"...የሰፋ ሀገር ይዘን፣ ጠቦ መሞት ይብቃን፤..."
(ገጣሚት፥ ህሊና ደሳለኝ)
---------------------
አይችለው የለ እንጂ - የልባም ትከሻ፣
ከውርደቱ ደጃፍ - ነውሩን ማምለጥ ሲሻ፣
ገርፎ ማሳመን ነው፣ የፈሪ ሰው በትር፣ የሽንታም ሰው ጋሻ።
እንመን ግድ የለም…
ፍትሕ አይታለምም - ሐቁን እየሸሹ፣
የጠፋው እንዲገኝ፣ እስኪ መጀመርያ፣ ይፈተሽ ፈታሹ፤
አቀርቅራ ታዝግም፣ ትጎናበስ እንጂ፣ መሔድ እስኪያድላት፣
ሰብረህ ስታበቃ፣ 'ምርኩዝ እንቺ' ብለህ ደርሰህ አትደልላት፤
'በኔ ብቻ' በሽታ - ጥበት እየቀጣን፣
በ'ናታችን ርስት፣ ባባታችን መሬት፣ መደገፊያ እያጣን፤
ቁልቁል እያሰቡ - ምንድነው ከፍታ፣
መብት እየነጠቁ - ምንድነው ግዴታ?
እስከ መቼ ተረት - ግዴለም ይነጋል፣
መንገድ እየቀሙ - ምርኩዝ ምን ያደርጋል?
አንተ እንደሁ ልማድህ አለስልሶ መግደል አሳስቆ መግፋት፣
'ካብኩ' እያሉ 'ማቅለል' 'ሳምኩ' እያሉ 'መትፋት'፣
የበደል ላይ ጀግና - ሬሳ ላይ መዛት፣
መዋረድን ሽሽት - የአሽቃባጭ አፍ መግዛት፤
እየሸሹ ትግል - እየሮጡ ዛቻ፣
በጉንዳን ልቡና - የነብር ዘመቻ፤
የበላ እያሠረ - የቀማ ቢገፈው፣
የሳተ እያረመ - ያጠፋ ቢገርፈው፤
ጀግና ልማዱ ነው፣ ባርያ ሆኖ ታሽቶ፣ ንጉሥ ኾኖ መግዛት፣
እያነሰ ገዝፎ - እየሞተ መብዛት፤
ያ ሽንታም ላመሉ - በሬሳ ይፎክራል፣
ከፈሪ ገዳይ 'ድል' - የጀግና 'ሞት' ያምራል፤
ይልቅ……
በእኔ ልቅደም ትርክት- የዘር ደዌ አያጥቃን፣
ከጎጥ ቀንበር ፍቱን - ጠቦ መሞት በቃን፤
የጸደይ ወይን ኾኖ - የሐቅ እንባ ቢጥም፣
በድሎ መጀገን - ጀብድ ሆኖ ቢረግጥም፣
የትግላችን ልኩ - ያሳር ደም ቢያስምጥም፣
በሰፋ ሀገር ጠበን - ኢትዮጵያን አንሰጥም!!!
@getem
@getem
@gebriel_19
(ገጣሚት፥ ህሊና ደሳለኝ)
---------------------
አይችለው የለ እንጂ - የልባም ትከሻ፣
ከውርደቱ ደጃፍ - ነውሩን ማምለጥ ሲሻ፣
ገርፎ ማሳመን ነው፣ የፈሪ ሰው በትር፣ የሽንታም ሰው ጋሻ።
እንመን ግድ የለም…
ፍትሕ አይታለምም - ሐቁን እየሸሹ፣
የጠፋው እንዲገኝ፣ እስኪ መጀመርያ፣ ይፈተሽ ፈታሹ፤
አቀርቅራ ታዝግም፣ ትጎናበስ እንጂ፣ መሔድ እስኪያድላት፣
ሰብረህ ስታበቃ፣ 'ምርኩዝ እንቺ' ብለህ ደርሰህ አትደልላት፤
'በኔ ብቻ' በሽታ - ጥበት እየቀጣን፣
በ'ናታችን ርስት፣ ባባታችን መሬት፣ መደገፊያ እያጣን፤
ቁልቁል እያሰቡ - ምንድነው ከፍታ፣
መብት እየነጠቁ - ምንድነው ግዴታ?
