የግጥም ጥግ
770 subscribers
56 photos
2 videos
7 files
39 links
ያ ዶሮዬ ጮኈ መንጋቱን ነገረኝ፥
ሲነጋጋ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ።

የተለያዩ ምርጥ ግጥሞችን እዚህ

ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት

@Esamif
@amen1995 መጠየቅና መስጠት ይችላሉ።
Download Telegram

ለመረሳት ተብሎ ኑረት
ለመታወቅ ሲሉ ውድቀት
'ልታይ ልታይ' መባከን ነው
የልብ ስር አጉል ሙቀት

ልኩራ ካሉስ በዝምታ
ልኑር ካሉ ከቅን ልብ ውስጥ
ከወደዱት ዘልቀው ገብተው
ነፃነትን ከእውነት ደጃፍ
ያለ እራስን ላለማጣት
መኖር ካሉስ ሁሉን ትተው
በቃ .........

✍️Mekdi
👍2

"ማፍቀር እንጂ መፈቀር መለኪያ የለውም፡፡ መፈቀር እምነት ነው፡፡ ማፍቀር ደግሞ እውነት፡፡ ....... ፍቅር ብፁዕነትም ነው፡፡ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው እነዲል መጽሐፍ፡፡"

                             "አለመኖር"
👍2

ይገርማል ....

ተፈጥሮ ልኩ ሲያምርበት
                ውበት መአዛው ሲደራ
ሰው መሻቱን ሲያጣጥም
               ድፍርስ እሳቤው ሲጠራ

ያይላል ግርማው ላዩበት
              ይስባል መልከ ፍጥረቱ
የጭንቅ እሪያውን ወስዶ
               ንፁህ ልቦናን መስጠቱ

                   ተመስገን!

✍️Mekdi
@getmtg
@getmtg

"የምናውቀው የሚመስለን ነገር በጥያቄ ሲቀርብ፡ በምናውቀው ከመቆም ይልቅ ሃሳብ መቀየር ይቀናናል፡፡ ለምን?"

"አለማወቅ"

"ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሃኒቱ!"

ግን የኛ ችግር እኮ ብቻችንን ስንሆን ስናማርር፡ ከሰው ጋር ስንሆን ደግሞ ስናሽቃብጥ መገኘታችን ነው፡፡ ይሄ ለሁሉም ጊዜ አለው የሚለውን የሚገልፅ ይመስለኛል፡፡😊

Mekdi
@getmtg
👍1

          ቀለም ስንጨልፍ

አይደለም ለመድረክ
በሰው ለመባረክ
ለሙገሳ አጀባ
ለአንባቢ ጭብጨባ
ለንግድና ለትርፍ
ፈራንክ ለመልቀም
እንደዚህ አይደለም ...
ልባዊ ነው ግጥም
ዜማው የቅዱሳን ጥዑም የነፍስያ
ተቀብሮም ወርቅ ነው
ተነጥሮም ወርቅ ነው
ሳይደርስ ተገበያ

                    "የፀሓይ እግሮች"

@getmtg
👍1

የወደደን ወዶ መያዝ
የናቀን ሰው ትቶ ለቀቅ
ከእራስ አለም ሞቅ ደመቅ

ሰላም ይዞ ወጣ ገባ
መልካም ሆኖ ሽር ብትን
የጠላን ሰው ግፍ እስኪያንቀው
የክፋቱን እስኪለው ትን

Mekdi

@getmtg
👍2

"መኖር! - በአንድ ወገን የሚሆኑትን እየተመኙ፡ በሌላው ደግሞ የነበሩትን መሻት መሆኑ ይገርማል፡፡ በሚሆነውና በነበረው መካከል መወጠር! የነበረውንም ሆነ የሚሆነውን አለማወቅ!"

"አለማወቅ"
👍2

ሰው ከማግኘት ሰው ከማጣት
ጊዜ በልጦ ለገዘፈ
መምጫው መንገድ ወይ መሄጃው
ሳያሳስብ ከእውነቱ አለም
ሁነታትን ለቀዘፈ

የ'እመን' ይዘት የቃል ከምር
በመውዛት ውስጥ እንደሚረክስ
የ'ማንነት አለኝ' ተግባር
አይሆን አፉን እንደሚከስ

ግልፅ ነው!

