ግጥም ብቻ 📘
64.3K subscribers
1.56K photos
31 videos
61 files
178 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
መልከኛ እውነት

ጉች ጉች ያሉ
ስኒ የመሠሉ
ጡቶቿ!!!.....እያሉ
አላፊና አግዳሚ ሊያዩሽ ይወዳሉ
አንቺም ተሽቀርቅረሽ
አውቀሽ አስጮልቀሽ
ለአይን ገበያ ታወጫቸዋለሽ
ታዲያ
ወጪና ወራጁ
እየነካሽ በእጁ
በቀን በቀን ታሽተሽ አይተው በጎመጁ
ጉቹ ይቀርና ጥልጥል ይሆናሉ
ከደረትሽ ወርደው ሆድሽ ይተኛሉ
እርቃን ቢወጡ እንኳን ተመልካች ያጣሉ
እናም ታዲያ ቆንጆ!
ውበት ጤዛነቱን
ስጋም ባዳነቱን
አይተው ቢታዘቡ
ሀበሾችም አሉ......ቁንጅናን ገደቡ
ለሰው ቅን ያሠበ...መልካም ሰው ነው ውቡ።
"አብርሀም ተክሉ"


@getem
@getem
ተለቀቀ ሲሉኝ ፣ ኔትወርኩ ነው ብዬ
ተለቀቀ ሲሉኝ ፣ መብራቱ ነው ብዬ
ተለቀቀ ሲሉኝ ፣ ውሀውን ነው ብዬ
ተለቀቀ ሲሉኝ ፣ ባጀቱ ነው ብዬ
ተለቀቀ ሲሉኝ ፣ ስልጣኑ ነው ብዬ
ለካስ አንዱ ኖሯል ፣ ታላቁ ሰውዬ።

በመለቀቁ ደስስ

።።። አላህና መድሐኒዓለም ተባብረው ያጎሳቁሏችሁ።።።

በላይ በቀለ ወያ

@getem
@getem
©

ህልሜ ከ'ኔ ሸሽቶ
በአንቺ እንቅልፍ ውስጥ
ማድባት ከጀመረ፣
(እመኚኝ ልንገርሽ)
የስጋዬ ሳይሆን
የነፍሴ ቁልፍ ነው
ካንቺ ዘንድ የኖረ፣

(ምክንያቱም)
ህልሜ ነው መኖሬ
በሌሊት አለም ውስጥ
አንቺን የሚያሳየኝ፣
ከስጋዬ አልፎ
ነፍሴን ሚጎበኘኝ...
(ለዚህ ነው)
...///...
ሻሸመኔ

@getem
@getem
👍1
መዋደድ መፋቀር፣ ከንቱነት ነው ብላ
ጨዋ-ነኝ ባይዋ ሴት፣ ቀረች በነጠላ፡፡

(ሲታዛዚን ;P )

@getem
@getem
*ያችን ልጅ ንገርዋት*
(ሠለሞን ሣህለ)

እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያችን ልጅ ንገርዋት
ልከ እንዳገሩ ነዉ የሚወድሽ በሉዋት

አወ እንዳገሬ ነዉ…
እንደ ምንጩ ጣእም እንደ አፈሩ ሽታ
ልጎንጭሽ የምላት…
ልዳብስሽ የምላት ጠዋትና ማታ
ለብሻት የምኖር…
እንደ ቀዩ ጃኖ እንደ ነጩ ኩታ
ጋቢዋ ነኝ እኔ…

ጠላት የተኮሰዉ ንፋስ እንዳይነካት
ሁለት ግዜ ዙሬ…
ወገቡዋ ላይ ያደርኩ የማርያም መቀነት

እንደ አገር አርጅታ…
እንደ አገር አዉግታ ደግሞ ተበሳጭታ
እድሜዉ ይሁን ንዴት ጸጉርዋን አሸብታ
አፋፉ ላይ ቁማ…ብቻዋን ቆዝማ
ድንገት ብታገኝዋት…

እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያችን ልጅ ንገርዋት
ልክ እንዳገሩ ነዉ የሚወድሽ በልዋት
ንገሩልኝ ዘመድ ንገሩልኝ ወገን
እኔ በሱዋ ፍቅር እንዴት እንደምሆን

