የግጥም ጥግ
769 subscribers
56 photos
2 videos
7 files
39 links
ያ ዶሮዬ ጮኈ መንጋቱን ነገረኝ፥
ሲነጋጋ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ።

የተለያዩ ምርጥ ግጥሞችን እዚህ

ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት

@Esamif
@amen1995 መጠየቅና መስጠት ይችላሉ።
Download Telegram

"ገና ሳይደርስ ተስፋ የሚቆረጥበት ተስፋ አለ፡፡"

"አልተዘዋወረችም"
👍1

‎አንቺዬዋ

‎ያን ጊዜ ከጎኔ ሳለሽ
‎ያልታየኝ ፍቅርሽ በርትቶ
‎ስትሄጂ ተገለጠልኝ
‎ዛሬ ላይ ከሰው ጋር ባይሽ
‎ይባሱን እያደር ቀናሁ
‎አረ እግዜር አንድ በልልኝ

‎ተስቶት የገፋሽ ልቤ
‎ብታዪው ፀፀት ከቦታል
‎ግድ የለም ተመለሽበት
‎ጥፋቴን ይቅርታ ፍቆት
‎ነጥቄ የኔ ባደርግሽ
‎ብትመጪ ምን ነበረበት

‎ተመለሽ በኔ አትጨክኚ
‎ነይ ስልሽ ተይ አትክፊብኝ
‎አይጠፋ አያረጅ ፍቅር
‎ከአንቺ ጋር ናፍቆት አለብኝ

ነይ ተመለሺ

@getmtg
@getmtg
👍3

አንዲት ፍሬ የአበባ ዘር
‎         ተራራ ጫፍ የበቀለች
‎ሳትታቀድ እንደ ድንገት
‎           አፈር ገልጣ ብቅ ያለች

‌‎ቅን ልቦናን የምትመኝ
‎               አጎልባቿን የምትሻ
‎ወተው ከቅርብ የማያዩያት
‎ቢያዩዋት እንኳን 'ምትታለፍ በጥቅሻ

ለአይን ሞልቶ የሚያማልል
‎      የሚያስቀና ፍካት ያላት                    
‎ደፍረው ጎኗ የማይቆሙ
‎በሩቁ ግን ሳር ቅጠሉ የሚመኛት

‎ያቺን ፍሬ ውብ አበባ
‎አንዱም ቆርጦ ሳይጠጋት
‎              ሳያንኳኳ የአለሟን ደጅ
‎ያስፈራኛል መሽቶ እንዳይቀር
‎እሰጋለሁ በጊዜዋ ሳትቀጠፍ እንዳታረጅ

