፡
ናፍቀሽኛል .......
የወሰደኝ የወሰደሽ
አራንባና ቆቦ መንገድ
ሩቅ ሆኖ ቢያራርቀን
የእኔና አንቺ መገናኛ
ሰአትና ቀን አለቱ
መች ይቀራል ሲናፍቀን
ሁሌም ከአይኔ ድቅን ይላል
በእውነት ፀዳል የተሞላው
የተዋበ ምሉዕ መልክሽ
ያለሽ ለዛ መች ይጠፋል
ቅን እሳቤሽ ያ ቁምነገር
ጨዋታና ደስታ ሳቅሽ
ሰርክ እንዲህ ነው የኔ ልማድ
ሌቱ ነግቶ አንቺን ማሰብ
የጀመርኩኝ ጧት ማለዳ
በናፍቆትሽ ቀኑን ውዬ
አንቺን ሳስብ አመሻለሁ
ፍቅሬ የኔ ፅጌሬዳ
ቀን ቅጠሪ ቀን ወስኚ
ልቤ ይረፍ ከሀሳቡ
አፎይ ልበል እረፍት ይቅናኝ
አረ እቱ ናፍቀሽኛል
ነይ ከደጄ ልጠየቅሽ
ልምጣ ደጅሽ እንገናኝ
....... ናፍቀሽኛል .......
@getmtg
@getmtg
ናፍቀሽኛል .......
የወሰደኝ የወሰደሽ
አራንባና ቆቦ መንገድ
ሩቅ ሆኖ ቢያራርቀን
የእኔና አንቺ መገናኛ
ሰአትና ቀን አለቱ
መች ይቀራል ሲናፍቀን
ሁሌም ከአይኔ ድቅን ይላል
በእውነት ፀዳል የተሞላው
የተዋበ ምሉዕ መልክሽ
ያለሽ ለዛ መች ይጠፋል
ቅን እሳቤሽ ያ ቁምነገር
ጨዋታና ደስታ ሳቅሽ
ሰርክ እንዲህ ነው የኔ ልማድ
ሌቱ ነግቶ አንቺን ማሰብ
የጀመርኩኝ ጧት ማለዳ
በናፍቆትሽ ቀኑን ውዬ
አንቺን ሳስብ አመሻለሁ
ፍቅሬ የኔ ፅጌሬዳ
ቀን ቅጠሪ ቀን ወስኚ
ልቤ ይረፍ ከሀሳቡ
አፎይ ልበል እረፍት ይቅናኝ
አረ እቱ ናፍቀሽኛል
ነይ ከደጄ ልጠየቅሽ
ልምጣ ደጅሽ እንገናኝ
....... ናፍቀሽኛል .......
@getmtg
@getmtg
👏7❤3
፡
TMRO
ሰባራ ያፈሳል ያለፈ ይረሳል
ውሃ ከ'ሳት ሲጣድ በ100 ይፈላል
የጠበቁት ቀርቶ የዘሩት ይበቅላል
ይሄንን ተምረን ሀገር ልናቀና
...........ስንል ደፋቀና
ህልምህን ተከተል የልብህን ፈልግ
ያፈቀረን መቅጫ
ህይወት የላትም ህግ
ይሄንን ተምረን ሀገር ልናሳድግ
......... ስንል ቁጭብድግ
ያ ሁሉ አለፈና ኮሌጅ በጥሰን
ለመቃብር ጉድጓድ ህይወት ልትምሰን
ህግን እንድንሽር
ኃፂአትን እንድንምር በተሰጠን ስልጣን
የሰበሰብነው ብር አደረገን ሰይጣን
እንኳን ሀገር ማቅናት ማሳደጉ ቀርቶ
ሀብታችን ሆነብን 'ያንገት ላይ ቀበቶ፡፡😊
✍ zemed
@getmtg
@getmtg
TMRO
ሰባራ ያፈሳል ያለፈ ይረሳል
ውሃ ከ'ሳት ሲጣድ በ100 ይፈላል
