ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ምስልሽ ይታየኛል
።።።።።።።።።።።
.
እረግቶ በቆመው
ደሞም በሚፈሰው
በሚንደረደረው
በውሃው ገፅ ላይ ውቤ አንቺን አያለው

በጉም ተበሳጭቶ
በመብረቅ አጓርቶ
ከውብ ገፁ ሸሽቶ
በጠቆረው ሰማይ ገፅሽ ሕብር ሰርቶ

ምስልሽን አያለው
ደሞም እቃኛለው
በቢጫው መስክ ላይ
በአደዩ አድባር በአደዩ ቀላይ
በዞማ ጠጉርሽ ላይ አበባ ሰክተሽ
ይታየኛል ገፅሽ ይታየኛል ምስልሽ

ደሞም በገሞራው በአፍዴራው ንዳድ
በሚንቀለቀለው ኃያል የሳት ሰደድ
ውቤ የኔ አበባ ገፅሽ ይስበኛል
እምዬ ሃገሬ ምስልሽ ይታየኛል!

ተፃፈ በዴቭ(Mr. Trump)

ለመላክ: @getem_sourcebot

@getem
@getem
ሶደሬ ከመፅሐፍት ገፆች ከቴዎድሮስ ፀጋዬ ነፍሰ ጡር ስንኞች የግጥም መድብል ዋዜማ
▲▼▲▼ ነፍሰ ጡር ስንኞች ▲▼▲▼
ከቴዎድሮስ ፀጋዬ

📗የግጥም መድብል ዋዜማ

@getem
@getem 😞😔
Dagmawi Dagmawi
በጠዋት...
በመስኮቴ በኩል አጮልቄ አያለሁ...
ከቤቴ ፊትለፊት ~ ባለች በጠባብ መንገድ ~ ሰዎች ይጎርፋሉ
ብዙ ተረከዞች ይመላለሳሉ!
ፍልቅልቅ ሚስቲቱን በክንዱ እንዳቀፈ
አይን አይኗን እያየ ያ ሰውዬ አለፈ!
...
ከቤቱ ተኝቶ ሰአት ያለፈበት ሰነፍ ሰራተኛ...
በጠባቧ መንገድ ሄደ እየከነፈ
ኮቱን አወላግዶ በበሬ ጋ አለፈ!
...
ያቻትና አለፈች...
ሽቶዋ ሰፈሩን ለጉድ የሚያውደው
ወንድ አዳሙ ሁሉ በፍቅሯ የሚያብደው
አለፈች በረረች...
በሩቁ እያየኋት ከአይኔ ተሰወረች!
...
ህፃናት አለፉ እየተሯሯጡ
አዛውቶች ሄዱ በእድሜ የጎበጡ!
...
እኔ እንዳጮለኩኝ ቀኑ ማታ ሆነ...
ጠዋት ያየኋቸው በሌሊት የወጡ
በዛው ጎዳና ላይ ሁሉም ሄደው መጡ!
መምጣት ብቻ አይደለም ወደየቤታቸው ሄደው ተሸሸጉ!
ጎዳናው ፀጥ አለ ~ ሁካታው አለቀ
ከፀጥታው መሀል ~ ጥያቄ እየመጣ ልቤ ላይ ወደቀ!
...
ያየኸው ሰው ሁሉ በዚህ ጎዳና ላይ እንዲህ ሲመላለስ
ሁሉም ከሄደበት ወደየማደሪያው በግዜ ሲመለስ
እሷ ወደየት ቀረች?
እመጣለሁ ብላህ ወደየት ተሰወረች?
...
አጮልቄ እያየሁ በመስኮቴ በኩል
በባዶ መሬት ላይ እርምጃሽን ስስል!
ቀን የነበረው ቀን ጨለማ ወረሰው...
ጎዳናው ፀጥ አለ ~ ሁካታው አለቀ
ከፀጥታው መሀል ~ ጥያቄ እየመጣ ልቤ ላይ ወደቀ!
[Dagmawi Dagmawi]
...
(ጥበብ ጠራችን የሚሉ ሰዎችን አንጋፋም ብለን እንጂ እንግጠም
ካልን እኮ እንገጥማለን )


@getem
@getem
@lula_al_greeko
☞ጮማና ሽምብራ☜

ጮማዬን ደብቄ ብቻዬን ልበላው
ጣፋጩን እርጎዬን ሸሽጌ ልጠጣው
ድርቡን ሸማዬን ደብቄ ልለብሰው
ደሀ ጎረቤቴን ምንም እንዳያምረው
"ቸግሮኛል"አልኩት ለአፌም የምቀምሰው

ጮማዬን ሸሽጌ እጦቴን ስነግረው
ደሀ ጎረቤቴን እንባ ተናነቀው

"እኔ አለኝ" እያለ ሄደ ከቤት ወጣ
ሽምብራውን ይዞም ሊያካፍለኝ መጣ።

ምንጭ: ቤቲ ተፈሪ
ገጣሚ:?????
@getem
@getem
..... ክራሩ ....