Mekdi
@getmtg
@getmtg
👍4

ዝግመተ ለውጥ

"እንጋባ" ሲል ጠየቃት አሳምነው፡፡

አልተቀበለችውም አስማሩ፡፡ "ወንድምና እህትነቱ ይበልጣል" አለችው፡፡

ተስማሙ፡፡

ቤቷ እየመጣ ይጠይቃታል፡፡

ቡና ታፈላለች ይጠጣሉ፡ ካላት ታቀርባለች - ይበላሉ፡፡

አውግተው ይለያያሉ፡፡

የትዳር ነገር ዳግም አልተነሳም፡፡

አሳምነው አንድ ቀን በጠራራ ፀሀይ መጣ፡፡

እንደመጣ የደረበውን ሹራብ አውልቆ አስቀመጠ፡፡ ስለሙቀቱ ብዙ አውርተው ተለያዩ፡፡

አስማሩ አሳምነው እረስቶት የሄደውን ሹራብ ልብሷን ስታጥብ አጠበችለት፡፡

ዳግም ሲመጣ ደርቦ ደራርቦ ነበርና የሚያወልቀው እንጂ የሚደርበው ልብስ አላስፈለገውም፡፡

ጃኬቱን አውልቅ ሄደ፡፡

አስማሩ አሁንም አጥባ አኖረችው፡፡

ሱሪውን ደርቦ መጣ "ወበቀኝ!" አወለቀው፡፡

አስማሩ አጥባ አኖረችው፡

ካፓርቱን ጥሎ ሄደ፡

አጥባ አኖረችው፡፡

አንድ ቀን በጠራራ ፀሀይ ብርድ ልብሱን ለብሶ መጣ፡

አስማሩ "ምነው?" አለችው፡፡

"በጠራራ ፀሀይ ብርድ ሆዴ ገባ" አላት፡፡

"ምች ይሆናል" አለችው፡፡ የምች መድኃኒት ብታሽለት ተሻለው፡፡

ሲሻለው ብርድ ልብሱ አላስፈለገውም ጥሎት ሄደ፡፡

አስማሩ አጥባ አኖረችው፡፡

ትንሽ ቆይቶ፡ ፍራሹን ተሸክሞ መጣ፡፡

"ምነው?" አለችው፡፡

"ላሳድሰው መሄዴ ነው፡፡ አይቼሽ ልለፍ ብዬ ነው" አላት፡፡

አመነችው፡፡

ጨዋታው ደራ፡ ፍራሹን እረስቶት ሄዶ ኖሮ እኩለ ሌሊት ቢመጣ አስማሩ ቦታ ስላጣች ፍራሹን ፍራሿ ላይ ደርባው ደረሰ፡፡ ያኔ "ተነሽ" ከማለት "ጠጋ በይ" ማለት ቀልሎ ተገኘ፡፡

ጠጋ አለች፡፡

(ኩርቢት)
😁8

‎አይክፋሽ ተይ አትዘኚ
‎ተይ ብቻሽን ከቶ አልይሽ
‎ ቤት ማረፊያ እንዳጣ ሰው
‎ነይ ልብ አለኝ ነይ ኑሪበት
‎አንቺን መውደድ መናፈቄ
‎ ጭንቅና እንባሽን ካበሰው

‎ብቻ ትንሽ ፍቅር ስጪኝ
‎ያንቺ ደስታ ወትሮ እያደር
‎ ያኖረኛል ግድ የለሽም
‎ማረፊያሽን ኪራይ ብዬ
‎ጊዜና ቀን እየጠበኩ
‎ በይ ክፈይኝ አልልሽም

‎በብቻነት ኖሮ የጤዘ
‎ሙሉነትን ያጣ ነፍሴን
‎ ፍቅር አሙቀሽ ተላመጂ
‎ልሂድም ካልሽ አልይዝሽም
‎ ካልተመቸሽ ካሻሽ ሂጂ

@getmtg
@getmtg
👍2
‎፡
እኔ ምን አውቃለሁ

‎ብቻ ይጨንቀኛል
‎ቅር ቅር እያለኝ ሆዴን ነገር ባሰው
‎ስተክዝ እይዩ
‎አይዞሽ ማለት እንጂ
‎የልቤን ስር ችንካር
‎ መች ያውቅልኛል ሰው

‌‎እነጫነጭ ጀመር
‎በሆነው ባልሆነው
‎ ደግሞም እብሰለሰል
‎እኔ ምን አውቃለሁ
‎ ናፍቀኸኛል መሰል😜

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👏51🤔1

ተ ሸ ክ መ ና ታ ል !!

እናቴ ሁልጊዜ እንድናጠና ስትመክረን እንዲህ ትላለች:-

“እናንተ ልጆች አጥኑ፣ ተማሩ እባካችሁ ! ...እኔ ባለመማሬ ነው ጉዴን ተሸክሜ የዋልኩት!"
ማንበብም መፃፍም ስለማትችል ንግግሯ በቁጭት ነበር፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ይሄ ተሸክማ የዋለችው ጉድ ምን እንደሆነ ለማወቅ ጓጉቼ ጠየቅኳት፣
"ማሚ የምን ጉድ ነው ተሽከመሽ የዋልሽው ?”
አወራችኝ ...

.......... ........ ..........

በደርግ ጊዜ መስከረም ሁለት ቀን ሕዝቡ በግድም ሆነ በውድ የድጋፍ ሰልፍ ይወጣ ነበር፡፡መስከረም ሁለት ደርግ ንጉሱን ገልብጦ ሥልጣን የያዘበት ቀን ነው፡፡ በአጭር አገላለፅ መስከረም ሁለት የደርግ ግንቦት ሃያ ነበር፡፡ ታዲያ እናቴ በወቅቱ የነበረውን የግዳጅ ውትድርና በመፍራት የመጀመሪያ ልጁን ወታደር ቤት እንዳይወስዱባት ከከተማው ወጣ ያለ አከስታችን ቤት ደብቃ፣ሁለተኛ ልጁንም ገጠር እናቷ ጋር ልካ፣ ሦስተኛውን ልጇን አልጋ ስር አስቀምጣ፣ አባቴንም
"ታምሜያለሁ በል!" ብላው፣ እሷ ግን ነጭ ልብስ ለብላ ሰልፍ ወጣች፡፡ ግዴታ ነዋ!

