ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
((በርናባስ ከበደ))

"ዘመዴ ነህ አሉ ...
በአያት በምንጅላት ፡ ሥሩ እጅግ ቢርቅም
ማን ብዬ ላንባልህ?...
ዝንጀሮዎች እንደሁ ፡ ዘር መቁጠር አናውቅም!!"

@getem
@getem
@getem
#እስኪ.....
(ቤዛዊት ከበደ)

ይስቃሉ በሀሣቤ
ይስቃሉ በጉልበቴ
ይስቃሉ በጥረቴ
.
.
ይበላሉ ከማጀቴ
ይጠጣሉ ከማጀቴ
ከእጄ ፍሬ ከደም ላቤ
ይቆርሣሉ ከስኬቴ
.
.
ያደንቃሉ ያን ሀሣቤን
ያደንቃሉ ያን ጉልበቴን
ያደንቃሉ ሙሉ ቤቴን
.
.
እንዲህ እንደዚ እያሉ
ይኖራሉ ከቤቴ ጎን አጥር ጋርደው
ወይ ለወሬ
ወይ ለስርቆት
ወይ ለፅድቅ እንዲመቻቸው::
.
.
እኔም አለሁ
እስኪፀዳ ማድጋዬ
እስኪከዳኝ ቀኝ ጉልበቴ
እስኪጎድል ሙሉ ቀኔ
.
.
ይሀው አለሁ
..
እኔም አለሁ
.
.
ምርቃቴን ይዤ
እርግማኔን ትቼ!!

@getem
@getem
@getem
ለኢትዮጵያ!!!
(በላይ በቀለ ወያ)
,
,
ይብላኝለት እንጂ...
በዘር ተከፋፍሎ ፣ ለሚታመስ ቤቷ
ይብላኝለት እንጂ...
ተሸርፎ ተሸርፎ ፣ ላለቀ መሬቷ
ይብላኝለት እንጂ...
ደረቷን ስትደቃ ፣ ለወረደው ጡቷ
ይብላኝለት እንጂ...
ባዘን ፀጉሯን ስትነጭ ፣ ለገጠበ አናቷ
ይብላኝለት እንጂ..
ቁንጅናውን ላጣ ፣ ማድያታም ፊቷ...
፡፡፡፡፡፡፡
ከዚ ሁሉ ኋላም
የዘመን ጥላሸት ፣ መልኳን ተለቅልቃ
ቁንጅናዋ ርቋት ፣ ፉንጋነትን ታጥቃ
ልንጠላት አንችልም ፣ ውብ ሀገር ነች በቃ!!!

@getem
@getem
@getem
ዝክረ _ኸሚስ
ልጅት ሳይሞቅ ፈላ
************
ባለ ሁለት ጆሮ ……ገንቦየን አንግቼ
በዋርማ በፎሌ…… ከሚንጩ ቀድቼ
ዳለች እና ቦራን ……ከወንዙ አጠጥቼ
ከጅረቱ አጠገብ… ካለችው አከያ እንጠላጠላለሁ
ከለምለሙ ዛፍ ላይ …… እመለምላለሁ
ለቤታችን ጉዝጓዝ ……ቅጠል እቆርጣለሁ።
ከዛፉ ላይ ሁኘ ዝቅዝቅ ስመለከት የበለጠ አያለሁ
በእየ ቀንዘሉ ላይ ጢብ ጢብ ብየ እታች እዳፋለሁ
ከጅረቱ በታች ወዳለችው ገደል እጄን እሰዳለሁ
ቄጠማ ጠጄ ሳር …… አደሱን አጭዳለሁ።

ለማለሙን ሁሉ ……ባንድነት ሸክፌ
ገንቦየን አዝየ ……ጉዝጓዜን ታቅፌ
ዳለች እና ቦራን…… ከፊት እየነዳሁ
ለአንድየ ምነግረው …… ዱአ እያሰናዳሁ
ስሄድ ስገሰግስ
ከቀየየ ስደርስ
አባባ እና አየዋ …… ጃኖ ተሸፋፍነው
ማዶ ማዶ እያዩ ……ከቀልባቸው ሁነው
አውዱማው አጠገብ …… ወግ እያወጉ ነው
እንዴት ነሁ አይወይ…… አማን ነው መንደሩ?
ሸጋ ነወይ አጥቢያው ……እንዴት ውሏል ዱሩ?
ብየ እጅ ነሳሁኝ………እንዳባት አደሩ
አየዋም ጭራዎን ……ከግራ ወደቀኝ እየነሰነሱ
«አማን ሁኚ!» ብለው ……ነገያ መለሱ።

