ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
Selemon sahle best pome
ሰለሞን ሳህለ
እሩብ ጉዳይ አንዴ ሳሚኝ 😊


ግጥሞን ይላኩ ▼▼▼▼▼
@Getem_sourcebot

@getem
@getem
😁1
ሟች እና ቀባሪ
(ፍፄ ሎሬት )

ከሩቅ ይሰማኛል የመንደር ጡረምባ
ቀጠሮ እያስያዘ ሰፈሩን ሊያስነባ
ጡሩምባ ለፋፊ ያ ሙጢ ምለሱ ካፎቱ
እንደወጣ
ዳናዉ ይሰማኛል ወደ እኔ ሲመጣ
አወይ... አንት ፈጣሪ
አወይ... አንት ጠሪ
አንዱ ጊዜው ከድቶት ወዳንተ ሲጠራ
አንድ ጡሩምባ ነፊ ይበላል እንጀራ
አሁንም ተሰማኝ ያ ጡሩምባ ነፊ
የሞት ዜና አዋጅ የህልፈት ለፋፊ
ሞተ አዎ ሞተ ያ ልጅ እንዲያ እንደዋተተ
ለሰዉ በሽተኛ ለራሱ ጤነኛ እንደሆነ ሞተ
የቱ...ያ ወፈፌዉ ያ ጅላጅል እብዱ
አትበሉ ባካችሁ ነገር ሳትረዱ
ካፎቱ እንደወጣ የሰላ ጎራዴ
ሊያንቅ እንደሚዳዳዉ የአንገት ግማዴ
ምላሳችሁ ሰልቶ ልቡን እንዳደማ
ጡረምባ ለፋፊ መሞቱን ሲያሰማ
እብድ ነዉ ብላችሁ ሳያብድ እንዳበደ
በሞቱ ለማፌዝ አፋችሁ ወደደ
ቢሆንማ ኖሮ....
የቃላት ጦር ሰብቆ ለገደለ ገዳይ
ሸንጎ ባይኖር እንጂ ፍርድ ችሎት አስቻይ
የምን ፍታብሄር ወንጀለኛ መቅጫ
ህገ-ኦሪት ነበር በደልን መወጫ።

@getem
@getem
#ከቀናቴ_መሃል ...
:
ላገኝሽ ካልሆነ ፣ የመንቃቴ ትርፉ
ተኝቼ ሳልምሽ ፣ ዘመናት ይለፉ
Ezana Mesfin

@getem
@getem
"ውሰጅ"
:
ሀሳቤንም ውሰጅ
ግጥሜንም ውሰጅ
ወንድነቴን ውሰጅ
እኔነቴን ውሰጅ
ሚጠቅምሽን ብቻ፣ ውሰጅ ውሰጅና
አንቺም ተቀላቀይ፣ ከዝነኞች ዝና
ደግሞም ንገሪያቸው፣ መድረክ ላይ ስትቆሚ
"አፍቃሪ ነበረኝ፣ ፍቅሩ እጅግ ገራሚ
ህይወቱን ዘንግቶ፣ እኔን አለምላሚ"
ይሄን እየሰማ፣ ጉድ ይበል ታዳሚ
ብቻ ምለምንሽ...
ህይወቴ እንዲሞላ፣ ኑሮዬ እንዲቃና
ማፍቀሬን ተይልኝ፣ አይጥቅምሽምና...
:
(((...ባባ...)))