እንደተዋለበት ጤናዉን እንዳጣ
በጠላ አስተናግር በጥብጦ እንደጠጣ
ያስለፈልፈኛል ጩህ ጩህ ያሰኘኛል
የቀኑ ሳይበቃዉ ሌሊት ያስዞረኛል

ጎርፉን እጠጣለሁ አፈር እቅማለሁ
ጎርፉን እየጠጣሁ….ሃገሬን እላለሁ
ጨለጥኩዋት እላለሁ
አፈሩን እየቃምኩ….ሃገሬን እላለሁ
በላሁዋት እላለሁ
ጸጉሬን እነጫለሁ ልብሴን እቀዳለሁ
እንዳይሆን እንዳይሆን እንዳይሆን ሁኛለሁ ፤

እናም ያች የኔ…
የምጠብቃት ሴት የመጣች እንደሆን
መስከረምን አልፋ…
ጥቅምትን ተሸግራ ህዳሩ ሲታጠን

ገላየ ቆሽሾ አካላቴ ዝሎ
ገጼ ተጎሳቅሎ
ድንገት አልፋኝ ብትሄድ…
ፍቅሬ ተዘንግትዋት…
ማንነቴ ጠፍትዋት…

እኔ ቃል ጨረስኩኝ ያችን ልጅ ንገርዋት
እንዳገሩ ነበር የሚወድሽ በልዋት፡፡

@getem
@getem
@lula_al_greekO
እኔ እንዳልጠራ
(ለእዮብ ዘማርያም ለስምረት እና ለመጨረሻው ገጣሚ)

አልልህም ነገር ቶሎ ና፡ ቶሎ ና
አልሠራሁምና አንዲት ነገር ደህና
ቅርም አልልህም
ወዜና ጥረቴ ሁሉም ቢደመርም
የልፋቴ ዋጋ ደሞዝ ቢታሠብም
ዕዳዬን አይከፍልም
ግና ግን ጌታዬ ይቺ ነዳይ ነፍሴ ስጋ የበደላት
ካንተ ፍቅር በቀር የለም የሚክሣት
የፈተናው ገመድ ግዜ ያከረረው
ዘመን ያደለበው
አንተ ስትመጣልን ብጣሽ ነው ሚሆነው

ያን ግዜ ነው መፍራት
ስጋ ከነፍስ ጋር በአንድ እንዳልተሠፋ
አላቅም ይላታል ጥግ እየተጋፋ

አንተም ትመጣና
እርቃን የቀረችው ቅንጣቢ ነፍሴን
ገላልጣ ብታየው ሀፍረቴን ሀጥአቴን
ክርፋቴ ገፋፍቶህ ጥለህ ትሄዳለህ
ለፀዓዳ ቤቴ አትመጥንም ብለህ

ባትመጣ ደሞ
ይህቺ ምስኪን ነፍሴ አለም የበደላት
ዝንት አለም ልትኖር ነው ስጋዬ ሲገዛት
ስጋዬ ሲወቅጣት

የቱ ነው ሚሻለው
የቱ ነው ሚበጀው?

ብትመጣ
በህግ ያልተገዛ ባንተ ያልታመነ
ነፍሴ ተኮነነ
ብትቀር
ዘመን የጠበቀ ዘመን የዋለለ
ይመጣል እያለ
ሁልግዜ ሊኖር ነው ነፍስ እያቃጠለ

ወዳጄ
መምጣትህ ቅጣት ነው
መቅረትህም ሞት ነው
እኛ ማለት ላንተ በደረቱ ሚድህ እንፉቅቅ ልጅ ነንና
ውስጡ ያልበሰለ ጉልበቱ ያልጠና
መምጣትህም መልካም መቅረትህም ደህና
ፍቃድህ ነንና፡፡