ቀበሌ ስትደርስ ሴት ወንዱ ያለውን ለብሶ ተሽቀርቅሮ፣ ቀበሌውም በተለያዩ መፈከሮችና በባለ ቀለም መብራቶች አጊጦ ጠበቃት፡፡ የቀበሌው የአ..ሴ.ማ ኃላፊ የነበረች ሴት በባለእጀታ የጣውላ ሰሌዳ ላይ ተፅፈው የተዘጋጁ በመቶ የሚቆጠሩ መፈከሮችን ለእናቴ እያሳየቻት፣ ምረጭና አንዱን ያዥ አለቻት፡፡

እናቴ ቀለል ያለችና በደማቅ ቀይ ቀለም የተሽሞነሞነች መፈክር መርጣ አነሳችና ወደ ሰልፉ ተቀላቀለች፡፡ ከለበሰችው የሚያምር የአበሻ ቀሚስ እና ከራሷም ቁንጅና ጋር ተዳምሮ የኦሎምፒክ መከፈቻ ላይ 'ኢትዮጲያ የሚል ምልከት ይዛ ሰልፉን የምትመራ ቆንጆ የአበሻ ሴት ትመስል ነበር፡፡

በዕለቱ መስቀል አደባባይ እናቴን በርካታ ሰዎች በግርምትና በአድናቆት ሲመለከቷት ዋሉ፡፡ ታዲያ በዚያ ሰሞን ማታ በቴሌቪዥን ደጋግመው እናቴን ከነመፈhሯ ያሳይዋት ጀመረ፡፡ ምን ይሄ ብቻ፡ አመቱን ሙሉ ፎክረውም እናቴን ማሳየት፣ ኢህአፓ ብለውም እናቴን፣ መኢሶን ብለውም እናቴን፣ ቀይ ሽብር ብለውም እናቴን፣ ጓድ ሊቀመንበር ተናግረው ሲያበቁም እናቴን ማሳየት::

ጭራሽ ብሔራዊ ውትድርና ተብሎ ምድረ ወጣት ሰጓፈፍ ፣ የብሔራዊ ውትድርና አገር አቀፍ ዓርማ የእናቴ ፎቶ ሆኖ በየቦታው ተለጠፈ፡፡ በነጭ ልብስ ተውባ መፈክር ይዛ የቆመች እናቴ የብሔራዊ ውትድርና አገር አቀፍ አርማ ሆነች፡፡ እንድ ጋዜጣ ላይ የእናቴ ፎቶ ስር እንዲህ የሚል ጽሑፍ ሰፍሮ ነበር
"እብዮታዊት ሶሻሊስት ኢትዮጵያ ነጭ ቀሚስ ለብሳ"

እናቴ ታዲያ መጀመሪያ አካባቢ በቴሌቪዥን በታየች ቁጥር በቁንጅናዋ የተመረጠች መስሏት አባቴ ላይ በኩራት ትነሰነስበት ነበር፣

"ጓዳ ለጓዳ ስውል ቀላል ሰው አድርገኸኝ፣ እግሬ ወጣ ካለ አገር ነው የሚሰግድልኝ" ትለዋለች ኮራ
ብላ፡፡ አባቴ አፉን ሸርመም አድርጎ፣ "እዩኝ እዩኝ ማለት ደብቁኝ ደብቁኝ ያመጣል !" ይላታል::

የቅናት ወሬ ነው ይሄ ትልና ሆነ ብላ ለማበሳጨት በቴሌቪዥን ደጋግሞ የሚታየውን ምስሏን አተኩራ እየተመለከተች፤
“እንዲት ፍሬ ልጅ እኮ ነኝ" ትላለች፡፡ አባባ ታዲያ “ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ…” ብሎ በረዥሙ ይስቅና
"ሰልፍ ላይማ መንግስትም አንድ ፍሬ ነኝ ነው የሚለው" ይላል፡፡

“ኤዲያ እንግዲህ ቦለቲካህን ልትጀምር ነው…” ብላ ወደ ጓዳዋ ትገባለች፡፡

ይሁንና እናቴ እየቆየች በቴሌቪዥን መታየቱ እና ስለ እርሷ መወራቱም ሲደጋገምባት ፈራች::