ግጥም ለመላክ @getem_sourcebot

@getem
@getem
👍1
ያፈቀረ ታጣቂ የሚፅፈው ግጥም
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
እንዴት ብዬ ልርሳሽ ፣ እንደምን አድርጌ
ልተውሽ አልቻልኩም ፣ ልረሳሽ ፈልጌ፡፡
፡፡፡፡፡፡
ይኸው በቀደም ለት...
ባንዳንድ ጠባቦች ፣ ረብሻ ተነስቶ
"እርምጃ ውሰዱ"
የሚል ቀጭን ትእዛዝ ፣ ከላይ አካል ወጥቶ
እርምጃ ለመውሰድ...
እየተራመድኩኝ ፣ አመፁን ላበርደው
እርምጃሽ ትዝ አለኝ ፣ እርምጃ ሚወስደው፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ይኸው ከዛ ወዲህ...
ከመንግስት እርምጃ ፣ እርምጃሽ አይሎ
ትዝታሽን ይዞ ፣ መጣ ተግተልትሎ
በእርምጃዬ ቁጥር...
እርምጃሽ ይመጣል ፣ ናፍቆትሽን አዝሎ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንዴት ነው እርምጃሽ ፣ የማያራምደው
እንዴት ነው ጠረንሽ ፣
እንደ አስለቃሽ ጭስ ፣ ደርሶ ሚያሳውረው
እንደምነው አይንሽ ፣ ነጥቶ የጠቆረው
እንደ እሬንጀር ልብስ ፣ የሚያስደነብረው
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንደምነው ጡትሽ
ልክ እንደመርማሪ ፣ ትክ ብሎ ሚያፈጠው
እንደምነው ዳሌሽ...
እንትኑን ተመቶ ፣
እንደወደቀ ሰው ፣ የሚንፈራገጠው፡
፡፡፡፡፡፡፡፡
እንደምነው ጭንሽ ፣ ካፈሙዝ ሚሞቀው
እንዴት ነው ያ ነገር...
እንደከስክስ ጫማ ፣ ቢረግጡት ማያልቀው
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንደምነው ጥርስሽ...
እንደ አድማ በታኝ ፣ የተደረደረው
እንዴት ነው አፍንጫሽ...
እንደተቃዋሚ ፣ ባጭሩ የቀረው
፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንዴት ነው ከንፈርሽ ፣ ከስልጣን ሚጥመው
እንዴት ነው ወገብሽ...
እንደ ክፉ ነገር ፣ የሚጠመጠመው
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንደምን ነው ፀጉርሽ
እንደሀገሬ ሰንደቅ ፣ በቁጥር የበዛው
እንደምነው ጉንጭሽ...
ጥፊ እንደተመታ ፣ ቀልቶ የሚወዛው
እንደምነሽ አንቺስ ፣ በናፍቆት ምትቀጪ
እንደ ሀገሬ ታሪክ
ባለፈ ጠባሳ ፣ ቁስል ይዘሽ ምትመጪ።
Share
👇👇👇
@getem
@getem
<<ጭንሽ ነው ምሽጌ>>

ከግርግዳው ጀርባ ድምጹ ይሰማኛል
ቡና እየጠጣችሁ እናትሽ ያሙኛል
ስጋየ ሲበላ ቁጭ ብየ እሰማለሁ
ጎኔን ሲቦጭቁት አህህ እላለሁ
አንዲህ ሲሉ ሰማሁ
እኚያ እናትሽ
ምክር አስመስለው እኔን ሲያሙልሽ
ፍቅረኛሽ መሆኔን መች አወቁልሽ
ስሚኝማ ልጄ,,,,,,
ይሄ ቀድረ ቀላል
ከጎናችን ያለው ማንነበረ ስሙ?
ተይው አትንገሪኝ
ብቻ እምነግርሽን አስረግጠሽ ስሚኝ
እያሉ ነገሩሽ ቀጣፊ መሆኔን
በቃሌ እማልገኝ ብኩን ሰውነቴን
ሲያሰኘኝ ሌባ በል ሲለኝ ቀማኛ
ነው አሉሽ ጉበኛ
ዛሬ አንዷን አድሬ ነግ ደሞ ሌላዋን
እንደምቀያይር ሴቶችን እንደ አሸን
አግብቼ መፍታቴን ጨምረው ነገሩሽ
እልልታው ቀርቶብኝ ጥላቻ እንዲወርስሽ
ሲጋራ ያጨሳል
ጫቱንም ይቅማል
ሲጠጣ ደ'ሞ አይጣል
ሰፈሩ በሙሉ በሱ ተበጥብጧል
ብለው አሰፉልሽ
ቱ ብለው ሲተፉት የስጋየን ልማጭ
ሰማሁና ከውጭ
እንዳይበሉት ሰጋሁ ያጥንቴን ቅጥቃጭ
ይሄን ሰማሽና........
ስትከንፊ መጣሽ እንደ ጉድ ደነፋሽ
ያሉኝን በሙሉ ነገርሽኝ ጨማምረሽ
ላስረዳሽ ሞክርኩኝ ልናዘዝ ሁሉንም
ግና ምን ያደርጋል
መታደል ነው እንጂ አይታገሉትም
ፍጥረትሽ ነውና መስማት አልታደልሺም
እውነቱ ግን ይህ ነው
አዎ እቅማለሁ..................
ስገርብሽ ውየ በዛው አመሻለሁ
በምርቃናዯ ውስጥ አንችን አይሻለሁ
አዎ ሰካራም ነኝ................
ሳጥን ተረግጬ
ቤቱን አዘግቼ
ጠጥቼ ጠጥቼ
ጨርቅ ሆኘ ሰክሬ
ወጥቶ ድንብርብሬ
እየተንገዳገድኩ
ተሳስሮ እጅ እግሬ
ስገባ እቤቴ ስምሽን ከሩቁ ጮኼ ጠራዋለሁ
ኩልትፍትፍ አድርጌ አሳምረዋለሁ
አዎ አጨሳለሁ................
በከንፈሬ መሃል አምጌሽ ወደውስጥ
ልቤን ያቆስለዋል የፍቅርሽ ረመጥ
ከዛም አንጋጥጬ ወደውጭ ሳወጣሽ
በሲጋራዮ ጭስ ይታየኛል መልክሽ
የጀመርኩት ሳያልቅ ሌላ ለኩሳለሁ
ደስ የሚል ስቃዩን እኔ ወደዋለሁ
የምን ሳምባ መቁሰል
የምን ከንፈር መጥቆር
አቦለው ይዣለሁ እያልኩ የኔፍቅር
ስሚኝማ ውዴ,,,,,,
ንዝንዙን እርሺው ንትርኩም ይቅር
መተሽ እንደሰት በምናውቀው ሃገር
ከእናትሽ ሃሜት
ከምርቃናው ህልሜ
ከመጠጡ አጎበር
ከጭሱ ህመሜ
ከለቅሶየ ድባቅ
ቶሎ እንድላቀቅ
ነይና ደብቂኝ ከጭንሽ ስር ልውደቅ


