ግሎባል ፋኖ ሚዲያ /ግፋሚ/GFM
432 subscribers
808 photos
104 videos
6 files
1.35K links
አማራ በዚህ ልክ ሲጨፈጨፍ ማየት ያማል። ይህን ለማስቆም የበኩላችን መረጃ በመስጠትና ማሰራጨት ተገቢ ነው
Download Telegram
የመን ድንበር ላይ ከ10ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች መታየታቸው አለምን አስደንግጧል።

ወጣቶቹ ኢትዮጵያ ሀገራቸው በጦርነትና በሙስና እንዲሁም በአንድ ብሔር የበላይነት ምስቅልቅሏ ስለወጣ ሀገሪቷን ጥለው እየተሰደዱ እንደሆነ ነው የታወቀው።

ብዛታቸው ከ10ሺ እንደሚልቅ የተነገረ ሲሆን፡ ብዛታቸውንና ያሉበትን ሁኔታ የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ከተለቀቀ በኋላ አለም ደንግጧል።

ያላባራ(እሱንም የእርስ በእርስ) ጦርነት፣ ሙስናና አድሎአዊ አሰራር፣ የብሔር የበላይነትና ባለጊዜነት፣ እነዚህ ሁሉ ተዳምረው ወጣቱን ተስፋ እንዲቆርጥ አድርገውታል።

ተወልዶ ባደገበት አከባቢ የመኖርና ሀብት ንብረት የማፍራት እድሉን በአገዛዙ የተነፈገ ሕዝብ፡ ከፊት ለፊቱ ሌላ ሞት እንዳለ እያወቀም ቢሆን ያንን ለመጋፈጥ ወስኖ ስደት የሚሉትን የመከራ ቋት ይጀምራል።

ሀገር በአላዋቂዎችና በመሀይማን ስትመራ ትውልዷ ይመክናል፣ እርስቷ ይደፈራል፣ እሴቷና ባህል ወጓ ይናዳል።

የነ ዐብይ አህመድ ብልፅግና ቡድን ሕዝቡን ሀገር አልባ አድርጎታል።
በአማራነታቸው የተነሳ በኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ከእየቤታቸውና ስራ ቦታቸው ከተወሰዱ በኋላ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ፍትህ ፈላጊ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞችን የጥቅምት 26/2018
የችሎት ውሎ በስፍራው ተገኝተው በመከታተል አጋርነትዎን ይግለጹ!

(1) በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ የክስ መዝገብ (23) ሰዎች፣
(2) በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው የክስ መዝገብ (16) ሰዎች እና
(3) በእነ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም የክስ መዝገብ (5) ሰዎች ጥቅምት 26/2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ይቀርባሉ።

በችሎት ተገኝተው በመከታተል በአማራነታቸው ያለ ፍትህ በግፍ ታስረው ለሚገኙ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች አጋርነትዎን ይግለጹ!

(አውሎግሶን አንድነት ፣ ጥቅምት 25/2018)
~ ከአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ  ግንባር ለፋኖ ኃይሎች የተሰጠ የአጋርነት መግለጫ!

የተከበራችሁ መላው የአፋር ህዝብና የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች በሙሉ  እንደምታወቀው የአፋር "ኡጉጉሞ" ነፃነት ግንባር፣ የአፋር ህዝብ ክብርና ጥቅም እንዲሁም ልዑላዊነትና ድህንነት ከየትኛውም የውስጥና የውጭ ጠላት እንዲጠበቅና እንዲከበር ለበርካታ አመታት በደምና በአጥንት ብዙ መስዋዕትነት እየከፈለ የመጣ ግንባር መሆኑ ይታወቃል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህም ወደመደበኛ የትጥቅ ትግል በመሸጋገር ላይ እንዳለን ይታወቃል።

