ግሎባል ፋኖ ሚዲያ /ግፋሚ/GFM
431 subscribers
808 photos
104 videos
6 files
1.35K links
አማራ በዚህ ልክ ሲጨፈጨፍ ማየት ያማል። ይህን ለማስቆም የበኩላችን መረጃ በመስጠትና ማሰራጨት ተገቢ ነው
Download Telegram
በህሊና እስረኞች ላይ የሚፈፀመው ኢ-ሰብአዊና የጥላቻ ድርጊት በአስቸኳይ ይቁም!

ይህ በምስሉ የሚታየው ግለሠብ ኢንስፔክተር ድሪባ ሰንበቶ ይባላል። የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የጥበቃና ደህንነት ክፍል ሀላፊ ነው። ለአመታት ያለፍትህ ታስረው በሚገኙ ወንድም እህቶቻችን ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በመፈፀም ላይ ይገኛል። 

ግለሰቡ በፍርድ ቤት ክስ ተመስርቶበት የሚገኝና በሂደት ላይ ያለ ቢሆንም በማንአለብኝነት በህገ-ወጥና የጥላቻ ተግባሩ ገፍቶበታል።

የክሱ ሂደት እስከሚጠናቀቅ በችሎቱ ከድርጊቱ እንዲቆጠብና ከጠበቃና ከቤተሰብ ጋር መገናኘትን ጨምሮ የከለከላቸውን መብቶቻቸውን እንዲያከብር ብሎም ስድብና ድብደባ እንዳይፈፅም  የተነገረው ሆኖ ሳለ ትእዛዙን ለመፈፀም ግን ፈቃደኛ አለመሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያስረዳል።

በህሊና እስረኞቹ ላይ ስድብና ዛቻ ከመፈፀም ባሻገር ከዚህ በፊት በመሪ ጌታ በላይ አዳሙ ላይ ድብደባ መፈፀሙ ተገልጿል። "ቅዘ*ና'ም አማራ ምን ታመጣለህ'' ብሎ በድፍረት የሚናገረው ይህ ሰው ፣ የታሳሪ ቤተሰቦችን ለጥየቃ ሲሄዱ ማንገላታትና መሳደብን ጨምሮ በርካታ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን እየፈፀመ እንደሚገኝ  ከቀረበው ክስ መረዳት ይቻላል። ችሎቱ  ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም ግለሰቡን  እንዲቀርብ በማድረግ ክሱን መመልከት የጀመረ ሲሆን ለመጪው ጥቅምት 26 ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱም ታውቋል!

በህሊና እስረኞች ላይ የሚፈፀመው ኢ-ሰብአዊና የጥላቻ ድርጊት በአስቸኳይ ይቁም!
የመን ድንበር ላይ ከ10ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች መታየታቸው አለምን አስደንግጧል።

ወጣቶቹ ኢትዮጵያ ሀገራቸው በጦርነትና በሙስና እንዲሁም በአንድ ብሔር የበላይነት ምስቅልቅሏ ስለወጣ ሀገሪቷን ጥለው እየተሰደዱ እንደሆነ ነው የታወቀው።

ብዛታቸው ከ10ሺ እንደሚልቅ የተነገረ ሲሆን፡ ብዛታቸውንና ያሉበትን ሁኔታ የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ከተለቀቀ በኋላ አለም ደንግጧል።

ያላባራ(እሱንም የእርስ በእርስ) ጦርነት፣ ሙስናና አድሎአዊ አሰራር፣ የብሔር የበላይነትና ባለጊዜነት፣ እነዚህ ሁሉ ተዳምረው ወጣቱን ተስፋ እንዲቆርጥ አድርገውታል።

ተወልዶ ባደገበት አከባቢ የመኖርና ሀብት ንብረት የማፍራት እድሉን በአገዛዙ የተነፈገ ሕዝብ፡ ከፊት ለፊቱ ሌላ ሞት እንዳለ እያወቀም ቢሆን ያንን ለመጋፈጥ ወስኖ ስደት የሚሉትን የመከራ ቋት ይጀምራል።

ሀገር በአላዋቂዎችና በመሀይማን ስትመራ ትውልዷ ይመክናል፣ እርስቷ ይደፈራል፣ እሴቷና ባህል ወጓ ይናዳል።

የነ ዐብይ አህመድ ብልፅግና ቡድን ሕዝቡን ሀገር አልባ አድርጎታል።
በአማራነታቸው የተነሳ በኦህዴድ ብልጽግና አገዛዝ ከእየቤታቸውና ስራ ቦታቸው ከተወሰዱ በኋላ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ፍትህ ፈላጊ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞችን የጥቅምት 26/2018
የችሎት ውሎ በስፍራው ተገኝተው በመከታተል አጋርነትዎን ይግለጹ!

(1) በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ የክስ መዝገብ (23) ሰዎች፣
(2) በእነ የተከበሩ ዮሃንስ ቧያሌው የክስ መዝገብ (16) ሰዎች እና
(3) በእነ ዶ/ር ቴዎድሮስ ኃይለማርያም የክስ መዝገብ (5) ሰዎች ጥቅምት 26/2018 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ይቀርባሉ።

በችሎት ተገኝተው በመከታተል በአማራነታቸው ያለ ፍትህ በግፍ ታስረው ለሚገኙ የፖለቲካ እና የሕሊና እስረኞች አጋርነትዎን ይግለጹ!

(አውሎግሶን አንድነት ፣ ጥቅምት 25/2018)