የግጥም ጥግ
769 subscribers
56 photos
2 videos
7 files
39 links
ያ ዶሮዬ ጮኈ መንጋቱን ነገረኝ፥
ሲነጋጋ ላርደው ቀጠሮ ነበረኝ።

የተለያዩ ምርጥ ግጥሞችን እዚህ

ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት

@Esamif
@amen1995 መጠየቅና መስጠት ይችላሉ።
Download Telegram
ቡቡዬ☺️ ብታምኚም ባታምኚም፣
ያላንቺ እኔ አይሆንልኝም!

አብዱ ኪያር

@getmtg
👍2
👍2
አላስቀየምኳትም ፍቅሬን ምን አስቆጣት፣
እወዳታለሁኝ ምንም አልበደልኳት።
ጥላኝ ከምጠፋ እኔን ብቸኛ አርጋኝ፣
ምን አለ ጥፋቴን ገልፃ ብታስረዳኝ፣

እሷን ትቼ ሌላ ፍፁም አልወደድኩም፣
ያለኝን ስሜቴን ልቤን አልደበኩም።
ምንድነው በደሌ ብግልፅ ይነገረኝ፣
ባልሰራሁት ጥፋት ቆርጣ ከምተወኝ።

አጥፍቼም እንደሆን ልካስ ልቀጣልሽ፣
ልገረፍ በጅራፍ ጀርባዬ ይንደድልሽ።
ልብሽ አይቸገር በሰርገኛ ወሬ፣
እኔ አልጠላሁሽም ተመለሽ ተይ ፍቅሬ።

አላስቀየምኳትም
ታደለ በቀለ


@getmtg
👍8
አትስጡኝ ምርጫ እኔ አለኝ መንገድ፡
አንዱን አልጠላም አንዱን ለመውደድ።
ያለኔ መንገድ አትሂድ ላለ፡
እየወደዱ መለየት አለ።!!!!
👏5
😁3👍1

"ሕይወት እንደ ሰዓት ናት፡፡ በሙላትና በጉድለት መሐል ይዛ የምትነጉድ፡፡ ሁልጊዜ ትቆጥራለች፡፡ ሩብ ጉዳይ፡ አስር ጉዳይ፡ አምስት ጉዳይ - ትሞላለች ፡ ከአምስት፡ ከአስር፡ ከሩብ - ትተርፋለች፡፡"

"ዶክተር አሸብር"
👍4
እግዜር ቅርብ ሳለ .......

እውነት ፍርዱ ሲታይ
ሀቅ እንቅጩን ሲመርጥ እያንዷን ሳይሰብር
ብርሀን ለወረደ
ቦታው ተብሎ ኖሯል የብርሀን ደብር

እግዜር ቅርብ ሳለ .......

ለትግል ቢያስፈራ
'ማይመች ቢመስል
ኮሳሳ አካል ሊጥል ግዙፉን ጎልያድ
ዳዊት አሳይቶናል
ደልዳላ ቁመናው
ምቹ እንደነበረ
በወንጭፍ ታልሞ በአንድ ጠጠር ሲናድ

እግዜር ቅርብ ሳለ ......

እንደ ጌትነቱ
የፃዲቅን ፍሬ በህዝቡ ሲዘራ ፍቅርን ሲያስተምር
ጭንቁን ሰው ከህመም
ድሃን ከችግሩ
ጨካኙን ከሀጥያት
በደልን ሲያነፃ ሲያድንና ሲምር

የአዳም የሞት እዳ
በእለተ አርብ ቀን ሲሻር በመስቀሉ
ሞቶ ያተረፈ
ሰላም ነው ትንሳኤው ጌታ በጥቅሉ

እግዜር ቅርብ ሳለ ......

ተፈጥሮ ውበቱ
ሰው ቀለቡ ፍቅር መሬት ምርቷ ፍሬ
የዘበት አይደለም
ድል መሆን ታውቆት ነው የጀግና ፉካሬ

ዘምቶ ቢደክም እንኳ
ከግንባሩ ታቹን ላቡ እንደጉድ ቸፎ
ጨውነቱን ቢያቁር
ፀሀይና ግለት
ዝናብና ብርዱ
ወዙን አሟጦበት ቢከሳ ቢጠቁር

በረገጣት መሬት
ክብር እንዲቀለም ንድፍ ሀሳብ ለሳለ
..... እግዜር ቅርብ ሳለ .....

