቃ የነ ጥና ጠሪ
እንደርቢ ቁጣ የአመድ ላይ ዘዋሪ
ለመቃብር አፈር መንገድ ላይ ቀጣሪ
መተተኛ ፍቅር ልብ ላይ ቀባሪ
የቀን ስደተኛ አርጋኝ የሌት ዟሪ
አቅሌን እያሳተች 'ምታስብለኝ እሪ
አስደግማብኝ ነው ....
"በርሶ መጀን" ብላ
የልቤ ሳይበቃት ልቦናየን በልታ
ጨፌ እየነከሰች በጉልበት ተደፍታ
ኩራቴን ልትነጥቀኝ ኮርታ ልትማታ
.... ተማ'ታም ልትረታ
ጥላዬን ጀማው ፊት መሬቱ ላይ ዘርታ
"ያዙልኝ" እያለች በጠንቋይ ቱፍታ
መለመላ ነፍሴን ወናየን ዘርግታ
'ታሞ ይኑር' ብላ እኔን አስወግታ
እርጋታዬን ነጥቃ እኔን ከኔ አጣልታ
በደብተራው ምርኩዝ ባስነካችው ኩታ
እንዳነክስላት ጅስሜን አስመትታ
ህልሜን እንዳልሰማ ልቤን አስደብታ
አስደግማብኝ ነው "ናልኝ" ብላ ጠርታ
የሆንኩ አንገት ደፊ የሆንኩት ከርታታ
መለየት ያቃተኝ ቀኑንና ማታ
አስደግማብኝ ነው ......
ለነ ጥላ ወጊ ለመጫኛ ነካሽ
ለነ አፍዝ አደንግዝ ለዱር ቅጠል በጣሽ
ላውልያ ለጠንቋዩ ለኑግ ቂጣ ቆራሽ
ለመንገድ ገርጋሪ ለውቃቢ ዘራሽ
ለገሃድ ስውሩ ለነ ጽናት አፍራሽ
ለምድር ላየሩ ለየሎስ አጎንባሽ
ለባህር ለየብሱ ለጠቋሪት ደጋሽ
አስደግማብኝ ነው
ወለም ያላለኝን ዘላለም የምታሽ
አስደግማብኝ ነው.......
አስደግማብኝ ነው ......
(ሰለሞን ሳህለ)
ለሰባት ጠንቋይ ልጅ ለደብተራ ምርኩዝ
ጠጠር ገበጣ አርጋ ላኬር እጣው እርኩዝ
"ይቺን ያየ" አስብላ
መሬት ልታስገባ ደቼ ልታስበላ
የስር ማሽ እንጉዳይ የኮከብ ቆጣሪ
የነ መገን ቦቃ የነ ጥና ጠሪ
እንደርቢ ቁጣ የአመድ ላይ ዘዋሪ
ለመቃብር አፈር መንገድ ላይ ቀጣሪ
መተተኛ ፍቅር ልብ ላይ ቀባሪ
የቀን ስደተኛ አርጋኝ የሌት ዟሪ
አቅሌን እያሳተች 'ምታስብለኝ እሪ
አስደግማብኝ ነው ....
"በርሶ መጀን" ብላ
የልቤ ሳይበቃት ልቦናየን በልታ
ጨፌ እየነከሰች በጉልበት ተደፍታ
ኩራቴን ልትነጥቀኝ ኮርታ ልትማታ
.... ተማ'ታም ልትረታ
ጥላዬን ጀማው ፊት መሬቱ ላይ ዘርታ
"ያዙልኝ" እያለች በጠንቋይ ቱፍታ
መለመላ ነፍሴን ወናየን ዘርግታ
'ታሞ ይኑር' ብላ እኔን አስወግታ
እርጋታዬን ነጥቃ እኔን ከኔ አጣልታ
በደብተራው ምርኩዝ ባስነካችው ኩታ
እንዳነክስላት ጅስሜን አስመትታ
ህልሜን እንዳልሰማ ልቤን አስደብታ
አስደግማብኝ ነው "ናልኝ" ብላ ጠርታ
የሆንኩ አንገት ደፊ የሆንኩት ከርታታ
መለየት ያቃተኝ ቀኑንና ማታ
አስደግማብኝ ነው ......