@getem
@getem
@lula_al_GREEKO
👍1
#ባላላጠሽ
:
:
ፀጉርሽ ጠልፎ ጣለኝ
ወድቄም ተነሳው
ዐይንሽ ጠቅሶ ጣለኝ
ወድቄም ተነሳው
መነሳቴ እንዳለ በጠጠር ተበሳው።
:
:
እኔም በተራዬ
ካንቺው ተከትዬ
በፀጉሬ እንዳልጥልሽ ፀጉሬ አጭር ነው
በጥቅሻ እንዳልጥልሽ ጥቅሻውን አላቀው።
:
:
ታዲያ በምን አቅሜ እንዴትስ ልጣልሽ
አምላክ በጥበቡ እሱ እንደፈጠረሽ
ጉልበታም አድርጎ በኔ እንዳስጀገነሽ
አሞሽ ከምጨነቅ እጅጉን ተጎድተሽ
በጣሙን ሳይበዛ ትንሽ ከፍ አድርጎሽ
ከዛም ከከፍታው ጥሎ ባላላጠሽ።

#ሄኖክ_ብርሃኑ
@Henokbirhabu

@getem
@getem
@getem
ምስልሽ ይታየኛል
።።።።።።።።።።።
.
እረግቶ በቆመው
ደሞም በሚፈሰው
በሚንደረደረው
በውሃው ገፅ ላይ ውቤ አንቺን አያለው

በጉም ተበሳጭቶ
በመብረቅ አጓርቶ
ከውብ ገፁ ሸሽቶ
በጠቆረው ሰማይ ገፅሽ ሕብር ሰርቶ

ምስልሽን አያለው
ደሞም እቃኛለው
በቢጫው መስክ ላይ
በአደዩ አድባር በአደዩ ቀላይ
በዞማ ጠጉርሽ ላይ አበባ ሰክተሽ
ይታየኛል ገፅሽ ይታየኛል ምስልሽ

ደሞም በገሞራው በአፍዴራው ንዳድ
በሚንቀለቀለው ኃያል የሳት ሰደድ
ውቤ የኔ አበባ ገፅሽ ይስበኛል
እምዬ ሃገሬ ምስልሽ ይታየኛል!

ተፃፈ በዴቭ(Mr. Trump)

ለመላክ: @getem_sourcebot

@getem
@getem
ሶደሬ ከመፅሐፍት ገፆች ከቴዎድሮስ ፀጋዬ ነፍሰ ጡር ስንኞች የግጥም መድብል ዋዜማ
▲▼▲▼ ነፍሰ ጡር ስንኞች ▲▼▲▼
ከቴዎድሮስ ፀጋዬ

