ግሎባል ፋኖ ሚዲያ /ግፋሚ/GFM
431 subscribers
809 photos
104 videos
6 files
1.35K links
አማራ በዚህ ልክ ሲጨፈጨፍ ማየት ያማል። ይህን ለማስቆም የበኩላችን መረጃ በመስጠትና ማሰራጨት ተገቢ ነው
Download Telegram
በአማራነቱ በግፍ እስር ላይ የሚገኘው ስንታየሁ ንጋቱ በምርመራ ወቅት ከተፈፀመበት ድብደባ ጋር በተያያዘ በከፍተኛ ሕመም ላይ ነው።

በደሴ ከተማ ተወልዶ ያደገው ስንታየሁ ንጋቱ ገብረየስ ባለ ትዳር እና የልጆች አባት ነው።

ጠቅላላ መካኒክና ማሽኖችን መጠገን እና በብየዳ ስራ ተሰማርቶ ራሱንና ቤተሰቦቹን እያስተዳደረ ባለበት ነው በዘረኝነት ልክፍት ያደገው ፀረ አማራው አቢይ አህመድ በሚመራው በኦህዴድ መራሹ የብልጽግና አገዛዝ አማራነቱ እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ለግፍ እስር የተዳረገው ብሎም በሽብር ወንጀል ተከሶ ያለፍትህ ለመሰቃየት የበቃው።

በተጻፈውም ባልተጻፈውም ሕጉ አማራነትን እንደ ወንጀል በመቁጠር በተለይም ከ2015 ጀምሮ በሰፊው የአማራ ሕዝብ ላይ ይፋዊ ጦርነት ከፍቶ በምድርና በአየር ኃይሉ የዘር ማጥፋትና የጦር ወንጀል በአረመኔነት እየፈፀመ ያለው አገዛዝ በፌደራል ማ/ቤቶች እንኳ በሕግ ስም ቢያንስ ከ300 በላይ አማራዎችን ያለፍትህ አግቶ ይገኛል።

ይህ በምርጫ ስም እያጭበረበረና ኮሮጆ እየገለበጠ ዘረኛ የሆነ የአንባገነን አገዛዙን ለማስቀጠል እየተንፈራገጠ የሚገኘው የአቢይ አህመድ የእኩይ ፣ የእብሪትና የድንቁርና ደመ ነፍሳዊ ስርዓት በማንነታቸው የተነሳ ፣ አትግደሉን ፣ አታፈናቅሉን ፣ እንደ ዜጋ እንታይ ፣ እኛም ሀገር እና መንግስት ይኑረን ማለታቸው እንደ ወንጀል እየቆጠረ በርካታ የአማራ ልጆችን ጾታ እና እድሜ ሳይለይ ያለ ፍትህ አግቷቸው ይገኛል ።

ከሞት ከተረፉት ነጻነትና ፍትህ ፈላጊ አማራዎች መካከል አንዱ የሆነው ስንታየሁ ንጋቱ ትናንትን በረሱ ፣ ነገ ሌላ ቀን መሆኑን በማያስተውሱ በአገዛዙ እኩይ የዘኝነትና የመጠፋፋት አላማ አስፈጻሚዎች ብዙ ፈተና አሳልፏል።

በምርመራ ስም በፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ (ሜክሲኮ) በጨለማ ክፍል ፣ በአዋሽ አርባ እና በሰመራ ተወስደውና ሲቪሎች ሕጉ በማይፈቅደው በወታደራዊ ካንብ ጭምር መንግስታዊ እገታ ተፈፅሞባቸው አሰቃቂ የሰብአዊ መብት ረገጣ ከተፈፀመባቸው የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች መካከል አንደኛው ገፈታ ቀማሽ ፣ ተጠቃሽ ነው።

በከፍተኛ ሕመም ላይ የሚገኘው ስንታየሁ ንጋቱ በሜክሲኮ በፀረ አማራው ኮማንደር አዱኛ ረጋሳ ቢሮ ክፉኛ ተገርፏል ፤ ብዙ ግፍ ተፈጽሞበታል።

