፡
ተ ሸ ክ መ ና ታ ል !!
እናቴ ሁልጊዜ እንድናጠና ስትመክረን እንዲህ ትላለች:-
“እናንተ ልጆች አጥኑ፣ ተማሩ እባካችሁ ! ...እኔ ባለመማሬ ነው ጉዴን ተሸክሜ የዋልኩት!"
ማንበብም መፃፍም ስለማትችል ንግግሯ በቁጭት ነበር፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ይሄ ተሸክማ የዋለችው ጉድ ምን እንደሆነ ለማወቅ ጓጉቼ ጠየቅኳት፣
"ማሚ የምን ጉድ ነው ተሽከመሽ የዋልሽው ?”
አወራችኝ ...
.......... ........ ..........
በደርግ ጊዜ መስከረም ሁለት ቀን ሕዝቡ በግድም ሆነ በውድ የድጋፍ ሰልፍ ይወጣ ነበር፡፡መስከረም ሁለት ደርግ ንጉሱን ገልብጦ ሥልጣን የያዘበት ቀን ነው፡፡ በአጭር አገላለፅ መስከረም ሁለት የደርግ ግንቦት ሃያ ነበር፡፡ ታዲያ እናቴ በወቅቱ የነበረውን የግዳጅ ውትድርና በመፍራት የመጀመሪያ ልጁን ወታደር ቤት እንዳይወስዱባት ከከተማው ወጣ ያለ አከስታችን ቤት ደብቃ፣ሁለተኛ ልጁንም ገጠር እናቷ ጋር ልካ፣ ሦስተኛውን ልጇን አልጋ ስር አስቀምጣ፣ አባቴንም
"ታምሜያለሁ በል!" ብላው፣ እሷ ግን ነጭ ልብስ ለብላ ሰልፍ ወጣች፡፡ ግዴታ ነዋ!
ቀበሌ ስትደርስ ሴት ወንዱ ያለውን ለብሶ ተሽቀርቅሮ፣ ቀበሌውም በተለያዩ መፈከሮችና በባለ ቀለም መብራቶች አጊጦ ጠበቃት፡፡ የቀበሌው የአ..ሴ.ማ ኃላፊ የነበረች ሴት በባለእጀታ የጣውላ ሰሌዳ ላይ ተፅፈው የተዘጋጁ በመቶ የሚቆጠሩ መፈከሮችን ለእናቴ እያሳየቻት፣ ምረጭና አንዱን ያዥ አለቻት፡፡
እናቴ ቀለል ያለችና በደማቅ ቀይ ቀለም የተሽሞነሞነች መፈክር መርጣ አነሳችና ወደ ሰልፉ ተቀላቀለች፡፡ ከለበሰችው የሚያምር የአበሻ ቀሚስ እና ከራሷም ቁንጅና ጋር ተዳምሮ የኦሎምፒክ መከፈቻ ላይ 'ኢትዮጲያ የሚል ምልከት ይዛ ሰልፉን የምትመራ ቆንጆ የአበሻ ሴት ትመስል ነበር፡፡
በዕለቱ መስቀል አደባባይ እናቴን በርካታ ሰዎች በግርምትና በአድናቆት ሲመለከቷት ዋሉ፡፡ ታዲያ በዚያ ሰሞን ማታ በቴሌቪዥን ደጋግመው እናቴን ከነመፈhሯ ያሳይዋት ጀመረ፡፡ ምን ይሄ ብቻ፡ አመቱን ሙሉ ፎክረውም እናቴን ማሳየት፣ ኢህአፓ ብለውም እናቴን፣ መኢሶን ብለውም እናቴን፣ ቀይ ሽብር ብለውም እናቴን፣ ጓድ ሊቀመንበር ተናግረው ሲያበቁም እናቴን ማሳየት::
ጭራሽ ብሔራዊ ውትድርና ተብሎ ምድረ ወጣት ሰጓፈፍ ፣ የብሔራዊ ውትድርና አገር አቀፍ ዓርማ የእናቴ ፎቶ ሆኖ በየቦታው ተለጠፈ፡፡ በነጭ ልብስ ተውባ መፈክር ይዛ የቆመች እናቴ የብሔራዊ ውትድርና አገር አቀፍ አርማ ሆነች፡፡ እንድ ጋዜጣ ላይ የእናቴ ፎቶ ስር እንዲህ የሚል ጽሑፍ ሰፍሮ ነበር
"እብዮታዊት ሶሻሊስት ኢትዮጵያ ነጭ ቀሚስ ለብሳ"
እናቴ ታዲያ መጀመሪያ አካባቢ በቴሌቪዥን በታየች ቁጥር በቁንጅናዋ የተመረጠች መስሏት አባቴ ላይ በኩራት ትነሰነስበት ነበር፣
"ጓዳ ለጓዳ ስውል ቀላል ሰው አድርገኸኝ፣ እግሬ ወጣ ካለ አገር ነው የሚሰግድልኝ" ትለዋለች ኮራ
ብላ፡፡ አባቴ አፉን ሸርመም አድርጎ፣ "እዩኝ እዩኝ ማለት ደብቁኝ ደብቁኝ ያመጣል !" ይላታል::