የጠበቁት ቀርቶ የዘሩት ይበቅላል
ይሄንን ተምረን ሀገር ልናቀና
...........ስንል ደፋቀና
ህልምህን ተከተል የልብህን ፈልግ
ያፈቀረን መቅጫ
ህይወት የላትም ህግ
ይሄንን ተምረን ሀገር ልናሳድግ
......... ስንል ቁጭብድግ
ያ ሁሉ አለፈና ኮሌጅ በጥሰን
ለመቃብር ጉድጓድ ህይወት ልትምሰን
ህግን እንድንሽር
ኃፂአትን እንድንምር በተሰጠን ስልጣን
የሰበሰብነው ብር አደረገን ሰይጣን
እንኳን ሀገር ማቅናት ማሳደጉ ቀርቶ
ሀብታችን ሆነብን 'ያንገት ላይ ቀበቶ፡፡😊
✍ zemed
@getmtg
@getmtg
👍6👏4❤1
፡
መልካም ነገር ይዉጣን
ጤነኛን መመረዝ የሞተን ሰው ማከም
ወዳጅን አጣልቶ ለማስታረቅ መድከም
ከበግ መሀል ቆሞ የቀበሮ ጸሎት
በእጅ አዙሪት ገድለው የዓዞ እንባ ቢያነቡት
ማንም ከእውነት ቢሸሽ ባድር ባይ ሆዱ
ይዘገያል እንጅ መች ይቀራል ፍርዱ
እናት ዶሮን ገድሎ ጭልፊት አባራሪ
አባት ገደል ገፍቶ የሙት ልጆች ጧሪ
የማስመሰል ኑሮ የሞት መንገድ ይብቃን
ክፋትን ሞከርነዉ መልካም ነገር ይውጣን፡፡
(ህሊና ደሳለኝ)
መልካም ነገር ይዉጣን
ጤነኛን መመረዝ የሞተን ሰው ማከም
ወዳጅን አጣልቶ ለማስታረቅ መድከም
ከበግ መሀል ቆሞ የቀበሮ ጸሎት
በእጅ አዙሪት ገድለው የዓዞ እንባ ቢያነቡት
ማንም ከእውነት ቢሸሽ ባድር ባይ ሆዱ
ይዘገያል እንጅ መች ይቀራል ፍርዱ
እናት ዶሮን ገድሎ ጭልፊት አባራሪ
አባት ገደል ገፍቶ የሙት ልጆች ጧሪ
የማስመሰል ኑሮ የሞት መንገድ ይብቃን
ክፋትን ሞከርነዉ መልካም ነገር ይውጣን፡፡
(ህሊና ደሳለኝ)
👏9
፡
ከእኔ እርቀሽ ከሄድሽማ
ተመለሺ አልልሽም
ምክንያቱም .......
ቀድሞም ከእኔ አልነበርሽም
...... በሀሳብማ .......
ሄደሽ ነበር
ተነሽ ነበር ጠፍተሽ ነበር
ልብሽ ከዛ ሆኖ ሳለ
ምን ያደርጋል ከዚህ ቅሪ
አትሂጂ ብሎ ነገር
ጨርቅ ሆኖልሽ ምድረ መሬት
ይመችሽ ሂጂ ግዴለም
ቢመሽ እንኳን የንጋት ቀን
ለኔ የሌለ ሆኖ አይደለም
ወዳሻሽ ጓዝሽን ውሰጅ
ተጠጊ ከምኞት ህልምሽ
ብቻ ግን ልቤን መልሺ
ሸክሙ እንዳያደክምሽ
@getmtg
@getmtg
ከእኔ እርቀሽ ከሄድሽማ
ተመለሺ አልልሽም
ምክንያቱም .......
ቀድሞም ከእኔ አልነበርሽም
...... በሀሳብማ .......