ግና ግን ጌታዬ የሀጥአቴን ጭቃ በእንባ ሳላጠራ
እኔ እንዳልጠራ፡፡

አንተ እንደፈለክ


@getem
@getem
@inluvwidart
--የሴት ልጅ ያሉኛል አዎ የሴት ልጅ ነኝ--

አዎ የሴት ልጅ ነኝ የውዲቷ እናቴ
ከግማሽ አካልዋ ተቆርጦዋል እትብቴ

አዎ የሴት ልጅ ነኝ የኔ አንድ ውዲቷ
ጡት የምታጠባ በታጠፈ አንጀቷ

ያንስብኛል እንዴ የሴት ልጅ ለመባል
የአንድ ቀን ጭነቅዋ ምጧ አኮ ያበቃል

እንዴት አልጠራ አልባል የሴት ልጂ
ውርደት አኮ አያደለም ክብር ቢሆን እንጂ

እንደሻማ ቀልታ ብርሀን ለሆነች
የሷን ኑሮ ትታ ለኔ እየኖረች
እኔን ለማቃናት እሷ አየጎበጠች

ለራሷ ታርዛ እኔን ያለበዘች
እርጥቡ ደረቁ ለ፡ሁሉ ሲነድባት
ዋጥ አድርጋ ችላ ሰው እንድሆንላት

ለዚህ ያበቃችኝ እንድዉል ከሰው ተራ
ክብር ማንነቴ ናት በስሟ ልጠራ


ምንጭ: የግጥም አምባ
@getem
@getem
✧✧✧ ብዙ ተባዙ

የእናትነት እጣ፣ ያባትነት ውርሱን
የፍጥረትን ምስጢር፣ የቤተሰብ ቅርሱን
የትውልድ አደራ፣ የብዙ ተባዙን፤
ለአእምሮህ ሳይሆን ባሻው ለሚከንፈው
ለልቦናሽ ሳይሆን ስርአት ለሚገድፈው
ለፈቃድህ ሳይሆን እብደት ለሚለክፈው
ለህሊናሽ ሳይሆን ዓለም ለሚያጎድፈው፤
ሰጠው ለሽፍደትህ ጦር ለማይመልሰው
ለመግነጢስ ገላሽ ጾም ለሚያስፈርሰው
ጻፈው በገበናሽ በጉያሽ ትኩሳት
በማትሟገተው የጭንህ ዲን እሳት፤
በሰጣችሁ ርስት በወጉ አንድትረቡ
በሴስ አቆራኝቶ በወሲብ ቀለቡ
ምድርን በሰው ሞላት በኪነጥበቡ።

ፋሲል ይትባረክ

@getem
@getem
@getem
የሰማይ ቤት ግሮሰሪ
(አሱ እንደፃፈዉ)
.
.
"ጨረቃ" ምንላት
ግሮሰሪ ቤት ናት!!!
"ሰማይ" ለምንለው ፣ ቀውጢ ከተማ
ሥራ ምትጀምረው ፣ሲሆን ነው ጨለማ!!!
..................................................
በር እንደከፈተች ፣ አብረው የሚወጡ
ከዋክብት ደሞ...
ሰካራሞች ናቸው ፣ እሷ ጋ ሚጠጡ!!!
*********************
በጣም የሰከረው...
ከሰማይ ፈጥፍጦ ፣ ራሱን ሲገድል
"ተወርዋሪ ኮከብ" ..
ማለት ነው የኛ እድል!!!
********************
ተወርዋሪ ጠርሙስ ሊሆንም ይችላል!
ማን ያውቃል?

@getem
1
👆👆👆 ገጣሚ (በላይ በቀለ ወያ)
❀ግጥም እና ግጣም ...

ኣውቃለሁ
የግጥምሽ መድፊያ ፣ የቅኔሽ መጣጣም
ስምረቱ ድንቅ ነው ፣ ቀልብ ይቀማል በጣም፡፡
#እኔን_የገረመኝ ...
ስንኝ ለመቋጠር ፣ የደረደሩት ቃል
ቤትና አጥር ዘሎ ፣ እንዴት ልብ ይመታል
Ezana Mesfin

@getem
@getem
@lula_al_greeko
ይህ ጠቅላይ ሚኒስቴር ፣ ፍቅሩ ያሸንፋል
እሰሩት ራሱን !!!
የመለስን ራዕይ ፣ ለምን ያንሻፍፋል

Belay Bekele Weya

@getem
@getem
@getem
ተኛ አትበዪኝ ፣ አልተኛም እንብየው
የስተዛሬ ህልሜን
አብይ ሲያስፈታው ፣ ነቅቼ ሳላየው

(በላይ በቀለ ወያ)

@getem
@getem
👍1
የፍቅር ቃል
(ዳጊ)

ድሮም አረማመድ አካሃድ አትችል፣

ታየች በጎዳና ወልቸም ወልቸም ስትል...