ክራሩ እየሮጠ መጮሁ ገረመኝ
ወዝወዝ ማለቱ እጅግ አስደነቀኝ
እኔም ጠጋ ብዬ ክራሩን ጠየኩኝ
የመጮሁን ምክንያት ለማወቅ ፈለኩኝ
እርሱም እንዲህ አለኝ
.
.
.
.
.
ዘልዬ እምጮኸው አምርሬ ማለቅሰው
ወድጄኮ አይደለም የሰው እጅ ገርፎኝ ነው


Betelhem Girma
@

@getem
@getem
©ዮሴፍ ብርሃን
ስስምሽ ከንፈርሽን
**
የዛን እለት ማታ፣
ከንፈርሽን ስስም፣
የተሰማኝ ደስታ፣
መግለጽ ሁሉ አልችልም፣
በቃላት ጋጋታ፣
ብቻ አልረሳዉም፣
የልቤን ትርታ፣
እና
የሳምኩሽን ቦታ፡፡

በቀኝ እጀ አዉሮፓን፣
በግራየ አፍሪቃን፣
የያዝኩ እስኪመስለኝ፣
በእልፍ አእላፍ ደስታ፣
ሲያራጀኝ ሲያቃጀኝ፣
የዛን እለት ማታ፣
ስስምሽ ከንፈርሽን፣
ጨረቃዋ በርታ፣
ባላሰብኩት ቅጽበት፣
አለሜ ሲሞላ፣
በገሀድ አየሁት፣
ፍቅርሽን ቀመስኩት፣
ከንፈርሽን መጠጥኩት፡፡

የዛን እለት ማታ፣
ከወሬ ያለፈ፣
ማያዉቀዉ ከንፈሬ፣
ከዉብ ከንፈሮችሽ፣
ሳቀርበዉ ደፍሬ፣
ያ ያንቀጠቀጠኝ፣
ብርዱ ከኔ ራቀ፣
መላ አካሌ ሞቀ፣
ፍቅራችን ደመቀ፡፡

የዛን እለት ማታ፣
በቅዱስዋ ምሽት፣
አምላኬን ለመንኩት፣
በግልጽ ባይገባኝም፣
ምን እንደጠየኩት፣
ብቻ ተዐምር ፈጥሮ፣
ሳይጎዳ ማንንም፣
አንቺን የኔ አድርጎሽ፣
ከህመሜ እንዳገግም፡፡

እንደዛ እለት ማታ፣
ከንፈርሽን ስስም፣
ጉንጮችሽን ስስም፣
ግንባርሽን ስስም፣
አንገትሽን ስስም፣
የኔ ብቻ ሆነሽ፣
እንድንኖር ዘላለም፡፡
**


@getem
@getem
@lula_al_greeko
# ኑ_እውሸት_እንስራ !
-
ዘጠኝ ቁና ውሸት
ከአንድ ቁና እውነት
አሙቀን አቅልጠን
ቀይጠን አላቁጠን
በተዋበ ተንኮል በረቀቀ ሴራ
ኑ! እውሸት እንስራ!
-
ቅጥፈት ነው እንዳይሉ፤
የእውነት መአዛ ያውዳል በሩቁ
ሀቅም ነው እንዳይሉ፤
መጠርጠር አይቀርም እያደር ሲነቁ!
-
እስከ ጊዜው ድረስ ...
እስኪተላለቁ እርስ በ'ርስ ተጋጭተው
ወይ እስኪያስተውሉ ከሰመመን ነቅተው ...
-
ከጓዳቸው ገብተን
የቻልነውን በልተን
ቀሪውን ሸክፈን አርገን በስልቻ
እንጓዝ በስውር እንሂድ ለብቻ
በጊዜ እናምልጥ እንምጠቅ እንብረር፤
አሻራ ሳንተው ...
ክንፋቸውን ሰርቀን ፥ ከአይን እንሰወር!
-
-
ዘጠኝ ቁና ውሸት
ከአንድ ቁና እውነት
አሙቀን አቅልጠን
ቀይጠን አላቁጠን
በተዋበ ተንኮል በረቀቀ ሴራ
ኑ! እውሸት እንስራ!!
--------//--------
( በርናባስ ከበደ )


@getem
@getem
@lula_al_greeko
ብቸኝነት !

/ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም/

——–

ቀኑ ተሰናብቷል

ጨለማው በርትቷል

ጨረቃ የት ጠፋች?

ምን ሆኑ ኮከቦች?

ጅቦች አይፈነጩ

ውሾች አይንጫጩ፡፡

ጨለማው ፍጹም ነው

ነፋስ ጭራሽ አይነፍስ

ዛፍ አይወዛወዝ አንድ ወፍ አይላወስ

ሁሉም ፀጥ

በያለበት ለጥ፡፡

ሰው ሁሉ ምን ነካው?

ድምፁ እንዲህ የጠፋው?

እኔንስ ምን ነካኝ?

እንቅልፍ የማይወስደኝ?

እኔ ብቻዬን ነኝ በዚህ ደረቅ ውድቅት፤

ልቤ እየቃተተ ጠልቶ ብቸኝነት፡፡

ሰው አለወይ ባገር?

ማረፊያ ለፍቅር?

ፈላጊና፤ ተፈላጊ ሁሉ

ቀናው ወይ በሙሉ?

የቀረ የለም ወይ በዓለም አለኔ

በምኞት ኩነኔ?

እኔ እንደዚህ ስዋኝ ባሳብ በትካዜ

የት ይሆን ያለሽው አንቺ ይህን ግዜ

ምን ታደርጊ ይሆን?

እንገናኝ ይሆን?

መች ይሆን ዕለቱ?

መች ይሆን ሰዓቱ?

የትስ ይሆን ቦታው?

እንዴት ይሆን እውቂያው?

እጠብቅሻለሁ ልቤን እየታዘዝሁ፤

አትቅሪ፤ ፈልጊኝ፤ እፈልግሻለሁ፡፡


@getem
@getem
@Poemempire
———
/////------/////


እንደ አባቴ ገዳይ ልክ እንደ ሉሲፈር ሁሌ እጠላሻለው፤

ድንገት ስቅ ሲለኝ እያነሳሺኝ መስሎኝ ፎቶሽን አያለው።
ይህው እስከዛሬ..........
ካንቺ ወይም ከኔ አለኝ ልቤ አልፀና፤
መጥላት እና መውደድ ሆነብኝ ፈተና።

[ በለጠ ተክሉ ]


@getem
@getem
@getem
//እኔና እንቺ//
===//===
አንቺ ማለት ጨረቃ:እኔ ማለት ፀሐይ፡
አብረን የማንወጣ አብረን የማንታይ፡
ሥጠልቂ ምወጣ ሥወጣ ምጠልቂ፡
ሢከፋሽ ምደሠት ሣዝን የምትሥቂ፡
መቼም ማንገናኝ አብረን የማንሆን፡
እኔና አንቺ ማለት ፍፁም ተቃርኖ ነን፡፡
(------)
እስኪ share አርጉት!!
@getem
@getem
@getem
ካልዳሰስኩ አላምንም !

..

( በዕውቀቱ ስዩም )

..

ሊነጋ ነው ሲሉኝ ለኮስኩት ፋኖሴን ፤

ሊወብቅ ነው ሲሉኝ ደረብኩት በርኖሴን ፤

ሰላም ወርዷል ሲሉኝ ጋሻዬን አራገፍኩ ፤

ሰው አልሰማ ብል ነው ክፉ ቀኔን ያለፍኩ !

ቃል ገብቶ ቃል ማፍረስ ፤

ያገር ልማድ ሆኗል..

እንጀራ እንደመብላት በበሬ እንደማረስ!

ፍቅር ስጋ ለብሶ በ'ጁ ካላቀፈኝ ፤

ተስፋም ብብቴ ስር ገብቶ ካልደገፈኝ ፤

ኢምንት ነው ምንም ፤

ካልዳሰስኩ አላምንም !!


