የግጥም ጥግ
769 subscribers
56 photos
2 videos
7 files
39 links
ያ ዶሮዬ ጮኈ መንጋቱን ነገረኝ፥
ሲነጋጋ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ።

የተለያዩ ምርጥ ግጥሞችን እዚህ

ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት

@Esamif
@amen1995 መጠየቅና መስጠት ይችላሉ።
Download Telegram

"ደህና ነህ ወይ?" ስለው
‎ሁሉ እንደሞላለት "ደህና ነኝ" ይለኛል
‎ለዚህ ጥያቄ መልስ
‎ተመሳሳይ ውሸት
‎"ደህና ነኝ" መሆኑን ቀድሞ አሳውቆኛል

‎የእውነት ደህና አይደለም .......

‎ምን ሆንክ እንዳልለው
‎ ምንም ነው መልሱ
‎አትዋሽ እንዳልል
‎ 'ለምን'ታ ነው ክሱ

‎ጭንቁን በፈገግታው
‎ሊሸፍን ቢቃጣም
‎ እንደተረበሸ ያስታውቅበታል
‎ይህ ጊዜ አደብ ገዝቶ
‎ተስፋው ያነሳው 'ለት
‎ሳይሰስት ከልቡ ሲያልፍ ይስቀበታል

‎ (መቼ እንደሚያልፍ ባላውቅም)

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👏9👍31

ተፈጥሮን ደጅ ልጥና

" እኔ ልሙትልሽ" እያልኩኝ አልምልም
ቃላቴን መንዝሬ፤ ለሞት ቀብድ አልከፍልም

ያኔ ትዝ ይልሻል?
"ራስህን ግደል" ብለሽ በረኪና የላክሽልኝ ጊዜ
እድሜ ለስጦታሽ፤ ታጠበ ሸሚዜ።

ገደብ ጫፍ በሌለው፤ በልቤ መጋዘን
ቢታጨቅ መከራ፤ ቢጠራቀም ሀዘን

"ባለፈልኝ" እንጂ "በሞትኩ" ብየ አላቅም
ካልጋ ላይ ነው እንጂ፤ ከፎቅ ላይ አልወድቅም።

በሀኪሙ ስተት፤ በቁሜ ብከፈን
በወርድ በቁመቴ፤ ሳጥኔ ቢደፈን

ከጭስ እቀጥናለሁ፤ እኔ መውጫ አላጣም
በጠጅ በወይን አገር፤ ሽጉጤን አልጠጣም።

የተመደበልኝ ዘመን ከባከነ
የተሰፈረልኝ፤ ቀን አልቆ ከሆነ

ተፈጥሮን ደጅ ልጥና
ባዲስ መንገድ ትስራኝ፤
ባዲስ የፍጥረት ውል
መስኮትሽ ላይ ሆና

ስትዘምር የምትውል ድንቢጥ ወፍ ታድርገኝ
ብኖር አንቺን አየሁ፤ ከመሞት ምን ሊገኝ።

        (በእውቀቱ ስዩም)
👏7

ካንተ ጋ እንዳልኖርኩኝ
‎ቀን መለየት ቆጥሮ ብቸኛም ቢያደርገኝ
‎ሳስብ ይቆጨኛል
‎መቼም ያንተን ያህል ሰው እንደማላገኝ

‎መች ይጠፋና ነው
‎የአነጋገር ለዛህ የአንተነትህ ምስል
‎መራቅህ ነው እንጂ
‎በጭንቅ ያማቀቀኝ የዘራብኝ ቁስል

‎መች ይረሳና ነው
‎ያለፍንበት ትላንት ያሳለፍነው ጊዜ
‎ዛሬን ጎኔ ባትሆን
‎ከፍቶኝ መሽቶ ነጋ ዋልኩኝ በትካዜ

‎ፍቅርህ ባይቆርጥልኝ
‎አንተነትክን ስራብ
‎             ናፍቆት ባይሆነኝ መልስ
‎እያልኩ አስባለሁ
‎ምናል ያ ደግ ቀን ዳግሙን ቢመለስ

@getmtg
@getmtg
👍7

ተው ብዬህ ነበረ ......