የቅናት ወሬ ነው ይሄ ትልና ሆነ ብላ ለማበሳጨት በቴሌቪዥን ደጋግሞ የሚታየውን ምስሏን አተኩራ እየተመለከተች፤
“እንዲት ፍሬ ልጅ እኮ ነኝ" ትላለች፡፡ አባባ ታዲያ “ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ…” ብሎ በረዥሙ ይስቅና
"ሰልፍ ላይማ መንግስትም አንድ ፍሬ ነኝ ነው የሚለው" ይላል፡፡
“ኤዲያ እንግዲህ ቦለቲካህን ልትጀምር ነው…” ብላ ወደ ጓዳዋ ትገባለች፡፡
ይሁንና እናቴ እየቆየች በቴሌቪዥን መታየቱ እና ስለ እርሷ መወራቱም ሲደጋገምባት ፈራች::
በተለይም ጓድ መንግስቱ ኃይለማሪያም መስቀል አደባባይ በትልቁ የተሰቀለውን የእናቴን ፎቶ ለተሰበሰበው ሕዝብ እያሳዩ በደም ፍላት፣
"እንደነዚህ ዓይነት ጀግና እናቶች ያሉባት አገር በማንም ወመኔ ከሃዲ ስትወረር እንዴት ወንዶቿ አልጋ ስር ይደበቃሉ? እነዚህን ቦቅቧቃ ወንዳገረዶች ቂጣቸውን በሳንጃ…” እያሉ ንግግር ካደረጉ በኋላ እናቴ ስጋቷ ከፍ አለ፡፡
ስጋቷን ለማስታገስ፣ “ኧረ ይሄ መፈክር ምንድን ነው የሚለው?” ብላ የተማረ ሰው ጠየቀች፡፡ መስከረም ሁለት ሰልፍ ላይ ይዛ ስለወጣችው መፈክር ተሸክማው ስለነበረው ጽሑፍ ሚያዚያ ላይ "ምንድን ነው?" ብላ ጠየቀች፡፡ሲነበብላት አመዷ ቡን አለ ፡ ብርክ ያዛት፡፡
መፈክሩ እንዲህ ነበር የሚለው....
"የአብዮት ጠላቶችን ለማደባየት እኛ እናቶች ልጆቻችንን፣ ካስፈለገም ባሎቻችንን በደስታ እናዘምታለን!!"
(ዶክተር አሸብር እና ሌሎችም)

😁8
ያኔ...
በልክ አርጊው ሲሉኝ ሁሉም ነገር ያልቃል
ያፋቸው ቃል እንጂ መች መስሎኝ ትንቢት ቃል
መቼም አያበቃም ገደብ የለው ያልኩት
መውደዴ ሲያልቅ ነው ልቤን የታዘብኩት።
ጥልቅ ነው እያልኩኝ ብዙ ነው እያልኩኝ
ከልብ አንጠፍጥፌ መውደድን ጨረስኩኝ
ያኔ....
ባገኝህ...ባዋይህ
እንደ ምስለ ቅዱስ ደጋግሜ ባይህ
እንደ አጥቢያ ደብር ነግቶ ብሳለምህ
ወይ እንደ ዉቃቢ ሠርክ ብለምንህ
አይበቃኝ የነበር
አፍታም አልፈጀበት መዉደዴ ሲሰበር።
ያኔ...
ጠዋት ፀሀይ ሞቃ
ሌት ጨረቃ ደምቃ
እወድህ የነበር ልኬት እሰካይኖረኝ
ዛሬ ምን ቀየረኝ?
ይኸው..
ፍቅር አንቱ ተብሎ እነዳልነገሰበት
ጥላቻም በኔ ልብ ተራዉ ደረሰለት
ጠላሁህ አንተዬ ከልቤ አወጣሁህ
ላይኔ እንደናፈከኝ አያሳየኝ አልኩህ
ደግሞ ጠብቃለሁ
ጊዜ በጎዳናዉ ተሸራርፎ ወድቆ
ምን እንደሚፈጠር ጥላቻዬም አልቆ
በልክ አርጊው ሲሉኝ ሁሉም ነገር ያልቃል
ያፋቸው ቃል እንጂ መች መስሎኝ ትንቢት ቃል
መቼም አያበቃም ገደብ የለው ያልኩት
መውደዴ ሲያልቅ ነው ልቤን የታዘብኩት።
ጥልቅ ነው እያልኩኝ ብዙ ነው እያልኩኝ
ከልብ አንጠፍጥፌ መውደድን ጨረስኩኝ
ያኔ....
ባገኝህ...ባዋይህ
እንደ ምስለ ቅዱስ ደጋግሜ ባይህ
እንደ አጥቢያ ደብር ነግቶ ብሳለምህ
ወይ እንደ ዉቃቢ ሠርክ ብለምንህ
አይበቃኝ የነበር
አፍታም አልፈጀበት መዉደዴ ሲሰበር።
ያኔ...
ጠዋት ፀሀይ ሞቃ
ሌት ጨረቃ ደምቃ
እወድህ የነበር ልኬት እሰካይኖረኝ
ዛሬ ምን ቀየረኝ?
ይኸው..