በተለይም ጓድ መንግስቱ ኃይለማሪያም መስቀል አደባባይ በትልቁ የተሰቀለውን የእናቴን ፎቶ ለተሰበሰበው ሕዝብ እያሳዩ በደም ፍላት፣

"እንደነዚህ ዓይነት ጀግና እናቶች ያሉባት አገር በማንም ወመኔ ከሃዲ ስትወረር እንዴት ወንዶቿ አልጋ ስር ይደበቃሉ? እነዚህን ቦቅቧቃ ወንዳገረዶች ቂጣቸውን በሳንጃ…” እያሉ ንግግር ካደረጉ በኋላ እናቴ ስጋቷ ከፍ አለ፡፡

ስጋቷን ለማስታገስ፣ “ኧረ ይሄ መፈክር ምንድን ነው የሚለው?” ብላ የተማረ ሰው ጠየቀች፡፡ መስከረም ሁለት ሰልፍ ላይ ይዛ ስለወጣችው መፈክር ተሸክማው ስለነበረው ጽሑፍ ሚያዚያ ላይ "ምንድን ነው?" ብላ ጠየቀች፡፡ሲነበብላት አመዷ ቡን አለ ፡ ብርክ ያዛት፡፡

መፈክሩ እንዲህ ነበር የሚለው....
"የአብዮት ጠላቶችን ለማደባየት እኛ እናቶች ልጆቻችንን፣ ካስፈለገም ባሎቻችንን በደስታ እናዘምታለን!!"


(ዶክተር አሸብር እና ሌሎችም)
😁8

ግጥም እንዲሁም የተለያዩ ፅሁፎች አሉኝ የምትሉ እና ስራችሁን በዚህ Channel ማሳየት የምትፈልጉ ካላችሁ
በውስጥ መስመር
👇👇👇
@Esamif
@amen1995
ስራዎቻችሁን መላክ ትችላላችሁ፡፡

መልካም ቆይታ🙏
👍2
ያኔ...
በልክ አርጊው ሲሉኝ ሁሉም ነገር ያልቃል
ያፋቸው ቃል እንጂ መች መስሎኝ ትንቢት ቃል
መቼም አያበቃም ገደብ የለው ያልኩት
መውደዴ ሲያልቅ ነው ልቤን የታዘብኩት።
ጥልቅ ነው እያልኩኝ ብዙ ነው እያልኩኝ
ከልብ አንጠፍጥፌ መውደድን ጨረስኩኝ
ያኔ....
ባገኝህ...ባዋይህ
እንደ ምስለ ቅዱስ ደጋግሜ ባይህ
እንደ አጥቢያ ደብር ነግቶ ብሳለምህ
ወይ እንደ ዉቃቢ ሠርክ ብለምንህ
አይበቃኝ የነበር
አፍታም አልፈጀበት መዉደዴ ሲሰበር።
ያኔ...
ጠዋት ፀሀይ ሞቃ
ሌት ጨረቃ ደምቃ
እወድህ የነበር ልኬት እሰካይኖረኝ
ዛሬ ምን ቀየረኝ?
ይኸው..
ፍቅር አንቱ ተብሎ እነዳልነገሰበት
ጥላቻም በኔ ልብ ተራዉ ደረሰለት
ጠላሁህ አንተዬ ከልቤ አወጣሁህ
ላይኔ እንደናፈከኝ አያሳየኝ አልኩህ
ደግሞ ጠብቃለሁ
ጊዜ በጎዳናዉ ተሸራርፎ ወድቆ
ምን እንደሚፈጠር ጥላቻዬም አልቆ
👍7👏2

ባዶነት ወዳጄ ነበር
‎ጠፍቼ ነበር ከራሴ አለኝ ያልኩትስ መች አለኝ
‎አሁን ላይ ቀኑ ተለየ
‎በድንገት አይኔን ሳማትር ሳይሽ ግን አለሜ ታየኝ

‎ሳላውቅሽ መናፈቅ ተማርኩ
‎ያልነጋው ጨለማው ልቤ የተስፋ ፀሀይ ወጣለት
‎እንቺነት ነፍስን ሲዘራ
‎የመኖር ትርጉሙ ገባኝ ያየሁሽ የዛችን እለት

‎በሳቅሽ ሰርክ አማረብኝ
‎እያደር መሻቴ ወዛ ምኞቴ ግቡን ተጓዘ
‎እጦት ስር ወድቆ የነበረ
‎በብሶት ዝብርቅርቅ ያለው እኔነት መስመሩን ያዘ