እስከ መቼ ተረት - ግዴለም ይነጋል፣
መንገድ እየቀሙ - ምርኩዝ ምን ያደርጋል?
አንተ እንደሁ ልማድህ አለስልሶ መግደል አሳስቆ መግፋት፣
'ካብኩ' እያሉ 'ማቅለል' 'ሳምኩ' እያሉ 'መትፋት'፣
የበደል ላይ ጀግና - ሬሳ ላይ መዛት፣
መዋረድን ሽሽት - የአሽቃባጭ አፍ መግዛት፤
እየሸሹ ትግል - እየሮጡ ዛቻ፣
በጉንዳን ልቡና - የነብር ዘመቻ፤
የበላ እያሠረ - የቀማ ቢገፈው፣
የሳተ እያረመ - ያጠፋ ቢገርፈው፤
ጀግና ልማዱ ነው፣ ባርያ ሆኖ ታሽቶ፣ ንጉሥ ኾኖ መግዛት፣
እያነሰ ገዝፎ - እየሞተ መብዛት፤
ያ ሽንታም ላመሉ - በሬሳ ይፎክራል፣
ከፈሪ ገዳይ 'ድል' - የጀግና 'ሞት' ያምራል፤
ይልቅ……
በእኔ ልቅደም ትርክት- የዘር ደዌ አያጥቃን፣
ከጎጥ ቀንበር ፍቱን - ጠቦ መሞት በቃን፤
የጸደይ ወይን ኾኖ - የሐቅ እንባ ቢጥም፣
በድሎ መጀገን - ጀብድ ሆኖ ቢረግጥም፣
የትግላችን ልኩ - ያሳር ደም ቢያስምጥም፣
በሰፋ ሀገር ጠበን - ኢትዮጵያን አንሰጥም!!!
@getem
@getem
@gebriel_19
👍1
✍እኔና አንቺ!✍
( በረከት በላይነህ).
በጥምር ነፍሳችን ፣ አረፍ ስንልበት ጨለማው ወገገ፤
ፈጣሪ ተገርሞ ለደስታ ፍቺ አዲስ ቃል ፈለገ።
እኔና አንቺን እኮ!
አበቦቹ ያጅቡናል፣
ፍራፍሬው ይከበናል፤
ሕይወት ጉንጯ ሲንቆረቆር ይሰማናል።
ወፎቹ!
እኔና አንቺን አይተው ተቃቅፈው በረሩ፤
ከጨረቃ ታርቀው በምሽት በረሩ።
ኮከቦቹ!
" ጨረቃ ወለደች! " እየተባባሉ፤
ከእኛ ተጠግተው ብርሀን ተሞሉ።
በቀቀኖች እንኳን!
ከፃድቃን ቃል ውጭ መድገም የማይችሉ፤
ከእኛ ሳቅ በሁዋላ " ድምፅ ሰማን! " አሉ።
‘ ባክሽ እንዳይገርምሽ!
በእኛ ሲከፋፈት ~ የምድር የሰማይ በር፣
እንዲህ ቀልቡን ሲሰጥ ~ የአዕዋፍ የአራዊተ ዘር ፣
ሁሉን ይሸምታል ~ ፍቅር ሲዘረዘር።
@getem
@getem
@getem
( በረከት በላይነህ).
በጥምር ነፍሳችን ፣ አረፍ ስንልበት ጨለማው ወገገ፤
ፈጣሪ ተገርሞ ለደስታ ፍቺ አዲስ ቃል ፈለገ።
እኔና አንቺን እኮ!
አበቦቹ ያጅቡናል፣
ፍራፍሬው ይከበናል፤
ሕይወት ጉንጯ ሲንቆረቆር ይሰማናል።
ወፎቹ!
እኔና አንቺን አይተው ተቃቅፈው በረሩ፤
ከጨረቃ ታርቀው በምሽት በረሩ።
ኮከቦቹ!
" ጨረቃ ወለደች! " እየተባባሉ፤
ከእኛ ተጠግተው ብርሀን ተሞሉ።
በቀቀኖች እንኳን!
ከፃድቃን ቃል ውጭ መድገም የማይችሉ፤
ከእኛ ሳቅ በሁዋላ " ድምፅ ሰማን! " አሉ።
‘ ባክሽ እንዳይገርምሽ!
በእኛ ሲከፋፈት ~ የምድር የሰማይ በር፣
እንዲህ ቀልቡን ሲሰጥ ~ የአዕዋፍ የአራዊተ ዘር ፣
ሁሉን ይሸምታል ~ ፍቅር ሲዘረዘር።
@getem
@getem
@getem
❤1
የማምሻ ዱብ ዕዳ!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።
ዓይኔ ሲቀላውጥ
አፌ ሰርቆ ሲውጥ
ዝም ያለኝ ልጋጋም
የግዜር እሾህ አጋም
ቀን እየጠበቀ.. .
ጊዜ እየሰረቀ..
እልፍ ዓመታት ቆጥሮ ፣ ሸንግሎ በዘመን
ብሎ እንኖራለን!
ገና ብዙ ስፍር.. . የዓመት ብዝሀ
አንዱ ለሀጥያት ፣ አንዱ ለንሰሃ
በሚል ከንቱ ምኞት.. .
ጉም እያስጨበጠ ፣ ቀናት እያስገፋ
በከሰመ ተስፋ
ዝም ብሎ ዝም ብሎ
መንፈሴን ሸንግሎ
ኗሪ ነኝ እያልሁኝ.. .
ስዘርፍ ፣ ስሳረር
ስሰርቅ ፣ ስናገር
ስገድል.. .ስቀጣ
እጆቼን ለበደል ፥ ዘርግቼ ስቃጣ
ዝም ብሎኝ የነበር ...
የሞቴ መልዐክ ፥ ሰተት ብሎ መጣ።
@getem
@getem
@getem
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።
ዓይኔ ሲቀላውጥ
አፌ ሰርቆ ሲውጥ
ዝም ያለኝ ልጋጋም
የግዜር እሾህ አጋም
ቀን እየጠበቀ.. .
ጊዜ እየሰረቀ..
እልፍ ዓመታት ቆጥሮ ፣ ሸንግሎ በዘመን
ብሎ እንኖራለን!
ገና ብዙ ስፍር.. . የዓመት ብዝሀ
አንዱ ለሀጥያት ፣ አንዱ ለንሰሃ
በሚል ከንቱ ምኞት.. .
ጉም እያስጨበጠ ፣ ቀናት እያስገፋ
በከሰመ ተስፋ
ዝም ብሎ ዝም ብሎ
መንፈሴን ሸንግሎ
ኗሪ ነኝ እያልሁኝ.. .
ስዘርፍ ፣ ስሳረር
ስሰርቅ ፣ ስናገር
ስገድል.. .ስቀጣ
እጆቼን ለበደል ፥ ዘርግቼ ስቃጣ
ዝም ብሎኝ የነበር ...
የሞቴ መልዐክ ፥ ሰተት ብሎ መጣ።
@getem
@getem
@getem
#የጡንቸኞች_ዓለም
.
ፍትሕ ዓይን የላትም ፡ አይታ እንዳታደላ
በጫንቃችን ቆመች ፡ መንገድ ምሩኝ ብላ!
-
ኧረ አሁንስ ፈራን ...
እንቅልፍ ያዛት መሰል ፡ ሚዛኑ እንዳይወድቃት
አትወርድም አትፈርድም ፡ ብናይ ብንጠብቃት፨
---------------------------//-------------------------
(በርናባስ ከበደ)
-
(In Picture; a Sculpture titled 'Survival of the Fattest' , Created by Gens Galschiot)
@getem
@getem
@getem
.
ፍትሕ ዓይን የላትም ፡ አይታ እንዳታደላ
በጫንቃችን ቆመች ፡ መንገድ ምሩኝ ብላ!
-
ኧረ አሁንስ ፈራን ...
እንቅልፍ ያዛት መሰል ፡ ሚዛኑ እንዳይወድቃት
አትወርድም አትፈርድም ፡ ብናይ ብንጠብቃት፨
---------------------------//-------------------------
(በርናባስ ከበደ)
-
(In Picture; a Sculpture titled 'Survival of the Fattest' , Created by Gens Galschiot)
@getem
@getem
@getem
ግጥም ብቻ 📘
Photo
"ዘምባባ ዛሬ በገበያ ላይ ውላለች "
ምንም ይሁን ማንም ዘምባባን የማይጠብቃት አይኖርም። እርግጥ ነው ምግባርን የማታውቁት ልትኖሩ ትችላላችሁ። ወደ ፊት ግን ታውቁታላችሁ፣ ታደንቁታላችሁ፣ ትደነቁበታላችሁ፤ ትደሰቱበታላችሁ፣ ትናፍቂታላችሁም ጭምር። እሱ ከዚህም በላይ ነው። አሁን የበኩር ድክ ድኩን ዛሬ ጀባ ብሎናል ተሰልፈን እንሻማት። አንብባችሁ የምትወዱትና ደጋግማችሁ የምታነቧት መፅሐፍ እንደምትሆን አንጠራጠርም።
#ዘምባባ
አዲስ መፅሐፍ
በምግባር ሲራጅ
@getem
@getem
@getem
ምንም ይሁን ማንም ዘምባባን የማይጠብቃት አይኖርም። እርግጥ ነው ምግባርን የማታውቁት ልትኖሩ ትችላላችሁ። ወደ ፊት ግን ታውቁታላችሁ፣ ታደንቁታላችሁ፣ ትደነቁበታላችሁ፤ ትደሰቱበታላችሁ፣ ትናፍቂታላችሁም ጭምር። እሱ ከዚህም በላይ ነው። አሁን የበኩር ድክ ድኩን ዛሬ ጀባ ብሎናል ተሰልፈን እንሻማት። አንብባችሁ የምትወዱትና ደጋግማችሁ የምታነቧት መፅሐፍ እንደምትሆን አንጠራጠርም።
#ዘምባባ
አዲስ መፅሐፍ
በምግባር ሲራጅ
@getem
@getem
@getem
ተፈወሽ🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ግን እማማዬ፣
በፊት እንዴት ነበርሽ?
ከኖህ ጊዜ አንስቶ እስከ ሙሴ ድረስ፣
ዘመናትን ነጉዶ፣
ከነ አክሱም ጥበብ አድዋ እስከ
መድረስ።
እንዴት ነበርሽ ያኔ?
ዮሐንስ መተማ ላይ አንገቱን ሲሰጥሽ፣
ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ፣
ራሱን በራሱ ሰውቶ ሲለይሽ።
እንዴት ነበርሽ ያኔ?
በእንስቶች ተምሳሌት በጣይቱ
ዘመን፣
የጥቁር ህዝብ ደም በአኩሪ ድል
ሲተመን፣
እስቲ ልጠይቅሽ....
አሁን ያለው እሳት ያኔ ከነበረ፣
ከአንድ ማህጸን የወጡ ልጆችን
ሲያፋጅ ከኖረ፣
ዳግም ልጠይቅሽ...
ፍቅር የሚሉት ግን ያኔ ምን ነበረ?
ከ 'መዋደድ' ትርጉም
መባላት ወደ ሚል መቼ ተቀየረ?
አሁን ግን እምዬ ለትንሳኤሽ ኑሪ፣
ኢትዮጵያ ተብለሽ በስም ብቻ አትቅሪ፣
ባለሽበት ቆመሽ...
ታናሽ ሞት በሆነው በእንቅልፍ
አትፍዘዢ!
ግብሽን ለመምታት...
የጥላቻ ሳይሆን የፍቅር ቀስት ያዢ፣
ይህን ግን አስቢ...
የተበከለ እርሾ ከጎንሽ እንዳለ፣
የዘር ፍቅር እሳት...
በፀደቁ አበቦች መሐል የበቀለ፣
ደግመሽም ተመልከች...
በሁለት ዛፎሽ መሐል ተተክለሽ
እንደቆምሽ፣
አንዱ ዛፍ ብልህ ነው...
ለስኬቱ ማማ ሽቅብ ሚመለከት፣
አንዱ ግን እሾህ ነው...
አንቆ የሚያስቀርሽ ከጸጋሽ በረከት
መንታ ልቦች ይዘሽ...
ደግነት ከክፋት ተፈራረቁብሽ፣
አሁን ደግሞ ብሶ...
ክፋት ከበደና ሚዛኑን ደፋብሽ።
አንዲት ምስኪን ዶሮ...
እንቁላሏን ልትጥል ቦታዋ
ጠፍቶባት፣
ቦታ ብታገኝም...
ሳትጥለው ቀረች ትንሽ አቅም
አንሷት፣
ዶሮዋ አንቺው ነሽ
እንቁላሏ ደግሞ ያሰብሻት ራእይሽ
ሽቅብ ከደረሱት
ከዘመኑት ተርታ የምታሰልፍሽ...
ቦታ ያልኩሽ ደግሞ..
ጥቂቶች ሚያምኑበት የስራው
ባህል ነው፣
ጥሪት አስገኝቶ....
ከስኬት ማማ ላይ ከፍ አርጎ
የሚያቆመው፣
ነገር ግን ይህ ሁሉ...
ትንሽ አቅም ያልኩት ፍቅርን ተነፈገ
'ታጥቦ ጭቃ' ተረበት
ፍቅርን በተራብሽው በአንቺ ላይ
ሰረገ።
ስለዚህ እምዬ...
ከጸጋሽ ተገፈሽ ባዶ እንዳትቀሪ
ጨለማው ተገፎ
ጸሐይ እንድትወጣ
የፍቅር እህል ዝሪ..
ሞትሽን አላይም...
በዘር ፍቅር እሳት መጠበስሽ ይብቃ፣
ቁስልሽን ላክመው ..
ካሰረኝ እንቅልፌ ከሰመመን ልንቃ፣
ይብቃሽ እማማዬ
የሀዘን ጠባሳሽ ወደ እኔ ይገልበጥ
እስቲ አንቺ ቀና በይ...
በጭንቀት ባህር ውስጥ እኔ
ቁልቁል ልስመጥ፣
መራቆትሽ ይብቃ!!!
የፍቅርን ሸማ ደራርበሽ ልበሺ፣
ዳገቱ መሐል ላይ..
እኔ ልውደቅና እስቲ አንቺ ጨርሺ፣
የተስፋ ጸሐይሽ...
ዳግም እንድትወጣ አምላክን ለምኚ፣
እኔ ይጨልምብኝ አንቺ ግን
አግኚ፣
በዚህ በአዲስ ዘመን...
አንድ የሚያደርግሽን ብሩህ ፍቅር
ይስጥሽ
እኔ መውደድ ልጣ አንቺን ግን
አይራብሽ
በእግሮችሽ መሐል...
ቆልፎ ያስቀረሽ የክፋት መርዝ
ይውጣ፣
የፍቅር ዶፍ ይዝነብ
አንቺ እፎይ ብለሽ እኔ ሰላም ልጣ፣
መንገዳገድ ይብቃ
በሰላም ምርኩዝሽ በሁለት እግርሽ ሂጂ
እኔ አንካሳ ልሁን መጓዝ የናፈቀሽ
አንቺ ተራመጂ..
ይብቃሽ እማማዬ🇪🇹
ብርሀን ተመልከች ይሄ ድቅድቅ
አልፎ፣
አንቺ ፈገግ በይ የእኔ ጥርስ ረግፎ፣
የረገፈው ጸጉርሽ...
ዳግም እንዲበቅል ያግዘው
ይህ ፍቅር፣
መክሳትሽም ይብቃ
ስጋዬን ውሰጂና የእኔ አጥንት
ይቅር...
«ኢትዮጵያ ታበጽሕ
ዕደዊሀ ሀበ እግዚአብሔር»
✍ዮሐንስ ገርማሜ
@getem
@getem
@getem
ግን እማማዬ፣
በፊት እንዴት ነበርሽ?
ከኖህ ጊዜ አንስቶ እስከ ሙሴ ድረስ፣
ዘመናትን ነጉዶ፣
ከነ አክሱም ጥበብ አድዋ እስከ
መድረስ።
እንዴት ነበርሽ ያኔ?
ዮሐንስ መተማ ላይ አንገቱን ሲሰጥሽ፣
ቴዎድሮስ መቅደላ ላይ፣
ራሱን በራሱ ሰውቶ ሲለይሽ።
እንዴት ነበርሽ ያኔ?
በእንስቶች ተምሳሌት በጣይቱ
ዘመን፣
የጥቁር ህዝብ ደም በአኩሪ ድል
ሲተመን፣
እስቲ ልጠይቅሽ....
አሁን ያለው እሳት ያኔ ከነበረ፣
ከአንድ ማህጸን የወጡ ልጆችን
ሲያፋጅ ከኖረ፣
ዳግም ልጠይቅሽ...
ፍቅር የሚሉት ግን ያኔ ምን ነበረ?
ከ 'መዋደድ' ትርጉም
መባላት ወደ ሚል መቼ ተቀየረ?
አሁን ግን እምዬ ለትንሳኤሽ ኑሪ፣
ኢትዮጵያ ተብለሽ በስም ብቻ አትቅሪ፣
ባለሽበት ቆመሽ...
ታናሽ ሞት በሆነው በእንቅልፍ
አትፍዘዢ!
ግብሽን ለመምታት...
የጥላቻ ሳይሆን የፍቅር ቀስት ያዢ፣
ይህን ግን አስቢ...
የተበከለ እርሾ ከጎንሽ እንዳለ፣
የዘር ፍቅር እሳት...
በፀደቁ አበቦች መሐል የበቀለ፣
ደግመሽም ተመልከች...
በሁለት ዛፎሽ መሐል ተተክለሽ
እንደቆምሽ፣
አንዱ ዛፍ ብልህ ነው...
ለስኬቱ ማማ ሽቅብ ሚመለከት፣
አንዱ ግን እሾህ ነው...
አንቆ የሚያስቀርሽ ከጸጋሽ በረከት
መንታ ልቦች ይዘሽ...
ደግነት ከክፋት ተፈራረቁብሽ፣
አሁን ደግሞ ብሶ...
ክፋት ከበደና ሚዛኑን ደፋብሽ።
አንዲት ምስኪን ዶሮ...
እንቁላሏን ልትጥል ቦታዋ
ጠፍቶባት፣
ቦታ ብታገኝም...
ሳትጥለው ቀረች ትንሽ አቅም
አንሷት፣
ዶሮዋ አንቺው ነሽ
እንቁላሏ ደግሞ ያሰብሻት ራእይሽ
ሽቅብ ከደረሱት
ከዘመኑት ተርታ የምታሰልፍሽ...
ቦታ ያልኩሽ ደግሞ..
ጥቂቶች ሚያምኑበት የስራው
ባህል ነው፣
ጥሪት አስገኝቶ....
ከስኬት ማማ ላይ ከፍ አርጎ
የሚያቆመው፣
ነገር ግን ይህ ሁሉ...
ትንሽ አቅም ያልኩት ፍቅርን ተነፈገ
'ታጥቦ ጭቃ' ተረበት
ፍቅርን በተራብሽው በአንቺ ላይ
ሰረገ።
ስለዚህ እምዬ...
ከጸጋሽ ተገፈሽ ባዶ እንዳትቀሪ
ጨለማው ተገፎ
ጸሐይ እንድትወጣ
የፍቅር እህል ዝሪ..
ሞትሽን አላይም...
በዘር ፍቅር እሳት መጠበስሽ ይብቃ፣
ቁስልሽን ላክመው ..
ካሰረኝ እንቅልፌ ከሰመመን ልንቃ፣
ይብቃሽ እማማዬ
የሀዘን ጠባሳሽ ወደ እኔ ይገልበጥ
እስቲ አንቺ ቀና በይ...
በጭንቀት ባህር ውስጥ እኔ
ቁልቁል ልስመጥ፣
መራቆትሽ ይብቃ!!!
የፍቅርን ሸማ ደራርበሽ ልበሺ፣
ዳገቱ መሐል ላይ..
እኔ ልውደቅና እስቲ አንቺ ጨርሺ፣
የተስፋ ጸሐይሽ...
ዳግም እንድትወጣ አምላክን ለምኚ፣
እኔ ይጨልምብኝ አንቺ ግን
አግኚ፣
በዚህ በአዲስ ዘመን...
አንድ የሚያደርግሽን ብሩህ ፍቅር
ይስጥሽ
እኔ መውደድ ልጣ አንቺን ግን
አይራብሽ
በእግሮችሽ መሐል...
ቆልፎ ያስቀረሽ የክፋት መርዝ
ይውጣ፣
የፍቅር ዶፍ ይዝነብ
አንቺ እፎይ ብለሽ እኔ ሰላም ልጣ፣
መንገዳገድ ይብቃ
በሰላም ምርኩዝሽ በሁለት እግርሽ ሂጂ
እኔ አንካሳ ልሁን መጓዝ የናፈቀሽ
አንቺ ተራመጂ..
ይብቃሽ እማማዬ🇪🇹
ብርሀን ተመልከች ይሄ ድቅድቅ
አልፎ፣
አንቺ ፈገግ በይ የእኔ ጥርስ ረግፎ፣
የረገፈው ጸጉርሽ...
ዳግም እንዲበቅል ያግዘው
ይህ ፍቅር፣
መክሳትሽም ይብቃ
ስጋዬን ውሰጂና የእኔ አጥንት
ይቅር...
«ኢትዮጵያ ታበጽሕ
ዕደዊሀ ሀበ እግዚአብሔር»
✍ዮሐንስ ገርማሜ
@getem
@getem
@getem
❤1👍1
''ለማያውቅሽ ታጠኚ''
————//————
.
አወይ እንዴት ያምራል አቋምሽ አለሜ
እንደ ጣና ደንገል
ተክነሽው የለ ፥ .....የተክሌን ዝማሜ
.
ከነገስታት እልፍኝ ፥ ከማጀትሽ ጓዳ
ሙገሳሽ ከአፄው ፥ ባንኳላ ቢቀዳ
ለማያቅሽ ጉብል…
ልዩ ነው ዘረፋሽ ፥ ቅኔሽም አንግዳ
.
እልፍ እያሰለፈ
....…እየደጋገፈ
ያ ወርቁ መቋሚያ ፥ የንጉሥ ግድግዳ
አስቸገረን እንጂ…
ላንቺ ምርኩዝ ሆኖ ፥ …እኛን እየከዳ
.