ለነ ጥላ ወጊ ለመጫኛ ነካሽ
ለነ አፍዝ አደንግዝ ለዱር ቅጠል በጣሽ
ላውልያ ለጠንቋዩ ለኑግ ቂጣ ቆራሽ
ለመንገድ ገርጋሪ ለውቃቢ ዘራሽ
ለገሃድ ስውሩ ለነ ጽናት አፍራሽ
ለምድር ላየሩ ለየሎስ አጎንባሽ
ለባህር ለየብሱ ለጠቋሪት ደጋሽ
አስደግማብኝ ነው
ወለም ያላለኝን ዘላለም የምታሽ
አስደግማብኝ ነው.......
❤5👍3
እየውልሽ ዉዴ ወንድ ልጅ አይደለሁ
አኮረፍሺኝ ብዬ እስኪነጋ ድረስ እጠጣልሻለሁ።
በተቀመጥኩበት ሌቱ እስከሚነጋ
በተፈጠርኩበት አለም እስኪረጋ
እሰክርልሻለሁ
ወንድ ልጅ አይደለሁ...
የላንቺ እንዳላልኩኝ ሴት ሁሉ አትፈጠር
ዛሬ ሰው አላውቅም ከ ኮማሪ በቀር
ደስታ እንደሞላኝ...
ቀ-ጭን ወገብሽን በጆቼ አቅፌ
ቅፅበቱ ይገርመኛል
ያረቄ መለኪያ ሲውል ከመዳፌ
የኮማሪት ገላ ሲኖር ከጉንፌ
ከትንፋሽሽ ውጪ አልሞቅም ያልኩኝ ሰው
ላረቄ ሽታ ነው ልቤ ሚናውዘው
ይምታታብኝ ያዘ
ያንቺና ያረቄው አመልና ነገር
ያንቺና መለኪያው አቋም አፈጣጠር
ብስቅ ብፈነድቅ ካንቺ ጋር አልነበር
ዛሬ አያምርብኝም ካልጠጣሁኝ በቀር
ካልሰከርኩኝ በቀር።
ተይ አታስኮንኚኝ
እንደ መጥፎ ቅዠት ደርሰሽ አታባኚኝ
ነይ እስኪ ልጋብዝሽ..
ትንሽ ጎንጨት በይ ይህን ካቲካላ
መውደዴን ቢያሳይሽ አስክሮ በመላ
ነይማ እንሞክረው...
ችለን ስንሔድበት የጣለንን መንገድ
ያሰምርልን እንደው ሰክሮ መንገዳገድ
ግድ የለም አትፍሪ ዝምብለን እንጠጣ
በዛ ከተባለ..
ብትወጂኝ ነውንጂ ሌላ ምን ሊመጣ።
ስካር የተባለ አንድ እንዳይቀርብሽ
አቅላችንን ስተን ሰፈር እንረብሽ
ማን ያውቃል
ስትሰክሪ ይሆናል 'ርምጃ ሚያምርብሽ።
ያዢና ፉት በይ እንጠጣ ገዴለም
የሰከርሽ ጊዜ 10 ብትሆን አለም
ኣላፊ አይጠፋበት ጎዳናው ምን ግዱ
ስትንገዳገጂ ቢቀናስ መንገዱ
ግዴለም ስከሪ
ቅጡን ያጣ መንደር በውሎ ትርምስ
ስትለፈልፊ ሰላሙስ ቢመለስ
ግዴለም እንጠጣ ግዴለም እንስከር
ሰበብ ስንፈልግ ተኳርፈን ከምንቀር
ግዴለም እንስከር...
@getmtg
@getmtg
አኮረፍሺኝ ብዬ እስኪነጋ ድረስ እጠጣልሻለሁ።
በተቀመጥኩበት ሌቱ እስከሚነጋ
በተፈጠርኩበት አለም እስኪረጋ
እሰክርልሻለሁ
ወንድ ልጅ አይደለሁ...
የላንቺ እንዳላልኩኝ ሴት ሁሉ አትፈጠር
ዛሬ ሰው አላውቅም ከ ኮማሪ በቀር
ደስታ እንደሞላኝ...