‎ሄድንበት ጎዳና ምድሩን
‎ዋልንበት ጫካ ሜዳውን ሀሴትን አጎናፀፈን
‎ከፍ አልን በመውደድ ግርማ
‎እንደልጅ ፍንድቅድቅ አልን አያረጅ ፍቅር አቀፈን

‎በምናብ ነገን ቃኘነው
‎አሰላን ኑሮ ቀመሩን አንድ ሆነ የእኛነት ውሉ
‎አሙቀሽ በረዶ አካሌን
‎ፈጥረሽኝ ነበር እንዳዲስ አድርገሽ አለሜን ሙሉ

‎ደምቄ ነበር ካንቺ ጋር
‎ታይቼ ነበር አምሮብኝ ሆነሽኝ የልቤ ሀገር
‎ምን ትርጉም ምንስ ዋጋ አለው
‎ይህ ሁሉ እያለሽ ነበር

‎ስትመጪ ቀን የወጣለት
‎ያነሳኝ ያቀናኝ ፍቅርሽ ስትሄጂ ጠቁሮ ዳመነ
‎የመኖር ትርጉሜን አጣሁ
‎ይባሱን ከራሴ ጠፋሁ ባዶነት ወዳጄ ሆነ

‎ያማረው ፊቴ ገረጣ
‎በናፍቆትሽ ጣር ከስሜ አግኝቶ ማጣት ሰበረኝ
‎ሄድሽ እንጂ በእኔ ጨክነሽ
‎ከአንቺነት መፅናኛ ፍቅር ሌላ እንኳ ምንስ ነበረኝ

‎ብሶቴን እንዳዲስ ዘራሽ
‎በፍቅርሽ የረጋው ልቤ ስትሄጂ መስመሩ ራቀው
‎መልሶ ዝብርቅርቅ አለ
‎ዳግሙን ፀንቶ እስኪፈካ ያንቺ ቃል እየናፈቀው

@getmtg
@getmtg
👏41👍1

የደራሲ ቅጣት ...

የሆነ ሰውዬ ይሞትና ገነትንም፣ ሲዖልንም ይጎበኛል፡፡ ገነት ሲደርስ በጎ ምግባሮች እንደቀጠሉ ናቸው። መልካም ሰርተው የፀደቁትንም አስተዋለ፡፡ ይልቅ የገረመው አንዲት ዛፍ ስር ቁጭ ብሎ የሚፅፍ ሰው ተመለከተ። ገረመውና ምን እንደሆነ ቢጠይቅ "ደራሲ ነው" አሉት። እየተደነቀ “አይ ደራሲ ፀድቆም አያርፍ፣ አሁኑም ይፅፋል” ሲል ተደመመ።

ከሚንቀለቀል የእሳት እቶትን ውስጥ የሲዖልም ሕይወት ቀጥላለች። አመፅ፣ ግርግሩ፣ ጦርነቱ…ኃጥያቱ አናት ባናቱ ይደራረባል። አሁንም አንድ ሰውዬ ከእሳት ዛፍ ስር አረፍ ብሎ በእሳት ብዕር፣ በእሳት ወረቀት ይቸከችካል። ተመልካቹ ሰውዬ ግራ ተጋባም ምን ሊሆን ይችላል ሲል እያሰበ ጠየቀ "ደራሲ ነው፣ ይከትባል" አሉት።

እየተገረመ፣ እየተደነቀ መልዓኩን "ቆይ ደራሲ እዚህም ሲፅፍ አይቼዋለሁ… እዛም ሲቸከችክ ተመልክቼዋለሁ ካዲያ ገነትም ገባ፣ ሲዖልም ወረደ ምን ቀረበት? ምንድነው ቅጣቱ? ምን ተጎዳ?" ሲል ጠየቀው።

መልዓኩም መለሰለት “ገነት ያሉት ይታተምላቸዋል"

(By Alemayew Gelagay)
😁9

"ደህና ነህ ወይ?" ስለው
‎ሁሉ እንደሞላለት "ደህና ነኝ" ይለኛል
‎ለዚህ ጥያቄ መልስ
‎ተመሳሳይ ውሸት
‎"ደህና ነኝ" መሆኑን ቀድሞ አሳውቆኛል

‎የእውነት ደህና አይደለም .......