‎እጅህን ከእሳት
‎ልብህን ከክፋት ከቶ እንዳታስጠጋ
‎መቃጠል መንደድ ነው
‎ይኮንናል እንጂ አይሰጥህም ፀጋ

‎ውስጥህ ካላመነ
‎ዝም ማለት ልመድ አፍህ አይቀባጥር
‎ብቅል ብቻ አይደለ
‎ሰውም ያወጣዋል የሆድህን ሚስጥር

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👏6

ናፍቀኸኛል

‎አይኔን ስገልጥ
የሚታየኝ ያንተ ምስል
‎ሆኛለሁኝ በናፍቆትህ
‎ጠዋት ማታ እየጠቆርኩ የምከስል

‎መንገድ ጊዜ ቢያለያየን
‎ ትዝታህ ነው ለኔ ስንቄ
‎አይግረምህ ዛሬን ሳጣህ
‎ በናፍቆትህ መንሰቅሰቄ

‎የሄድኩበት የሄድክበት
‎ እንደው ወዴት አደረሰን
‎ምን እንደሆን ያንተን ባላውቅ
‎ ያሳለፍነው እልፍ ፍቅር
‎ ይመስለኛል የከሰሰን

‎ናፍቀኸኛል

‎ከከደንኩት የአይኔ ሽፋን
‎ ያንተ ምስል የገለጠው
‎መለየትን በመርሳት ልክ
‎ አንተነትክን መች ለወጠው

‎ምናልባቱን ከናፈኩህ
‎ ፈጥነህ መቼ ትመጣለህ
‎ራቅከኝ እንጂ አልወጣህም
‎ ዛሬም እኮ ከውስጤ አለህ

@getmtg
@getmtg
👍6

ቅናቴ
‎ (በአበባው መላኩ)

‎ፍቅሬን ሜዳ ላይ ጥላ
‎ ስትከዳኝ አይቻታለሁ
‎እንደገፋችኝ ትገፋ
‎ እያልኩ እረግማታለሁ

‎ዘወትር ሙሾ ታላዝን
‎ የእንባ ማዕበል ይጠባት
‎ደስታዬን እንዳጨለመች
‎ ደስታዋ ይጨልምባት
‎ሺህ እጥፍ ትጨድ አበሳ
‎ ለዘራችብኝ ጥፋት

‎ እያልኩ እረግማታለሁ(2)

‎የኮራችበትን ገላ
‎ መብረቅ ያንድደው በቁጣ
‎በላይዋ ዲም ይውረድባት
‎ ጥጋት መሸሻ ትጣ

‎ እያልኩ እረግማታለሁ(2)

‎የምድር የቀላይ ጥፋት
‎ በላዩዋ ይውረድ ኩነኔ
‎ኑሮዋን ሲኦል ያድርገው
‎ ስቃዩዋን የያሳየኝ በአይኔ

‎እንደከዳችኝ ትከዳ
‎ የኔ ያለችው ይሽሻት
‎ቀላዋጭ አይኗን ያፍርጠው
‎ ከውካዋ እግሯን ያልምሻት

‎ እያልኩ እረግማታለሁ(2)