📗የግጥም መድብል ዋዜማ

@getem
@getem 😞😔
Dagmawi Dagmawi
በጠዋት...
በመስኮቴ በኩል አጮልቄ አያለሁ...
ከቤቴ ፊትለፊት ~ ባለች በጠባብ መንገድ ~ ሰዎች ይጎርፋሉ
ብዙ ተረከዞች ይመላለሳሉ!
ፍልቅልቅ ሚስቲቱን በክንዱ እንዳቀፈ
አይን አይኗን እያየ ያ ሰውዬ አለፈ!
...
ከቤቱ ተኝቶ ሰአት ያለፈበት ሰነፍ ሰራተኛ...
በጠባቧ መንገድ ሄደ እየከነፈ
ኮቱን አወላግዶ በበሬ ጋ አለፈ!
...
ያቻትና አለፈች...
ሽቶዋ ሰፈሩን ለጉድ የሚያውደው
ወንድ አዳሙ ሁሉ በፍቅሯ የሚያብደው
አለፈች በረረች...
በሩቁ እያየኋት ከአይኔ ተሰወረች!
...
ህፃናት አለፉ እየተሯሯጡ
አዛውቶች ሄዱ በእድሜ የጎበጡ!
...
እኔ እንዳጮለኩኝ ቀኑ ማታ ሆነ...
ጠዋት ያየኋቸው በሌሊት የወጡ
በዛው ጎዳና ላይ ሁሉም ሄደው መጡ!
መምጣት ብቻ አይደለም ወደየቤታቸው ሄደው ተሸሸጉ!
ጎዳናው ፀጥ አለ ~ ሁካታው አለቀ
ከፀጥታው መሀል ~ ጥያቄ እየመጣ ልቤ ላይ ወደቀ!
...
ያየኸው ሰው ሁሉ በዚህ ጎዳና ላይ እንዲህ ሲመላለስ
ሁሉም ከሄደበት ወደየማደሪያው በግዜ ሲመለስ
እሷ ወደየት ቀረች?
እመጣለሁ ብላህ ወደየት ተሰወረች?
...
አጮልቄ እያየሁ በመስኮቴ በኩል
በባዶ መሬት ላይ እርምጃሽን ስስል!
ቀን የነበረው ቀን ጨለማ ወረሰው...
ጎዳናው ፀጥ አለ ~ ሁካታው አለቀ
ከፀጥታው መሀል ~ ጥያቄ እየመጣ ልቤ ላይ ወደቀ!
[Dagmawi Dagmawi]
...
(ጥበብ ጠራችን የሚሉ ሰዎችን አንጋፋም ብለን እንጂ እንግጠም
ካልን እኮ እንገጥማለን )


@getem
@getem
@lula_al_greeko
☞ጮማና ሽምብራ☜

ጮማዬን ደብቄ ብቻዬን ልበላው
ጣፋጩን እርጎዬን ሸሽጌ ልጠጣው
ድርቡን ሸማዬን ደብቄ ልለብሰው
ደሀ ጎረቤቴን ምንም እንዳያምረው
"ቸግሮኛል"አልኩት ለአፌም የምቀምሰው

ጮማዬን ሸሽጌ እጦቴን ስነግረው
ደሀ ጎረቤቴን እንባ ተናነቀው

"እኔ አለኝ" እያለ ሄደ ከቤት ወጣ
ሽምብራውን ይዞም ሊያካፍለኝ መጣ።

ምንጭ: ቤቲ ተፈሪ
ገጣሚ:?????
@getem
@getem
..... ክራሩ ....

ክራሩ እየሮጠ መጮሁ ገረመኝ
ወዝወዝ ማለቱ እጅግ አስደነቀኝ
እኔም ጠጋ ብዬ ክራሩን ጠየኩኝ
የመጮሁን ምክንያት ለማወቅ ፈለኩኝ
እርሱም እንዲህ አለኝ
.
.
.
.
.
ዘልዬ እምጮኸው አምርሬ ማለቅሰው
ወድጄኮ አይደለም የሰው እጅ ገርፎኝ ነው


Betelhem Girma
@

@getem
@getem
©ዮሴፍ ብርሃን
ስስምሽ ከንፈርሽን
**
የዛን እለት ማታ፣
ከንፈርሽን ስስም፣
የተሰማኝ ደስታ፣
መግለጽ ሁሉ አልችልም፣
በቃላት ጋጋታ፣
ብቻ አልረሳዉም፣
የልቤን ትርታ፣
እና
የሳምኩሽን ቦታ፡፡