የአሁኑን ትግላችን ከዚህ ቀደሙ የተለየ ያደረገው፦

አንደኛ፡- የብልፅግና ቡድን የአፋር ህዝብ ልዑላዊ ግዛት ለሌላ አሳልፎ ሊሰጥ በመሆኑ፤

ሁለተኛ፦ ቀይ ባህርን የኢትዮጵያ አካል እናደርጋለን በማለት የብልጽግና አገዛዝ የሚቀሰቅሰው ጦርነት፣ በይበልጥ አፋርና አፋርን ለማጋደል የተጠነሰሰው ሴራ በመሆኑ፤

ሦስተኛ፡- ክልሉን በለውጥ ስም ስልጣን የተቆጣጠረውና ለ7 አመታት እየመራ የሚገኘው የብልፅግና ቡድን በማናለበኝነት የህዝብ ሀብት መበዝበዝና ጎሳን ከጎሳ በማጋጨት ወንጀል  እየፈፀመ የሚገኝ በመሆኑ፤

አራተኛ፡- በአፋር መሬት ላይ ለአብይ አህመድና የአገዛዙ ፍላጎት ማስፈፀሚያ እየሰለጠኑ ያሉ የታጠቁ ኃይሎች አፋርን የደም መሬት ሊያደርጉት እየሰሩ በመሆኑ፤

በእነዚህና ሌሎች የትግል መነሻ ምክንያቶች   የአፋር ህዝብ ያልተገባ የመስዋዕትነት እንዲከፍሉ ለማድረግ እየተሰራ በመሆኑ የአሁኑን የትጥቅ ትግላችን የተለየ ያደርገዋል።

በአሁኑ ሰዓት በምናደርገው የተደራጀ ትግል የአብይ አህመድ ወኪል፣  አድርጎ ያስቀመጠውን የአወል አርባን አገዛዝ ከውጭም፣ ከውስጥም ሁነን እያፈረስነው እንገኛለን።

በዚህም አመርቂ ውጤቶችን አግኝተንበታል። በዚህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ አገዛዝ ያንገሸገሻቸው የአወል አርባን ወታደራዊ አመራሮችና ሲቭል አመራሮች እየተቀበልን እንገኛለን።

ከዚህ በፊት በመግለጫችን እንዳስታወቅነው፣ በሶማሌ ክልል እጅ አዙር መሪነትና በጂቡቲ ስፖንሰርነት፣ የተባበሩት የሶማሌ አሸባሪዎች የአፋር ህዝብ ላይ በኢሳ ሽፋን ያወጁት ወረራ ለ7 አመታት በንጹሃን ላይ ጥቃት ሲሰነዝሩ ቆይተዋል። 

ከወትሮ በተለዬ የአፋር ህዝብ በገዛ ቤቱ እያሸበሩና እየገደሉ ቢሆንም የአፋር ህዝብ በብርቱ ክንድና በሙሉ ልብ እየመከታቸው ከራሱ አልፎ ኢትዮጲያን ከዚያድ ባሬ ህልምና ቅዠት እየታደጉ አብዛኛው አሸባሪዎችን ወደ መሬት እቀበሩ የተቀሩት ደሞ በመመከት ወደ መጡበት ሀገር እንዲመለሱ ማድረግ ላይ ነው።

ሕዝባችን በራሱ ትግል ክልሉን ከወራሪው ነፃ ያደረገ ቢሆንም በሚያሳዝን መልኩ ይሄንን የተባበሩት ሶማሌ ተስፋፊያን የከፈቱብን ግልፅ ወረራ የፌድራል መንግስት ወራራውን ከማስቆምና ከመከላከል በተቃራኒ የአብይ ቡድን በጂቡቲ ያለውን የሥልጣን ጥቅምና ቀጠናዊ የቡድን ፍላጎት በማስቀደም በአፋር ህዝብ ላይ የሚፈፀም የተባበሩት ሶማሌ ወረራ በግልፅ እየደገፍ ይገኛል።

አፋርን በቴክኒካል ሴራና የእጅ አዙር ተፅዕኖ በማዳከም አሸባሪዎቹን ወደ አፋር ልዑላዊ ግዛት እምብርት ላይ እንዲመለስ ግፊት በማድረግ ላይ ነው። ይህ እንደ ሀገር ክህደት የሚቆጠር ወንጀል ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ወንድም የሆነውን የኤርትራ ህዝብን ለመውጋትና የሚሰለጥኑ ኃይሎች ለአፋር ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያና ለአካባቢው የከፋ አደጋ እንደሚያመጣ ህዝባችን ያምናል።