ሄደሽ ነበር
ተነሽ ነበር ጠፍተሽ ነበር
ልብሽ ከዛ ሆኖ ሳለ
ምን ያደርጋል ከዚህ ቅሪ
አትሂጂ ብሎ ነገር
ጨርቅ ሆኖልሽ ምድረ መሬት
ይመችሽ ሂጂ ግዴለም
ቢመሽ እንኳን የንጋት ቀን
ለኔ የሌለ ሆኖ አይደለም
ወዳሻሽ ጓዝሽን ውሰጅ
ተጠጊ ከምኞት ህልምሽ
ብቻ ግን ልቤን መልሺ
ሸክሙ እንዳያደክምሽ
@getmtg
@getmtg
❤4👏3🔥1
🧔🧑 መስተ-ዋድድ
አስማት ቢሉሽ አስማት...የማዋደድ የማስማማት
ለፃምራ ልብ የቀመምኳት... መስተፋቅር ጥበቤ ናት
........
በዝቅታ ከፍታዬ ተሰብሬ የጠገንሁት
በቂም በቀል ካራ ስለት ተወግቼ ያተረፍኩት
በደም ጅረት በሞት ባህር ሰምጬ ያንሳፈፍኩት
አለት...ብረት ያልሰበረው አስማት ያልሁሽ ትግስቴን ነው።
ጠላቶቼን ማቀልጥበት
እኔነቴን የሳልሁበት
ተአምራት የሆነበት
ችግር ማጣት ያልበተነው
አስማት ያልሁሽ እምነቴን ነው።
ደናግላን የተሳሉት
ቆነጃጅት የሞቱለት
የወንድነት አርማ ምልክት የሆነው
አስማት ያልሁሸ ውበቴን ነው ።
......እና የኔዋ
ገላሽ ከገላዬ የተጣመረበት
ደምሽም ከደሜ የተዋሀደበት
ጸንተን የቆምንበት ትናንትናን ዛሬ
ፍቅራችን ተባርኮ ያፈራነው ፍሬ
በዚህ ቅዱስ አስማት በዚህ መስተዋድድ
ዘመንሽ ዘመኔ ፩ ይሆንልን ዘንድ ...አሜን!
✍️zemed
@getmtg
@getmtg
አስማት ቢሉሽ አስማት...የማዋደድ የማስማማት
ለፃምራ ልብ የቀመምኳት... መስተፋቅር ጥበቤ ናት
........
በዝቅታ ከፍታዬ ተሰብሬ የጠገንሁት
በቂም በቀል ካራ ስለት ተወግቼ ያተረፍኩት
በደም ጅረት በሞት ባህር ሰምጬ ያንሳፈፍኩት
አለት...ብረት ያልሰበረው አስማት ያልሁሽ ትግስቴን ነው።
ጠላቶቼን ማቀልጥበት
እኔነቴን የሳልሁበት
ተአምራት የሆነበት
ችግር ማጣት ያልበተነው
አስማት ያልሁሽ እምነቴን ነው።
ደናግላን የተሳሉት
ቆነጃጅት የሞቱለት
የወንድነት አርማ ምልክት የሆነው
አስማት ያልሁሸ ውበቴን ነው ።
......እና የኔዋ
ገላሽ ከገላዬ የተጣመረበት
ደምሽም ከደሜ የተዋሀደበት
ጸንተን የቆምንበት ትናንትናን ዛሬ
ፍቅራችን ተባርኮ ያፈራነው ፍሬ
በዚህ ቅዱስ አስማት በዚህ መስተዋድድ
ዘመንሽ ዘመኔ ፩ ይሆንልን ዘንድ ...አሜን!
✍️zemed
@getmtg
@getmtg
❤5👍3🔥1
እነሆ አዲስ የግጥም አልብም በ ዮሃንስ ዘካርያስ!!!!!
