፡
ሩብ ጉዳይ(የሳምሽኝ ልጅ)
በሰለሞን ሳህለ
ነፍሴን ከነፍስሽ አጣምረሽ
የአለም ጥግ ላይ ያኖርሽው
ሩብ ጉዳይ የሳምሽኝ ልጅ
ጥበቡን ከየት ተማርሽው
እውነት እውነት
ከንፈርሽ በጣም ልዩ ነው
የሜንት ጠረን ታድሏል
ሰሞኑን የሳምሺው ጉንጬ
አየር ማስገባት ጀምሯል
በሩብሽ እንዲህ የሆነው
የጉንጬ ከንፈር ጥጉ
በሙሉ ቢሆን ኖሮማ
ልቤና ነፍሴ ተማክረው
እኔኑ ጥለውኝ ባረጉ
እውነት እውነት
ለካንስ የመሳም ጥበብ
እጅጉን እጅግ ተራቋል
በሜንት ጠረን ታጅቦ
በሩብ ጉዳይ ልብ ይሰልባል
እኔ እምልሽ
ይሄ የምሄድበት ጎዳና
ጠረኑ በሜንት የናኘው
ንፋሱንም ልክ እንደኔ
ሩብ ጉዳይ ስመሽው ነው?
እውነት እውነት
የምጠጣው የእግዜር ውሀ
ጠአም መልኩ ተቀይሯል
ግድየለችም አትደብቂኝ
ውሀውንም ስመሽዋል
ከሳሙስ አይቀር እንዲህ ነው
ለስለስ አርጎ ሸረፍ አርጎ
መአዛ ጠረን ደባልቆ
በከንፈር አብሾ ልኮ
እንዴነችና ሩብ ጉዳይ ወፈፍ አረገኝ እኮ
እናልሽ ከሳምሽኝ በኋላ
ለሩብ ጉዳይ እጅ ሰጠሁ
ሰአቱ ሙሉ ሆኖ እንኳን
ሩብ ጉዳይ ነው እላለሁ
እውነት እውነት
ከመስታወት ፊት ቆሜ
በውስጡ እኔን እያየሁ
መተት አርጋብኝ ይሆን
እያልኩ እጠይቃለሁ
የጉንጬን የከንፈሬን ጥግ
በእጆቼ እዳብሳለሁ
የዳበስኩትን እጄን
ሩብ ጉዳይ እስመዋለሁ
ወይ ጣጣዬ ወይ መከራ
ግድ የለሽም ልለምንሽ
ግድ የለሽም ተለመኝኝ
አንድ ያጣላል ወዳጄ ሆይ
ሩብ ጉዳይ አንዴ ሳሚኝ
@getmtg
@getmtg
ሩብ ጉዳይ(የሳምሽኝ ልጅ)
በሰለሞን ሳህለ
ነፍሴን ከነፍስሽ አጣምረሽ
የአለም ጥግ ላይ ያኖርሽው
ሩብ ጉዳይ የሳምሽኝ ልጅ
ጥበቡን ከየት ተማርሽው
እውነት እውነት
ከንፈርሽ በጣም ልዩ ነው
የሜንት ጠረን ታድሏል
ሰሞኑን የሳምሺው ጉንጬ
አየር ማስገባት ጀምሯል
በሩብሽ እንዲህ የሆነው
የጉንጬ ከንፈር ጥጉ
በሙሉ ቢሆን ኖሮማ
ልቤና ነፍሴ ተማክረው
እኔኑ ጥለውኝ ባረጉ
እውነት እውነት
ለካንስ የመሳም ጥበብ
እጅጉን እጅግ ተራቋል
በሜንት ጠረን ታጅቦ
በሩብ ጉዳይ ልብ ይሰልባል
እኔ እምልሽ
ይሄ የምሄድበት ጎዳና
ጠረኑ በሜንት የናኘው
ንፋሱንም ልክ እንደኔ
ሩብ ጉዳይ ስመሽው ነው?
እውነት እውነት
የምጠጣው የእግዜር ውሀ
ጠአም መልኩ ተቀይሯል
ግድየለችም አትደብቂኝ
ውሀውንም ስመሽዋል
ከሳሙስ አይቀር እንዲህ ነው
ለስለስ አርጎ ሸረፍ አርጎ
መአዛ ጠረን ደባልቆ
በከንፈር አብሾ ልኮ
እንዴነችና ሩብ ጉዳይ ወፈፍ አረገኝ እኮ
እናልሽ ከሳምሽኝ በኋላ
ለሩብ ጉዳይ እጅ ሰጠሁ
ሰአቱ ሙሉ ሆኖ እንኳን
ሩብ ጉዳይ ነው እላለሁ
እውነት እውነት
ከመስታወት ፊት ቆሜ
በውስጡ እኔን እያየሁ
መተት አርጋብኝ ይሆን
እያልኩ እጠይቃለሁ
የጉንጬን የከንፈሬን ጥግ
በእጆቼ እዳብሳለሁ
የዳበስኩትን እጄን
ሩብ ጉዳይ እስመዋለሁ
ወይ ጣጣዬ ወይ መከራ
ግድ የለሽም ልለምንሽ
ግድ የለሽም ተለመኝኝ
አንድ ያጣላል ወዳጄ ሆይ
ሩብ ጉዳይ አንዴ ሳሚኝ
@getmtg
@getmtg
👏6😁2
፡
አንደበቴ ፈርቶ
ፍቅሬን ሳልናገር እንዳለሁት አለሁ
እንዴት እንደው ሳላውቅ
'ለምን?'ታው ሳይገባኝ ብቻ እወድሻለሁ
እንደማይዳስሱት
ሊነካ እንደማይችል ከፍ ያለ ሩቅ ሰማይ
በውበቷ ደምቀው
ይኖሩባት እንጂ
እንደማይጨብጧት የንጋቷ ፀሀይ
እንደማይደርሱበት
አያልቅ ሩቅ መንገድ
እንዳልደፈረሰ
እንዳዲስ ምንጭ ውሃ
ሲሆን የኔ መውደድ
ልክ እንደ ሰአሊ
ጥበብ የለኝ ነገር ከሸራው አልሳልኩሽ
ወይ እንደ ደራሲ
ውብ ቃላት ከትቤ ፅፌ አላወደስኩሽ
ብቻ ግን በሩቁ
የአንቺ መሆን ናፍቆኝ ውበትሽን እያየሁ
ዛሬም በዝምታ
ሳልናገር ፍቅሬን እንዳለሁት አለሁ
ብቻ እወድሻለሁ
@getmtg
@getmtg
አንደበቴ ፈርቶ
ፍቅሬን ሳልናገር እንዳለሁት አለሁ
እንዴት እንደው ሳላውቅ
'ለምን?'ታው ሳይገባኝ ብቻ እወድሻለሁ
እንደማይዳስሱት
ሊነካ እንደማይችል ከፍ ያለ ሩቅ ሰማይ
በውበቷ ደምቀው
ይኖሩባት እንጂ
እንደማይጨብጧት የንጋቷ ፀሀይ
እንደማይደርሱበት
አያልቅ ሩቅ መንገድ
እንዳልደፈረሰ
እንዳዲስ ምንጭ ውሃ
ሲሆን የኔ መውደድ
ልክ እንደ ሰአሊ
ጥበብ የለኝ ነገር ከሸራው አልሳልኩሽ
ወይ እንደ ደራሲ
ውብ ቃላት ከትቤ ፅፌ አላወደስኩሽ
ብቻ ግን በሩቁ
የአንቺ መሆን ናፍቆኝ ውበትሽን እያየሁ
ዛሬም በዝምታ
ሳልናገር ፍቅሬን እንዳለሁት አለሁ
ብቻ እወድሻለሁ
@getmtg
@getmtg
👏8👍2
፡
ትመጫለሽ ብዬ
አካላቴን በእንዶድ
ልብሴን በእቃ ሽቦ ወንዙ ዳር አነጣሁ
ትመጫለሽ ብዬ
ስፀልይ ለማደር
'ቀጨኔ' ሚካኤል ተራራ ላይ ወጣሁ
ፀለይኩ እስኪነጋ
እንባየ በዥቅዥቅ
ጉቶ ሜዳ ድረስ መሬቱን አራሰው
እንዲህ ሆኖ ቢያገኙት
አይከፋም ነበር ያፈቀሩትን ሰው
ቀጨኔ የኔ እንባና ኳስ
የዋንጫ!