በቀኝ እጀ አዉሮፓን፣
በግራየ አፍሪቃን፣
የያዝኩ እስኪመስለኝ፣
በእልፍ አእላፍ ደስታ፣
ሲያራጀኝ ሲያቃጀኝ፣
የዛን እለት ማታ፣
ስስምሽ ከንፈርሽን፣
ጨረቃዋ በርታ፣
ባላሰብኩት ቅጽበት፣
አለሜ ሲሞላ፣
በገሀድ አየሁት፣
ፍቅርሽን ቀመስኩት፣
ከንፈርሽን መጠጥኩት፡፡

የዛን እለት ማታ፣
ከወሬ ያለፈ፣
ማያዉቀዉ ከንፈሬ፣
ከዉብ ከንፈሮችሽ፣
ሳቀርበዉ ደፍሬ፣
ያ ያንቀጠቀጠኝ፣
ብርዱ ከኔ ራቀ፣
መላ አካሌ ሞቀ፣
ፍቅራችን ደመቀ፡፡

የዛን እለት ማታ፣
በቅዱስዋ ምሽት፣
አምላኬን ለመንኩት፣
በግልጽ ባይገባኝም፣
ምን እንደጠየኩት፣
ብቻ ተዐምር ፈጥሮ፣
ሳይጎዳ ማንንም፣
አንቺን የኔ አድርጎሽ፣
ከህመሜ እንዳገግም፡፡

እንደዛ እለት ማታ፣
ከንፈርሽን ስስም፣
ጉንጮችሽን ስስም፣
ግንባርሽን ስስም፣
አንገትሽን ስስም፣
የኔ ብቻ ሆነሽ፣
እንድንኖር ዘላለም፡፡
**


@getem
@getem
@lula_al_greeko
# ኑ_እውሸት_እንስራ !
-
ዘጠኝ ቁና ውሸት
ከአንድ ቁና እውነት
አሙቀን አቅልጠን
ቀይጠን አላቁጠን
በተዋበ ተንኮል በረቀቀ ሴራ
ኑ! እውሸት እንስራ!
-
ቅጥፈት ነው እንዳይሉ፤
የእውነት መአዛ ያውዳል በሩቁ
ሀቅም ነው እንዳይሉ፤
መጠርጠር አይቀርም እያደር ሲነቁ!
-
እስከ ጊዜው ድረስ ...
እስኪተላለቁ እርስ በ'ርስ ተጋጭተው
ወይ እስኪያስተውሉ ከሰመመን ነቅተው ...
-
ከጓዳቸው ገብተን
የቻልነውን በልተን
ቀሪውን ሸክፈን አርገን በስልቻ
እንጓዝ በስውር እንሂድ ለብቻ
በጊዜ እናምልጥ እንምጠቅ እንብረር፤
አሻራ ሳንተው ...
ክንፋቸውን ሰርቀን ፥ ከአይን እንሰወር!
-
-
ዘጠኝ ቁና ውሸት
ከአንድ ቁና እውነት
አሙቀን አቅልጠን
ቀይጠን አላቁጠን
በተዋበ ተንኮል በረቀቀ ሴራ
ኑ! እውሸት እንስራ!!
--------//--------
( በርናባስ ከበደ )


@getem
@getem
@lula_al_greeko
ብቸኝነት !

/ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም/

——–

ቀኑ ተሰናብቷል

ጨለማው በርትቷል

ጨረቃ የት ጠፋች?

ምን ሆኑ ኮከቦች?

ጅቦች አይፈነጩ

ውሾች አይንጫጩ፡፡

ጨለማው ፍጹም ነው

ነፋስ ጭራሽ አይነፍስ

ዛፍ አይወዛወዝ አንድ ወፍ አይላወስ

ሁሉም ፀጥ

በያለበት ለጥ፡፡

ሰው ሁሉ ምን ነካው?

ድምፁ እንዲህ የጠፋው?

እኔንስ ምን ነካኝ?

እንቅልፍ የማይወስደኝ?

እኔ ብቻዬን ነኝ በዚህ ደረቅ ውድቅት፤

ልቤ እየቃተተ ጠልቶ ብቸኝነት፡፡

ሰው አለወይ ባገር?

ማረፊያ ለፍቅር?

ፈላጊና፤ ተፈላጊ ሁሉ

ቀናው ወይ በሙሉ?

የቀረ የለም ወይ በዓለም አለኔ

በምኞት ኩነኔ?

እኔ እንደዚህ ስዋኝ ባሳብ በትካዜ

የት ይሆን ያለሽው አንቺ ይህን ግዜ

ምን ታደርጊ ይሆን?

እንገናኝ ይሆን?

መች ይሆን ዕለቱ?