ፍቅር አንቱ ተብሎ እነዳልነገሰበት
ጥላቻም በኔ ልብ ተራዉ ደረሰለት
ጠላሁህ አንተዬ ከልቤ አወጣሁህ
ላይኔ እንደናፈከኝ አያሳየኝ አልኩህ
ደግሞ ጠብቃለሁ
ጊዜ በጎዳናዉ ተሸራርፎ ወድቆ
ምን እንደሚፈጠር ጥላቻዬም አልቆ
👍7👏2
፡
ባዶነት ወዳጄ ነበር
ጠፍቼ ነበር ከራሴ አለኝ ያልኩትስ መች አለኝ
አሁን ላይ ቀኑ ተለየ
በድንገት አይኔን ሳማትር ሳይሽ ግን አለሜ ታየኝ
ሳላውቅሽ መናፈቅ ተማርኩ
ያልነጋው ጨለማው ልቤ የተስፋ ፀሀይ ወጣለት
እንቺነት ነፍስን ሲዘራ
የመኖር ትርጉሙ ገባኝ ያየሁሽ የዛችን እለት
በሳቅሽ ሰርክ አማረብኝ
እያደር መሻቴ ወዛ ምኞቴ ግቡን ተጓዘ
እጦት ስር ወድቆ የነበረ
በብሶት ዝብርቅርቅ ያለው እኔነት መስመሩን ያዘ
ሄድንበት ጎዳና ምድሩን
ዋልንበት ጫካ ሜዳውን ሀሴትን አጎናፀፈን
ከፍ አልን በመውደድ ግርማ
እንደልጅ ፍንድቅድቅ አልን አያረጅ ፍቅር አቀፈን
በምናብ ነገን ቃኘነው
አሰላን ኑሮ ቀመሩን አንድ ሆነ የእኛነት ውሉ
አሙቀሽ በረዶ አካሌን
ፈጥረሽኝ ነበር እንዳዲስ አድርገሽ አለሜን ሙሉ
ደምቄ ነበር ካንቺ ጋር
ታይቼ ነበር አምሮብኝ ሆነሽኝ የልቤ ሀገር
ምን ትርጉም ምንስ ዋጋ አለው
ይህ ሁሉ እያለሽ ነበር
ስትመጪ ቀን የወጣለት
ያነሳኝ ያቀናኝ ፍቅርሽ ስትሄጂ ጠቁሮ ዳመነ
የመኖር ትርጉሜን አጣሁ
ይባሱን ከራሴ ጠፋሁ ባዶነት ወዳጄ ሆነ
ያማረው ፊቴ ገረጣ
በናፍቆትሽ ጣር ከስሜ አግኝቶ ማጣት ሰበረኝ
ሄድሽ እንጂ በእኔ ጨክነሽ
ከአንቺነት መፅናኛ ፍቅር ሌላ እንኳ ምንስ ነበረኝ
ብሶቴን እንዳዲስ ዘራሽ
በፍቅርሽ የረጋው ልቤ ስትሄጂ መስመሩ ራቀው
መልሶ ዝብርቅርቅ አለ
ዳግሙን ፀንቶ እስኪፈካ ያንቺ ቃል እየናፈቀው
@getmtg
@getmtg
ባዶነት ወዳጄ ነበር
ጠፍቼ ነበር ከራሴ አለኝ ያልኩትስ መች አለኝ
አሁን ላይ ቀኑ ተለየ
በድንገት አይኔን ሳማትር ሳይሽ ግን አለሜ ታየኝ
ሳላውቅሽ መናፈቅ ተማርኩ
ያልነጋው ጨለማው ልቤ የተስፋ ፀሀይ ወጣለት
እንቺነት ነፍስን ሲዘራ
የመኖር ትርጉሙ ገባኝ ያየሁሽ የዛችን እለት
በሳቅሽ ሰርክ አማረብኝ
እያደር መሻቴ ወዛ ምኞቴ ግቡን ተጓዘ
እጦት ስር ወድቆ የነበረ
በብሶት ዝብርቅርቅ ያለው እኔነት መስመሩን ያዘ
ሄድንበት ጎዳና ምድሩን
ዋልንበት ጫካ ሜዳውን ሀሴትን አጎናፀፈን
ከፍ አልን በመውደድ ግርማ
እንደልጅ ፍንድቅድቅ አልን አያረጅ ፍቅር አቀፈን
በምናብ ነገን ቃኘነው
አሰላን ኑሮ ቀመሩን አንድ ሆነ የእኛነት ውሉ
አሙቀሽ በረዶ አካሌን
ፈጥረሽኝ ነበር እንዳዲስ አድርገሽ አለሜን ሙሉ
ደምቄ ነበር ካንቺ ጋር
ታይቼ ነበር አምሮብኝ ሆነሽኝ የልቤ ሀገር
ምን ትርጉም ምንስ ዋጋ አለው
ይህ ሁሉ እያለሽ ነበር
ስትመጪ ቀን የወጣለት
ያነሳኝ ያቀናኝ ፍቅርሽ ስትሄጂ ጠቁሮ ዳመነ
የመኖር ትርጉሜን አጣሁ
ይባሱን ከራሴ ጠፋሁ ባዶነት ወዳጄ ሆነ
ያማረው ፊቴ ገረጣ
በናፍቆትሽ ጣር ከስሜ አግኝቶ ማጣት ሰበረኝ
ሄድሽ እንጂ በእኔ ጨክነሽ
ከአንቺነት መፅናኛ ፍቅር ሌላ እንኳ ምንስ ነበረኝ
ብሶቴን እንዳዲስ ዘራሽ
በፍቅርሽ የረጋው ልቤ ስትሄጂ መስመሩ ራቀው
መልሶ ዝብርቅርቅ አለ
ዳግሙን ፀንቶ እስኪፈካ ያንቺ ቃል እየናፈቀው
@getmtg
@getmtg
👏4❤1👍1
፡
የደራሲ ቅጣት ...