መሸከም ቢከብዳት አንዲት የፍቅር ቃል።




@getem
@getem
@lula_al_greeko
..ዝምታዮ..

ጉርምርምታው ሲፋተግ
ነፋሱ ሲያፋሽክ
ለመርዶ ነጋሪ
ለጧሪ ቀባሪ
ያሰኘው እሪታ
ፀሀይ ያለወትሮ በስተምዕራብ ወጥታ
በግማሽ ተገምሶ
ጨረቃ ደም ለብሶ
የሰማዩ መብረቅ
ጎሚ እንዳለው መልህቅ
ላንዴ ተወርውሮ ከምድር ሲጣበቅ
ደመናው ተቀዶ ዝናም ሲጥለቀለቅ
ውሽንፍሩ አይሎ ነፍሴ ስትል ጭንቅ
ጣራዮ አፍስሶ
ኮርኒሴ እርሶ
ጠብ ጠብ የሚለው
ከወለሉ ሲደርስ ጧ ብሎ ሚወድቀው
ላለቅሰው ፈልጌ ስመኘው ያጣሁት
የኔ እምባ መሰለኝ
ሰዉ ያልተረዳልኝ
ዝምታ ሸፍኖት ስቅ ስቅ የሚለኝ
.ዝ
.ም
.ም
.ም
ህመሜ በርትቶ ሳላገግም በልክ
ይማርህ የሚል ሰው ኩርማን እንኳ ሚልክ
በሌለበት መንደር ጩኸት ይሰማኛል
አውቀው የመሰለኝ ድምጹ ይጠራኛል
መልስ ችዮ እንዳልሰጥ ሰቅዞ ይዞኛል
በውሸት ድንበር ላይ ለእውነት መታገል
ወንጀለኛነት ነው ያስከትላል ገድል
እንደተነቀለ ስሩ እንደጠፋ ዛፍ
ዝምታ ይሻላል ተኝቶ መንዘፍዘፍ



ቅጥ የሌለው እበለት
ወዲያ ሲበሸከት
አላስችልህ ብሎ ለማረቅ የቃጣኝ
የእውነት አስተኔው መደማመጥ መስሎኝ
በነሱ አረዳድ ክፋት ሆኖ ቢገኝ
ልሟገታቸው ስል.......
ህመሙ ጠናና ቆበሬ ደፈቀኝ
ሞት አፋፍ ላይ ሆኘ ከሩቅ ለሚጠራኝ
ዝምታዮ በዝቶ ይሄው አስገመተኝ
ለንቶፈንቶ ወሬ አፉ የማያርፈው
ለዝምታ ጊዜ ሁሉም ምክንያት አለው
ብላችሁ ንገሩት ቢረዳልኝ ቢያውቀው



(ማሜ)


ግጥም ለማላክም ሆነ ለ አስታየት
👉@Getem_sourcebot

@getem
@getem
@lula_al_greeko
የ ገራፊ ምሬት


እንግዲህ አንተ ፍረድ
ገርፋችሁ ረገጣችሁ ፣ ኑሩ ያልከን ጌታ
ምን ሰርተን እንብላ
እኛ ያሰርነውን ፣ አብይ እየፈታ
።።።።።።
በላይ በቀለ ወያ

ለአስታየት @getem_sourcebot

@getem
@getem
ጠ-ረ*ጠ-ር*-ኩ-ሽ(ልዑል ሀይሌ)

ንፋሱ ገልቦሻል
ምን አስለምደሽው?
ፀሐዩን ስታዪ
ለምን ነው ልብስሽን ቶሎ ያወለቅሽው?
ምነው መራቆትሽ
ለወጪ ወራጁ ላማተረሽ ሁሉ
አሁን ጠረጠርኩሽ
የወጡ የገቡ አስወለቅናት ሲሉ

