ግሎባል ፋኖ ሚዲያ /ግፋሚ/GFM
430 subscribers
808 photos
104 videos
6 files
1.35K links
አማራ በዚህ ልክ ሲጨፈጨፍ ማየት ያማል። ይህን ለማስቆም የበኩላችን መረጃ በመስጠትና ማሰራጨት ተገቢ ነው
Download Telegram
በቋራ አራተኛ ቀኑን ያስቆጠረ አዉደዉጊያ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተሰማ።

በቋራ፣በሙር፣ወንበልጌ እና የወረዳዉ መቀመጫ ገለጎ ከተማ ወጣ ባሉ አካባቢዎች ጠንከር ያለ አዉደዉጊያ ሲደረግ ሰንብቷል ሲሉ የአካባቢው ኗሪዎች መረጃዉን ለግሎባል ፋኖ ሚዲያ ተናግረዋል።

ፋኖ እና የአገዛዙ ጥምር ጦር እያደረጉት ባለዉ አዉደዉጊያ በርካታ ወታደሮች የተገደሉ ሲሆን ገደል የገቡ ስለመኖራቸዉም አያይዘዉ ተናግረዋል።

አራተኛ ቀኑን ያስቆጠረዉ አዉደዉጊያ በጨበጣ፣በመካናይድ እንዲሁም በደፈጣ የተደረገ ሲሆን ፋኖ ድል ቀንቶታል ተብሏል።ጠንካራ የፋኖ ሰራዊት እንዳለ የሚነገርለት ቋራ እና አካባቢው ላለፉት ሁለት አመታት በርካታ የአገዛዙን ብልፅግና ጦር ማፈራረሱ ይታወሳል።

ከሁለት ክፍለጦር በላይ የሚሆን የብልፅግና ጦር በካሳ ምድር ቋራ ስለመደምሰሱ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ሳይቀር ምስክርነታቸዉን ሰተዋል።ከሰሞኑም ቋራ የአብይ አህመድ ወታደርን ስልጥ አድርጋ በልታለች ሲሉ ከአዉደዉጊያዉ ሾልከዉ የወጡ ወታደሮች ተናግረዋል።

በቋራ ላለፉት ሁለት አመታት በአየር ሀይል እና በሜካናይዝድ የታገዘ መደበኛ ጦርነት በማድረግ ዉጊያ የከፈተዉ ብልፅግና ከፍተኛ ሽንፈት አስተናግዷል።በዚህም የአገዛዙ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች የቋራን ፅንፈኛ ሀገሪቱ ባላት የጦር መሳሪያ ሁሉ ተጠቅማ ፅንፈኛዉን መምታት አልተቻለም ሲሉ ሪፖርት ማቅርባቸዉ ይታወሳል።

አራተኛ ቀኑን የየዛዉ አዉደዉጊያ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሁለተኛ መይሳዉ ካሳ ኮር የክፍለጦር አሀዶች በጋራ በመቀናጀት እየተፈለሙ መሆኑ ተገልጿል።
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ሶስት (3)ቀናትን የወሰደ የአዉደ ዉጊያ ጥልቅ ዳሰሳ:-

በእየጊዜዉ ሽንፈትን እየተከናነበ ያለዉ አረመኔዉ የአገዛዙ ስርዓት ከተለያዩ ቦታዎች በብዛት የሰበሰባቸዉን ወንበሩን ጠባቂ እረኛ ወታደሮች በመያዝ ወደ ጃዊ ወረዳ ማቡልክ ቀበሌ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ከባድ ሰባዊ እና ቁሳዊ ኪሳራን አስተናግዶ ወደ መጣበት ለመመለስ ቢሞክርም የበረሃ መብረቆቹ የጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ከበባ ዉስጥ በማስገባት እየቀጠቀጡት ይገኛሉ።