አልበሙ Youtube ላይ በራሱ ቻናል ተለቋል። አዲስ ቻናል ነው እና ገብታችሁ በግጥሞቹ ከመደመም በተጨማሪ ሌሎች አዳዲስ ግጥሞች እንዲደርሷችሁ Subscribe እና Like በማድረግ አበረታቱት።
https://www.youtube.com/playlist?list=PLVYalcpBgjm-jByhJ2rvwUbNh1xEBp23d
አልበሙ Youtube ላይ በራሱ ቻናል ተለቋል። አዲስ ቻናል ነው እና ገብታችሁ በግጥሞቹ ከመደመም በተጨማሪ ሌሎች አዳዲስ ግጥሞች እንዲደርሷችሁ Subscribe እና Like በማድረግ አበረታቱት።
https://www.youtube.com/playlist?list=PLVYalcpBgjm-jByhJ2rvwUbNh1xEBp23d
👍4
፡
እቺን ቃል ንገሯት
ተፈርዶብኝ እንጂ
መለየት ተስኖኝ ጥሬውን ከብስል
ሀገሬው ምድር ላይ
እሷ ብቻ ቆንጆ የቀረች ይመስል
ዞር ባለች ቁጥር
አትራቂኝ እያልኩኝ የምለማመጣት
ልቻለው ብዬ እንጂ
ምሳሌ ከምሆን አፍቅሮ ከማጣት
.... ገደል ግቢ በሏት ....
ይሄው ደግሞ ዛሬ
ገላዋን በሙሉ አወደችው ሎሽን
ፀጉሯን አጎፈረች ደመቀች በሽንሽን
ከንፈሯን ምን ይሆን ደግሞ የቀባችው
የእጇን አይበሉባ በቄንጥ
አኮናትራ ሰአቷን አየችው
ገናነው መሰለኝ ጊዜን ታዘበችው
መንቀር አለችና መስታወት ፊት ቆመች
ደግሞ ፈገግ አለች ጥርሷ ይርገፍና።
......ማርያምን ታምራለች
ዘከርኳት በወዳች መከርኳት በዘመድ
ቀለበት አይጠቅማት አሰርኳት በገመድ
.... ገደል ግቢ በሏት .....
ልቤን ከጋረደው
ወዳጅ ከከለላት ስውር አይነጥላ
እንዲ እዳማረባት
መሄድ ከጀመረች አፍቃሪ ሰውጥላ
ልክ እደገላዋ
ይለስልስ መንገዱ
ፍፁም አይጎርብጣት
አየሩ በሙሉ ፍክት ይበልላት
እንደ ጥርሷ ንጣት
እያልኩኝ ፎክሬ
እንደ ገጣሚ ቃል ልቤ አልጀነጅን
የት አባቷንና
በፀበል ካልወጣች ትረሳለች በጅን
..... ገደል ግቢ በሏት ......
የት አባቷን እና እንዲህ የሚያምርባት
የት እናቷን እና እንዲህ የሚደምቅባት
.... ገደል ግቢ በሏት ......
እስከ መቼ ድረስ
ስቀባ እኖራለው ጉድፍ ልቧን ስኩል
ገደል ግቢ በሏት .....
እኔ ገደል ስር ነኝ
ድንገት ከወደቀች በቆሻሻዉ በኩል
(አስታወሰኝ ረጋሳ)
እቺን ቃል ንገሯት
ተፈርዶብኝ እንጂ
መለየት ተስኖኝ ጥሬውን ከብስል
ሀገሬው ምድር ላይ
እሷ ብቻ ቆንጆ የቀረች ይመስል
ዞር ባለች ቁጥር
አትራቂኝ እያልኩኝ የምለማመጣት
ልቻለው ብዬ እንጂ
ምሳሌ ከምሆን አፍቅሮ ከማጣት
.... ገደል ግቢ በሏት ....
ይሄው ደግሞ ዛሬ
ገላዋን በሙሉ አወደችው ሎሽን
ፀጉሯን አጎፈረች ደመቀች በሽንሽን
ከንፈሯን ምን ይሆን ደግሞ የቀባችው
የእጇን አይበሉባ በቄንጥ
አኮናትራ ሰአቷን አየችው
ገናነው መሰለኝ ጊዜን ታዘበችው
መንቀር አለችና መስታወት ፊት ቆመች
ደግሞ ፈገግ አለች ጥርሷ ይርገፍና።
......ማርያምን ታምራለች
ዘከርኳት በወዳች መከርኳት በዘመድ
ቀለበት አይጠቅማት አሰርኳት በገመድ
.... ገደል ግቢ በሏት .....