እኔም እየጠደፍኩ…… ወደ ቤቴ አቅንቼ
ገንቦና ዋርማየን …… ኸማጄት ከትቼ
እቅፍ ሙሉ ለምለም…… ለእማማ ሰጥቼ፤
እናት አለም ሆዴ …
ያወዱድ ያወዱድ …… ያወዱድ እያለች
የቀልብ የሙራዷን …… እያንጎራጎረች
ከመደብ እስከ ዘብጥ…… ትጎዘጉዛለች
እታለም ከምድጃው…… ወይራ ታጬሳለች።

ሰማይ ሲጨላልም…… አዱኒያን በበረት
ፍየሎቹን በጋጥ …… ደጃፉን በብረት
ሸክፎ ቢገባ …… አባታለም ክንዴ
የቤታችን ድባብ ……መለወጡ ባንዴ፤
ግር አለው ሁናቴው ……ገረመው በጠና
ቀኑ ሀሙስ መሆኑን …… ዘንግቶታልና፤

ከቀጠላው አናት…… እየተሰየመ
በወይራ በአድሩሱ ……እየተደመመ
ከጭሱ ጋር ስበን ……ቃል ሳይናገረኝ
ቀልብ የሚገዛውን……ፈገግታዉን ቸረኝ ።
ፈዋሽ ልዝብ እጆቹን……ሰዶ ወደ አናቴ
«ጎሽሽ!» ሲል አባባ …… «አበጀሽ እናቴ!»
ከነበረው በእጥፍእመረቅናለሁ …ይብሳል ፍጥነቴ
አይ ነብስ አለማወቅ…… አወይ ልጅነቴ!

በፋኖስ ታጅቦ … እንጀራው በሞሰብ ወጡ በሰታቴ
ከቀረበ ወድያ…… ብሉ እየተባለ ጠጡልኝ በሞቴ
በሳቅ በፍስሀ …… እንደተጎራረስን ይነሳል ገበታ
እምድጃውን ከበን…ቡና እየተቆላ ይደራል ጫወታ
እኔ ሀድራ ወዳጅ…
ልጅት ሳይሞቅ ፈላ…
ማጨዱ ሳይበቃኝ ……ቀጤማ እና አሪቲ
አደስና ከሴ ……ጠጀሳር አሽኩቲ
መጎዝጎዝ ሳያንሰኝ…… ጓሳ እና ሉባንጃ
ኸሚስ አመሻሹን ያቅበጠብጠኛል የነካኝን እንጃ

ጥፍጥሬ ማህል ልጅ ……ምርቃት ለምጄ
«አወል ጀባ!» እላለሁ …… ጀበና ጨምድጄ
የቤታችን አውራ የምኞትሽ ይሁን ብሎ ቢመርቀኝ
«በአሚን»ተቀብየው…… ቀይ ባህር ዘፈቀኝ
ይሄው በዛን ዘመን ……ምኞት አጣምሜ
በስደት አለቀ …… ተጋመሰ አለሜ !
ምፅ!ምፅፅ!


ውዶቼ
የምኞታችሁ አይሁን ይልቅስ የሚበጃችሁ ይሁን!
አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ሰይድና ወሀቢበና ሙሀመድ ወአላ አሊሂ ወአስሀቢሂ አጅመኢን!!

ሸጋ ኸሚስ ሸጎቼ!


@getem
@getem
@balmbaras
👍2
ከላይ!!!!!


የታች ሰፈር ልጆች ፤
የታች ቤት ግርደኞች፤
ደግሞ ይኸን ሰሞን፤
በጭራቅ ፉከራ፤
እየወዘወዙን ፤

\

\

\

እየሳቡን ፤ ይዘዋል ጉተታ፤
አላወቁም መሰል፤
ከ"ላይኛው" ሆነው፤ አገር እንዳፀኑ ሃጅና መርጌታ።
መገን የላይኛው!!"