መች ይሆን ሰዓቱ?

የትስ ይሆን ቦታው?

እንዴት ይሆን እውቂያው?

እጠብቅሻለሁ ልቤን እየታዘዝሁ፤

አትቅሪ፤ ፈልጊኝ፤ እፈልግሻለሁ፡፡


@getem
@getem
@Poemempire
———
/////------/////


እንደ አባቴ ገዳይ ልክ እንደ ሉሲፈር ሁሌ እጠላሻለው፤

ድንገት ስቅ ሲለኝ እያነሳሺኝ መስሎኝ ፎቶሽን አያለው።
ይህው እስከዛሬ..........
ካንቺ ወይም ከኔ አለኝ ልቤ አልፀና፤
መጥላት እና መውደድ ሆነብኝ ፈተና።

[ በለጠ ተክሉ ]


@getem
@getem
@getem
//እኔና እንቺ//
===//===
አንቺ ማለት ጨረቃ:እኔ ማለት ፀሐይ፡
አብረን የማንወጣ አብረን የማንታይ፡
ሥጠልቂ ምወጣ ሥወጣ ምጠልቂ፡
ሢከፋሽ ምደሠት ሣዝን የምትሥቂ፡
መቼም ማንገናኝ አብረን የማንሆን፡
እኔና አንቺ ማለት ፍፁም ተቃርኖ ነን፡፡
(------)
እስኪ share አርጉት!!
@getem
@getem
@getem
ካልዳሰስኩ አላምንም !

..

( በዕውቀቱ ስዩም )

..

ሊነጋ ነው ሲሉኝ ለኮስኩት ፋኖሴን ፤

ሊወብቅ ነው ሲሉኝ ደረብኩት በርኖሴን ፤

ሰላም ወርዷል ሲሉኝ ጋሻዬን አራገፍኩ ፤

ሰው አልሰማ ብል ነው ክፉ ቀኔን ያለፍኩ !

ቃል ገብቶ ቃል ማፍረስ ፤

ያገር ልማድ ሆኗል..

እንጀራ እንደመብላት በበሬ እንደማረስ!

ፍቅር ስጋ ለብሶ በ'ጁ ካላቀፈኝ ፤

ተስፋም ብብቴ ስር ገብቶ ካልደገፈኝ ፤

ኢምንት ነው ምንም ፤

ካልዳሰስኩ አላምንም !!


ለመላክ: @getem_sourcebot
@getem
@getem
@huluezih
@huluezih
ፍቅር እና መሪ

በቃኝ ካልኩኝ ደክሞኝ ከሬት ከመረረኝ የጥንቱ ማር ፍቅርሽ
ግራ እንዳትጋቢ ምክንያቱን ልንገርሽ
ሁሌ ሽሮ ብቻ ለትውልድ ካቃመ
መንግስትም ይሻራል ህዝብም ከጠመመ
እና በቃኝ ስልሽ
አሎርድ ካልሽ ከልቤ
አንቺ ያ መንግስት ነሽ
ሽሮ እያስጠማ ህዝብ በራብ ገሎ ኖርኩ የሚል ለህዝቤ።

መሌያዊ እልፉ

@getem_sourcebot
@getem
@getem
@getem
(በላይ በቀለ ወያ)


እኔ ወድሻለሁ
እንደ በውቄ ግጥም ፣ እንደ ጂጂ ዘፈን
እንደ ዜና ውሸት ፤ እንደ አጋዚ ማፈን
እንደ ተጀመረው ፣ እንደ አባይ ግድብ
እንዳልተጀመረው ፣ እንደ ትራምፕ ግንብ
እንደ መስከረም ንብ
ወይ እንደ ግንቦት ዝንብ፡፡
እንዳሜሪካ ሀብት ፣ እንደ ኢትዮጵያ ህዝብ፡፡
እኔ ወድሻለሁ
እንዳስራስድስት ሉክ ፣ የልጅነት ደብተር
ሞቶ እንደሚነሳ ፣ ልክ እንደ ህንድ አክተር
እንደ ፈነከተኝ ፣ የመምህር ዳስተር፡፡
እኔ ወድሻለሁ
እንደ እፉዬ ገላ ፣ ወይም እንዳንበጣ
እንደ ብይ ጭዌ ፣ ወይ እንደገበጣ
እንደ ቃጤ ቃጤ ፣ እንደ ባገረጣ
እኔ ወድሻለሁ ፣ ክረምቱ እስኪወጣ


@getem_sourcebot

@getem
@getem