የሆነ ሰውዬ ይሞትና ገነትንም፣ ሲዖልንም ይጎበኛል፡፡ ገነት ሲደርስ በጎ ምግባሮች እንደቀጠሉ ናቸው። መልካም ሰርተው የፀደቁትንም አስተዋለ፡፡ ይልቅ የገረመው አንዲት ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ የሚፅፍ ሰው ተመለከተ። ገረመውና ምን እንደሆነ ቢጠይቅ "ደራሲ ነው" አሉት። እየተደነቀ “አይ ደራሲ ፀድቆም አያርፍ፣ አሁኑም ይፅፋል” ሲል ተደመመ።
ከሚንቀለቀል የእሳት እቶትን ውስጥ የሲዖልም ሕይወት ቀጥላለች። አመፅ፣ ግርግሩ፣ ጦርነቱ…ኃጥያቱ አናት ባናቱ ይደራረባል። አሁንም አንድ ሰውዬ ከእሳት ዛፍ ስር አረፍ ብሎ በእሳት ብዕር፣ በእሳት ወረቀት ይቸከችካል። ተመልካቹ ሰውዬ ግራ ተጋባም ምን ሊሆን ይችላል ሲል እያሰበ ጠየቀ "ደራሲ ነው፣ ይከትባል" አሉት።
እየተገረመ፣ እየተደነቀ መልዓኩን "ቆይ ደራሲ እዚህም ሲፅፍ አይቼዋለሁ… እዛም ሲቸከችክ ተመልክቼዋለሁ ካዲያ ገነትም ገባ፣ ሲዖልም ወረደ ምን ቀረበት? ምንድነው ቅጣቱ? ምን ተጎዳ?" ሲል ጠየቀው።
መልዓኩም መለሰለት “ገነት ያሉት ይታተምላቸዋል"
(By Alemayew Gelagay)

😁9
፡
"ደህና ነህ ወይ?" ስለው
ሁሉ እንደሞላለት "ደህና ነኝ" ይለኛል
ለዚህ ጥያቄ መልስ
ተመሳሳይ ውሸት
"ደህና ነኝ" መሆኑን ቀድሞ አሳውቆኛል
የእውነት ደህና አይደለም .......
ምን ሆንክ እንዳልለው
ምንም ነው መልሱ
አትዋሽ እንዳልል
'ለምን'ታ ነው ክሱ
ጭንቁን በፈገግታው
ሊሸፍን ቢቃጣም
እንደተረበሸ ያስታውቅበታል
ይህ ጊዜ አደብ ገዝቶ
ተስፋው ያነሳው 'ለት
ሳይሰስት ከልቡ ሲያልፍ ይስቀበታል
(መቼ እንደሚያልፍ ባላውቅም)
✍ Mekdi
@getmtg
@getmtg
"ደህና ነህ ወይ?" ስለው
ሁሉ እንደሞላለት "ደህና ነኝ" ይለኛል
ለዚህ ጥያቄ መልስ
ተመሳሳይ ውሸት
"ደህና ነኝ" መሆኑን ቀድሞ አሳውቆኛል
የእውነት ደህና አይደለም .......
ምን ሆንክ እንዳልለው
ምንም ነው መልሱ
አትዋሽ እንዳልል
'ለምን'ታ ነው ክሱ
ጭንቁን በፈገግታው
ሊሸፍን ቢቃጣም
እንደተረበሸ ያስታውቅበታል
ይህ ጊዜ አደብ ገዝቶ
ተስፋው ያነሳው 'ለት
ሳይሰስት ከልቡ ሲያልፍ ይስቀበታል
(መቼ እንደሚያልፍ ባላውቅም)
✍ Mekdi
@getmtg
@getmtg
👏9👍3❤1
፡
ተፈጥሮን ደጅ ልጥና
" እኔ ልሙትልሽ" እያልኩኝ አልምልም
ቃላቴን መንዝሬ፤ ለሞት ቀብድ አልከፍልም
ያኔ ትዝ ይልሻል?
"ራስህን ግደል" ብለሽ በረኪና የላክሽልኝ ጊዜ
እድሜ ለስጦታሽ፤ ታጠበ ሸሚዜ።
ገደብ ጫፍ በሌለው፤ በልቤ መጋዘን
ቢታጨቅ መከራ፤ ቢጠራቀም ሀዘን
"ባለፈልኝ" እንጂ "በሞትኩ" ብየ አላቅም
ካልጋ ላይ ነው እንጂ፤ ከፎቅ ላይ አልወድቅም።
በሀኪሙ ስተት፤ በቁሜ ብከፈን
በወርድ በቁመቴ፤ ሳጥኔ ቢደፈን
ከጭስ እቀጥናለሁ፤ እኔ መውጫ አላጣም
በጠጅ በወይን አገር፤ ሽጉጤን አልጠጣም።
የተመደበልኝ ዘመን ከባከነ
የተሰፈረልኝ፤ ቀን አልቆ ከሆነ
ተፈጥሮን ደጅ ልጥና
ባዲስ መንገድ ትስራኝ፤
ባዲስ የፍጥረት ውል
መስኮትሽ ላይ ሆና
ስትዘምር የምትውል ድንቢጥ ወፍ ታድርገኝ
ብኖር አንቺን አየሁ፤ ከመሞት ምን ሊገኝ።
(በእውቀቱ ስዩም)
ተፈጥሮን ደጅ ልጥና
" እኔ ልሙትልሽ" እያልኩኝ አልምልም
ቃላቴን መንዝሬ፤ ለሞት ቀብድ አልከፍልም
ያኔ ትዝ ይልሻል?