ቀ-ጭን ወገብሽን በጆቼ አቅፌ
ቅፅበቱ ይገርመኛል
ያረቄ መለኪያ ሲውል ከመዳፌ
የኮማሪት ገላ ሲኖር ከጉንፌ
ከትንፋሽሽ ውጪ አልሞቅም ያልኩኝ ሰው
ላረቄ ሽታ ነው ልቤ ሚናውዘው
ይምታታብኝ ያዘ
ያንቺና ያረቄው አመልና ነገር
ያንቺና መለኪያው አቋም አፈጣጠር
ብስቅ ብፈነድቅ ካንቺ ጋር አልነበር
ዛሬ አያምርብኝም ካልጠጣሁኝ በቀር
ካልሰከርኩኝ በቀር።
ተይ አታስኮንኚኝ
እንደ መጥፎ ቅዠት ደርሰሽ አታባኚኝ
ነይ እስኪ ልጋብዝሽ..
ትንሽ ጎንጨት በይ ይህን ካቲካላ
መውደዴን ቢያሳይሽ አስክሮ በመላ
ነይማ እንሞክረው...
ችለን ስንሔድበት የጣለንን መንገድ
ያሰምርልን እንደው ሰክሮ መንገዳገድ
ግድ የለም አትፍሪ ዝምብለን እንጠጣ
በዛ ከተባለ..
ብትወጂኝ ነውንጂ ሌላ ምን ሊመጣ።
ስካር የተባለ አንድ እንዳይቀርብሽ
አቅላችንን ስተን ሰፈር እንረብሽ
ማን ያውቃል
ስትሰክሪ ይሆናል 'ርምጃ ሚያምርብሽ።
ያዢና ፉት በይ እንጠጣ ገዴለም
የሰከርሽ ጊዜ 10 ብትሆን አለም
ኣላፊ አይጠፋበት ጎዳናው ምን ግዱ
ስትንገዳገጂ ቢቀናስ መንገዱ
ግዴለም ስከሪ
ቅጡን ያጣ መንደር በውሎ ትርምስ
ስትለፈልፊ ሰላሙስ ቢመለስ
ግዴለም እንጠጣ ግዴለም እንስከር
ሰበብ ስንፈልግ ተኳርፈን ከምንቀር
ግዴለም እንስከር...
@getmtg
@getmtg
👏5❤3👍2🥰1😍1
፡
።።።።።በእንተ ቅንዐት።።።።።።
መቼም! መቼም! አላቅ ዝቼም ፡
አላውቅም ተኩሼ ስቼም፣
ያባቴ ልጅ ፀጉሬ ጎፈር ፡
ያምላኬ ልጅ ገላዬ አፈር፣
ሰራሁ ብዬ ጠንከር ደፈር ፡
ሲሳካ መጠጡ ከንፈር፣
ሳብ አረጉኝ ትንሽ ጎተት ፡
ግን አልፈራም አስማት መተት፣
ትንቢት አናጋሪ ፡ እውነት አመስካሪ ፣
እኔው ነኝ ጠበቃው የቅዬው ተጠሪ ፣
አሳየሁት ለነገሌ ፡ ያለመውን ይዤ ግሌ፣
ገና ብዙ ታያላችሁ ፡
ክብሬ ዱዳ እስኪያረጋችሁ!
©Based on true story
✍️Zemed
@getmtg
@getmtg
።።።።።በእንተ ቅንዐት።።።።።።
መቼም! መቼም! አላቅ ዝቼም ፡
አላውቅም ተኩሼ ስቼም፣
ያባቴ ልጅ ፀጉሬ ጎፈር ፡
ያምላኬ ልጅ ገላዬ አፈር፣
ሰራሁ ብዬ ጠንከር ደፈር ፡
ሲሳካ መጠጡ ከንፈር፣
ሳብ አረጉኝ ትንሽ ጎተት ፡
ግን አልፈራም አስማት መተት፣
ትንቢት አናጋሪ ፡ እውነት አመስካሪ ፣
እኔው ነኝ ጠበቃው የቅዬው ተጠሪ ፣
አሳየሁት ለነገሌ ፡ ያለመውን ይዤ ግሌ፣
ገና ብዙ ታያላችሁ ፡
ክብሬ ዱዳ እስኪያረጋችሁ!
©Based on true story
✍️Zemed
@getmtg
@getmtg
🔥4❤3👏3
፡
ላየኝማ ......
