የግጥም ጥግ
769 subscribers
56 photos
2 videos
7 files
39 links
ያ ዶሮዬ ጮኈ መንጋቱን ነገረኝ፥
ሲነጋጋ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ።

የተለያዩ ምርጥ ግጥሞችን እዚህ

ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት

@Esamif
@amen1995 መጠየቅና መስጠት ይችላሉ።
Download Telegram

"ምቾት ችግሩ ወደፊት እንጂ ወደ ኋላ መመለስን አለመፍቀዱ፡ ወደ ላይ እንጂ ወደ ታች መውረድን አለመፈለጉ ነው፡፡ ምቾት ጥሩ ቢሆንም ከደረጃ ላለመውረድ የሚያስከትለው ትግል በራሱ ጭንቀት ፈጥሮ ቆይቶ ምቾትን መልሶ መንሳቱ አይቀርም፡፡ በምቾት ወስጥ ምቾት የለም!"

"ሰበዝ"
👍2

የተስፋ ቃል

ለማይሆነው
ለማይሰምረው
         ይሁን ብሎ ችክ ማለት
እንዴት ይሆን የቃል ውሉ
         ከሀሳብ ጋራ ግብብነት

በላዩ አለም ተሸፍኖ
እውነት አለ ያልተሰማ
ምላሽ ፍርዱ ላልተሰጠው
አገኘሁ ሲል እጦት ሞልቶት
አካል ልቡም ለከዳው ሰው
  ....... መኖር ለሱ ቅጣቱ ነው

እንግዲያውስ የመረታት
ላመኑበት ብኩን መሆን
ምላሽ ይሄ ከሆነማ
የላይ ላዩን ማመን ገዶት
ምስኪን ልቡን ለተቀማ
ያልፋል የሚል ሀቅ ረስቶ
   ጊዜያዊን ቃል ከቶ አይስማ

ላያዛልቅ ወሳጅ መንገድ
ትርፉ ሊሆን ከዛው መንጎድ
ሳይጀመር ይብቃም ይባል
ምን ሊረባ ካልኖሩበት
አለሁ የሚል የተስፋ ቃል

Mekdi

@getmtg
@getmtg
1👍1

አብሮ ሲሆን ጊዜ ይከንፋል
  ብቻን ሲሆን
ካላልፍ ቀን ያሳርፋል

አብረው ሆነው የሄዱበት
    ያለፉበት መንገድ ድባብ
                  ሳይታወቅ ያደረሰ
ብቻን ሆነው ቀን ሰአቱ
      ፈጥኖ ነገን አይጠጋም
                   ትዝታን እያጎረሰ

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍1

"ብዙ ጊዜ ሰው አደገኛ ወጥመድ ውስጥ የሚወድቀው በሁለት መንገድ ነው፡፡ አንዱ የሰራሁትን ሰው አያውቅብኝም ሲል ሁለተኛው መቼም ታውቆብኛል ይሁን ምናባቱ ሲል ነው፡፡"

"ፍቅር_እስከ_መቃብር"
👍3

እንዳልታጣ እንዳልጎደለ
ሁሉ ሀሳቡ እንደሞላለት
      ሀዘን ደርሶ እንዳልጎበኘው
ተስፋን ይዞ የጠበቀ
ከደስታ አለም ሰላም ደጃፍ
          ከርሞ ራሱን ባያገኘው

ሲያመጣ ቀን ሁሉን ባንዴ
ሲደራርብ እለት በእለት
         ባይቀል እንኳን ኑሮ ጓዙ
በጊዜው ልክ በእድሜ ጥላ
ያልሆኑትን አይሆን ሆነው
         የሚያልፍ ቀን አለ ብዙ

ላይወራ ላይነገር
        ዝም ማለት ያደረጀው
የጠቆረው እስኪነጣ
       ሆድ ያባውን እስኪፈጀው
                            
ነገር ሊጥል ሲጠላለፍ
      ቀን ሊያነሳ ሲያንገዳግድ
ወደ ቀናው ኑሮ መንገድ
         ብርቱነትን እስኪማግድ
          
ቀን ማለፉ ተስፋው ሆኖ
በነጋልኝ 'ለት ጥበቃ
ወትሮ ራሱን ያባበለ            
ከዛሬው ላይ በድን ሆኖ
አለ መባል እየቀጣው
            ስንቱን ስቃይ ተቀበለ