Mekdi
@getmtg
👍3

"በጫካ ስታልፍ አንድ ትል ብትጨፈልቅ አይታወቅህም ፡ የትሉ ሚስት ግን አለም ይጨልምባታል፡፡"

"ትኩሳት"
@getmtg
👍3
(ከሰው ፎፁምነትን ለሚጠብቁ)

ከብዙ መልካም ጎን ገኖ
የነበር ቅንጣት ስህተት
እንደሚያስነሳ ወቀሳ
በሰው ፊት እንደሚያካስስ
ቅያሜን እንደሚፈጥር
መናናቅ እንደሚያመጣ
ማንነት እንደሚያረክስ

ግልፅ ነው!

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍2

"ብዙሀኑን የኔ ከምንለው ሰው ጋር በአንድ ሚዛን ልናስቀምጠው አይገባም፡፡ ለብዙሀኑ ብዙ ሆነው መገኘት በመፈለጋቸው አንዱንም ሳይዙት ምንም ሆነው እንዲቀሩ ያደረጋቸው ብዙ ናቸው፡፡"

"ዙቤይዳ"
👍2

ከመኖር ጋር ስንፋጠጥ
ላለመኖር ስናደላ
ክፉ ጊዜን ስንቆጥር
የውድቀት ቀን ስናሰላ

እድሜ ትቶን
ተስፋ ገፍቶን የሄደ 'ለት
እኛው ከእኛው ከጠፋብን
ምድር ሰማይ ሳር ቅጠሉ
ያኔ ነው የሚከፋብን

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍3

ያሻግራል ጊዜ
ያሳያል ቀን ደርሶ የእጅ እየቆጠረ
.... ዘመኑ ነው መሰል ....
ያወቀ ዝም ይላል
ያላወቀ ምላስ እየቀባጠረ

@getmtg
@getmtg
👍2

"ልቦናችንን ከእውነቱ ይልቅ እውነት ነው ብለን የያዝነው፡ ያመንነው ጉዳይ ይገዛዋል፡፡ የውሸት ኀይል ደግሞ እውነት መስሎት በተቀበለው አእምሮ ላይ ነው፡፡ ምድር በውሸታሞች የተሞላች ከመሆኗም ባሻገር ውሸትን በቀላሉ እውነት አድርገው የሚቀበሉ ሰዎችም ከዚያው አይተናነሱም፡፡ ስሜታችን የተጠመደበት ጉዳይ ሲሆን ደግሞ የበለጠ ለውሸት የተጋለጥን ያደርገናል፡፡ ይህም ምናልባት ስሜት ከምክንያትና ከማስረጃ ይልቅ በእምነትና በግንኙነት ላይ ስለሚደገፍ ይሆናል፡፡ ያመንነውና የተጠጋነው ሰው ደግሞ የስሜታችን ሹፌር መሆኑ አይቀርም፡፡"

"የተቆለፈበት ቁልፍ"
👍2

ይረሳ አይመስልም ነበር
ህመምም ሰውን ላኖረ
                  ምላሹ ሲሆን ዝቅታ
የልቡ እውነት ሊያቀናው
ዛሬን ግን በ'ይለፍ' ታስሮ
                ሲረታው በልጦ ዝምታ

ከኑረት ጋር አለሁኝ ባይ
ጠፊ መሆኑን ላመነ
              ተከብሮ አክባሪ ወዳጅ
እንዳለ ሁሉ የሰው ቅን
አይጠፋም ደግሞ ከአመሉ
                  እራሱን ነዶት አናዳጅ

ይሰምራል የቀን ናፍቆቱ
ብሶቱን ጠራርጎ እንዲሄድ
                 የእርካታ ወዙ ሲመጣ
ለሚያልፍ በጊዜ ሂደት
የማያልፍ ህመም የጫረ
                     ገፊ ነው የሚገረጣ

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍2

በተሰጠበት ፍርድ
እዬዬን ሲያነባ አይተው ዝም የሚሉት
ከማየት በስተቀር
ቅንጣት ፍቅር አጥተው ጭርሱን የጠሉት
     ........ ቅዩም ሰው እንዳሉ

ሺ ጊዜ የጣለን
ሺ ጊዜ አንስተው
         ቅንጣት ደስታን ሰጥተው
ምን ያህሉን ጥፋት
የቱን ያክል ቅጣት
በይቅርታ ሽረት ደጉን ቀን አምጥተው
          ....... የሚኖሩም አሉ

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍2
እንሳከር ሲለኝ ...