ስፈግግ ደልቶኝ ይመስላል
ሳቀና ያልጎደለብኝ
ለቃኘኝ ለአይን ሞልቼ
እንደፈካሁኝ ታይቼ
ለእኔ ግን መች አማረብኝ
ባዶ ነው ሁለ ድባቡ
ተማምነውበት አለልኝ
ያሉት ሰው ሲታጣ ከጎን
ምን አለ ልብ የሚያጨልም
ሙሉነት እየናፈቁ
ሰው ከቦት ብቻ እንደመሆን
ተጓዝኩኝ በቀናው መንገድ
ወና ቤት መሆኔን ሳ'ቅ ነው
ተስቶኝ የምንገዳገድ
እረገጥኩ የእግዜር ደጁን
ዝምታው ቢበረታ እንኳ
አይተውምና ወዳጁን
፡
ከራስ ጋር መኗኗር ይዞት
ብቻነት ዙሯን ስታጦፍ ለፀና እየታገለ
ምንጊዜም ከርሞ እንዳዲስ
ሰው መቅረብ ያስፈራስ የለ?
ቀን ደርሶ ስኬት ሲለግስ
"ታድሎ" ሲሉ ሰማሁኝ
ለራሴ ከሰው ጎድዬ
በናቀኝ ባከበረኝ አፍ
ስመጥር ሆኜ ታማሁኝ
መች አዩትና የውስጤን
ወዳጁ በራቀው ቁጥር
ተዛዝኖ እንደጠቆረ
አብሮነት ትርጉሙን ሲያጣ
ያኔ ነው እንደ ልማዱ
............ ባዶነት ጓዙን ያቆረ፡፡
(ሀሳቡን በግጥም እንድፅፍለት ለጠየቀኝ ሰው ይድረስልኝ😊)
✍ Mekdi
@getmtg
@getmtg
ላየኝማ ......
ስፈግግ ደልቶኝ ይመስላል
ሳቀና ያልጎደለብኝ
ለቃኘኝ ለአይን ሞልቼ
እንደፈካሁኝ ታይቼ
ለእኔ ግን መች አማረብኝ
ባዶ ነው ሁለ ድባቡ
ተማምነውበት አለልኝ
ያሉት ሰው ሲታጣ ከጎን
ምን አለ ልብ የሚያጨልም
ሙሉነት እየናፈቁ
ሰው ከቦት ብቻ እንደመሆን
ተጓዝኩኝ በቀናው መንገድ
ወና ቤት መሆኔን ሳ'ቅ ነው
ተስቶኝ የምንገዳገድ
እረገጥኩ የእግዜር ደጁን
ዝምታው ቢበረታ እንኳ
አይተውምና ወዳጁን
፡
ከራስ ጋር መኗኗር ይዞት
ብቻነት ዙሯን ስታጦፍ ለፀና እየታገለ
ምንጊዜም ከርሞ እንዳዲስ
ሰው መቅረብ ያስፈራስ የለ?
ቀን ደርሶ ስኬት ሲለግስ
"ታድሎ" ሲሉ ሰማሁኝ
ለራሴ ከሰው ጎድዬ
በናቀኝ ባከበረኝ አፍ
ስመጥር ሆኜ ታማሁኝ
መች አዩትና የውስጤን
ወዳጁ በራቀው ቁጥር
ተዛዝኖ እንደጠቆረ
አብሮነት ትርጉሙን ሲያጣ
ያኔ ነው እንደ ልማዱ
............ ባዶነት ጓዙን ያቆረ፡፡
(ሀሳቡን በግጥም እንድፅፍለት ለጠየቀኝ ሰው ይድረስልኝ😊)
✍ Mekdi
@getmtg
@getmtg
👏6👍2❤1😭1
፡
በዜሮ ...