‎ክንዷ በመጅ ይሰበር
‎ ሌላ ያቀፈችበት
‎አባጨጓራ ይሙላው
‎ ፍራሹ የተኛችበት

‎ እያልኩ እረግማታለሁ(2)
የሌላ ሆና ብትከዳኝ
‎ አይጠሉ ጠልቻታለሁ

‎ስለ ማህተቤ ብጠየቅ
‎ከአለም ላይ ካለኝ የምሻው
‎ የረገምኳትን እላለሁ
‎ሌላም እርካታም የለኝ
‎ እሷን አምጡልኝ እላለሁ

‎ጥላቻዬና ፍቅሬ ናት
‎ እርግማንና በረከቴ
‎ያለሷ ህይወት የሌለኝ
‎ ያሳበደችን ቅናቴ

‎ ቅናቴ

‎ ቅናቴ

@getmtg
@getmtg
👏5👍1

ከሄድኩማ ርቄ
‎ማወቅ አልፈልግም
‎የመወደዴን ልክ የመውደዴን መጠን
‎ሳለን ነበር እንጂ
‎ስንሆን በአንድ መንገድ
‎ ትርጉም የሚሰጠን

‎ካለዚያማ .....
‎ሀሳብ እዛ እና እዚህ አራምባና ቆቦ
‎ህይወት ፍሬ ምርቷ
‎ መቼ ያምርና ነው
‎ ስሩ ያልተነቀለ አረም ተሰብስቦ

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍6👏4

የንፁህ ደም በየቀዬው እንደኩሬ ይንሳፈፋል
ስንቱ ተስፋ የሰነቀ መንፈቅ እድሜ ሳይኖር ያልፋል
ለሰርጉ ቀን የተከሉት እንሶስላው አልበቀለም
እንኳን ወልዶ መሳም ቀርቶ ወጥቶ መግባት አልቀለለም

ቀኔ ደርሶ ከሰው እኩል በድኔን ዶዘር እሲኪያነሳው
  ( ይህንን ቃል እንዳልረሳው!)

ጩኽት ብቻ ነጋ ጠባ ዋይታ ብቻ መሸም ነጋም
መኖር ፍፁም አያጓጓም
በየ ደጁ በየ ጓዳው የሲቃ ድምፅ ሲያስገመግም
ምንም ተስፋ በሌለበት ተስፋ ማድረግ አልፈልግም

አታልቅሺ አትዘኚ  በድኔን ከሞት ላታስነሺው
ቢሆንም ግን (ይህንን ቃል እንዳትረሺው)

ሳልደነቅፍ _ ሳልሸራርፍ   አንዲት ፊደል ሳልሳሳት
ያሰብኩትን ሳልናገር  አፈር ልቤን አይቅመሳት
ታሪክ ህልሜን _ ገላ ጨርቄን  ጉድጓድ አፈር ሳይቀበል 
  አንዴ ብቻ ይህን ልበል!

የጥም ውሃ ባያጠጡኝ  ህመም ቁስሌን ባያክሙት
እንደምንም አንዴ ብቻ "ወድሻለሁ" ብዬ ልሙት።

        እወድሻለሁ

(አስታወሰኝ_ረጋሳ)
👏7

"ማን ለ ማን?" ያሉኝ 'ለት
‎ ካላልኩ እኔ ለእኔ
‎ለካ ምንም ነው
‎አለሁ ያልኩበት ቃል
‎ ኖርኩ ያልኩበት ወኔ

‎ላላንስ ያኮሰሱኝ
‎ልችል አጣጥለው ዝግ አርገው ቢነጉዱ
‎አላወቁም ኖሯል
‎ከአፍ አፍታ በላይ
‎ተግባር እንደሆነ ብርቱ ሰው መንገዱ😊

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍51👏1

ሩብ ጉዳይ(የሳምሽኝ ልጅ)
‎ በሰለሞን ሳህለ

‎ነፍሴን ከነፍስሽ አጣምረሽ
‎ የአለም ጥግ ላይ ያኖርሽው
‎ሩብ ጉዳይ የሳምሽኝ ልጅ
‎ ጥበቡን ከየት ተማርሽው

‎እውነት እውነት
‎ከንፈርሽ በጣም ልዩ ነው
‎ የሜንት ጠረን ታድሏል
‎ሰሞኑን የሳምሺው ጉንጬ
‎ አየር ማስገባት ጀምሯል
‎በሩብሽ እንዲህ የሆነው
‎ የጉንጬ ከንፈር ጥጉ
‎በሙሉ ቢሆን ኖሮማ
‎ልቤና ነፍሴ ተማክረው
‎ እኔኑ ጥለውኝ ባረጉ