‎ምን ሆንክ እንዳልለው
‎ ምንም ነው መልሱ
‎አትዋሽ እንዳልል
‎ 'ለምን'ታ ነው ክሱ

‎ጭንቁን በፈገግታው
‎ሊሸፍን ቢቃጣም
‎ እንደተረበሸ ያስታውቅበታል
‎ይህ ጊዜ አደብ ገዝቶ
‎ተስፋው ያነሳው 'ለት
‎ሳይሰስት ከልቡ ሲያልፍ ይስቀበታል

‎ (መቼ እንደሚያልፍ ባላውቅም)

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👏9👍31

ተፈጥሮን ደጅ ልጥና

" እኔ ልሙትልሽ" እያልኩኝ አልምልም
ቃላቴን መንዝሬ፤ ለሞት ቀብድ አልከፍልም

ያኔ ትዝ ይልሻል?
"ራስህን ግደል" ብለሽ በረኪና የላክሽልኝ ጊዜ
እድሜ ለስጦታሽ፤ ታጠበ ሸሚዜ።

ገደብ ጫፍ በሌለው፤ በልቤ መጋዘን
ቢታጨቅ መከራ፤ ቢጠራቀም ሀዘን

"ባለፈልኝ" እንጂ "በሞትኩ" ብየ አላቅም
ካልጋ ላይ ነው እንጂ፤ ከፎቅ ላይ አልወድቅም።

በሀኪሙ ስተት፤ በቁሜ ብከፈን
በወርድ በቁመቴ፤ ሳጥኔ ቢደፈን

ከጭስ እቀጥናለሁ፤ እኔ መውጫ አላጣም
በጠጅ በወይን አገር፤ ሽጉጤን አልጠጣም።

የተመደበልኝ ዘመን ከባከነ
የተሰፈረልኝ፤ ቀን አልቆ ከሆነ

ተፈጥሮን ደጅ ልጥና
ባዲስ መንገድ ትስራኝ፤
ባዲስ የፍጥረት ውል
መስኮትሽ ላይ ሆና

ስትዘምር የምትውል ድንቢጥ ወፍ ታድርገኝ
ብኖር አንቺን አየሁ፤ ከመሞት ምን ሊገኝ።

        (በእውቀቱ ስዩም)
👏7

ካንተ ጋ እንዳልኖርኩኝ
‎ቀን መለየት ቆጥሮ ብቸኛም ቢያደርገኝ
‎ሳስብ ይቆጨኛል
‎መቼም ያንተን ያህል ሰው እንደማላገኝ

‎መች ይጠፋና ነው
‎የአነጋገር ለዛህ የአንተነትህ ምስል
‎መራቅህ ነው እንጂ
‎በጭንቅ ያማቀቀኝ የዘራብኝ ቁስል

‎መች ይረሳና ነው
‎ያለፍንበት ትላንት ያሳለፍነው ጊዜ
‎ዛሬን ጎኔ ባትሆን
‎ከፍቶኝ መሽቶ ነጋ ዋልኩኝ በትካዜ

‎ፍቅርህ ባይቆርጥልኝ
‎አንተነትክን ስራብ
‎             ናፍቆት ባይሆነኝ መልስ
‎እያልኩ አስባለሁ
‎ምናል ያ ደግ ቀን ዳግሙን ቢመለስ

@getmtg
@getmtg
👍7

ተው ብዬህ ነበረ ......

‎እጅህን ከእሳት
‎ልብህን ከክፋት ከቶ እንዳታስጠጋ
‎መቃጠል መንደድ ነው
‎ይኮንናል እንጂ አይሰጥህም ፀጋ

‎ውስጥህ ካላመነ
‎ዝም ማለት ልመድ አፍህ አይቀባጥር
‎ብቅል ብቻ አይደለ
‎ሰውም ያወጣዋል የሆድህን ሚስጥር

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👏6

ናፍቀኸኛል

‎አይኔን ስገልጥ
የሚታየኝ ያንተ ምስል
‎ሆኛለሁኝ በናፍቆትህ
‎ጠዋት ማታ እየጠቆርኩ የምከስል

‎መንገድ ጊዜ ቢያለያየን
‎ ትዝታህ ነው ለኔ ስንቄ
‎አይግረምህ ዛሬን ሳጣህ
‎ በናፍቆትህ መንሰቅሰቄ

‎የሄድኩበት የሄድክበት
‎ እንደው ወዴት አደረሰን
‎ምን እንደሆን ያንተን ባላውቅ
‎ ያሳለፍነው እልፍ ፍቅር
‎ ይመስለኛል የከሰሰን