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋ ሸጊቱ ጁምኣ!💚

@getem
@getem
@balmbaras
👍1
( አቢ ጌቱ )
.
ከነመፈጠሬ
እርሳኝ ብለሽኝ
ለትውስታ እሚሆን ፥ ትዝታ ነፍገሽኝ
ደግሜ አፈቀርኩሽ ፥ ሌላ ሴት መስለሽኝ።

@getem
@getem
@getem
ብትቀሪ ጊዜ
(ቡሩክ ኮርሳዊ ዘ ቀለሟ)


የቆሙቱ ነቁ
ጅምሮች አለቁ
ብርድ ሆነ ወበቁ
:
መጉደልሽን አይቶ መሙላቴ ኮሰሰ
ንቃቴ ቦዝዞ ድባቴን ለበሰ
:
ብትመጪስ ጊዜ?
በነገ መያዜ
በማጣት መፍዘዜ
በናፍቆት መንፈዜ
:
አ ል ጥ ም አለሽና
ነጎድሽ እንዳገና
ወደ ሩብ ዘላለም
ያኔ ዛሬ አይደለም::


@getem
@getem
@getem
👍1
አደይ ሚክስድ አርት !

ዩቶጵያ ቪዥዋል አርትስ ክለብ ከ አዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር በወጣት የስነ-ጥበብ ባለሙያዎች የተከሸነ የድብልቅ ጥበባት (Mixed art) ኤግዝቢሽን ከመስከረም 14-20 ደረስ በአዲስ አበባ ሙዚየም ለእይታ ይበቃል ፡፡ የጥበብ ድግሳችን ተካፋይ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል !

መክፈቻ ሰዓት ፡- 11:30

ለበለጠ መረጃ

0984871096
0942600644
0973950532

@Utopiavisualarts
@utopiavisualarts
( አለሙ አዳፋ)
አክባሪ ተንቆ - ተከባሪ ልቆ
አዳማጭ ተረስቶ - ተናጋሪ ደምቆ
ከማወቅ - መታወቅ
ከማየት - መታየት...
ከመውደድ - መወደድ
ከመስማት - መሰማት...
ከሚመኝ ኗሪ ጋር
በምጓዘው መንገድ - በማልፋቸው ቀናት
ካንቺ ውጭ ለሌላ
ልቤ ቀጣፊ ነች - ነፍሴም ዱርየ ናት፡፡
.
አድባሬ ...
ሀገሬ❤️
@getem
@getem
@kaleab_1888
የሀበሻ ቅጥፈት
በሚካኤል አስጨናቂ


@getem
@getem
@getem
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

መውደድ በዝምታ
_____________

የኔ ልብ እንዲሁ ነው...

ዝምታ ያነቀው
ተጓዥ መስሎ ፈሪ፣
ለፍቅር ሸፍቶ፣
ተመልሶ ደግሞ፣
ፍቅርን አባራሪ።

ያንቺን ብርቅዬ ልብ፣
አጠምዳለሁ ብሎ፣
አሰሳ ፍለጋ
ሲንከራተት ውሎ፣
ኢምንት ስትቀረው፣
ፍርሀት የሚያጠምደው
ቆርጦ ይነሳና፣
አለሁኝ ይልና፣
የዝምታ ነፋስ፣
መልሶ የሚሰደው።

አይኖቼም ያው ናቸው....

አንቺ የሌለሽ ጊዜ፣
አንቺን ያልማሉ፣
ፀጥ ባለው ሌሊት
ከዕንቅልፍ ይሸሻሉ።
ካይኖችሽ ተዋደው፣
በፍቅር እሳት ነደው፣
ልተኛ ስላቸው፣
እምቢ ነው መልሳቸው።

ወዲያ ወዲህ እያሉ፣
በድቅድቅ ጨለማ፣
ያንከራትቱኛል፣
ጥርት አርገው ስለው፣
ከነ መላው አካልሽ፣
አንቺን ያሳዩኛል።

ድንገት ስትመጪ ግን...
ውልብልብ አይኖቼ፣
እንዳልተርክልሽ፣
የልቤን አውጥቼ፣
አይንሽን እንዳላይ፣
ፍርሀቴን እንዳልተው፣
ይከለክሉኛል፣
አትያት ይሉኛል፣
ገላጣው መሬት ላይ፣
ቁልቁል ተሰክተው።

አንደበቴም ያው ነው....

ሲያገኝሽ ይዘጋል፣
ሲያጣሽ ይከፈታል፣
ቀን ቀን ዝም ይልና፣
ሌሊት ይበረታል።

ማንም በሌለበት
ያለ አንዳች ፍራቻ፣
እልፍ አእላፍ ቃላት፣
እየደረደርኩኝ፣
አንቺን ማሰብ ብቻ።

ድንገት ሳገኝሽግን...
ከንፈሬ ታትሞ፣
ምላሴ ይታሰራል፣
ድንጉጥ አንደበቴ፣
"ምን ልበል" እያለ፣
በቃላቶች መሐል፣
ተለጉሞ ይቀራል።

እጆቼም ያው ናቸው....