15-09-10

ለመላክ: @getem_sourcebot

@getem
@getem
"ጥጋብ እና ሚዛን"
እዛ ማዶ ጋራ፣
ምን ይንኮሻኮሻል፣
ፍየል ተደብቆ፣
ያንን ቦርጩን ያሻል፣
እዚህ ማዶ ዋሻ፣
ዝምታው በርትቷል፣
በጉ ተደብቆ፣
ምራቁን ይውጣል፣
የሚለውን ቀመር፣
የበጉን ረሀብ፣
የፍየሉን ሲሳይ፣
ይሄኛው ልዩነት፣
ለምን መጣ ብለን፣
መነሻውን ስናይ፣
ፍየል ማለት ተግባር፣
ጎርሶ አጣጥሞ፣
ጠግቦ የሚያገሳ፣
በግ ማለት አባባል፣
ለህሊናው ብሎ፣
ሆዱን የሚረሳ፣
የሚል ተረት ይዘን፣
ለከሰረ ውጤት፣
ነፍስን ከስጋ ጋር፣
ከምናወዳድር፣
እስኪ ምን አለበት፣
ህሊናም ቅን ሆኖ፣
ሆድም ጠግቦ ቢያድር፣
ብለን ስንጠይቅ፣
የሚሰራው ጠፍቶ፣
የተፈጥሮን ሒሳብ፣
በግ በደግነቱ፣
ለህሊናው ብሎ፣
ሆዱን እየረሳ፣
ምግብ ትቶ ሲራብ፣
ቆጡን እያሳዩ፣
ፍየሎች ወሰዱት፣
የብብቱን ጥጋብ፡፡

መርዕድ ተስፋዬ

03/06/2008ዓ.ም

👉👉@getem_sourcebot

@getem
@getem
👍1
አንቆቅልሽ?

ሙሉ ናት ሙሉ ናት ፡ ስትባል የኖረች
ሁሉም የሚወዷት ፡ አንድ አካል ነበረች

እንቆቅልሽ? ብላ ፊቷን ታዞርና፡
ምን አውቅልሽ ስላት፡
ጥላኝ ትሄዳለች ፡ መልሳ እንደገና

እንዲሁ ብትሄድ ፡ መልካም በነበረ
ዙሩን አጠማዛው ፡ ሆኗል የከረረ፡፡

ደግሞ ወዳጅ አላት ፡ የምትለው ጊዜ
ቦታና ሁኔታን ፡ የያዘው አባዜ

አነኚህ ፍጥረቶች ፡ አብረው ካልገጠሙ
ሀገር ስትሰጣት ፡ ቆመው ካልታደሙ፡

የሰጠሃትን ሀገር ፡ ብታስገባ ከእጇ፡
ሁሉንም በእጇ ፡ ብታደርግ በደጇ፡

መልስ የለውም ብላ ፡ ስትሰጥ ቀጠሮ
ጊዜና ሁኔታ ቦታም እስኪመጣ ትጠብቃታለህ፡
ሁለተኛ ዞሮ፡፡

By SaMaL Afrique


@getem
@getem
@samalafrique
'ካንሰር' ፍቅር(ልዑል ሀይሌ)

አጭር ነኝ አጭር ነሽ
ቁመት የምንለምን በነጋ በጠባ
ቀጭን ነኝ ቀጭን ነሽ
ስጋ የናፈቀን ካጥንት የሚጠጋ
.
ዓይን የለኝ ዓይን የለሽ
ህልሜንም አታይው ህልምሽንም አላይ
ጥርስ የለኝ ጥርስ የለሽ
ደስታዬን ማትቀጂ
ማልቀዳ ደስታሽን ከአንቺነትሽ ሰማይ
.
እግር የለኝ እግር የለሽ
የሚራመድ ላንቺ የሚራመድ ለኔ
እጅ የለኝ እጅ የለሽ
ስላንቺ የሚፅፍ
ስለኔ የሚዘርፍ ነፍስ የሞላው ቅኔ
.
መለያየት 'ካንሰር'
እጅ እግሬን ጥርስ ዓይኔን
ሰውነቴን ሁሉ እየቆራረጠ
ስላንቺ ያኖርኩት
ግዝፈ-አካሌን ወስዶ ለሌላ እየሰጠ
.
ይኸው ቀሪ ዕድሜዬን
እየቆጠርኩኝ ነው ነይ አብረን እንቁጠር
ወትሮም አንድ አይደለን
ለ -የ-ቅል ፍቅር ነው እኛ ስንፈጠር

23-09-10

@getem
@getem