"ራስህን ግደል" ብለሽ በረኪና የላክሽልኝ ጊዜ
እድሜ ለስጦታሽ፤ ታጠበ ሸሚዜ።
ገደብ ጫፍ በሌለው፤ በልቤ መጋዘን
ቢታጨቅ መከራ፤ ቢጠራቀም ሀዘን
"ባለፈልኝ" እንጂ "በሞትኩ" ብየ አላቅም
ካልጋ ላይ ነው እንጂ፤ ከፎቅ ላይ አልወድቅም።
በሀኪሙ ስተት፤ በቁሜ ብከፈን
በወርድ በቁመቴ፤ ሳጥኔ ቢደፈን
ከጭስ እቀጥናለሁ፤ እኔ መውጫ አላጣም
በጠጅ በወይን አገር፤ ሽጉጤን አልጠጣም።
የተመደበልኝ ዘመን ከባከነ
የተሰፈረልኝ፤ ቀን አልቆ ከሆነ
ተፈጥሮን ደጅ ልጥና
ባዲስ መንገድ ትስራኝ፤
ባዲስ የፍጥረት ውል
መስኮትሽ ላይ ሆና
ስትዘምር የምትውል ድንቢጥ ወፍ ታድርገኝ
ብኖር አንቺን አየሁ፤ ከመሞት ምን ሊገኝ።
(በእውቀቱ ስዩም)
👏7
፡
ካንተ ጋ እንዳልኖርኩኝ
ቀን መለየት ቆጥሮ ብቸኛም ቢያደርገኝ
ሳስብ ይቆጨኛል
መቼም ያንተን ያህል ሰው እንደማላገኝ
መች ይጠፋና ነው
የአነጋገር ለዛህ የአንተነትህ ምስል
መራቅህ ነው እንጂ
በጭንቅ ያማቀቀኝ የዘራብኝ ቁስል
መች ይረሳና ነው
ያለፍንበት ትላንት ያሳለፍነው ጊዜ
ዛሬን ጎኔ ባትሆን
ከፍቶኝ መሽቶ ነጋ ዋልኩኝ በትካዜ
ፍቅርህ ባይቆርጥልኝ
አንተነትክን ስራብ
ናፍቆት ባይሆነኝ መልስ
እያልኩ አስባለሁ
ምናል ያ ደግ ቀን ዳግሙን ቢመለስ
@getmtg
@getmtg
ካንተ ጋ እንዳልኖርኩኝ
ቀን መለየት ቆጥሮ ብቸኛም ቢያደርገኝ
ሳስብ ይቆጨኛል
መቼም ያንተን ያህል ሰው እንደማላገኝ
መች ይጠፋና ነው
የአነጋገር ለዛህ የአንተነትህ ምስል
መራቅህ ነው እንጂ
በጭንቅ ያማቀቀኝ የዘራብኝ ቁስል
መች ይረሳና ነው
ያለፍንበት ትላንት ያሳለፍነው ጊዜ
ዛሬን ጎኔ ባትሆን
ከፍቶኝ መሽቶ ነጋ ዋልኩኝ በትካዜ
ፍቅርህ ባይቆርጥልኝ
አንተነትክን ስራብ
ናፍቆት ባይሆነኝ መልስ
እያልኩ አስባለሁ
ምናል ያ ደግ ቀን ዳግሙን ቢመለስ
@getmtg
@getmtg
👍7
፡
ናፍቀኸኛል
አይኔን ስገልጥ
የሚታየኝ ያንተ ምስል
ሆኛለሁኝ በናፍቆትህ
ጠዋት ማታ እየጠቆርኩ የምከስል
መንገድ ጊዜ ቢያለያየን
ትዝታህ ነው ለኔ ስንቄ
አይግረምህ ዛሬን ሳጣህ
በናፍቆትህ መንሰቅሰቄ
የሄድኩበት የሄድክበት
እንደው ወዴት አደረሰን
ምን እንደሆን ያንተን ባላውቅ
ያሳለፍነው እልፍ ፍቅር
ይመስለኛል የከሰሰን
ናፍቀኸኛል
ከከደንኩት የአይኔ ሽፋን
ያንተ ምስል የገለጠው
መለየትን በመርሳት ልክ
አንተነትክን መች ለወጠው
ምናልባቱን ከናፈኩህ
ፈጥነህ መቼ ትመጣለህ
ራቅከኝ እንጂ አልወጣህም
ዛሬም እኮ ከውስጤ አለህ
@getmtg
@getmtg
ናፍቀኸኛል
አይኔን ስገልጥ
የሚታየኝ ያንተ ምስል
ሆኛለሁኝ በናፍቆትህ
ጠዋት ማታ እየጠቆርኩ የምከስል
መንገድ ጊዜ ቢያለያየን
ትዝታህ ነው ለኔ ስንቄ
አይግረምህ ዛሬን ሳጣህ
በናፍቆትህ መንሰቅሰቄ
የሄድኩበት የሄድክበት
እንደው ወዴት አደረሰን
ምን እንደሆን ያንተን ባላውቅ
ያሳለፍነው እልፍ ፍቅር