ሀገሩን ሲያቀጥን ቦለቲካ ኳሱን
ውሽማ ቅምጡን .. ቢራው አረቂውን
ሽምግልና ጠቡን ቁማሩን ካርታውን
ሲንከራተት ውሎ ተንከርታቹ ባሌ
  ..... ከቤቱ እንዳይገባ
በየጠላ ቤቱ ሲዞር እንቧለሌ
ያንን ... ጫማ አውልቄ
እግሩን አጣጥቤ
ፍትፍቱን ምናምን ተአፏ ላይ አድርጌ
ጉዴ እንዳይሰማ ተሰው ተሸሽጌ
ቡጢውንም ችየ ዱላውንም ችየ
ልኑር ታንተ ጋር ባልኩ
ኑሮውንም በቻልኩ
አሁን ምን ይል ጀመር
አብረን እንሳከር

         .... እከከከከ

ያው ተዛ በኋላ እኔም ተጣጥቤ
ቀሚሴን አጥልቄ ነጠላ ደርቤ
ተባሌ .... አብሬ
ጠጥቼ ሰክሬ
ኑሮን ጀምሪያለሁ
እንሳከር ታለኝ አበጀ ብያለሁ
......
ሰክረን ሲደግፈኝ
ሰክሮ  ስደግፈው
መደጋገፋችን
አሁን አሳመርነው
ትዳር እንደዚ ነው

    ..... እረ ተው እሜቴ
           ሽማግሌ ይፍሩ
           አብረው ከሰከሩ
           ይህም አይደል ነውሩ
           ሚሽት ጥበብ አላት
           ባሏ እንዲያዳምጣት
           ተአምላክ የተሰጣት
           እርሶ ጎበዝ ኖት
           መጠጣት ይተው
           ለማንም አልበጀ
           ጥሪት ሳንቲም ፈጀ

ደግ እሱ ተሰማ
መች እንቢ አልኩ እኔማ
         
           አንተስ ምን ትላለህ
           ሻለቃ መጠጣት ...

እኔ እንግዲህ ምለው
ይህን ሽምግልና
ውሳኔ እምንሰጠው
ጠላ ቢጤ ነገር
ስንቀማምስ ነው
            
           እውነት ብሏል እረ
           በሉ አምጡ እንግዲያውስ
           እሱኑ እየጠጣን
           ተግሳፅ እንሰጣለን
                     ....
ብለው ሽማግሌው
ተነሱው ተሳክረው
በሰው ታዝለው ሄዱ
መች ያልቅና ጉዱ
ከነ ሻለቃ ቤት
ከተግሳጹ በፊት ......
👍4

በመኖር ውስጥ መኖርን ማወቅ በራሱ ትልቅ ፀጋነት ነው፡፡ እየኖርን እንደሆነ ሳናውቅ ባለመኖር ውስጥ ተከልለን የምናማርር ብዙዎች ነን፡፡

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍2

ሲታይማ ይቀላል
በራስ ካልደረሰ ካልተኖረ ፍርዱ
ለመስማት አይከብድም
ህመም ካልተማሰ
                    ካልታለፈ እንክርዱ

እንደው በደፈና
ኖረውም ያላዩት የራስ ላይሆን ውሉ
ላይሆን ያፀደቁት
መሆን ያዘለን ልብ ላያደርገው ሙሉ

እንዲሁ በጭፍን
ሳያክሉ ሀቅን ሳያውቁበት መፍረድ
በቃላትም ሀይል
ላያድኑ ቁስልን
            ህመምን ስር ማስደድ

         ምን ይሉት ምላሽ ነው?

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍1