የግጥም ጥግ
770 subscribers
56 photos
2 videos
7 files
39 links
ያ ዶሮዬ ጮኈ መንጋቱን ነገረኝ፥
ሲነጋጋ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ።

የተለያዩ ምርጥ ግጥሞችን እዚህ

ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት

@Esamif
@amen1995 መጠየቅና መስጠት ይችላሉ።
Download Telegram
እግዜር ቅርብ ሳለ .......

እውነት ፍርዱ ሲታይ
ሀቅ እንቅጩን ሲመርጥ እያንዷን ሳይሰብር
ብርሀን ለወረደ
ቦታው ተብሎ ኖሯል የብርሀን ደብር

እግዜር ቅርብ ሳለ .......

ለትግል ቢያስፈራ
'ማይመች ቢመስል
ኮሳሳ አካል ሊጥል ግዙፉን ጎልያድ
ዳዊት አሳይቶናል
ደልዳላ ቁመናው
ምቹ እንደነበረ
በወንጭፍ ታልሞ በአንድ ጠጠር ሲናድ

እግዜር ቅርብ ሳለ ......

እንደ ጌትነቱ
የፃዲቅን ፍሬ በህዝቡ ሲዘራ ፍቅርን ሲያስተምር
ጭንቁን ሰው ከህመም
ድሃን ከችግሩ
ጨካኙን ከሀጥያት
በደልን ሲያነፃ ሲያድንና ሲምር

የአዳም የሞት እዳ
በእለተ አርብ ቀን ሲሻር በመስቀሉ
ሞቶ ያተረፈ
ሰላም ነው ትንሳኤው ጌታ በጥቅሉ

እግዜር ቅርብ ሳለ ......

ተፈጥሮ ውበቱ
ሰው ቀለቡ ፍቅር መሬት ምርቷ ፍሬ
የዘበት አይደለም
ድል መሆን ታውቆት ነው የጀግና ፉካሬ

ዘምቶ ቢደክም እንኳ
ከግንባሩ ታቹን ላቡ እንደጉድ ቸፎ
ጨውነቱን ቢያቁር
ፀሀይና ግለት
ዝናብና ብርዱ
ወዙን አሟጦበት ቢከሳ ቢጠቁር

በረገጣት መሬት
ክብር እንዲቀለም ንድፍ ሀሳብ ለሳለ
..... እግዜር ቅርብ ሳለ .....

ቢዳፋ ቢያቀና
ፍርዱ እስኪለይለት እስኪጠራ መልኩ
አረ እናንተሆዬ
ሀገር አይደለም ወይ ሰው የመሆን ልኩ

Mekdi
👍3

"ዕድሜ በየትኛውም ደረጃ መጥፎ አይደለም፡፡ እንደ ዕድሜ ካለመሆን በላይ በሽታ ግን ምን አለ፡፡"

"ዙቤይዳ"
👍6

"ህይወት ረቂቅ ሚስጢር ናት፡ አምላክ በጥበቡ በዚህ አለም ላይ ይህችን ሚስጥራዊት ሕይወት እድሜ በሚባል አነስተኛ የጊዜ ከረጢት ዐደለን፡፡ ይህቺም ከረጢት በውስጧ እድል በተሰኙ ፈርጦች ተሞልታለች፡፡ ከረጢቷን እንዳትሰረቅና ያለጊዜዋ አርጅታ ከጥቅም ውጪ እንዳትሆን፡ ኀላፊነቱን ፈጣሪ ለኛው ነው የሰጠን፡፡ በከረጢቷ ውስጥ ያሉትም ፈርጦች አንድ በአንድ፡ አንዳንዴም ከአንድ በላይ ባንዴ እያብለጨለጩ ከባለከረጢቱ እጅ ላይ ይወድቃሉ፡፡ ከጊዜ ጋር የተቆራኙ ናቸውና በጊዜው ያልተጠቀምንባቸው የእድል ፈርጦች ከጊዜ ጋር ላይመለሱ ትዝታቸውን አስታቅፈውን ይነጉዳሉ፡፡"