ይኸው የዛን ለሊት
ይኸው የዛን ለሊት
ባስለቀሽኝ እንባ
ደጋፊው በሙሉ ደርሶ አቀረቀረ
'የማርገጃ' ቡድን
መሬት በሰብሶበት
ከ'መቀጠያ' ጋር ኳስ መጋጠም ቀረ
ቀረ ቀረ ቀረ!
(አስታወሰኝ ረጋሳ)
ትመጫለሽ ብዬ
አካላቴን በእንዶድ
ልብሴን በእቃ ሽቦ ወንዙ ዳር አነጣሁ
ትመጫለሽ ብዬ
ስፀልይ ለማደር
'ቀጨኔ' ሚካኤል ተራራ ላይ ወጣሁ
ፀለይኩ እስኪነጋ
እንባየ በዥቅዥቅ
ጉቶ ሜዳ ድረስ መሬቱን አራሰው
እንዲህ ሆኖ ቢያገኙት
አይከፋም ነበር ያፈቀሩትን ሰው
ቀጨኔ የኔ እንባና ኳስ
የዋንጫ!
ይኸው የዛን ለሊት
ይኸው የዛን ለሊት
ባስለቀሽኝ እንባ
ደጋፊው በሙሉ ደርሶ አቀረቀረ
'የማርገጃ' ቡድን
መሬት በሰብሶበት
ከ'መቀጠያ' ጋር ኳስ መጋጠም ቀረ
ቀረ ቀረ ቀረ!
(አስታወሰኝ ረጋሳ)
👍4👏2
፡
እንዴት እንደመጣሁ
እንዳትጠይቂኝ
ለምን? ............ ስለምትናፍንቂኝ፡፡
አውቀዋለሁኛ
አንድ የበደለሽ ሰው ናፍቀሺኛል ቢልሽ
ላንቺ
ፌዝ ነው የሚመስልሽ
...... ግን ናፍቀሽኛል
አዎ .......
በድያለሁ በግፍ
ደግሞም ናፍቀሽኛል በእጥፍ
ማርያምን የምሬን በዝቷል መናፈቄ
የትም እገኛለሁ
የትም እስቃለሁ ግን ያለቅሳል ሳቄ
ብራመድ በሀገሩ
ብክንፍ እንኳ ብበር
ተከፍቶ አያለሁ ቆለፍኩት ያልኩት በር
ቀን የከረቸምኩት
ሌት በምን ከፈትኩት?
በለሊትሽ መጣሁ
አለሜን ስላጣሁ
ከትናንት የባሰ እንደማጣሽ ሳስብ
በደሌን አየሁት እጥፍ መውደድ ሲስብ
አንቺዬዋ ወዴ
የበደለ ሁሉ አይናፍቅም እንዴ ....
ማቀፍ እንኳ ባልችል ምሕረት ባለምንም
አትሳቂብኝ እንጂ
ግጥሙን እያነበብኩ ናፍቀሽኝ አሁንም
ፀሀይዋን ከተትኳት
አይንሽን ለማየት ከቤቴ እየወጣሁ
የበደለ አይኔን እንዳታይኝ ብዬ
በጨለማ መጣሁ
ደረስኩኝ ከደጅሽ መፍራቴ በነነ
እሰይ አገኘሁሽ ናፍቆቴ ሰው ሆነ
እከንፋለሁ ይኸው ስደርስም አልሳምሺኝ
አጃኢብ ሰው መሆን
ሳጠፋ ጊዜ ነው ጭራሽ የናፈቅሽኝ
አጥፍቻለሁ አዎ መውደዴን ቀብሬ
አትሳቂብኝ እንጂ
ልክ ስበድልሽ ጨመረብኝ ፍቅሬ፡፡
.... ናፈቅሽኝ ...