ይመስለኛል የከሰሰን
ናፍቀኸኛል
ከከደንኩት የአይኔ ሽፋን
ያንተ ምስል የገለጠው
መለየትን በመርሳት ልክ
አንተነትክን መች ለወጠው
ምናልባቱን ከናፈኩህ
ፈጥነህ መቼ ትመጣለህ
ራቅከኝ እንጂ አልወጣህም
ዛሬም እኮ ከውስጤ አለህ
@getmtg
@getmtg
👍6
፡
ቅናቴ
(በአበባው መላኩ)
ፍቅሬን ሜዳ ላይ ጥላ
ስትከዳኝ አይቻታለሁ
እንደገፋችኝ ትገፋ
እያልኩ እረግማታለሁ
ዘወትር ሙሾ ታላዝን
የእንባ ማዕበል ይጠባት
ደስታዬን እንዳጨለመች
ደስታዋ ይጨልምባት
ሺህ እጥፍ ትጨድ አበሳ
ለዘራችብኝ ጥፋት
እያልኩ እረግማታለሁ(2)
የኮራችበትን ገላ
መብረቅ ያንድደው በቁጣ
በላይዋ ዲም ይውረድባት
ጥጋት መሸሻ ትጣ
እያልኩ እረግማታለሁ(2)
የምድር የቀላይ ጥፋት
በላዩዋ ይውረድ ኩነኔ
ኑሮዋን ሲኦል ያድርገው
ስቃዩዋን የያሳየኝ በአይኔ
እንደከዳችኝ ትከዳ
የኔ ያለችው ይሽሻት
ቀላዋጭ አይኗን ያፍርጠው
ከውካዋ እግሯን ያልምሻት
እያልኩ እረግማታለሁ(2)
ክንዷ በመጅ ይሰበር
ሌላ ያቀፈችበት
አባጨጓራ ይሙላው
ፍራሹ የተኛችበት
እያልኩ እረግማታለሁ(2)
የሌላ ሆና ብትከዳኝ
አይጠሉ ጠልቻታለሁ
ስለ ማህተቤ ብጠየቅ
ከአለም ላይ ካለኝ የምሻው
የረገምኳትን እላለሁ
ሌላም እርካታም የለኝ
እሷን አምጡልኝ እላለሁ
ጥላቻዬና ፍቅሬ ናት
እርግማንና በረከቴ
ያለሷ ህይወት የሌለኝ
ያሳበደችን ቅናቴ
ቅናቴ
ቅናቴ
@getmtg
@getmtg
ቅናቴ
(በአበባው መላኩ)
ፍቅሬን ሜዳ ላይ ጥላ
ስትከዳኝ አይቻታለሁ
እንደገፋችኝ ትገፋ
እያልኩ እረግማታለሁ
ዘወትር ሙሾ ታላዝን
የእንባ ማዕበል ይጠባት
ደስታዬን እንዳጨለመች
ደስታዋ ይጨልምባት
ሺህ እጥፍ ትጨድ አበሳ
ለዘራችብኝ ጥፋት
እያልኩ እረግማታለሁ(2)
የኮራችበትን ገላ
መብረቅ ያንድደው በቁጣ
በላይዋ ዲም ይውረድባት
ጥጋት መሸሻ ትጣ
እያልኩ እረግማታለሁ(2)
የምድር የቀላይ ጥፋት
በላዩዋ ይውረድ ኩነኔ
ኑሮዋን ሲኦል ያድርገው
ስቃዩዋን የያሳየኝ በአይኔ
እንደከዳችኝ ትከዳ
የኔ ያለችው ይሽሻት
ቀላዋጭ አይኗን ያፍርጠው
ከውካዋ እግሯን ያልምሻት
እያልኩ እረግማታለሁ(2)
ክንዷ በመጅ ይሰበር
ሌላ ያቀፈችበት
አባጨጓራ ይሙላው
ፍራሹ የተኛችበት
እያልኩ እረግማታለሁ(2)
የሌላ ሆና ብትከዳኝ
አይጠሉ ጠልቻታለሁ
ስለ ማህተቤ ብጠየቅ
ከአለም ላይ ካለኝ የምሻው
የረገምኳትን እላለሁ
ሌላም እርካታም የለኝ
እሷን አምጡልኝ እላለሁ
ጥላቻዬና ፍቅሬ ናት
እርግማንና በረከቴ
ያለሷ ህይወት የሌለኝ
ያሳበደችን ቅናቴ
ቅናቴ
ቅናቴ
@getmtg
@getmtg
👏5👍1
፡
የንፁህ ደም በየቀዬው እንደኩሬ ይንሳፈፋል
ስንቱ ተስፋ የሰነቀ መንፈቅ እድሜ ሳይኖር ያልፋል
ለሰርጉ ቀን የተከሉት እንሶስላው አልበቀለም
እንኳን ወልዶ መሳም ቀርቶ ወጥቶ መግባት አልቀለለም
ቀኔ ደርሶ ከሰው እኩል በድኔን ዶዘር እሲኪያነሳው
( ይህንን ቃል እንዳልረሳው!)