(አሌክስ አብርሃም)
አንድ ጓደኛየ መንጃ ፈቃድ አውጥቶ መኪና መንዳት በጀመረ በመጀመሪያው ቀን በሰላም በእግሬ ከምሄድበት ጠራኝና
"ና ግባ አደባባዮን ላሻግርህ" አለኝ
"ግዴለም በእግሬ እሻገራለሁ" አልኩ። ነዝንዞ አስገባኝና ጋቢና አስቀመጠኝ። መንግስትና ህዝብ ንዳ ብሎ ፈቃድ ከሰጠው እኔ ማነኝ ችሎታውን የምጠራጠር ብየ ተመቻቸሁ። ገና በሩን ከመዝጋቴ ስለመኪና ባህሪና ስለአነዳድ ቴክኒክ ልቤ እስኪደክም ያስረዳኝ ጀመር። ያለምንም ዓላማ ከተማችንን አንድ ጊዜ አዞረኝ። እስከዚህ ደህና ነበር።
"ይሄ ፍሬን ይባላል፣ ድንገተኛ ነገር ...ለምሳሌ ሰው ፣ አህያ ወይም የተናኘ ባል የሚነዳው መኪና ቢገቡብህ ማቆሚያ ነው" አለና አጎንብሶ ፍሬኑንን ይፈልግ ጀመረ...(ተናኘ ሹፌር ያገባች የቀድሞ ፍቅረኛው ናት፤ከነቂሙ ነው መንጃ ፈቃድ የያዘው?) "ፍሬኑን እስክትፈልግ ግን ....ከማለቴ ፍሬኑን አግኝቶ ባለ በሌለ ሀይሉ ረገጠው። ወደፊት ተወርውሬ የሆነ ነገር ጋር ተጋጭቸ ተመለስኩ። ዘና ብሎ "አሁን የገጨኸው ዳሽ ቦርድ ይባላል የትም አገር የሚያጋጥም ነገር ነው" አለና ቀጠለ። ደረቴን ደግፌ እያሳልኩ ዝም አልኩ።
ብቻ እንዲህ አሰቃይቶኝ በመጨረሻ "አንዲት ብዙ ሹፌሮች ያልባነኑባት ቴክኒክ ላሳይህ ወደፊት ይጠቅምህ ይሆናል" አለኝ። ወይ እዳየ። ከዚህ ሁሉ ለዓመታት የነዳ ሹፌር ተደብቆ ገና በአንድ ቀን ምን ተገልጦለት ይሆን እያልኩ ሳስብ በከተማችን አለ ወደሚባለው ቁልቁለት መንገድ ወሰደኝና "አሁን እዚህ ቁልቁለት ላይ ሞተሩን ታጠፋውና በዜሮ ትሄዳለህ ...መሪዋ ላይ ብቻ መጫወት ነው...ነዳጅ አተረፍክ ማለት ነው አባቴ" ብሎ ትልቅ ግኝት እንደነገረኝ አይነት በኩራት ሀሀሀሀሀ ብሎ ሳቀ። እኔ ግን ነፍሴ ተጨነቀች። መኪናው ወደታች ፍጥነት እየጨመረ መምዘግዘግ ጀመረ ። ወገኖቸ ባጭሩ ፍሬን ቢረግጥ ምን ቢረግጥ (እኔን ሁሉ እግሬን ቢረግጥ) መኪናው አልቆምም አለ። አታምኑኝም ዞር ስል የሹፌሩ በር ተከፍቶ አጅሬው ሲዘል ተገጣጠምን። ለደይቃወች ራሱን በሚነዳ መኪና ከተጓዝኩ በኋላ .... መኪናዋና እኔ ለግንባታ ፒራሚድ መስሎ የተከመረ አሸዋና ጠጠር ክምር ጫፍ ላይ ጉብ አልን። እዚህ ቴውድሮስ አደባባይ ያለውን የአፄ ቴውድሮስን የመድፍ ሀውልት ነበር የምንመስለው።
አሁን ያለንበትን የኑሮ ሁኔታ ሳየው፣ የሆነ ቴክኒክ ላሳያችሁ ብሎ ያሳፈረን ሹፌር ዘሎ የወረደ እስኪመስለኝ ቀላል እየተምዘገዘግን ነው?! ብቻ ማረፊያችንን ያሳምረው። ለእኔ በነጠላው የደረሰ አምላክ በጅምላ ይድረስልን።
@getmtg
@getmtg
በዜሮ ...