ለመላክ: @getem_sourcebot
@getem
@getem
@huluezih
@huluezih
ፍቅር እና መሪ

በቃኝ ካልኩኝ ደክሞኝ ከሬት ከመረረኝ የጥንቱ ማር ፍቅርሽ
ግራ እንዳትጋቢ ምክንያቱን ልንገርሽ
ሁሌ ሽሮ ብቻ ለትውልድ ካቃመ
መንግስትም ይሻራል ህዝብም ከጠመመ
እና በቃኝ ስልሽ
አሎርድ ካልሽ ከልቤ
አንቺ ያ መንግስት ነሽ
ሽሮ እያስጠማ ህዝብ በራብ ገሎ ኖርኩ የሚል ለህዝቤ።

መሌያዊ እልፉ

@getem_sourcebot
@getem
@getem
@getem
(በላይ በቀለ ወያ)


እኔ ወድሻለሁ
እንደ በውቄ ግጥም ፣ እንደ ጂጂ ዘፈን
እንደ ዜና ውሸት ፤ እንደ አጋዚ ማፈን
እንደ ተጀመረው ፣ እንደ አባይ ግድብ
እንዳልተጀመረው ፣ እንደ ትራምፕ ግንብ
እንደ መስከረም ንብ
ወይ እንደ ግንቦት ዝንብ፡፡
እንዳሜሪካ ሀብት ፣ እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ፡፡
እኔ ወድሻለሁ
እንዳስራስድስት ሉክ ፣ የልጅነት ደብተር
ሞቶ እንደሚነሳ ፣ ልክ እንደ ህንድ አክተር
እንደ ፈነከተኝ ፣ የመምህር ዳስተር፡፡
እኔ ወድሻለሁ
እንደ እፉዬ ገላ ፣ ወይም እንዳንበጣ
እንደ ብይ ጭዌ ፣ ወይ እንደገበጣ
እንደ ቃጤ ቃጤ ፣ እንደ ባገረጣ
እኔ ወድሻለሁ ፣ ክረምቱ እስኪወጣ


@getem_sourcebot

@getem
@getem
ኤርሚ

.....
ይኸው ተክዣለው
ፎቶ በላክሽልኝ፤
በቆሪጥ እያየሽ
ልቤን ወሰድሽብኝ፤
እንዲ እንደፈጠጥኩ
ለኔ እንደሳቅሽልኝ፤
በኔ እንደሳቅሽብኝ፤
እራሴን ስጠይቅ
ዘመናት አለፋኝ፡፡

ከናፈርሽ ሹሎ
አሞጥሙጠሸብኝ፤
ከተነሳሻቸው
እስቲ አንዱን ላኪልኝ፤
ቀሪውን ዘመኔን
እያሾፈች ነው
ወይ እስቲ'ና ሳመኝ፤
እያለችኝ ይሆን
ብዬ እየጠየኩኝ፤
ቀሪውን ዘመኔን
ደሞ ልግፋው ውዴ
ከምስልሽ ጋራ
ሰርክ እያወጋሁኝ፡፡


@getem
@getem
@audio_poems
@Air_me1
❀ፍርሃት

የህይወት ዛፍ አድጎ
ተስፋን ካላፈራ
ከመሞትም ይልቅ
መኖር ነው 'ሚያስፈራ።
Ezana Mesfin

@getem
@getem
እምዬ ኢትዮጵያ ፣ ሞኝ ነሽ ተላላ
ትዝ ትይኛለሽ ፣ ሸንኮራ ስበላ፡፡
"እንዴት " አትበይኝ!
እንደዚህ ነው ብዬ ፣ ካንቺ አልሟገትም
ጥርሳም ገዢ ሁሉ...
ጠአምሽን መጦ ፣ ይጥልሻል የትም!!!
(☞የለሁበትም


በላይ በቀለ ወያ
@getem_sourcebot
@getem
@getem
እምዬ ኢትዮጵያ ፣ ሞኝ ነሽ ተላላ
ትዝ ትይኛለሽ ፣ ሸንኮራ ስበላ፡፡
"እንዴት " አትበይኝ!
እንደዚህ ነው ብዬ ፣ ካንቺ አልሟገትም
ጥርሳም ገዢ ሁሉ...
ጠአምሽን መጦ ፣ ይጥልሻል የትም!!!
(☞የለሁበትም


በላይ በቀለ ወያ
@getem_sourcebot
@getem
@getem
~ላንቺ ነው የፃፍኩት~
© እሱባለው ኢ.