በትላንትናው ዕለትም የአፋር ሕዝብ ይሄ ነገር መቆም እንዳለበት ተቃውሟውን በተለያዩ መንገድ ገልጿል፣ ይሄ ጉዳይም እስከ ነጻነት ድረስ የሚቀጥል መሆኑን የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር ያስታውቃል።

የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር ከሰሞኑ በአማራ ክልል ወሎ ግንባር በአገዛዙና በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ በኩል እየተደረጉ ያሉ ውጊያዎችን በትኩረት እየተከታተለ ይገኛል።

የፋኖ ኃይሎች ከባዶ እጅ በመነሳት ዛሬ ላይ በመካናይዝድ የታገዘ መደበኛ ውጊያ እያደረጉ መሆኑን ተገንዝበናል። የተሰየመው ዘመቻም ዘመቻ አደም አሊ የሚል መሆኑን፣ ዘመቻው የተሰየመለት ፋኖ፣ በትግል ላይ የተሰዋ ሙስሊም ፋኖ መሆኑንም አረጋግጠናል።

ይህ የፋኖ ኃይሎችን የአንድ ኃይማኖት ሰዎች ናቸው፣ የቀድሞውን ሥርዓት ለመመለስ ነው የሚታገሉ የሚለውን የብልጽግና አገዛዝ የሐሰት ፍረጃ፣ እንዲሁም በፍረጃው ለተሳሳቱ ሁሉ ምላሽ የሚሰጥ ሁኖ አግንተነዋል።

የፋኖ ኃይሎች እያደረጉ ላለው ከባድ ትግል እውቅና የምንሰጥ መሆኑን እንገልጻለን።

የአማራ ሕዝብና የአፋር ሕዝብ ከትናንት እስከዛሬ በመከራም፣ በደስታም የጋራ እጣ ፈንታ ያላቸው መሆኑ ይታወቃል።  አሁን ላይ በአብይ አህመድ የሚመራው የብልጽግና አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተው ጦርነት ተቀባይነት የሌለውና ለሀገር ወዳዱ የአማራ ሕዝብም ይሄ የማይገባው መሆኑን መግለጽ እንፈልጋለን።

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ኃይሎች እያደረጉት ያለው ተጋድሎ ከነሱም መግለጫዎች በተደጋጋሚ እንደተረዳነው የመላው ኢትዮጵያ ብሄረሰቦች ነጻነት እንደሆነ ድርጅታችን ያምናል።

እኛም የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር በቀጣይ ከፋኖ ኃይሎች ጋር በጋራ በመታገል የአብይ አህመዱን የብልጽግና አገዛዝ ለአንዴና ከመጨረሻ ጊዜ በመጣል በእኩልነት የጋራ አገር ለመገንባት  በትብብር እንደምንሰራ ስንገልጽ በደስታ ነው።

በመጨረሻም አፋርን እንደመሸጋገሪያ በማድረግ የአማራ ሕዝብን ለማውድም የሚያደርገውን እንቅስቃሴ መላው የአፋር ሕዝብ እንዲቃወምና እንዲያስቆም የአፋር ብሔራዊ አንድነት አብዮታዊ ግንባር ይጠይቃል፣ እንዲቆም እንደምንሰራ መግለጽ እንፈልጋለን።

መላው የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች የትግል መነሻዎቻችን ተረድቶ በሀገራችን ላይ የተደቀነው ብሄራዊ አደጋ በጋራ ትግል እንዲቀለብስ ጥሪ እናቀርባለን።

ግመሎቻችን ጭምር የሚያውቋት የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዳትወድቅ፣ ነፃ ሀገር እንድትኖረን ለትግላችን አስፈላጊውች ትብብር እንዲያደርጉ እንጠይቃለን !

ድልና ድምቀት ለአፋር ኡጉጉሞ
2