ጩኽት ብቻ ነጋ ጠባ ዋይታ ብቻ መሸም ነጋም
መኖር ፍፁም አያጓጓም
በየ ደጁ በየ ጓዳው የሲቃ ድምፅ ሲያስገመግም
ምንም ተስፋ በሌለበት ተስፋ ማድረግ አልፈልግም
አታልቅሺ አትዘኚ በድኔን ከሞት ላታስነሺው
ቢሆንም ግን (ይህንን ቃል እንዳትረሺው)
ሳልደነቅፍ _ ሳልሸራርፍ አንዲት ፊደል ሳልሳሳት
ያሰብኩትን ሳልናገር አፈር ልቤን አይቅመሳት
ታሪክ ህልሜን _ ገላ ጨርቄን ጉድጓድ አፈር ሳይቀበል
አንዴ ብቻ ይህን ልበል!
የጥም ውሃ ባያጠጡኝ ህመም ቁስሌን ባያክሙት
እንደምንም አንዴ ብቻ "ወድሻለሁ" ብዬ ልሙት።
እወድሻለሁ
(አስታወሰኝ_ረጋሳ)
የንፁህ ደም በየቀዬው እንደኩሬ ይንሳፈፋል
ስንቱ ተስፋ የሰነቀ መንፈቅ እድሜ ሳይኖር ያልፋል
ለሰርጉ ቀን የተከሉት እንሶስላው አልበቀለም
እንኳን ወልዶ መሳም ቀርቶ ወጥቶ መግባት አልቀለለም
ቀኔ ደርሶ ከሰው እኩል በድኔን ዶዘር እሲኪያነሳው
( ይህንን ቃል እንዳልረሳው!)
ጩኽት ብቻ ነጋ ጠባ ዋይታ ብቻ መሸም ነጋም
መኖር ፍፁም አያጓጓም
በየ ደጁ በየ ጓዳው የሲቃ ድምፅ ሲያስገመግም
ምንም ተስፋ በሌለበት ተስፋ ማድረግ አልፈልግም
አታልቅሺ አትዘኚ በድኔን ከሞት ላታስነሺው
ቢሆንም ግን (ይህንን ቃል እንዳትረሺው)
ሳልደነቅፍ _ ሳልሸራርፍ አንዲት ፊደል ሳልሳሳት
ያሰብኩትን ሳልናገር አፈር ልቤን አይቅመሳት
ታሪክ ህልሜን _ ገላ ጨርቄን ጉድጓድ አፈር ሳይቀበል
አንዴ ብቻ ይህን ልበል!
የጥም ውሃ ባያጠጡኝ ህመም ቁስሌን ባያክሙት
እንደምንም አንዴ ብቻ "ወድሻለሁ" ብዬ ልሙት።
እወድሻለሁ
(አስታወሰኝ_ረጋሳ)
👏7
፡
ሩብ ጉዳይ(የሳምሽኝ ልጅ)
በሰለሞን ሳህለ
ነፍሴን ከነፍስሽ አጣምረሽ
የአለም ጥግ ላይ ያኖርሽው
ሩብ ጉዳይ የሳምሽኝ ልጅ
ጥበቡን ከየት ተማርሽው
እውነት እውነት
ከንፈርሽ በጣም ልዩ ነው
የሜንት ጠረን ታድሏል
ሰሞኑን የሳምሺው ጉንጬ
አየር ማስገባት ጀምሯል
በሩብሽ እንዲህ የሆነው
የጉንጬ ከንፈር ጥጉ
በሙሉ ቢሆን ኖሮማ
ልቤና ነፍሴ ተማክረው
እኔኑ ጥለውኝ ባረጉ
እውነት እውነት
ለካንስ የመሳም ጥበብ
እጅጉን እጅግ ተራቋል
በሜንት ጠረን ታጅቦ
በሩብ ጉዳይ ልብ ይሰልባል
እኔ እምልሽ
ይሄ የምሄድበት ጎዳና
ጠረኑ በሜንት የናኘው
ንፋሱንም ልክ እንደኔ
ሩብ ጉዳይ ስመሽው ነው?