አንቺ እንደልቡ
የከፍታሽ ነገር ፥ የዙፋንሽ ደርቡ
የለበጥሽው መዳብ ወርቅ አርገሽ በዕቡ'
የጉባዬ ቃናው ፥ ..የቅኔሽ ድባቡ
ገመገም ነውና…
ፈቺ ስላልጠፋ ፥ ገብቶናል ሀሳቡ
.
እንደ ተ'ኩላት ጥሎሽ
እንደ ሰማይ ጭሬ ፥ ያየር ምልልስሽ
ጠቦት በበዛበት ፥ የማንጃበብ ውልሽ
ሥጋ ለማጋዝ ነው…
በክሽን አጀንዳ ፥ በመልካም ወጣትሽ
.
ስራሽንም አውቆ
ፊደልን ጠንቅቆ
ስውር ስፍ ሙያሽን ፥ ለጠየቀ ርቆ
በነብዩ አፍሽ ፥ ተጠቅመሽ ላመሉ
የቅናት መንፈስ ነው ፥ ትይኛለሽ አሉ
.
አሁን ለሸመታ
እንዳዘነ ኩታ
ላላወቀ ታጥነሽ ፥ ድርቡን ለብሰሽው
በጆንያ ፊልተር ፥ ..ጅሉን አስክረሽው
ሚስጥር ሳታወርጂ ፥ እንዳሻ ፈተሽው
ሰሙን በመናገር…
ታግዢያለሽ አሉ ፥ ወርቁን ደብቀሽው
.
«ሚኪ እንዳለ»
@getem
@getem
@getem
@mmiku
————//————
.
አወይ እንዴት ያምራል አቋምሽ አለሜ
እንደ ጣና ደንገል
ተክነሽው የለ ፥ .....የተክሌን ዝማሜ
.
ከነገስታት እልፍኝ ፥ ከማጀትሽ ጓዳ
ሙገሳሽ ከአፄው ፥ ባንኳላ ቢቀዳ
ለማያቅሽ ጉብል…
ልዩ ነው ዘረፋሽ ፥ ቅኔሽም አንግዳ
.
እልፍ እያሰለፈ
....…እየደጋገፈ
ያ ወርቁ መቋሚያ ፥ የንጉሥ ግድግዳ
አስቸገረን እንጂ…
ላንቺ ምርኩዝ ሆኖ ፥ …እኛን እየከዳ
.
አንቺ እንደልቡ
የከፍታሽ ነገር ፥ የዙፋንሽ ደርቡ
የለበጥሽው መዳብ ወርቅ አርገሽ በዕቡ'
የጉባዬ ቃናው ፥ ..የቅኔሽ ድባቡ
ገመገም ነውና…
ፈቺ ስላልጠፋ ፥ ገብቶናል ሀሳቡ
.
እንደ ተ'ኩላት ጥሎሽ
እንደ ሰማይ ጭሬ ፥ ያየር ምልልስሽ
ጠቦት በበዛበት ፥ የማንጃበብ ውልሽ
ሥጋ ለማጋዝ ነው…
በክሽን አጀንዳ ፥ በመልካም ወጣትሽ
.
ስራሽንም አውቆ
ፊደልን ጠንቅቆ
ስውር ስፍ ሙያሽን ፥ ለጠየቀ ርቆ
በነብዩ አፍሽ ፥ ተጠቅመሽ ላመሉ
የቅናት መንፈስ ነው ፥ ትይኛለሽ አሉ
.
አሁን ለሸመታ
እንዳዘነ ኩታ
ላላወቀ ታጥነሽ ፥ ድርቡን ለብሰሽው
በጆንያ ፊልተር ፥ ..ጅሉን አስክረሽው
ሚስጥር ሳታወርጂ ፥ እንዳሻ ፈተሽው
ሰሙን በመናገር…
ታግዢያለሽ አሉ ፥ ወርቁን ደብቀሽው
.
«ሚኪ እንዳለ»
@getem
@getem
@getem
@mmiku