"የተቆለፈበት ቁልፍ"
👍2

ለመረሳት ተብሎ ኑረት
ለመታወቅ ሲሉ ውድቀት
'ልታይ ልታይ' መባከን ነው
የልብ ስር አጉል ሙቀት

ልኩራ ካሉስ በዝምታ
ልኑር ካሉ ከቅን ልብ ውስጥ
ከወደዱት ዘልቀው ገብተው
ነፃነትን ከእውነት ደጃፍ
ያለ እራስን ላለማጣት
መኖር ካሉስ ሁሉን ትተው
በቃ .........

✍️Mekdi
👍2

"ማፍቀር እንጂ መፈቀር መለኪያ የለውም፡፡ መፈቀር እምነት ነው፡፡ ማፍቀር ደግሞ እውነት፡፡ ....... ፍቅር ብፁዕነትም ነው፡፡ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው እነዲል መጽሐፍ፡፡"

                             "አለመኖር"
👍2

ይገርማል ....

ተፈጥሮ ልኩ ሲያምርበት
                ውበት መአዛው ሲደራ
ሰው መሻቱን ሲያጣጥም
               ድፍርስ እሳቤው ሲጠራ

ያይላል ግርማው ላዩበት
              ይስባል መልከ ፍጥረቱ
የጭንቅ እሪያውን ወስዶ
               ንፁህ ልቦናን መስጠቱ

                   ተመስገን!

✍️Mekdi
@getmtg
@getmtg

"የምናውቀው የሚመስለን ነገር በጥያቄ ሲቀርብ፡ በምናውቀው ከመቆም ይልቅ ሃሳብ መቀየር ይቀናናል፡፡ ለምን?"

"አለማወቅ"

"ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሃኒቱ!"

ግን የኛ ችግር እኮ ብቻችንን ስንሆን ስናማርር፡ ከሰው ጋር ስንሆን ደግሞ ስናሽቃብጥ መገኘታችን ነው፡፡ ይሄ ለሁሉም ጊዜ አለው የሚለውን የሚገልፅ ይመስለኛል፡፡😊

Mekdi
@getmtg
👍1

          ቀለም ስንጨልፍ

አይደለም ለመድረክ
በሰው ለመባረክ
ለሙገሳ አጀባ
ለአንባቢ ጭብጨባ
ለንግድና ለትርፍ
ፈራንክ ለመልቀም
እንደዚህ አይደለም ...
ልባዊ ነው ግጥም
ዜማው የቅዱሳን ጥዑም የነፍስያ
ተቀብሮም ወርቅ ነው
ተነጥሮም ወርቅ ነው
ሳይደርስ ተገበያ

                    "የፀሓይ እግሮች"

@getmtg
👍1

የወደደን ወዶ መያዝ
የናቀን ሰው ትቶ ለቀቅ
ከእራስ አለም ሞቅ ደመቅ

ሰላም ይዞ ወጣ ገባ
መልካም ሆኖ ሽር ብትን
የጠላን ሰው ግፍ እስኪያንቀው
የክፋቱን እስኪለው ትን

Mekdi

@getmtg
👍2

"መኖር! - በአንድ ወገን የሚሆኑትን እየተመኙ፡ በሌላው ደግሞ የነበሩትን መሻት መሆኑ ይገርማል፡፡ በሚሆነውና በነበረው መካከል መወጠር! የነበረውንም ሆነ የሚሆነውን አለማወቅ!"

"አለማወቅ"
👍2

ሰው ከማግኘት ሰው ከማጣት
ጊዜ በልጦ ለገዘፈ
መምጫው መንገድ ወይ መሄጃው
ሳያሳስብ ከእውነቱ አለም
ሁነታትን ለቀዘፈ

የ'እመን' ይዘት የቃል ከምር
በመውዛት ውስጥ እንደሚረክስ
የ'ማንነት አለኝ' ተግባር
አይሆን አፉን እንደሚከስ

ግልፅ ነው!