ሰላም ነግቶ እንደመሸለት
ከዙሪያው ጋር ተመሳስሎ
     ባይሞላ እንኳን ላለመጉደል
ሰው ብሶቱን እያሰበ
ለአይን ደስታን ተመስሎ
             ያሳልፋል ስንቱን በደል

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍1

                🌼 እንቁጣጣሽ 🌼

እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም በጤና አሸጋግረን፡፡

2018
°°°°°°°°°°°°°°°
            🌼መልካም አዲስ ዓመት!🌼


        🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
👍21
🌼

አደይ ፍኪ
አምጪ አዲስ ቀን
እንቁጣጣሽ
እኔም ልድመቅ
አንቺም ኑሪ ሁኚ ጎኔ ደስታ አልጣሽ

ነይ እንዳሻን .....
ልባችን ላይ ሰላም ነገሶ
ተያይዘን እንቦርቅ
...... እስኪ እንፍካ ......
የእስር ትብታብ ተፈቆልን
ነፃ መሆን ይሁነን እርቅ😊

🌼🌼🌼

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍41

ሊያልፍ እንደሆን የደስታ አመል
               ጥግ ጥጉን ተያይዞ
መሃሉ ግን አልድን መሳይ
     በጭንቅ እቅፍ እንባ አርግዞ

ሊያልፍ እንደሆን የሚመጣው
               አልገፋ የሚል ቀንም
ሲለዋወጥ እንደ እውነታው
        የሚያኗኑር ሸሽቶ አመልም

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍2
.

እንደው ቀና ቀና
እንደው ሳቅ ፈገግ
የጠፋውን ደስታ ልክ እንደመፈለግ

አይችል የለ ነገር
ቀን ሲፈትን ጊዜ ደህና ነኝ እያሉ
ህመም ሲያስተጋባ
በደህንነትም ቃል እየተከለሉ

ይመሻል ይነጋል
እንዲህ በመምሰል ውስጥ
             ...... እውነት ይወለዳል

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍31

"ሰው ጥሩ ሲሆንልህ ጥሩ ለመሆን የሚያስገድድ አፀፋዊ ግዴታን የሚፈጥር ነገር በሰው ውስጥ ሳይኖር አይቀርም፡፡"

"የተቆለፈበት ቁልፍ"

ለምን እንደው ባላውቀውም
ሳይታሰብ እንደድንገት
ሰላምታችን ተቋረጠ
ወትሮ ወሬ 'ማይጠፋበት
ቅን አሰሚ ልሳናችን
ዝም ማለትን መረጠ

የሆንነውን ሀቅ እንቅጩን
ወይ ተናግረን አልወጣልን
መች ተገኘ ውስጠ ሰላም
የላይ ላዩን ሆንን እንጂ
ዝም ብለን ዝም አላልን

ብቻ እንዲሁ ዛሬም አለን

ዝም ..........

Mekdi

@getmtg
@getmtg
2👍2

"እውነተኛ ነጻነት የኅሊና ነጻነት ነው፡፡ የኅሊና ነጻነት ደግሞ እውነትን በማወቅና በመኖር ነጻ ከወጣ አእምሮ ብቻ የሚገኝ ጸጋ ነው፡፡"

"የተቆለፈበት ቁልፍ"
👍2

"በመምከር ውስጥ ተመካሪውን ደካማ አድርጎ የማየት ስስ መታበይ አለ፡ ሲኖሩት ግን ሌላ አለም ነው፡፡""

"አልተዘዋወረችም"
👍1

"ምናልባትም እያንዳንዱ ጓደኝነት ውስጥ ትንሽ ትንሽ ጠላትነት ሳይኖር አይቀርም፡፡"

"አልተዘዋወረችም"
👍3

ይቆጭ የለም እንዴ ....