ከ 16/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ 18/02/2017 ዓ.ም ለሶስት ቀናት በተደረገ ፍልሚያ በጃዊ መተከል ቀጠናዎች የተደረጉ ዉጊያዎች:-
1. በ 16/02/2018 ዓ.ም :-
_ብሔራዊ ቀጠና ፍልዉሃ (አባሆይ ድንግራ)ተብሎ ከሚጠራዉ ቦታ ላይ በተደረገ ዉጊያ በርካታ የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።
_ጃዊ ፈንድቃ ከተማ ሞሰቢት ከተባለ የጠላት ካምፕ ላይ በጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት ማድረስ ተችሏል።
_ወርቅ ሜዳ እና ደቅ ላይ በተደረገ ዉጊያ የጠላት ሃይልን ማሽመድመድ ተችሏል።
2.በ17/02/2018 ዓ.ም:-
_ማቡልክ ቀጠና የጀግኖች አምባ ተራራ ላይ በተደረገ ከባድ ተጋድሎ አንድ ኦራል ሙሉ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። አንድ ኦራል መኪናም ከጥቅም ዉጭ ማድረግ ተችሏል።
_በተመሳሳይ ወርቅ ሜዳ እና ደቅ ላይ የወገን ጦር በወሰደዉ የሰርጎ ገብ ድንገተኛ ጥቃት በጠላት ላይ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።
3.በ18/02/2018 ዓ.ም:-
_ደረቅ ወንዝ ከተባለ ቦታ ላይ በተደረገ ትንቅንቅ በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። እንደ እብድ ዉሻ እየተክለፈለፈ የገባዉ የጠላት ኃይል እንደ ቅጠል ረግፏል።
_ይህንን የተከበበ የጠላት ኃይል ለማዉጣት ተጨማሪ ኃይል የተጨመረ ቢሆንም ቦታዉ ላይ ሳይደርስ በመንገድ ላይ ተቀጥቅጧል።
_በተመሳሳይ ጃዊ ፈንድቃ ከተማ ሞሰቢት ከተባለ የጠላት ካምፕ ላይ በድጋሜ በተደረገ ድንገተኛ ጥቃት ጠላትን መግደል እና ማብረክረክ ተችሏል።
_ወርቅ ሜዳ፣ ደቅ፣ መንደር 11፣ መንደር 12፣ መንደር 14፣ መንደር 26 ከተባሉ የፓዊ ወረዳ ቀበሌዎች ላይ በተደረጉ ድንገተኛ ተመሳሳይ የሰርጎ ገብ ጥቃት በጠላት ላይ ድል መቀዳጀት ተችሏል። በተለይ መንደር 11 ከተባለ ቦታ ላይ ሰባት(7) የሚሊሻ አባላት እስከ ትጥቃቸዉ ተማርከዋል።

ዉጊያዉ ዛሬም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የጠለት ኃይል ለመዉጣት እየተፍጨረጨረ ይገኛል።

"አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ"
        