‎ናፍቀኸኛል

‎ከከደንኩት የአይኔ ሽፋን
‎ ያንተ ምስል የገለጠው
‎መለየትን በመርሳት ልክ
‎ አንተነትክን መች ለወጠው

‎ምናልባቱን ከናፈኩህ
‎ ፈጥነህ መቼ ትመጣለህ
‎ራቅከኝ እንጂ አልወጣህም
‎ ዛሬም እኮ ከውስጤ አለህ

@getmtg
@getmtg
👍6

ቅናቴ
‎ (በአበባው መላኩ)

‎ፍቅሬን ሜዳ ላይ ጥላ
‎ ስትከዳኝ አይቻታለሁ
‎እንደገፋችኝ ትገፋ
‎ እያልኩ እረግማታለሁ

‎ዘወትር ሙሾ ታላዝን
‎ የእንባ ማዕበል ይጠባት
‎ደስታዬን እንዳጨለመች
‎ ደስታዋ ይጨልምባት
‎ሺህ እጥፍ ትጨድ አበሳ
‎ ለዘራችብኝ ጥፋት

‎ እያልኩ እረግማታለሁ(2)

‎የኮራችበትን ገላ
‎ መብረቅ ያንድደው በቁጣ
‎በላይዋ ዲም ይውረድባት
‎ ጥጋት መሸሻ ትጣ

‎ እያልኩ እረግማታለሁ(2)

‎የምድር የቀላይ ጥፋት
‎ በላዩዋ ይውረድ ኩነኔ
‎ኑሮዋን ሲኦል ያድርገው
‎ ስቃዩዋን የያሳየኝ በአይኔ

‎እንደከዳችኝ ትከዳ
‎ የኔ ያለችው ይሽሻት
‎ቀላዋጭ አይኗን ያፍርጠው
‎ ከውካዋ እግሯን ያልምሻት

‎ እያልኩ እረግማታለሁ(2)

‎ክንዷ በመጅ ይሰበር
‎ ሌላ ያቀፈችበት
‎አባጨጓራ ይሙላው
‎ ፍራሹ የተኛችበት

‎ እያልኩ እረግማታለሁ(2)
የሌላ ሆና ብትከዳኝ
‎ አይጠሉ ጠልቻታለሁ

‎ስለ ማህተቤ ብጠየቅ
‎ከአለም ላይ ካለኝ የምሻው
‎ የረገምኳትን እላለሁ
‎ሌላም እርካታም የለኝ
‎ እሷን አምጡልኝ እላለሁ

‎ጥላቻዬና ፍቅሬ ናት
‎ እርግማንና በረከቴ
‎ያለሷ ህይወት የሌለኝ
‎ ያሳበደችን ቅናቴ

‎ ቅናቴ

‎ ቅናቴ

@getmtg
@getmtg
👏5👍1

ከሄድኩማ ርቄ
‎ማወቅ አልፈልግም
‎የመወደዴን ልክ የመውደዴን መጠን
‎ሳለን ነበር እንጂ
‎ስንሆን በአንድ መንገድ
‎ ትርጉም የሚሰጠን

‎ካለዚያማ .....
‎ሀሳብ እዛ እና እዚህ አራምባና ቆቦ
‎ህይወት ፍሬ ምርቷ
‎ መቼ ያምርና ነው
‎ ስሩ ያልተነቀለ አረም ተሰብስቦ

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍6👏4

የንፁህ ደም በየቀዬው እንደኩሬ ይንሳፈፋል
ስንቱ ተስፋ የሰነቀ መንፈቅ እድሜ ሳይኖር ያልፋል
ለሰርጉ ቀን የተከሉት እንሶስላው አልበቀለም
እንኳን ወልዶ መሳም ቀርቶ ወጥቶ መግባት አልቀለለም

ቀኔ ደርሶ ከሰው እኩል በድኔን ዶዘር እሲኪያነሳው
  ( ይህንን ቃል እንዳልረሳው!)