ልቤን ከጋረደው
ወዳጅ ከከለላት ስውር አይነጥላ
እንዲ እዳማረባት
መሄድ ከጀመረች አፍቃሪ ሰውጥላ
ልክ እደገላዋ
ይለስልስ መንገዱ
ፍፁም አይጎርብጣት
አየሩ በሙሉ ፍክት ይበልላት
እንደ ጥርሷ ንጣት
እያልኩኝ ፎክሬ
እንደ ገጣሚ ቃል ልቤ አልጀነጅን
የት አባቷንና
በፀበል ካልወጣች ትረሳለች በጅን
..... ገደል ግቢ በሏት ......
የት አባቷን እና እንዲህ የሚያምርባት
የት እናቷን እና እንዲህ የሚደምቅባት
.... ገደል ግቢ በሏት ......
እስከ መቼ ድረስ
ስቀባ እኖራለው ጉድፍ ልቧን ስኩል
ገደል ግቢ በሏት .....
እኔ ገደል ስር ነኝ
ድንገት ከወደቀች በቆሻሻዉ በኩል
(አስታወሰኝ ረጋሳ)
👏6👍1
.............ቅኔ ዘ ብልሁ ............
ውስጤ ቢተራመስ ጎዶሎዬ ጎልቶ፣
ማስተዋል ቢርቀኝ ልቤ ገደል ገብቶ፣
ምነው ከጦር ሜዳው አላየነው ቀርቶ፣
ተቀምጧል ከሩቁ ተደብቆ ፈርቶ፣
ስመ-አርዱ አፍራሰ-ፍርዱ፣
ሰናስል-ቋዱ መፃዝዝ-ክንዱ፣
የተባልኩቱ ...........
.......ቃል አናጋሪ በትረ-ሰሎሞን፣
ብለው ፎከሩ ፈታው ዝናሩን ጣለው በትሩን፣
ምን ቢሉ ቢያብጠለጥሉ ቅሉ ግድ አይሰጠኝ፣
እንኳን ቅሉ ቀርቶ ቅቤው አያድጠኝ፣
......[(የቅቤ ቅል እንዲሉ)].........
......ግና የሚሉት ሁሉ እውነትነቱን አስረዳኝ ብባል፣
ፍርሀት አይደል ወይ አቅም ማጣት፣
ጠላቴን መቅበር ለኔ ቀላል ነው ነጭ እንደማንጣት፣
ለራሴ ስል ነው ሁሉን የተውኩት ፣
ስለተማርኩኝ አንበሳ ሲያረጅ ከኃይሉ ሲጎል ፣
ባጎረሰው ጅብ በመራው መንጋ እንደሚገደል።
ለዛነው !
ፍቺ
[ሰናስል=ሰንሰለት]
[ መፃዝዝ=ተፈጥሮተ እሳት]
[አርዱ=አስፈሪው]
[አፍራሰ ፍርዱ= የፍርድ ፈረሶች የተገሩለት]
✍️Zemed
@getmtg
@getmtg
ውስጤ ቢተራመስ ጎዶሎዬ ጎልቶ፣
ማስተዋል ቢርቀኝ ልቤ ገደል ገብቶ፣
ምነው ከጦር ሜዳው አላየነው ቀርቶ፣
ተቀምጧል ከሩቁ ተደብቆ ፈርቶ፣
ስመ-አርዱ አፍራሰ-ፍርዱ፣
ሰናስል-ቋዱ መፃዝዝ-ክንዱ፣
የተባልኩቱ ...........
.......ቃል አናጋሪ በትረ-ሰሎሞን፣
ብለው ፎከሩ ፈታው ዝናሩን ጣለው በትሩን፣
ምን ቢሉ ቢያብጠለጥሉ ቅሉ ግድ አይሰጠኝ፣
እንኳን ቅሉ ቀርቶ ቅቤው አያድጠኝ፣
......[(የቅቤ ቅል እንዲሉ)].........