በእጅ የያዙትን ወርቅ
መዳብ ነው እያሉ ክብሩን ያረክሱታል
እንደሆነ እንዳይሆን
  ካለበት አውርደው ሁሉን ይነሱታል

ታድያ ......
የይለፍ ይለፍ ቀን
    የረከሰ ስሙን የትዝብቱን ውጦ
ህያው እሱነቱን
መዳብነት ወርቁን ያሳያል ገልብጦ

ይለፍለት እንጁ
ቀላል አልነበረም ባልሆኑት መታሰብ
ወትሮም ያለ ቦታው
ቅይምትን የሚጭር ከንቱ ቃል መሰብሰብ

ቀላል አልነበረም
ከሆኑበት ወርደው በአጉል ስም መጠራት
በሰው አፍ ውሎ አድሮ
      በይሉኝታ እሳቤ
               የአልሆን ኑሮን መፍራት

              ....... ቀላል አልነበረም

Mekdi

@getmtg
@getmtg

"ሰው ካልታወሰ ምኑ ይፈቀራል? የመፈቀር ተቃራኒው መጠላት አይደለም ፡ መረሳት ነው፡፡"

"አልተዘዋወረችም"
👍2

ብሶት እየቆጠርክ
        በችግር አታማር
ይልቅ ቀና ብለህ ብርቱነትን ሰንቅ
እኛም በሆዳችን
         ጭንቃችንን ውጠን
በአፋችን "ደህና ነኝ" እያልን ነው 'ምንስቅ

           ችርስ ተስፋችንን😊

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍61

እልህ

ለጥበብ ቀዳሚው
ጥበብ መጀመሪያው ሲጋራ ማጤስ ነው
እያለ የሚያወራው
ያ ከንቱ ወዳጅሽ
እንዲህ ስላወራሽ .... ስቀሽ ነበር አሉ
ያውም .....
እጅሽን ዘርግተሽ
እግርሽን አንስተሽ
ይሁን
ይሁን
ይሁን
ሳቂ ችግር የለም
ግን
እኔ የምናደድ የምበሽቅ መስሎሽ
እንዴት ከ"ማንም" ጋር የትም ትሆኛለሽ፡፡

(በኤፍሬም ስዩም)
👍2

"ገና ሳይደርስ ተስፋ የሚቆረጥበት ተስፋ አለ፡፡"

"አልተዘዋወረችም"
👍1

‎አንቺዬዋ

‎ያን ጊዜ ከጎኔ ሳለሽ
‎ያልታየኝ ፍቅርሽ በርትቶ
‎ስትሄጂ ተገለጠልኝ
‎ዛሬ ላይ ከሰው ጋር ባይሽ
‎ይባሱን እያደር ቀናሁ
‎አረ እግዜር አንድ በልልኝ

‎ተስቶት የገፋሽ ልቤ
‎ብታዪው ፀፀት ከቦታል
‎ግድ የለም ተመለሽበት
‎ጥፋቴን ይቅርታ ፍቆት
‎ነጥቄ የኔ ባደርግሽ
‎ብትመጪ ምን ነበረበት

‎ተመለሽ በኔ አትጨክኚ
‎ነይ ስልሽ ተይ አትክፊብኝ
‎አይጠፋ አያረጅ ፍቅር
‎ከአንቺ ጋር ናፍቆት አለብኝ

ነይ ተመለሺ

@getmtg
@getmtg
👍3

አንዲት ፍሬ የአበባ ዘር
‎         ተራራ ጫፍ የበቀለች
‎ሳትታቀድ እንደ ድንገት
‎           አፈር ገልጣ ብቅ ያለች

‌‎ቅን ልቦናን የምትመኝ
‎               አጎልባቿን የምትሻ
‎ወተው ከቅርብ የማያዩያት
‎ቢያዩዋት እንኳን 'ምትታለፍ በጥቅሻ

ለአይን ሞልቶ የሚያማልል
‎      የሚያስቀና ፍካት ያላት                    
‎ደፍረው ጎኗ የማይቆሙ
‎በሩቁ ግን ሳር ቅጠሉ የሚመኛት

‎ያቺን ፍሬ ውብ አበባ
‎አንዱም ቆርጦ ሳይጠጋት
‎              ሳያንኳኳ የአለሟን ደጅ
‎ያስፈራኛል መሽቶ እንዳይቀር
‎እሰጋለሁ በጊዜዋ ሳትቀጠፍ እንዳታረጅ

Mekdi
@getmtg
@getmtg
👍4