አንቺን ያዩ ጊዜ፣
ከሁዋላዬ ዞረው፣
ይቆላለፋሉ፣
ቀጭኑ ወገቤን፣
ምሽግ ያደርጋሉ፣
ለስላሳ ጉንጭሽን፣
ሊዳብሱ ብለው፣
ፈርተው ይመለሳሉ።

ደግሞ አንቺ ሳትኖሪ...

ድንግርግር እጆቼ፣
"ብዕር አምጣ" ይሉኛል
ስንኝ አሰባስበው፣
ለሚያሰቃይ ፍቅርሽ፣
ግጥም ያፅፉኛል።

የኔ ፍቅር እንዲህ ነው...
ብቻዬን በመሆን፣
ያለአንዳች ፍራቻ፣
እልፍ አእላፍ ቃላት፣
እየደረደርኩኝ፣
አንቺን ማሰብ ብቻ።

በቃ እንዲህ ልውደድሽ....

ከጥርሶችሽ ጋራ፣
የሚስቅ ፊትሽን፣
በማያዩ አይኖቼ፣
አካልሽን መንካት፣
በሚፈሩ እጆቼ፣
በህልፍ አክናፍ ብቻ፣
በሩቁ እያሰብኩሽ፣
ሳልቀርብሽ ሸሽቼ።

ግን አንድ ተስፋ አለኝ....

በጨለማው አለም፣
አጥርተው የሚያዩሽን፣
አይኖቼን ከፍቼ ፣
ታትመው የቆዩትን፣
ፈሪ ከንፈሮቼን፣
ለቃላት ፈትቼ፣
ልብሽን መማረክ፣
የተሳነው ልቤን፣
በግድ አበርትቼ፣
እንቀፋት ብለው፣
ይንደረደሩና፣
ደረስን ይሉና፣
ፈርተው የሚደበቁ፣
ተሸናፊ እጆቼን፣
እንደ አሞራ ክንፍ፣
በሰፊው ዘርግቼ፣
በህይወት እስካለሽ ፣
በህይወት እስካለሁ፣
ግድ የለም ጠብቂኝ ፣
የሚርቅ ቢመስልም፣
አንድ ቀን መጣለሁ።

( ጠብቂኝ)

ዮሐንስ ገርማሜ

@getem
@getem
@getem
👍2
እረክተን ሳንጠጣ ፥ አለቀ ተደፍቶ
በቅጡ ሳይፈላ ፥ ሚገነፍል በዝቶ
.
« ሚኪ እንዳለ»

@getem
@getem
@getem
ቅድሚያ ለሀገሬ
_____

ጥሩ ሰራህ ብለው.... ወርቅን
ቢሸልሙኝ፣
የስኬት ዘውድ ብለው...አክሊል
ቢደፉልኝ፣
ምኑ ሊያስደስተኝ...
........ ..........
እናት ኢትዮጵያዬን
መሰረት ዋልታዬን...
ከወዟ ሊቀማት፣
ከርስቷ ሊሻማት፣
በስውር የመጣ፣
ካየሁኝ ምቀኛ፣
እንኳን አንድ ሌሊት
ደቂቃም አልተኛ!!!
…………… …………………

ዮሐንስ ገርማሜ

@getem
@getem
@getem
ወንዘኛ!!!!!!!


በቆሙበት መሬት ፤
የተደበቀውን፤
ያንን የውሃ ጋን፤
ቆፈር ቆፈር አርገው ፤
የእርሻውን ማጠጫ በውሃ እንዳይሞሉ፤
የኛ አገር ጥመኞች፤
ወደ ገዛ እርሻቸው፤
ውሃ እንፈልግ ብለው ፤ ጠልቀው ሳይቆፍሩ፤
በአጀብ በሆሆታ፤
ወንዝ እናምጣ ብለው ፤
የገዛ እርሻቸውን፤ ጥለው ኮበለሉ፤
ውሃ ባልጠፋበት፤
ወንዝ እንፈልግ ብለው፤ ወንዝ ገብተው ቀሩ።