(ኤልያስ ሽታሁን)
እንዴት እንደመጣሁ
እንዳትጠይቂኝ
ለምን? ............ ስለምትናፍንቂኝ፡፡
አውቀዋለሁኛ
አንድ የበደለሽ ሰው ናፍቀሺኛል ቢልሽ
ላንቺ
ፌዝ ነው የሚመስልሽ
...... ግን ናፍቀሽኛል
አዎ .......
በድያለሁ በግፍ
ደግሞም ናፍቀሽኛል በእጥፍ
ማርያምን የምሬን በዝቷል መናፈቄ
የትም እገኛለሁ
የትም እስቃለሁ ግን ያለቅሳል ሳቄ
ብራመድ በሀገሩ
ብክንፍ እንኳ ብበር
ተከፍቶ አያለሁ ቆለፍኩት ያልኩት በር
ቀን የከረቸምኩት
ሌት በምን ከፈትኩት?
በለሊትሽ መጣሁ
አለሜን ስላጣሁ
ከትናንት የባሰ እንደማጣሽ ሳስብ
በደሌን አየሁት እጥፍ መውደድ ሲስብ
አንቺዬዋ ወዴ
የበደለ ሁሉ አይናፍቅም እንዴ ....
ማቀፍ እንኳ ባልችል ምሕረት ባለምንም
አትሳቂብኝ እንጂ
ግጥሙን እያነበብኩ ናፍቀሽኝ አሁንም
ፀሀይዋን ከተትኳት
አይንሽን ለማየት ከቤቴ እየወጣሁ
የበደለ አይኔን እንዳታይኝ ብዬ
በጨለማ መጣሁ
ደረስኩኝ ከደጅሽ መፍራቴ በነነ
እሰይ አገኘሁሽ ናፍቆቴ ሰው ሆነ
እከንፋለሁ ይኸው ስደርስም አልሳምሺኝ
አጃኢብ ሰው መሆን
ሳጠፋ ጊዜ ነው ጭራሽ የናፈቅሽኝ
አጥፍቻለሁ አዎ መውደዴን ቀብሬ
አትሳቂብኝ እንጂ
ልክ ስበድልሽ ጨመረብኝ ፍቅሬ፡፡
.... ናፈቅሽኝ ...
(ኤልያስ ሽታሁን)
👏6👍1🔥1
፡
አልፎ_አልፎ_መሞት
ሰው ......
አንድም - በእግዜር
አንድም - በመውዜር
እያዋሀደ የዕድሜውን አመል
ማታ በውስኪ ጠዋት በጠበል
ሰው ቢያጣ መንገድ
ሰው ቢያጣ ምርጫ
ተከፋፍለው ተስፋን ለቅርጫ
ተመዳደቡብኝ የመኖሬን ኮታ
አንድ ላይ ለበሱት ነፍሴን እንደኩታ
እኔ ግን ......
ይጥቀማቸው ብዬ አልተወው መኖሬን
ብረግፍም አለሁኝ እድሜ ይስጠው ስሬን
ሰው .....
ይመስለዋል እንጂ መተንፈስ አክራሞት
ስንቱን ያሻግራል አልፎ አልፎ መሞት።
(ኤልያስ ሽታሁን)
አልፎ_አልፎ_መሞት
ሰው ......
አንድም - በእግዜር
አንድም - በመውዜር
እያዋሀደ የዕድሜውን አመል
ማታ በውስኪ ጠዋት በጠበል
ሰው ቢያጣ መንገድ
ሰው ቢያጣ ምርጫ
ተከፋፍለው ተስፋን ለቅርጫ
ተመዳደቡብኝ የመኖሬን ኮታ
አንድ ላይ ለበሱት ነፍሴን እንደኩታ
እኔ ግን ......
ይጥቀማቸው ብዬ አልተወው መኖሬን
ብረግፍም አለሁኝ እድሜ ይስጠው ስሬን
ሰው .....
ይመስለዋል እንጂ መተንፈስ አክራሞት
ስንቱን ያሻግራል አልፎ አልፎ መሞት።
(ኤልያስ ሽታሁን)
👏7🤔1
፡
ናፍቀሽኛል .......