(አሌክስ አብርሃም)
አንድ ጓደኛየ መንጃ ፈቃድ አውጥቶ መኪና መንዳት በጀመረ በመጀመሪያው ቀን በሰላም በእግሬ ከምሄድበት ጠራኝና
"ና ግባ አደባባዮን ላሻግርህ" አለኝ
"ግዴለም በእግሬ እሻገራለሁ" አልኩ። ነዝንዞ አስገባኝና ጋቢና አስቀመጠኝ። መንግስትና ህዝብ ንዳ ብሎ ፈቃድ ከሰጠው እኔ ማነኝ ችሎታውን የምጠራጠር ብየ ተመቻቸሁ። ገና በሩን ከመዝጋቴ ስለመኪና ባህሪና ስለአነዳድ ቴክኒክ ልቤ እስኪደክም ያስረዳኝ ጀመር። ያለምንም ዓላማ ከተማችንን አንድ ጊዜ አዞረኝ። እስከዚህ ደህና ነበር።
"ይሄ ፍሬን ይባላል፣ ድንገተኛ ነገር ...ለምሳሌ ሰው ፣ አህያ ወይም የተናኘ ባል የሚነዳው መኪና ቢገቡብህ ማቆሚያ ነው" አለና አጎንብሶ ፍሬኑንን ይፈልግ ጀመረ...(ተናኘ ሹፌር ያገባች የቀድሞ ፍቅረኛው ናት፤ከነቂሙ ነው መንጃ ፈቃድ የያዘው?) "ፍሬኑን እስክትፈልግ ግን ....ከማለቴ ፍሬኑን አግኝቶ ባለ በሌለ ሀይሉ ረገጠው። ወደፊት ተወርውሬ የሆነ ነገር ጋር ተጋጭቸ ተመለስኩ። ዘና ብሎ "አሁን የገጨኸው ዳሽ ቦርድ ይባላል የትም አገር የሚያጋጥም ነገር ነው" አለና ቀጠለ። ደረቴን ደግፌ እያሳልኩ ዝም አልኩ።
ብቻ እንዲህ አሰቃይቶኝ በመጨረሻ "አንዲት ብዙ ሹፌሮች ያልባነኑባት ቴክኒክ ላሳይህ ወደፊት ይጠቅምህ ይሆናል" አለኝ። ወይ እዳየ። ከዚህ ሁሉ ለዓመታት የነዳ ሹፌር ተደብቆ ገና በአንድ ቀን ምን ተገልጦለት ይሆን እያልኩ ሳስብ በከተማችን አለ ወደሚባለው ቁልቁለት መንገድ ወሰደኝና "አሁን እዚህ ቁልቁለት ላይ ሞተሩን ታጠፋውና በዜሮ ትሄዳለህ ...መሪዋ ላይ ብቻ መጫወት ነው...ነዳጅ አተረፍክ ማለት ነው አባቴ" ብሎ ትልቅ ግኝት እንደነገረኝ አይነት በኩራት ሀሀሀሀሀ ብሎ ሳቀ። እኔ ግን ነፍሴ ተጨነቀች። መኪናው ወደታች ፍጥነት እየጨመረ መምዘግዘግ ጀመረ ። ወገኖቸ ባጭሩ ፍሬን ቢረግጥ ምን ቢረግጥ (እኔን ሁሉ እግሬን ቢረግጥ) መኪናው አልቆምም አለ። አታምኑኝም ዞር ስል የሹፌሩ በር ተከፍቶ አጅሬው ሲዘል ተገጣጠምን። ለደይቃወች ራሱን በሚነዳ መኪና ከተጓዝኩ በኋላ .... መኪናዋና እኔ ለግንባታ ፒራሚድ መስሎ የተከመረ አሸዋና ጠጠር ክምር ጫፍ ላይ ጉብ አልን። እዚህ ቴውድሮስ አደባባይ ያለውን የአፄ ቴውድሮስን የመድፍ ሀውልት ነበር የምንመስለው።
አሁን ያለንበትን የኑሮ ሁኔታ ሳየው፣ የሆነ ቴክኒክ ላሳያችሁ ብሎ ያሳፈረን ሹፌር ዘሎ የወረደ እስኪመስለኝ ቀላል እየተምዘገዘግን ነው?! ብቻ ማረፊያችንን ያሳምረው። ለእኔ በነጠላው የደረሰ አምላክ በጅምላ ይድረስልን።
@getmtg
@getmtg
😁7👏3❤2
፡
አለሽ ወይ
(በዕውቀቱ ስዩም)
አለሽ ወይ አለሽ ወይ
አለሽ ወይ በጤና
ይመስገን ደመና
በገበሬው አጥንት መሬቴን እያረስኩ
እንጀራ ሲጠፋ ገበሬ እየጎረስኩ
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ደመና
ሰው ሲያፈርስ እያየሁ ሰው ሆኖ ቡልዶዘር