እውነት እውነት
የምጠጣው የእግዜር ውሀ
ጠአም መልኩ ተቀይሯል
ግድየለችም አትደብቂኝ
ውሀውንም ስመሽዋል
ከሳሙስ አይቀር እንዲህ ነው
ለስለስ አርጎ ሸረፍ አርጎ
መአዛ ጠረን ደባልቆ
በከንፈር አብሾ ልኮ
እንዴነችና ሩብ ጉዳይ ወፈፍ አረገኝ እኮ
እናልሽ ከሳምሽኝ በኋላ
ለሩብ ጉዳይ እጅ ሰጠሁ
ሰአቱ ሙሉ ሆኖ እንኳን
ሩብ ጉዳይ ነው እላለሁ
እውነት እውነት
ከመስታወት ፊት ቆሜ
በውስጡ እኔን እያየሁ
መተት አርጋብኝ ይሆን
እያልኩ እጠይቃለሁ
የጉንጬን የከንፈሬን ጥግ
በእጆቼ እዳብሳለሁ
የዳበስኩትን እጄን
ሩብ ጉዳይ እስመዋለሁ
ወይ ጣጣዬ ወይ መከራ
ግድ የለሽም ልለምንሽ
ግድ የለሽም ተለመኝኝ
አንድ ያጣላል ወዳጄ ሆይ
ሩብ ጉዳይ አንዴ ሳሚኝ
@getmtg
@getmtg
ሩብ ጉዳይ(የሳምሽኝ ልጅ)
በሰለሞን ሳህለ
ነፍሴን ከነፍስሽ አጣምረሽ
የአለም ጥግ ላይ ያኖርሽው
ሩብ ጉዳይ የሳምሽኝ ልጅ
ጥበቡን ከየት ተማርሽው
እውነት እውነት
ከንፈርሽ በጣም ልዩ ነው
የሜንት ጠረን ታድሏል
ሰሞኑን የሳምሺው ጉንጬ
አየር ማስገባት ጀምሯል
በሩብሽ እንዲህ የሆነው
የጉንጬ ከንፈር ጥጉ
በሙሉ ቢሆን ኖሮማ
ልቤና ነፍሴ ተማክረው
እኔኑ ጥለውኝ ባረጉ
እውነት እውነት
ለካንስ የመሳም ጥበብ
እጅጉን እጅግ ተራቋል
በሜንት ጠረን ታጅቦ
በሩብ ጉዳይ ልብ ይሰልባል
እኔ እምልሽ
ይሄ የምሄድበት ጎዳና
ጠረኑ በሜንት የናኘው
ንፋሱንም ልክ እንደኔ
ሩብ ጉዳይ ስመሽው ነው?
እውነት እውነት
የምጠጣው የእግዜር ውሀ
ጠአም መልኩ ተቀይሯል
ግድየለችም አትደብቂኝ
ውሀውንም ስመሽዋል
ከሳሙስ አይቀር እንዲህ ነው
ለስለስ አርጎ ሸረፍ አርጎ
መአዛ ጠረን ደባልቆ
በከንፈር አብሾ ልኮ
እንዴነችና ሩብ ጉዳይ ወፈፍ አረገኝ እኮ
እናልሽ ከሳምሽኝ በኋላ
ለሩብ ጉዳይ እጅ ሰጠሁ
ሰአቱ ሙሉ ሆኖ እንኳን
ሩብ ጉዳይ ነው እላለሁ
እውነት እውነት
ከመስታወት ፊት ቆሜ
በውስጡ እኔን እያየሁ
መተት አርጋብኝ ይሆን
እያልኩ እጠይቃለሁ
የጉንጬን የከንፈሬን ጥግ
በእጆቼ እዳብሳለሁ
የዳበስኩትን እጄን
ሩብ ጉዳይ እስመዋለሁ
ወይ ጣጣዬ ወይ መከራ
ግድ የለሽም ልለምንሽ
ግድ የለሽም ተለመኝኝ
አንድ ያጣላል ወዳጄ ሆይ
ሩብ ጉዳይ አንዴ ሳሚኝ
@getmtg
@getmtg
👏6😁2
፡
አንደበቴ ፈርቶ
ፍቅሬን ሳልናገር እንዳለሁት አለሁ
እንዴት እንደው ሳላውቅ
'ለምን?'ታው ሳይገባኝ ብቻ እወድሻለሁ
እንደማይዳስሱት
ሊነካ እንደማይችል ከፍ ያለ ሩቅ ሰማይ
በውበቷ ደምቀው
ይኖሩባት እንጂ
እንደማይጨብጧት የንጋቷ ፀሀይ
እንደማይደርሱበት
አያልቅ ሩቅ መንገድ
እንዳልደፈረሰ
እንዳዲስ ምንጭ ውሃ
ሲሆን የኔ መውደድ
ልክ እንደ ሰአሊ
ጥበብ የለኝ ነገር ከሸራው አልሳልኩሽ
ወይ እንደ ደራሲ
ውብ ቃላት ከትቤ ፅፌ አላወደስኩሽ
ብቻ ግን በሩቁ
የአንቺ መሆን ናፍቆኝ ውበትሽን እያየሁ
ዛሬም በዝምታ
ሳልናገር ፍቅሬን እንዳለሁት አለሁ
ብቻ እወድሻለሁ
@getmtg
@getmtg
አንደበቴ ፈርቶ
ፍቅሬን ሳልናገር እንዳለሁት አለሁ
እንዴት እንደው ሳላውቅ
'ለምን?'ታው ሳይገባኝ ብቻ እወድሻለሁ
እንደማይዳስሱት
ሊነካ እንደማይችል ከፍ ያለ ሩቅ ሰማይ
በውበቷ ደምቀው
ይኖሩባት እንጂ
እንደማይጨብጧት የንጋቷ ፀሀይ
እንደማይደርሱበት
አያልቅ ሩቅ መንገድ
እንዳልደፈረሰ
እንዳዲስ ምንጭ ውሃ
ሲሆን የኔ መውደድ
ልክ እንደ ሰአሊ
ጥበብ የለኝ ነገር ከሸራው አልሳልኩሽ
ወይ እንደ ደራሲ
ውብ ቃላት ከትቤ ፅፌ አላወደስኩሽ
ብቻ ግን በሩቁ
የአንቺ መሆን ናፍቆኝ ውበትሽን እያየሁ
ዛሬም በዝምታ
ሳልናገር ፍቅሬን እንዳለሁት አለሁ
ብቻ እወድሻለሁ
@getmtg
@getmtg
👏8👍2