የወሰደኝ የወሰደሽ
አራንባና ቆቦ መንገድ
ሩቅ ሆኖ ቢያራርቀን
የእኔና አንቺ መገናኛ
ሰአትና ቀን አለቱ
መች ይቀራል ሲናፍቀን
ሁሌም ከአይኔ ድቅን ይላል
በእውነት ፀዳል የተሞላው
የተዋበ ምሉዕ መልክሽ
ያለሽ ለዛ መች ይጠፋል
ቅን እሳቤሽ ያ ቁምነገር
ጨዋታና ደስታ ሳቅሽ
ሰርክ እንዲህ ነው የኔ ልማድ
ሌቱ ነግቶ አንቺን ማሰብ
የጀመርኩኝ ጧት ማለዳ
በናፍቆትሽ ቀኑን ውዬ
አንቺን ሳስብ አመሻለሁ
ፍቅሬ የኔ ፅጌሬዳ
ቀን ቅጠሪ ቀን ወስኚ
ልቤ ይረፍ ከሀሳቡ
አፎይ ልበል እረፍት ይቅናኝ
አረ እቱ ናፍቀሽኛል
ነይ ከደጄ ልጠየቅሽ
ልምጣ ደጅሽ እንገናኝ
....... ናፍቀሽኛል .......
@getmtg
@getmtg
ናፍቀሽኛል .......
የወሰደኝ የወሰደሽ
አራንባና ቆቦ መንገድ
ሩቅ ሆኖ ቢያራርቀን
የእኔና አንቺ መገናኛ
ሰአትና ቀን አለቱ
መች ይቀራል ሲናፍቀን
ሁሌም ከአይኔ ድቅን ይላል
በእውነት ፀዳል የተሞላው
የተዋበ ምሉዕ መልክሽ
ያለሽ ለዛ መች ይጠፋል
ቅን እሳቤሽ ያ ቁምነገር
ጨዋታና ደስታ ሳቅሽ
ሰርክ እንዲህ ነው የኔ ልማድ
ሌቱ ነግቶ አንቺን ማሰብ
የጀመርኩኝ ጧት ማለዳ
በናፍቆትሽ ቀኑን ውዬ
አንቺን ሳስብ አመሻለሁ
ፍቅሬ የኔ ፅጌሬዳ
ቀን ቅጠሪ ቀን ወስኚ
ልቤ ይረፍ ከሀሳቡ
አፎይ ልበል እረፍት ይቅናኝ
አረ እቱ ናፍቀሽኛል
ነይ ከደጄ ልጠየቅሽ
ልምጣ ደጅሽ እንገናኝ
....... ናፍቀሽኛል .......
@getmtg
@getmtg
👏7❤3
፡
TMRO
ሰባራ ያፈሳል ያለፈ ይረሳል
ውሃ ከ'ሳት ሲጣድ በ100 ይፈላል
የጠበቁት ቀርቶ የዘሩት ይበቅላል
ይሄንን ተምረን ሀገር ልናቀና
...........ስንል ደፋቀና
ህልምህን ተከተል የልብህን ፈልግ
ያፈቀረን መቅጫ
ህይወት የላትም ህግ
ይሄንን ተምረን ሀገር ልናሳድግ
......... ስንል ቁጭብድግ
ያ ሁሉ አለፈና ኮሌጅ በጥሰን
ለመቃብር ጉድጓድ ህይወት ልትምሰን
ህግን እንድንሽር
ኃፂአትን እንድንምር በተሰጠን ስልጣን
የሰበሰብነው ብር አደረገን ሰይጣን
እንኳን ሀገር ማቅናት ማሳደጉ ቀርቶ
ሀብታችን ሆነብን 'ያንገት ላይ ቀበቶ፡፡😊
✍ zemed
@getmtg
@getmtg
TMRO
ሰባራ ያፈሳል ያለፈ ይረሳል
ውሃ ከ'ሳት ሲጣድ በ100 ይፈላል
የጠበቁት ቀርቶ የዘሩት ይበቅላል
ይሄንን ተምረን ሀገር ልናቀና
...........ስንል ደፋቀና
ህልምህን ተከተል የልብህን ፈልግ
ያፈቀረን መቅጫ
ህይወት የላትም ህግ