አንዱ ጭቃ ነገድ ሌላው የብረት ዘር
በፈረሰ ሰው ላይ በቆመ ሰገነት
ሲዖል አናቱ ላይ በታነፀ ገነት
ይኽን ኑሮ ብለው ጥቂቶች ሲኖሩ
ያለምንም ፀፀት ያለምንም ሃፍረት
ይህንን እያየሁ በታላቅ ፅሞና
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ዳመና
በምቾት መዲና የምንዱባን ትዝብት
እንደ ሀሩር ልፎኝ
በጠዳው ጎዳና
ለማኝ ብላቴና
እንደ ጉቶ አናቅፎኝ
ሃፍረት እንደ ዝናር ከፊት ከኋላ ኣቅፎኝ
ልክ እንደ ገባሮች ለመኖር እያቀድሁ
በጌቶች መሶብም እጄን እየሰደድሁ
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ደመና
ወይ በሩን አሳዪን ወይ ጠቁሚን መላ
ማዕበል ሲቃረብ ያመልጣል ሺመላ
በነፋስ ገፅ ፊት ይሸሻል ደመና
የኔ አዚም ያለበት ያ’ገሬ ሰው ግና
በስጋ ደም አጥንት የተሰራ አይመስል
እንደ ኮንሶ ሃውልት የመቃብር ምስል
አይሸሽ አያባርር ወይ አይተነፍስ ቃል
እንጨት ሆኖ ቆሞ ሰደድ ይጠብቃል
ይህንን እያየሁ
ሁኘ በጥሞና
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ደመና
አንቺ ግን አለሽ ወይ እኔ አለሁ በደህና
አለሁ ግርምት ወሮኝ
ምላሱን በምላጭ እንደተሰለበ
ምናገረው ኖሮኝ
የምለው ቸግሮኝ።
@getmtg
@getmtg
አለሽ ወይ
(በዕውቀቱ ስዩም)
አለሽ ወይ አለሽ ወይ
አለሽ ወይ በጤና
ይመስገን ደመና
በገበሬው አጥንት መሬቴን እያረስኩ
እንጀራ ሲጠፋ ገበሬ እየጎረስኩ
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ደመና
ሰው ሲያፈርስ እያየሁ ሰው ሆኖ ቡልዶዘር
አንዱ ጭቃ ነገድ ሌላው የብረት ዘር
በፈረሰ ሰው ላይ በቆመ ሰገነት
ሲዖል አናቱ ላይ በታነፀ ገነት
ይኽን ኑሮ ብለው ጥቂቶች ሲኖሩ
ያለምንም ፀፀት ያለምንም ሃፍረት
ይህንን እያየሁ በታላቅ ፅሞና
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ዳመና
በምቾት መዲና የምንዱባን ትዝብት
እንደ ሀሩር ልፎኝ
በጠዳው ጎዳና
ለማኝ ብላቴና
እንደ ጉቶ አናቅፎኝ
ሃፍረት እንደ ዝናር ከፊት ከኋላ ኣቅፎኝ
ልክ እንደ ገባሮች ለመኖር እያቀድሁ
በጌቶች መሶብም እጄን እየሰደድሁ
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ደመና
ወይ በሩን አሳዪን ወይ ጠቁሚን መላ
ማዕበል ሲቃረብ ያመልጣል ሺመላ
በነፋስ ገፅ ፊት ይሸሻል ደመና
የኔ አዚም ያለበት ያ’ገሬ ሰው ግና
በስጋ ደም አጥንት የተሰራ አይመስል
እንደ ኮንሶ ሃውልት የመቃብር ምስል
አይሸሽ አያባርር ወይ አይተነፍስ ቃል
እንጨት ሆኖ ቆሞ ሰደድ ይጠብቃል
ይህንን እያየሁ
ሁኘ በጥሞና
አለሁኝ በደህና
ይመስገን ደመና
አንቺ ግን አለሽ ወይ እኔ አለሁ በደህና
አለሁ ግርምት ወሮኝ
ምላሱን በምላጭ እንደተሰለበ
ምናገረው ኖሮኝ
የምለው ቸግሮኝ።
@getmtg
@getmtg
❤3👏2