በእነ ስንታየሁና በማይተዋወቁ አባሪዎቹ ላይ "የከሸፈው ሴራ" በሚል የተለመደ እና እጅ እጅ የሚል እርካሽ ፕሮፖጋንዳ የሰራ መሆኑ አይዘነጋም።

ከደረሰበት ድብደባ ጋር በተያያዘ የቀኝ ኩላሊቱ ፌል አድርጓል ፤ የዘር ፍሬው ላይ ድብደባ በመፈፀም ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውበታል።

አሁን ላይ በቂሊንጦ ፣ በቃሊቲ ፣ በአባ ሳሙኤል ፣ በዝዋይ እና በሌሎች ማ/ቤት በግፍ እስር ላይ የሚገኙ አማራዎች እጣፈንታ እንደሆነው በቤተሰቦቹ ላይ ማስፈራሪያ ፣ ማዋከብ እና ዛቻ ተፈጽሟል ፤ እንዲበተኑም ተደርጓል።

"የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ኃላፊዎች ፍርድ ቤቱ በነፃ ቢለቅህ እኛ መንግስት ስለሆንን አፍነን ወስደን እንገልሃለን" ብለው ዝተውበታል።

ማህተቡን በመቁረጥም "አይደለም ይህችን ያረጀች ሐይማኖት ነውና ገና ሁላችሁንም እናጠፋችሃለን" በማለት እንዳስፈራሩትና የነውረኝነትና የጥላቻ ጥግ እንዳሳዩት ለማወቅ ተችሏል።

ስንታየሁ ንጋቱ አሁንም ካለበት የጤንነት ከባድ ችግር አንጻር በቂ እና የተሻለ የሚባል ሕክምና እያገኘ እንዳልሆነ ይናገራል ፤ መፍትሄ በሌለው በተንዛዛ ቀጠሮ ተማሯል።

በግፈኞች የደረሰበትን ጉዳት ተከትሎ ገና ለገና በማስረጃነት እንዳይያዝባቸውና ለምን መረጃ ሰጣችሁ በሚል እንዳይባረሩ የሚሰጉ የሕክምና አካላትም በቂ መረጃ አይሰጡትም።

ስንታየሁን ጨምሮ አያሌ በግፍ እስር ላይ የሚገኙ እና በሕመም ብቻ ሳይሆን በሁለንተናዊ ችግር እየተጠበሱ ያሉ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች ብሎም የተበተኑ ቤተሰቦቻቸው የወገንን ሁሉንአቀፍ ድጋፍ በእጅጉ ይሻሉ።

የጊዜ ጉዳይ ነው እንጅ ከዘመንና ከትውልድ ጋር የተጣሉ ሆድ አምላኩ ፣ ጨካኝና ዘረኛ ግፍ ፈጻሚዎች ከሞራል ፣ ከሕግ እና ከታሪክ ተወቃሽነትና ተጠያቂነት መቼም አያመልጡ!

ይህ ሞትን ንቆ ለነጻነትና ክብሩ ፣ ለፍትህና ለእኩልነት እንዲሁም ለአብሮነት እየተዋደቀ ያለ ፣ እየተነሳ ያለ ትውልድ ይፋረዳቸዋል ፤ በስራቸው ልክ የሚገባቸውን ይሰጣቸዋል ~ አንጠራጠርም ፤ እየሰጣቸውም ነው!

(አውሎግሶን አንድነት ፣ መጋቢት 21/2018)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአርበኛ ሸጋ ጌታቸው ጥብቅ መልዕክት
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አፋብን በጎንደር ጠቅላይ ግዛት በላይ እዝ መይሳው ካሳ 2ኛ ኮር ቋራ ኦሜድላ ክ/ጦር አርበኛ ታዴ ሉሌ መልእክት አስተላለፈ።