ይሄንን ተምረን ሀገር ልናሳድግ
......... ስንል ቁጭብድግ
ያ ሁሉ አለፈና ኮሌጅ በጥሰን
ለመቃብር ጉድጓድ ህይወት ልትምሰን
ህግን እንድንሽር
ኃፂአትን እንድንምር በተሰጠን ስልጣን
የሰበሰብነው ብር አደረገን ሰይጣን
እንኳን ሀገር ማቅናት ማሳደጉ ቀርቶ
ሀብታችን ሆነብን 'ያንገት ላይ ቀበቶ፡፡😊
✍ zemed
@getmtg
@getmtg
👍6👏4❤1
፡
መልካም ነገር ይዉጣን
ጤነኛን መመረዝ የሞተን ሰው ማከም
ወዳጅን አጣልቶ ለማስታረቅ መድከም
ከበግ መሀል ቆሞ የቀበሮ ጸሎት
በእጅ አዙሪት ገድለው የዓዞ እንባ ቢያነቡት
ማንም ከእውነት ቢሸሽ ባድር ባይ ሆዱ
ይዘገያል እንጅ መች ይቀራል ፍርዱ
እናት ዶሮን ገድሎ ጭልፊት አባራሪ
አባት ገደል ገፍቶ የሙት ልጆች ጧሪ
የማስመሰል ኑሮ የሞት መንገድ ይብቃን
ክፋትን ሞከርነዉ መልካም ነገር ይውጣን፡፡
(ህሊና ደሳለኝ)
መልካም ነገር ይዉጣን
ጤነኛን መመረዝ የሞተን ሰው ማከም
ወዳጅን አጣልቶ ለማስታረቅ መድከም
ከበግ መሀል ቆሞ የቀበሮ ጸሎት
በእጅ አዙሪት ገድለው የዓዞ እንባ ቢያነቡት
ማንም ከእውነት ቢሸሽ ባድር ባይ ሆዱ
ይዘገያል እንጅ መች ይቀራል ፍርዱ
እናት ዶሮን ገድሎ ጭልፊት አባራሪ
አባት ገደል ገፍቶ የሙት ልጆች ጧሪ
የማስመሰል ኑሮ የሞት መንገድ ይብቃን
ክፋትን ሞከርነዉ መልካም ነገር ይውጣን፡፡
(ህሊና ደሳለኝ)
👏9
፡
ከእኔ እርቀሽ ከሄድሽማ
ተመለሺ አልልሽም
ምክንያቱም .......
ቀድሞም ከእኔ አልነበርሽም
...... በሀሳብማ .......
ሄደሽ ነበር
ተነሽ ነበር ጠፍተሽ ነበር
ልብሽ ከዛ ሆኖ ሳለ
ምን ያደርጋል ከዚህ ቅሪ
አትሂጂ ብሎ ነገር
ጨርቅ ሆኖልሽ ምድረ መሬት
ይመችሽ ሂጂ ግዴለም
ቢመሽ እንኳን የንጋት ቀን
ለኔ የሌለ ሆኖ አይደለም
ወዳሻሽ ጓዝሽን ውሰጅ
ተጠጊ ከምኞት ህልምሽ
ብቻ ግን ልቤን መልሺ
ሸክሙ እንዳያደክምሽ
@getmtg
@getmtg
ከእኔ እርቀሽ ከሄድሽማ
ተመለሺ አልልሽም
ምክንያቱም .......
ቀድሞም ከእኔ አልነበርሽም
...... በሀሳብማ .......
ሄደሽ ነበር
ተነሽ ነበር ጠፍተሽ ነበር
ልብሽ ከዛ ሆኖ ሳለ
ምን ያደርጋል ከዚህ ቅሪ
አትሂጂ ብሎ ነገር
ጨርቅ ሆኖልሽ ምድረ መሬት
ይመችሽ ሂጂ ግዴለም
ቢመሽ እንኳን የንጋት ቀን
ለኔ የሌለ ሆኖ አይደለም
ወዳሻሽ ጓዝሽን ውሰጅ
ተጠጊ ከምኞት ህልምሽ
ብቻ ግን ልቤን መልሺ
ሸክሙ እንዳያደክምሽ
@getmtg
@getmtg
❤4👏3🔥1