......ግና የሚሉት ሁሉ እውነትነቱን አስረዳኝ ብባል፣
ፍርሀት አይደል ወይ አቅም ማጣት፣
ጠላቴን መቅበር ለኔ ቀላል ነው ነጭ እንደማንጣት፣
ለራሴ ስል ነው ሁሉን የተውኩት ፣
ስለተማርኩኝ አንበሳ ሲያረጅ ከኃይሉ ሲጎል ፣
ባጎረሰው ጅብ በመራው መንጋ እንደሚገደል።
ለዛነው !
ፍቺ
[ሰናስል=ሰንሰለት]
[ መፃዝዝ=ተፈጥሮተ እሳት]
[አርዱ=አስፈሪው]
[አፍራሰ ፍርዱ= የፍርድ ፈረሶች የተገሩለት]
✍️Zemed
@getmtg
@getmtg
👏6❤5🤔1
፡
ያማል!
(በሰለሞን ሳህለ)
እና እንደነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ
የነፍሰጡርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ
ባልታሰበ ናዳ ተመቶ እንደመድቀቅ
ከተስፋ ጉልላት ተከፍቶ እንደመውደቅ
ተአምር በበዛባት በዚች ቧልተኛ አለም
ከዚህ የበለጠ ምንም ህመም የለም
አውቶቢሱ ያማል
ሚኒባሱ ያማል
ላዳ ታክሲው ያማል
የማይጎል የሰው ጎርፍ ደራሽ ማዕበሉ
የእንባ ቅጥልጥሉ
ምን ብዬ ልንገርሽ ያማል ይሄ ሁሉ(2)
እና እንደነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥረው ካረፈደ
የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥረው ካረፈደ
ነገር ተበላሸ
ህመም ተወለደ ጨጓራ በገነ
እሳት በእንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ሁሉም ተቀይሮ ተተካ በሲቃ
ምን ብዬ ልንገርሽ ይሄም ያማል በቃ
ወጪ ተራማጁ
አስመሳይ ሰጋጁ
ፀሀዩ ዝናቡ
የለምን ምክንያት የለምን ሰበቡ
ተቆራጭ አበባ ሊቆረጥ ማበቡ
ውል የለሽ ደመና ተራራን መክበቡ
እልፍ አእላፍ ኮከብ ጨረቃን ማጀቡ
ደግሞ ለእሷ ግጥም እናቷን ጨረቃ
ምን ብዬ ልንገርሽ ይሄም ያማል በቃ
.... እናቷን ጨረቃ ....
እና እንደነገርኩሽ
ጉንጭ የማትሞላ ኬክ 10 ብር የሸጠ
የካፌ አሳላፊ ወደኔ አፈጠጠ
ዘይት የነካውን መንታ እጁን አጣምሮ
ምን ልታዘዝ ይላል ቁልቁል አቀርቅሮ
ምን ልታዘዝ ይላል(2)
እንዴት ቅጥሉ ሰው ቅጥሉን ሰው ያዛል
ማኪያቶ ልዘዝ?
ካፕቺኑ ልዘዝ?
ጥቁር ቡና ልዘዝ?
ለምን ሰው አላዝም?
መታዘዝ መናዘዝ ርግማን የሆነው
ካፌውን ሲያሳልፍ
እራሱ ግን የሚያልፍ
ቁልቁል አቀርቅሮ
ሞቱን በአንገት ቀብሮ
ምን ልታዘዝ ይላል
አንድ ካፕቺኖ ከአንድ እሷ ጋር ልበል?
አንድ ጥቁር ቡና ከአንድ እሷ ጋር ልበል?
ከማኪያቶ ጋር እሷን አምጣ ልበል?
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
እና እንደነገርኩሽ
የላስቲክ አበባ የአርቲ ቡርቲ ስዕል
የጭቃ እሾህ ወግቶት እዥ ያወጣ ቁስል
ትልቁ ነቀዝ ሰው የማንቀዙን ያህል
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
እና እነንደነገርኩሽ ......