ባለሁበት ቀየ ፤
የመሬት ስር ውሃ፤
ቆፍሩኝ እያለ ቁሞ በተጠንቀቅ፤ ልክ እንደበረኛ፤
ወንዝ አምጡልኝ ብሎ ይኸው ይናውዛል ስስታም ወንዘኛ።
በቆምኩበት ምድር ፤
የቆመ ውሃ አለኝ፤
ዶማየን አምጡልኝ ፤
ወንዝ እፈልግ ብየ፤ውሃየን አልሰጥም፤
ግን እስከዚያ ድረስ፤
ውሃ ጠማኝ ብየ ወንዝና ወንዘኛን አልለማመጥም።

(( ጃ ኖ ))💚💛❤️

ሸጋዋ እምወድሽዋ ቅዳሜ! ለናተም ያማረ ቅዳሜ ይሁንላቹ!

@getem
@getem
@balmbaras
We do have a Turkey scholarship opportunities in advance for each department. Hopefully students who take their Entrance exam in 2011 can benefit alot from this chance. Wait us for the detail of scholarship.
@foreignwork
@Coolrepublic
Any one who is university or college graduate who wants to work in Poland can contact us now. For this round we need individual who do have a renewed Ethiopian passport and willing to work in a factory with a granted safety and reasonable payment. This will enables you to get two years work permit and Schengen VISA.
@foreignwork
@Coolrepublic
ግራ ነው መንገዴ
°°°
፰\፩\፪፳፲፪ ©ዘርዓሰብ
°°°

ሰዎች ይመክራሉ በለመዱት መንገድ በዚህ ሂድ እያሉ
የቀደመውን ሰው ያልተመረመረ ህይወት ሳያሰሉ፤

እኔ ግራ ተጓዥ፣ ብቻ ጉዞ መራጭ፣
ሰው የማይደርስብኝ፣ ከሰው የማልጋጭ፤

የግራውን መንገድ ማንም አልሄደበት፤
ከሊቅ እስከ ደቂቅ በቀኙ ብቻ ነው ሁሌ የሚጋፉበት።

አምላክን በጸሎት ግራ አውለኝ አልኩት፣ አዋለኝ በግራ
ቃሌ አከበረችኝ የጸሎቴን ምላሽ ቃልህን አክብራ።

አይዝልም ጉልበቴ ምን ቢርቅ መንገዱ
አጀብ ይቅርብኝ ቀኝ በሚል ሰበብ በጅምላ መሄዱ

ሁሉ በቀኝ ብሎ ግራውን ቢተወው
ፍኖቱ ባይሰምር ባይሄዱበት ቀድመው
ጠልፎ ጣይ የለውም መንገዱ ቀና ነው።

ጻድቁም እርኩሱም፣ ደግም ይሁን ክፉ
ሁሉም በቀኝ ነው ታትረው የሚጋፉ።
ከሰይጣን ሰይጥነው የሚጠላለፉ።
ከመተራመስ ውጭ አልታየኝም ትርፉ።

በኑሮ ትጋት ውስጥ፣ ግራው ቀንቶልኛል፣ ይመስክር ጅማቴ
በርምጃ ነው እንጂ፣ በጠልፎ ጣይ ሰዎች፣ አልዛለም ጉልበቴ።

ከሚተመው ጋራ በቀኝ ለመብረር ከማብቀል ይልቅ ክንፍ
ለብቻ ባርምሞ ባልተሄደበት ላይ ያደርሳል እግር ጽንፍ።

\ዘርዓሰብ\

@getem
@getem
@getem
#ጥላዬ

ፊን-ፊን ስትይ ፥ በሰማዩ ጋሪ
ሽቦ የታደለ ፥ ዣንጥላ ወጣሪ
ጥበብ ከነ መርፌ ፥ መጨበጡን ረሳሽ
ያገው ጥላ መሰል
ከፍ ያልሽበት ሰማይ ፥ ለዝንት የዘረጋሽ።
ይልቅ ተመከሪ ፥ ገርነት አይግፋሽ
አውታርሽ መብዛቱ
ገትሮ የሚውል ፥ የሚጥል ቃሬዛ
አይምሰልሽ ዋዛ !!!
ዝናብ ካላስጣለ ፥ ሽንቁሩ እየበዛ
ፀሀይ ካልከለለ ፥ ማድያት ከነዛ
ማን ወዶ ሊጠለል ...ማን ስርሽ ሊገዛ
የከበበ ሳይሆን
ያስተዳደረ ነው ፥ እድሜ የሚገዛ።

ነሀሴ 2011
#አብርሀም_ተክሉ

@getem
@getem
@getem