አይደለም አመታት፣
ሳምንት ና ወራት ፣
መኖር እንደማልችል ፤ ካንቺ ተለይቼ፣
ባዶ እንደሆንኩኝ ፤ ካንቺ ስር ወጥቼ ፣
ተስፋ እንደማይኖረኝ ፤ ባክኜ እንደምቀር፣
ጨለምተኛ ሆነሽ ፤ የሰጠሽኝ ምክር፣
ዛሬ ላይ ሳስበው፤ ዞሬ ወደኋላ፣
እውነቱ ባዶ ነው ፤ ካንቺ ቅናት ሌላ።

ይኸው እኖራለሁ ፣
አንቺን ያሰብኩ ዕለት፣
ልቤ ቢቃጠልም ፤በጥርሴ እስቃለሁ።

~~~~~~~~~~~~~~
አይደለም አንድ ሰው ፤ ከወደደው ርቆ፣
በሀጥያቱ ብዛት ፤በበደል ታጭቆ፣
በሲኦል ይኖራል፤ ካምላኩ ተሳቆ።

አንድ ቦታ ቆሜ ፤ብቻዬን እላለሁ፣
አንቺን በማሰቤ ፤ግራ እየተጋባሁ፣
ደስታዬ ርቆኝ ፤ ይኸው እኖራለሁ ፣
ውስጤ ቢቃጠልም ፤ በጥርሴ እስቃለሁ።

~16/03/10

@getem
@getem
@getem
የቃል ስደት(ልዑል ሀይሌ)
ህልሜ ቆረቆረኝ
ነይ ቀስቅሺኝ ልንቃ
ቅዠት ሰልችቶኛል
እኔ አንቺን ጥበቃ
.
አንቺን ስጠብቅሽ...
ወንበር ተሰበረ
ድንጋይ ጎደጎደ
እግሬን እሾህ ወጋው
ምን ልሁን ቸገረኝ
ህመሜን ያላየ በኔ እየፈረደ
.
ህልሜ ቆረቆረኝ..
.
የሚመጣው ነፋስ
አፈር እየነዳ
እያላተመው ነው
ከተቀመጥኩበት ጣራና ግድግዳ
.
ተው ንፋስ እንዳልል
ጉልበቴ እየከዳኝ
አፈሩን ላልሸሽግ
ጉልበቴ እየከዳኝ
እንዴት ልገላግል
እንዴት ብዬ ልዳኝ?
.
አንቺን ስጠብቅሽ...
'መጠበቅ' ሰልችቶት
ከፊደል ላይ ወድቋል
'ናፍቆት'ም ሰልችቶ
ከቃልነት ርቋል
ለናፍቆቴ ልኬት
ከ'መጠበቅ' ውጪ
ከ'ናፍቆት' ባሻገር
ኬት ላምጣ ሌላ ቃል
.
ህልሜ ቆረቆረኝ
ነይ ቀስቅሺኝ ልንቃ
ቅዠት ሰልችቶኛል
እኔ አንቺን ጥበቃ
25-09-10


@getem_sourcebot

@getem
@getem
👍2
#ስለማይታወቅ
:
:
ዛሬ ባይኖረኝም ባዶ ቢሆን ኪሴ
እንኳን ለሰው ቀርቶ ባልበቃም ለራሴ
አንጀቴ ቢታጠፍ ሆዴ ቢጣበቅ
ችግር አቆርቁዞኝ ጎዳናም ብወድቅ
ምንም ድል ብመታ ማጣት ቢዘፍቀኝም
አትናቁኝ ሰው አይናቅም።
:
:
እንደው ሰነፍ ሆኜ ባይኖረኝም እውቀት
ቢከብደኝም እንኳ «ሀ» እና «ለ»ን መለየት
አንድ ሳይባል መቼም ሁለት ካልተባለ
አሁን ደቂቅ ብሆን ሊቅ መሆን ስላለ
በቃ ተሸንፌ ከናንተ ጋር እኩል ባልወዳደርም
አትናቁኝ ሰው አይናቅም።
:
:
ዛሬ ብንደላቀቅ ብሆንም ባለሀብት
ዝናን ከመዳፌ ተቀምጣም ባገኛት
ያሻኝን ለማድረግ ባስፈለገኝ ጊዜ
ከሰው ሁሉ ብበልጥ በደምና ወዜ
ነገ መድረሻዬን ካላወቀው ማንም
ከፍ አታርጉኝ አልፈልግም።
:
:
እልፍ ነገር ባውቅም የቀለም ቀንድ ሆኜ
በማረግ ላይ ድርብ ሌላ ማረግ ጭኜ
በሄድኩበት ሁሉ ቢያጅበኝ ጭብጨባ
እጅግ ምሁር ሆኜ ቢሉኝ እዚ ግባ
በህይወት መንገድ ላይ ስለማይታወቅ ምን እንደሚያጋጥሞ
ተክቦ ተክቦ ስላለ መፍረስም
ከፍ አታርጉኝ አልፈልግም።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
አስተያየት ካሎት @henokbirhanu

@getem_sourcebot
@getem
@getem