Mekdi
@getmtg
👍3

"በጫካ ስታልፍ አንድ ትል ብትጨፈልቅ አይታወቅህም ፡ የትሉ ሚስት ግን አለም ይጨልምባታል፡፡"

"ትኩሳት"
@getmtg
👍3
(ከሰው ፎፁምነትን ለሚጠብቁ)

ከብዙ መልካም ጎን ገኖ
የነበር ቅንጣት ስህተት
እንደሚያስነሳ ወቀሳ
በሰው ፊት እንደሚያካስስ
ቅያሜን እንደሚፈጥር
መናናቅ እንደሚያመጣ
ማንነት እንደሚያረክስ

ግልፅ ነው!

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍2

"ብዙሀኑን የኔ ከምንለው ሰው ጋር በአንድ ሚዛን ልናስቀምጠው አይገባም፡፡ ለብዙሀኑ ብዙ ሆነው መገኘት በመፈለጋቸው አንዱንም ሳይዙት ምንም ሆነው እንዲቀሩ ያደረጋቸው ብዙ ናቸው፡፡"

"ዙቤይዳ"
👍2

ከመኖር ጋር ስንፋጠጥ
ላለመኖር ስናደላ
ክፉ ጊዜን ስንቆጥር
የውድቀት ቀን ስናሰላ

እድሜ ትቶን
ተስፋ ገፍቶን የሄደ 'ለት
እኛው ከእኛው ከጠፋብን
ምድር ሰማይ ሳር ቅጠሉ
ያኔ ነው የሚከፋብን

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍3

ያሻግራል ጊዜ
ያሳያል ቀን ደርሶ የእጅ እየቆጠረ
.... ዘመኑ ነው መሰል ....
ያወቀ ዝም ይላል
ያላወቀ ምላስ እየቀባጠረ

@getmtg
@getmtg
👍2

"ልቦናችንን ከእውነቱ ይልቅ እውነት ነው ብለን የያዝነው፡ ያመንነው ጉዳይ ይገዛዋል፡፡ የውሸት ኀይል ደግሞ እውነት መስሎት በተቀበለው አእምሮ ላይ ነው፡፡ ምድር በውሸታሞች የተሞላች ከመሆኗም ባሻገር ውሸትን በቀላሉ እውነት አድርገው የሚቀበሉ ሰዎችም ከዚያው አይተናነሱም፡፡ ስሜታችን የተጠመደበት ጉዳይ ሲሆን ደግሞ የበለጠ ለውሸት የተጋለጥን ያደርገናል፡፡ ይህም ምናልባት ስሜት ከምክንያትና ከማስረጃ ይልቅ በእምነትና በግንኙነት ላይ ስለሚደገፍ ይሆናል፡፡ ያመንነውና የተጠጋነው ሰው ደግሞ የስሜታችን ሹፌር መሆኑ አይቀርም፡፡"

"የተቆለፈበት ቁልፍ"
👍2

ይረሳ አይመስልም ነበር
ህመምም ሰውን ላኖረ
                  ምላሹ ሲሆን ዝቅታ
የልቡ እውነት ሊያቀናው
ዛሬን ግን በ'ይለፍ' ታስሮ
                ሲረታው በልጦ ዝምታ

ከኑረት ጋር አለሁኝ ባይ
ጠፊ መሆኑን ላመነ
              ተከብሮ አክባሪ ወዳጅ
እንዳለ ሁሉ የሰው ቅን
አይጠፋም ደግሞ ከአመሉ
                  እራሱን ነዶት አናዳጅ

ይሰምራል የቀን ናፍቆቱ
ብሶቱን ጠራርጎ እንዲሄድ
                 የእርካታ ወዙ ሲመጣ
ለሚያልፍ በጊዜ ሂደት
የማያልፍ ህመም የጫረ
                     ገፊ ነው የሚገረጣ

Mekdi

@getmtg
@getmtg
👍2