‎እውነት እውነት
‎ለካንስ የመሳም ጥበብ
‎ እጅጉን እጅግ ተራቋል
‎በሜንት ጠረን ታጅቦ
‎ በሩብ ጉዳይ ልብ ይሰልባል

‎እኔ እምልሽ
‎ይሄ የምሄድበት ጎዳና
‎ ጠረኑ በሜንት የናኘው
‎ንፋሱንም ልክ እንደኔ
‎ ሩብ ጉዳይ ስመሽው ነው?

‎እውነት እውነት
‎የምጠጣው የእግዜር ውሀ
‎ ጠአም መልኩ ተቀይሯል
‎ግድየለችም አትደብቂኝ
‎ ውሀውንም ስመሽዋል

‎ከሳሙስ አይቀር እንዲህ ነው
‎ለስለስ አርጎ ሸረፍ አርጎ
‎መአዛ ጠረን ደባልቆ
‎በከንፈር አብሾ ልኮ
‎እንዴነችና ሩብ ጉዳይ ወፈፍ አረገኝ እኮ

‎እናልሽ ከሳምሽኝ በኋላ
‎ ለሩብ ጉዳይ እጅ ሰጠሁ
‎ሰአቱ ሙሉ ሆኖ እንኳን
‎ ሩብ ጉዳይ ነው እላለሁ

‎እውነት እውነት
‎ከመስታወት ፊት ቆሜ
‎ በውስጡ እኔን እያየሁ
‎መተት አርጋብኝ ይሆን
‎ እያልኩ እጠይቃለሁ

‎የጉንጬን የከንፈሬን ጥግ
‎ በእጆቼ እዳብሳለሁ
‎የዳበስኩትን እጄን
‎ ሩብ ጉዳይ እስመዋለሁ

‎ወይ ጣጣዬ ወይ መከራ
‎ግድ የለሽም ልለምንሽ
‎ ግድ የለሽም ተለመኝኝ
‎አንድ ያጣላል ወዳጄ ሆይ
‎ ሩብ ጉዳይ አንዴ ሳሚኝ

@getmtg
@getmtg
👏6😁2

ስንቶቻችን ሰው እያየን
‎ ከእኛነት ጋር ጥል አግባባን
‎እንዳሻቸው "ሆ" በል ሲሉ
‎ "ሆ" እያልን ገደል ገባን

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👏7👍1

አንደበቴ ፈርቶ
‎ፍቅሬን ሳልናገር እንዳለሁት አለሁ
‎እንዴት እንደው ሳላውቅ
‎'ለምን?'ታው ሳይገባኝ ብቻ እወድሻለሁ

‎እንደማይዳስሱት
‎ሊነካ እንደማይችል ከፍ ያለ ሩቅ ሰማይ
‎በውበቷ ደምቀው
‎ይኖሩባት እንጂ
‎እንደማይጨብጧት የንጋቷ ፀሀይ

‎እንደማይደርሱበት
‎ አያልቅ ሩቅ መንገድ
‎እንዳልደፈረሰ
‎እንዳዲስ ምንጭ ውሃ
‎ ሲሆን የኔ መውደድ

‎ልክ እንደ ሰአሊ
‎ጥበብ የለኝ ነገር ከሸራው አልሳልኩሽ
‎ወይ እንደ ደራሲ
‎ውብ ቃላት ከትቤ ፅፌ አላወደስኩሽ

‎ብቻ ግን በሩቁ
‎የአንቺ መሆን ናፍቆኝ ውበትሽን እያየሁ
‎ዛሬም በዝምታ
‎ሳልናገር ፍቅሬን እንዳለሁት አለሁ

‎ ብቻ እወድሻለሁ

@getmtg
@getmtg
👏8👍2

አንዲት ሴት .....
‎ወዳጇን ዘውትር ብትገፋ
‎ ሂድ ብላ የግዷን ብትስቅ
‎አይመስልም ሁነቷን ላየ
‎እንደቀልድ ሂድ ባለችበት
‎ ያንን ሰው እንደምትናፍቅ