የሚወዱትን ሰው ቀጥረው ካረፈደ
የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
ነገር ተበላሸ
ህመም ተወለደ ጨጓራ በገነ
እሳት እንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ሁሉም ተቀድሮ ተተካ በሲቃ
ምን ብዬ ልነንገርሽ ይሄም ያማል በቃ
እና እንደነገርኩሽ .......
ላንቺ የያዝኩት አበባ መጠውለግ አመጣ
ፀሀይ ገባ ወጣ
ዝናብ ቀረት መጣ
ጨረቃም የለችም
እናቷን ስላልኳት
ደግሜ ሰድቤ ሺ አመት እንዳይገርማት
እናቷን
እናቷን ጨረቃ
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄም ያማል በቃ
እናቷ ግን ማነች
እናቷን ጨረቃ
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄም ያልፋል በቃ
ግን ......
እኔ አንቺን ስወድሽ
ይሄን ሁሉ ችዬ ነው የምጠብቅሽ
ቢሆንም ግን ያማል!
@getmtg
@getmtg
ያማል!
(በሰለሞን ሳህለ)
እና እንደነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥሮ እንደመጠበቅ
የነፍሰጡርን ሞት አይቶ እንደመሳቀቅ
ባልታሰበ ናዳ ተመቶ እንደመድቀቅ
ከተስፋ ጉልላት ተከፍቶ እንደመውደቅ
ተአምር በበዛባት በዚች ቧልተኛ አለም
ከዚህ የበለጠ ምንም ህመም የለም
አውቶቢሱ ያማል
ሚኒባሱ ያማል
ላዳ ታክሲው ያማል
የማይጎል የሰው ጎርፍ ደራሽ ማዕበሉ
የእንባ ቅጥልጥሉ
ምን ብዬ ልንገርሽ ያማል ይሄ ሁሉ(2)
እና እንደነገርኩሽ
የሚወዱትን ሰው ቀጥረው ካረፈደ
የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥረው ካረፈደ
ነገር ተበላሸ
ህመም ተወለደ ጨጓራ በገነ
እሳት በእንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ሁሉም ተቀይሮ ተተካ በሲቃ
ምን ብዬ ልንገርሽ ይሄም ያማል በቃ
ወጪ ተራማጁ
አስመሳይ ሰጋጁ
ፀሀዩ ዝናቡ
የለምን ምክንያት የለምን ሰበቡ
ተቆራጭ አበባ ሊቆረጥ ማበቡ
ውል የለሽ ደመና ተራራን መክበቡ
እልፍ አእላፍ ኮከብ ጨረቃን ማጀቡ
ደግሞ ለእሷ ግጥም እናቷን ጨረቃ
ምን ብዬ ልንገርሽ ይሄም ያማል በቃ
.... እናቷን ጨረቃ ....
እና እንደነገርኩሽ
ጉንጭ የማትሞላ ኬክ 10 ብር የሸጠ
የካፌ አሳላፊ ወደኔ አፈጠጠ
ዘይት የነካውን መንታ እጁን አጣምሮ
ምን ልታዘዝ ይላል ቁልቁል አቀርቅሮ
ምን ልታዘዝ ይላል(2)
እንዴት ቅጥሉ ሰው ቅጥሉን ሰው ያዛል
ማኪያቶ ልዘዝ?
ካፕቺኑ ልዘዝ?
ጥቁር ቡና ልዘዝ?
ለምን ሰው አላዝም?
መታዘዝ መናዘዝ ርግማን የሆነው
ካፌውን ሲያሳልፍ
እራሱ ግን የሚያልፍ
ቁልቁል አቀርቅሮ
ሞቱን በአንገት ቀብሮ
ምን ልታዘዝ ይላል
አንድ ካፕቺኖ ከአንድ እሷ ጋር ልበል?
አንድ ጥቁር ቡና ከአንድ እሷ ጋር ልበል?
ከማኪያቶ ጋር እሷን አምጣ ልበል?
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
እና እንደነገርኩሽ
የላስቲክ አበባ የአርቲ ቡርቲ ስዕል
የጭቃ እሾህ ወግቶት እዥ ያወጣ ቁስል
ትልቁ ነቀዝ ሰው የማንቀዙን ያህል
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄ ሁሉ ያማል
እና እነንደነገርኩሽ ......