ጩኽት ብቻ ነጋ ጠባ ዋይታ ብቻ መሸም ነጋም
መኖር ፍፁም አያጓጓም
በየ ደጁ በየ ጓዳው የሲቃ ድምፅ ሲያስገመግም
ምንም ተስፋ በሌለበት ተስፋ ማድረግ አልፈልግም

አታልቅሺ አትዘኚ  በድኔን ከሞት ላታስነሺው
ቢሆንም ግን (ይህንን ቃል እንዳትረሺው)

ሳልደነቅፍ _ ሳልሸራርፍ   አንዲት ፊደል ሳልሳሳት
ያሰብኩትን ሳልናገር  አፈር ልቤን አይቅመሳት
ታሪክ ህልሜን _ ገላ ጨርቄን  ጉድጓድ አፈር ሳይቀበል 
  አንዴ ብቻ ይህን ልበል!

የጥም ውሃ ባያጠጡኝ  ህመም ቁስሌን ባያክሙት
እንደምንም አንዴ ብቻ "ወድሻለሁ" ብዬ ልሙት።

        እወድሻለሁ

(አስታወሰኝ_ረጋሳ)
👏7

"ማን ለ ማን?" ያሉኝ 'ለት
‎ ካላልኩ እኔ ለእኔ
‎ለካ ምንም ነው
‎አለሁ ያልኩበት ቃል
‎ ኖርኩ ያልኩበት ወኔ

‎ላላንስ ያኮሰሱኝ
‎ልችል አጣጥለው ዝግ አርገው ቢነጉዱ
‎አላወቁም ኖሯል
‎ከአፍ አፍታ በላይ
‎ተግባር እንደሆነ ብርቱ ሰው መንገዱ😊

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍51👏1

ሩብ ጉዳይ(የሳምሽኝ ልጅ)
‎ በሰለሞን ሳህለ

‎ነፍሴን ከነፍስሽ አጣምረሽ
‎ የአለም ጥግ ላይ ያኖርሽው
‎ሩብ ጉዳይ የሳምሽኝ ልጅ
‎ ጥበቡን ከየት ተማርሽው

‎እውነት እውነት
‎ከንፈርሽ በጣም ልዩ ነው
‎ የሜንት ጠረን ታድሏል
‎ሰሞኑን የሳምሺው ጉንጬ
‎ አየር ማስገባት ጀምሯል
‎በሩብሽ እንዲህ የሆነው
‎ የጉንጬ ከንፈር ጥጉ
‎በሙሉ ቢሆን ኖሮማ
‎ልቤና ነፍሴ ተማክረው
‎ እኔኑ ጥለውኝ ባረጉ

‎እውነት እውነት
‎ለካንስ የመሳም ጥበብ
‎ እጅጉን እጅግ ተራቋል
‎በሜንት ጠረን ታጅቦ
‎ በሩብ ጉዳይ ልብ ይሰልባል

‎እኔ እምልሽ
‎ይሄ የምሄድበት ጎዳና
‎ ጠረኑ በሜንት የናኘው
‎ንፋሱንም ልክ እንደኔ
‎ ሩብ ጉዳይ ስመሽው ነው?

‎እውነት እውነት
‎የምጠጣው የእግዜር ውሀ
‎ ጠአም መልኩ ተቀይሯል
‎ግድየለችም አትደብቂኝ
‎ ውሀውንም ስመሽዋል

‎ከሳሙስ አይቀር እንዲህ ነው
‎ለስለስ አርጎ ሸረፍ አርጎ
‎መአዛ ጠረን ደባልቆ
‎በከንፈር አብሾ ልኮ
‎እንዴነችና ሩብ ጉዳይ ወፈፍ አረገኝ እኮ

‎እናልሽ ከሳምሽኝ በኋላ
‎ ለሩብ ጉዳይ እጅ ሰጠሁ
‎ሰአቱ ሙሉ ሆኖ እንኳን
‎ ሩብ ጉዳይ ነው እላለሁ

‎እውነት እውነት
‎ከመስታወት ፊት ቆሜ
‎ በውስጡ እኔን እያየሁ
‎መተት አርጋብኝ ይሆን
‎ እያልኩ እጠይቃለሁ

‎የጉንጬን የከንፈሬን ጥግ
‎ በእጆቼ እዳብሳለሁ
‎የዳበስኩትን እጄን
‎ ሩብ ጉዳይ እስመዋለሁ

‎ወይ ጣጣዬ ወይ መከራ
‎ግድ የለሽም ልለምንሽ
‎ ግድ የለሽም ተለመኝኝ
‎አንድ ያጣላል ወዳጄ ሆይ
‎ ሩብ ጉዳይ አንዴ ሳሚኝ

@getmtg
@getmtg
👏6😁2