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍101

እርሳኝ አልኩት
‎ ከልቡ ውስጥ አነገሰኝ
‎በኔ ክፋት በሱ መቻል
‎ እያሳቀ ሆድ አስባሰኝ

‎በቃህ ስለው
‎ በእጥፍ መውደድ ተከለለ
‎እንዲጠላኝ ሳሾፍበት
‎ መናፈቁን አልተው አለ

‎ራቀኝ አልኩት ግን ቀረበኝ
‎ተወኝ አልኩት አለሁ አለኝ
‎ እየናኩት አከበረኝ
‎እንዲህ ሆኖ
‎ በልቡ ነው የሰበረኝ😊

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👏11👍1

ትመጫለሽ ብዬ
አካላቴን በእንዶድ
ልብሴን በእቃ ሽቦ ወንዙ ዳር አነጣሁ
ትመጫለሽ ብዬ
ስፀልይ ለማደር
'ቀጨኔ' ሚካኤል ተራራ ላይ ወጣሁ

ፀለይኩ እስኪነጋ
እንባየ በዥቅዥቅ
   ጉቶ ሜዳ ድረስ መሬቱን አራሰው
እንዲህ ሆኖ ቢያገኙት
     አይከፋም ነበር ያፈቀሩትን ሰው

      ቀጨኔ የኔ እንባና ኳስ
               የዋንጫ!

ይኸው የዛን ለሊት

ይኸው የዛን ለሊት
ባስለቀሽኝ እንባ
     ደጋፊው በሙሉ ደርሶ አቀረቀረ
'የማርገጃ' ቡድን
መሬት በሰብሶበት
ከ'መቀጠያ' ጋር ኳስ መጋጠም ቀረ

                 ቀረ ቀረ ቀረ!

(አስታወሰኝ ረጋሳ)
👍4👏2

‎ሳቅ
‎      ሳቅ
‎            ሳቅ ካካካካካካ
‎ጥርስን ለአይን ገልጦ
‎                        እነክሽ እነካ

‎ቀን የደራው ሁሉ
‎ትንሽ መሸት ሲል አይጠፋ ይመስል
‎በሳቅ ይሸፍናል
‎      በትዝታ ታመው
‎                       ያልዳኑበት ቁስል

‎ላይ ላዩን ለታይታ
‎            እስኪ ሳቅ ፈገግ
‎ደስታ 'ሚሉት ነገር
‎             ከየት ነው የሚፈለግ¿😁

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👏8👍4

እንዴት እንደመጣሁ
እንዳትጠይቂኝ
ለምን? ............ ስለምትናፍንቂኝ፡፡

አውቀዋለሁኛ
አንድ የበደለሽ ሰው ናፍቀሺኛል ቢልሽ
ላንቺ
ፌዝ ነው የሚመስልሽ

...... ግን ናፍቀሽኛል

አዎ .......
በድያለሁ በግፍ
ደግሞም ናፍቀሽኛል በእጥፍ
ማርያምን የምሬን በዝቷል መናፈቄ
የትም እገኛለሁ
የትም እስቃለሁ ግን ያለቅሳል ሳቄ
ብራመድ በሀገሩ
                    ብክንፍ እንኳ ብበር
ተከፍቶ አያለሁ ቆለፍኩት ያልኩት በር
ቀን የከረቸምኩት
ሌት በምን ከፈትኩት?