ቢዳፋ ቢያቀና
ፍርዱ እስኪለይለት እስኪጠራ መልኩ
አረ እናንተሆዬ
ሀገር አይደለም ወይ ሰው የመሆን ልኩ

Mekdi
👍3

"ዕድሜ በየትኛውም ደረጃ መጥፎ አይደለም፡፡ እንደ ዕድሜ ካለመሆን በላይ በሽታ ግን ምን አለ፡፡"

"ዙቤይዳ"
👍6

"ህይወት ረቂቅ ሚስጢር ናት፡ አምላክ በጥበቡ በዚህ አለም ላይ ይህችን ሚስጥራዊት ሕይወት እድሜ በሚባል አነስተኛ የጊዜ ከረጢት ዐደለን፡፡ ይህቺም ከረጢት በውስጧ እድል በተሰኙ ፈርጦች ተሞልታለች፡፡ ከረጢቷን እንዳትሰረቅና ያለጊዜዋ አርጅታ ከጥቅም ውጪ እንዳትሆን፡ ኀላፊነቱን ፈጣሪ ለኛው ነው የሰጠን፡፡ በከረጢቷ ውስጥ ያሉትም ፈርጦች አንድ በአንድ፡ አንዳንዴም ከአንድ በላይ ባንዴ እያብለጨለጩ ከባለከረጢቱ እጅ ላይ ይወድቃሉ፡፡ ከጊዜ ጋር የተቆራኙ ናቸውና በጊዜው ያልተጠቀምንባቸው የእድል ፈርጦች ከጊዜ ጋር ላይመለሱ ትዝታቸውን አስታቅፈውን ይነጉዳሉ፡፡"

"የተቆለፈበት ቁልፍ"
👍2

ለመረሳት ተብሎ ኑረት
ለመታወቅ ሲሉ ውድቀት
'ልታይ ልታይ' መባከን ነው
የልብ ስር አጉል ሙቀት

ልኩራ ካሉስ በዝምታ
ልኑር ካሉ ከቅን ልብ ውስጥ
ከወደዱት ዘልቀው ገብተው
ነፃነትን ከእውነት ደጃፍ
ያለ እራስን ላለማጣት
መኖር ካሉስ ሁሉን ትተው
በቃ .........

✍️Mekdi
👍2

"ማፍቀር እንጂ መፈቀር መለኪያ የለውም፡፡ መፈቀር እምነት ነው፡፡ ማፍቀር ደግሞ እውነት፡፡ ....... ፍቅር ብፁዕነትም ነው፡፡ ሳያዩ የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው እነዲል መጽሐፍ፡፡"

                             "አለመኖር"
👍2

ይገርማል ....

ተፈጥሮ ልኩ ሲያምርበት
                ውበት መአዛው ሲደራ
ሰው መሻቱን ሲያጣጥም
               ድፍርስ እሳቤው ሲጠራ

ያይላል ግርማው ላዩበት
              ይስባል መልከ ፍጥረቱ
የጭንቅ እሪያውን ወስዶ
               ንፁህ ልቦናን መስጠቱ

                   ተመስገን!

✍️Mekdi
@getmtg
@getmtg

"የምናውቀው የሚመስለን ነገር በጥያቄ ሲቀርብ፡ በምናውቀው ከመቆም ይልቅ ሃሳብ መቀየር ይቀናናል፡፡ ለምን?"

"አለማወቅ"

"ከአንድ ብርቱ ሁለት መድሃኒቱ!"

ግን የኛ ችግር እኮ ብቻችንን ስንሆን ስናማርር፡ ከሰው ጋር ስንሆን ደግሞ ስናሽቃብጥ መገኘታችን ነው፡፡ ይሄ ለሁሉም ጊዜ አለው የሚለውን የሚገልፅ ይመስለኛል፡፡😊

Mekdi
@getmtg
👍1

          ቀለም ስንጨልፍ

አይደለም ለመድረክ
በሰው ለመባረክ
ለሙገሳ አጀባ
ለአንባቢ ጭብጨባ
ለንግድና ለትርፍ
ፈራንክ ለመልቀም
እንደዚህ አይደለም ...
ልባዊ ነው ግጥም
ዜማው የቅዱሳን ጥዑም የነፍስያ
ተቀብሮም ወርቅ ነው
ተነጥሮም ወርቅ ነው
ሳይደርስ ተገበያ

                    "የፀሓይ እግሮች"

@getmtg
👍1

የወደደን ወዶ መያዝ
የናቀን ሰው ትቶ ለቀቅ
ከእራስ አለም ሞቅ ደመቅ

ሰላም ይዞ ወጣ ገባ
መልካም ሆኖ ሽር ብትን
የጠላን ሰው ግፍ እስኪያንቀው
የክፋቱን እስኪለው ትን

Mekdi

@getmtg
👍2

"መኖር! - በአንድ ወገን የሚሆኑትን እየተመኙ፡ በሌላው ደግሞ የነበሩትን መሻት መሆኑ ይገርማል፡፡ በሚሆነውና በነበረው መካከል መወጠር! የነበረውንም ሆነ የሚሆነውን አለማወቅ!"

"አለማወቅ"
👍2

ሰው ከማግኘት ሰው ከማጣት
ጊዜ በልጦ ለገዘፈ
መምጫው መንገድ ወይ መሄጃው
ሳያሳስብ ከእውነቱ አለም
ሁነታትን ለቀዘፈ

የ'እመን' ይዘት የቃል ከምር
በመውዛት ውስጥ እንደሚረክስ
የ'ማንነት አለኝ' ተግባር
አይሆን አፉን እንደሚከስ

ግልፅ ነው!

Mekdi
@getmtg
👍3

"በጫካ ስታልፍ አንድ ትል ብትጨፈልቅ አይታወቅህም ፡ የትሉ ሚስት ግን አለም ይጨልምባታል፡፡"

"ትኩሳት"
@getmtg
👍3