ግሎባል ፋኖ ሚዲያ /ግፋሚ/GFM
431 subscribers
808 photos
104 videos
6 files
1.35K links
አማራ በዚህ ልክ ሲጨፈጨፍ ማየት ያማል። ይህን ለማስቆም የበኩላችን መረጃ በመስጠትና ማሰራጨት ተገቢ ነው
Download Telegram
ሚያዝያ 18 ቀን 2019 ዓ.ም

"አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ያለዉን የዘር ማጥፋት ጦርነት እና በዚህ ጦርነት ውስጥ ያለዉን ህዝብ በምርጫ ስም ለማታለል የሚያደርገዉን ሩጫ ለዓለም ለማጋለጥ የተዘጋጀዉ ዓለም አቀፍ ሰልፍ ያለንን ድጋፍ እንገልፃለን።"

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ

የአማራ ህዝብ በታሪክ ውስጥ የራሱን እና የሌላዉን ኢትዮጵያዋ ማንነት እና ታሪክ በመስዋዕትነት ያስከበረ ከመሆኑም ባሻገር በጋራ ሀገር ላይ በእኩልነት መኖርን እሴቱ ያደረገ ህዝብ ነው።

ይሁን እንጅ ከስምንት ዓመታት በፊት በለውጥ ስም በድራማ ታጅቦ ወደ ስልጣን ላይ በወጣው የብልፅግና ዘር አጥፊ አገዛዝ አማካኝነት ይህ ህዝብ መዋቅራዊ የዘር ፍጅት ታውጆበት የህልውና አደጋ ውስጥ ይገኛል። በህዝቡ ላይ የሚፈፀሙ ቀጥተኝም ጥቃቶች፣ የጦር ወንጀሎች፣ የሰላም እጦት እና የመብት ጥሰቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መጥተዋል።

ይህንንም ተከትሎ የአገዛዙን ወንጀል ማጋለጥን ጨምሮ በተለያዬ መልኩ ተጋድሎ ሲያደርጉ የቆዩት በውጭ የሚገኙ ወገኖቻችን በአገዛዙ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች እና ህጋዊ ጨፍጫፊ ለመሆን የሚያደርጋቸውን የምርጫ እንቅስቃሴወች አስመልክቶ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተቃውሞ ሰልፍ ድምፃቸውን ለማሰማት መዘጋጀታቸውን ተረድተናል።

በመሆኑም:-

• አገዛዙ በዘር ማጥፋት ወንጀል
ተጠያቂ መሆን የሚገባው ስብስብ እንጅ በጦርነት ቀጣና ውስጥ ያለን ህዝብ በምርጫ ስም አታሎ ተጨማሪ የጭፍጨፋ ዓመታትን ሊያገኝ የማይገባው በመሆኑ፤

• አገዛዙ የአፍሪካ ቀንድ የቀውስ ጠማቂ ኃይል በመሆን ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ሳይሆን የቀንዱን ህዝቦች ሰላም ጭምር የነፈገ እና በኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገሮች የውስጥ ጉዳይም ጣልቃ እየገባ ያለ እንደመሆኑ በዲፕሎማሲ መድረኮች ተገቢዉ ሊደረግበት እና ሊወገዝም የሚገባው ስለሆነ፤

• የብልፅግና አገዛዝ እያደረሰ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በማጋለጥ ምርጫ የአገዛዙን ስርዓት
አልበኝነት እና የህዝብን ሰቆቃ የሚያራዝም መሆኑን ማሳወቅ አስፈላጊ ስለሆነ፤

• ዘር አጥፊ እና አምባገነን አገዛዝን እያደረሰ ያለውን ሰቆቃ በማሳወቅ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ችግሩን ተረድቶ ከአማራ ህዝብ ጎን እንዲቆም እና ለአገዛዙ የሚያደርገዉን ድጋፍ እንዲያቆም ግፊት ማድረግ ይቻል ዘንድ በውጭ ሀገራት የሚኖረው ማህበረሰባችን ሊያደር ያሰበዉን ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ እንደግፋለን።

በመሆኑም የዲያስፖራው ማህበረሰብ በነቂስ ወጥቶ ድምፅ ለተነፈገው ህዝብ ድምፅ በመሆን ታሪካዊ ግዴታዉን እንደሚወጣ እና ለተነፈጉት ፍትሕ በመጠየቅ የተሳካ ሰልፍ እንደሚያደርግ እናምናለን።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
ክቡራን ተከታታዮቻችን፣
ዛሬ ማታ ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ ሰበር የፋኖ ተጋድሎ መረጃዎች/ እስክንድር ነጋን እንዳታመጡብን: ህወሓት

በእነዚህና በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ የምናቀርበውን ልዩ ዝግጅት ይጠብቁን።
https://youtube.com/@globalfanomedia-v4s?si=FlUZkncOJ1VMnhjH