በለሊትሽ መጣሁ
አለሜን ስላጣሁ
ከትናንት የባሰ እንደማጣሽ ሳስብ
በደሌን አየሁት እጥፍ መውደድ ሲስብ

አንቺዬዋ ወዴ
የበደለ ሁሉ አይናፍቅም እንዴ ....

ማቀፍ እንኳ ባልችል ምሕረት ባለምንም
አትሳቂብኝ እንጂ
ግጥሙን እያነበብኩ ናፍቀሽኝ አሁንም

ፀሀይዋን ከተትኳት
አይንሽን ለማየት ከቤቴ እየወጣሁ 
የበደለ አይኔን እንዳታይኝ ብዬ
                      በጨለማ መጣሁ
ደረስኩኝ ከደጅሽ መፍራቴ በነነ
እሰይ አገኘሁሽ ናፍቆቴ ሰው ሆነ
እከንፋለሁ ይኸው ስደርስም አልሳምሺኝ
አጃኢብ ሰው መሆን
ሳጠፋ ጊዜ ነው ጭራሽ የናፈቅሽኝ

አጥፍቻለሁ አዎ መውደዴን ቀብሬ
አትሳቂብኝ እንጂ
ልክ ስበድልሽ ጨመረብኝ ፍቅሬ፡፡

.... ናፈቅሽኝ ...

         (ኤልያስ ሽታሁን)
👏6👍1🔥1

"አንድ ሰው በየቀኑ ከተመሳሳይ ሰዎች ጋር የሚገናኝ ከሆነ፡ በመጨረሻ እነዚህ ሰዎች የህይወቱ አካላት ይሆናሉ፡፡ እናም ሰውየው እንዲለወጥ ይፈልጋሉ፡፡ እነሱ እንደሚፈልጉት ካልሆነላቸው ይናደዱበታል፡፡ ሁሉም ሰው ስለሌሎች ሰዎች አኗኗር በደንብ የሚያውቅ የራሱን ግን የማያውቅ ይመስላል፡፡"

‎ "አልኬሚስቱ"

@getmtg
@getmtg
👍4👏1🤔1

‎ብሩህ ጠዋት
‎      ብሩህ ተስፋ
‎                  አምረን ደምቀን
‎በቅን ሀሳብ
‎           ውብ ጅማሬ
‎                           አሸብርቀን
‎        ...... ይሁንልን .....
‎መልካም ውሎ
‎                     ደስ የሚል ቀን😊

አሜን🙏

Mekdi

@getmtg
@getmtg
6👍2

አልፎ_አልፎ_መሞት

ሰው ......
አንድም - በእግዜር
አንድም - በመውዜር
እያዋሀደ የዕድሜውን አመል
ማታ በውስኪ ጠዋት በጠበል

ሰው ቢያጣ መንገድ 
ሰው ቢያጣ ምርጫ
ተከፋፍለው ተስፋን ለቅርጫ

ተመዳደቡብኝ የመኖሬን ኮታ
አንድ ላይ ለበሱት ነፍሴን እንደኩታ

እኔ ግን ......
ይጥቀማቸው ብዬ አልተወው መኖሬን
ብረግፍም አለሁኝ እድሜ ይስጠው ስሬን

ሰው .....
ይመስለዋል እንጂ መተንፈስ አክራሞት
ስንቱን ያሻግራል አልፎ አልፎ መሞት።

(ኤልያስ ሽታሁን)
👏7🤔1

‎እርግጥ ሆኖ ሳለ
‎ጉዞ መንገዳችን ኑሯችን ለየቅል
‎ምን ነገር ተገኘ
‎     መሃላችን ገብቶ ከቶ የሚያመሳቅል

‎እንዳልነበርን ጓድ
‎አብሮ እንዳልቀለለ ኑሮ ውረድ ውጣው
‎አንዳችን ላንዳችን
‎  እንዳልሰጠን ምክር
‎    ደርሶ ፉክክርን ከእኛ ምን አመጣው¿

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👏8🤔1