የሚወዱትን ሰው ቀጥረው ካረፈደ
የሚያፈቅሩትን ሰው ቀጥሮ ካረፈደ
ነገር ተበላሸ
ህመም ተወለደ ጨጓራ በገነ
እሳት እንፋሎት መልክ በእህታ ተነነ
የሚሆነው ሳይሆን የማይሆነው ሆነ
ሁሉም ተቀድሮ ተተካ በሲቃ
ምን ብዬ ልነንገርሽ ይሄም ያማል በቃ
እና እንደነገርኩሽ .......
ላንቺ የያዝኩት አበባ መጠውለግ አመጣ
ፀሀይ ገባ ወጣ
ዝናብ ቀረት መጣ
ጨረቃም የለችም
እናቷን ስላልኳት
ደግሜ ሰድቤ ሺ አመት እንዳይገርማት
እናቷን
እናቷን ጨረቃ
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄም ያማል በቃ
እናቷ ግን ማነች
እናቷን ጨረቃ
ተይ አታስለፍልፊኝ ይሄም ያልፋል በቃ
ግን ......
እኔ አንቺን ስወድሽ
ይሄን ሁሉ ችዬ ነው የምጠብቅሽ
ቢሆንም ግን ያማል!
@getmtg
@getmtg
❤7👏5
.........ዘ-ተቃራኒ........
እኔ የምወዳት ቁመት የምበልጣት፣
እኔ የምወዳት ገንዘብ የማልሰጣት፣
እኔ የምወዳት ምርጥ ባለሙያ የኪቺኗ እመቤት፣
እኔ የምወዳት መልኳ ስዕል አድን፣
ሲያዩአት የምታክም የምትፈውስ በድን ፣
እኔ የምወዳት በኔ የምትረጋ፣
ትቶኝ ይሄድ ይሆን? ብላ የምትሰጋ፣
................
እኔን የምትወደኝ ወርቅ ቆፋሪዋ (gold digger)፣
እኔን የምትወደኝ ዋሌት ፈርፋሪዋ፣
እኔን የምትወደኝ ቁመቷ ቀጀላ፣
ከኔጋ ተጋድማ ተጨማሪ ሚያምራት የሌላ .....
እኔን የምትወደኝ ወጡን አገንፍታ እንጀራ የምትከትፍ፣
በወጣሁ በገባሁ በነገር የምትለክፍ፣
እኔን የምትወደኝ መልኳ ፎጣ መሳይ፣
እንኳን ለጀለሶች ለናቴም አላሳይ።
ምነው ጌታዬ?
✍️Zemed
@getmtg
@getmtg
እኔ የምወዳት ቁመት የምበልጣት፣
እኔ የምወዳት ገንዘብ የማልሰጣት፣
እኔ የምወዳት ምርጥ ባለሙያ የኪቺኗ እመቤት፣
እኔ የምወዳት መልኳ ስዕል አድን፣
ሲያዩአት የምታክም የምትፈውስ በድን ፣
እኔ የምወዳት በኔ የምትረጋ፣
ትቶኝ ይሄድ ይሆን? ብላ የምትሰጋ፣
................
እኔን የምትወደኝ ወርቅ ቆፋሪዋ (gold digger)፣
እኔን የምትወደኝ ዋሌት ፈርፋሪዋ፣
እኔን የምትወደኝ ቁመቷ ቀጀላ፣
ከኔጋ ተጋድማ ተጨማሪ ሚያምራት የሌላ .....
እኔን የምትወደኝ ወጡን አገንፍታ እንጀራ የምትከትፍ፣
በወጣሁ በገባሁ በነገር የምትለክፍ፣
እኔን የምትወደኝ መልኳ ፎጣ መሳይ፣
እንኳን ለጀለሶች ለናቴም አላሳይ።
ምነው ጌታዬ?
✍️Zemed
@getmtg
@getmtg
😁6❤5😭2👍1👏1