         ፋኖ ያዕቆብ ጌታሁን
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ
በቋራ ወረዳ በበራየ 504 ኮር 96 ክፍለ ጦር ም/ል አዛዥ ኮኔርል ታከለ ቁስለኛ መሆኑ ተረጋግጧል!!!
በዝርዝር እንመለስበታለን!!
@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!
👍3
በምስራቅ ደንቢያ ወረዳ አገዛዙ የአርሶ አደር  ትጥቆችን በኃይል መንጠቁ ታወቀ።
     ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም በምስራቅ ደንቢያ ወረዳ በተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች ነዋሪዎችን ህጋዊ ጠመንጃዎች በሃይል መንጠቅ ጀምሯል።
    ብልጽግና የአማራ ፋኖን የኃይል እርምጃ መቋቋም ሲያቅተው በንጹሃን የአማራ ተወላጆች ላይ በተለይም በአርሶ አደሮች ላይ የበቀል በትሩን ማሳረፍ ከጀመረ ውሎ አድሯል።
   የበቀል በትሩ በህይወት ብቻ የሚቆም ሳይሆን በኢኮኖሚ ላይም ጭምር ነው።
   በትላንትናው እለት በሱፍቃራና በሌሎች ቀበሌዎች
   ከ15 በላይ የንጹሃን አርሶ አደሮችን ነብስ ወከፍ መሳሪያዎችን በየቤታቸው ገብቶ በመፈተሽ ዘርፈው ወስደዋል።
    በመከላከያና ሚሊሻ ዝርፊያ ተፈጸመበት አርሶ አደሩ ከፍተኛ ቁጣ ላይ መሆኑም ታውቋል። ዝርፊያው ቀጣይም በሌሎች የምስራቅ ደንቢያ ቀበሌዎችና በሌሎች በሁሉም የደንቢያ አባቢዎች እንደሚቀጥል የመረጃ ምንጫችን ያስረዳል።
    በዚህም መሠረት ሁሉም ትጥቅ ያለው የአማራ ተወላጅ በተጠንቀቅ እንዲቆም መልእክት ተላልፏል።
       በሌላ በኩል ደግሞ በአማራ ላይ ጭፍን ጥላቻ ያለበት እና አማራን ለአንዴና ለመጨረሻ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት አበክሮ እየሰራ ያለዉ የእናት ጡት ነካሹ እና ቆራጩ ብልፅግና በአማራ ምድር ላይ ያለ የሌለ ሀይሉን እያሰማራ እና እያሰፈረ ይገኛል።
   የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ፫ኛ ኮር ተቆጣጥሯቸዉ እና እያስተዳደራቸዉ ባሉ ቀጠናወች ላይ ይህ ወራሪ ሀይል ይዞት እና እንደቀበሮ ተደብቆበት ከነበረዉ ጥቁር አስፓልት እና የወረዳ ብሎም የዞን ከተሞች ወጥቶ እንቅስቃሴ ሊያደርግ ሲል የ፫ኛ ኮር አካል ክ/ጦሮች እየገደቡትና እያሽመደመዱት ይገኛሉ።በዘሪማ ወደ ጥራይና ለመግባት ሙከራ አድርጎ ጭና እና ድብ ጠለምት ክ/ጦር በተቀናጀ መልኩ መብረቃዊ ጥቃት ሲያደርሱበት ወደ ደባርቅ ከተማ ተሠልሶ ገብቷል።በዚህም የተጠና እና ቅንጅታዊ የ2ቱ ክ/ጦር ሰራዊት በአደረሱበት ከፍተኛ በትር መጠነ ሰፊ ሙትና ቁስለኛ አስተናግዶ ተመልሷል።በጭና በኩል እንቅስቃሴ ያደረገዉ ገዳይ ሰራዊት አያሌዉ ብሩ ክ/ጦር በአደረሰበት ከፍተኛ ምት አፍሮና ተሸማቆ ተመልሶ ወደ ወቀን እንዲገባ ተድርጎ እና ተገዷል።
    ሌላዉ ገዳዩ እና አራጁ ስርአት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲል የፋኖ ጭንብል ለባሾችን በየቀጠናዉ  በማሰማራት ህዝብን
     በማገት
     በመዝረፍ
     በመግደል  እና በማሰር ፋኖ ሰራቸዉ በማለት ፋኖን ከህዝብ ለመነጠል ታላቅ ጥረት እያደረገ ነዉ።ይህን እኮይ ሴራቸዉን የነቃባቸዉ የአማራ የቁርጥ ቀን አናብስቶች ማፈን እና እርምጃ መዉሰድ ሲጀምር የፋኖ ትግል አላማ የሌለዉ መሆኑን ተገንዝበን እጅ ሰጥተናል ብሎ በገዳዩ ስርአት የሚዲያ መስኮት በመዉጣት መግለጫ ሲሰጡ ተመልክተናል።
     ታዲያ ገዳዩ ማን ነዉ?እጅ የሰጠዉ ማን ነዉ?
ፋኖ ወይስ ጡት ቆራጩ ስርአት።
         
         ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
         አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
          ጥቅምት 22/2018ዓ.ም
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር
ጣና ገላውዲዎስ ክ/ጦር
ጥቅምት 22/2018

                   የአገዛዙ አራዊት ሰራዊት መነሸውን ሐሙሲት ከተማ በማድረግ ወደ ወረታና ደብረ ታቦር ከተማ እየተንቀሳቀሰ እያለ ጉማራ ከተማ ሢደርሥ በጣና ገላውዴዎሥ ክፍለ ጦር አብራከ አናብስቶች ጣና ብርጌድ እና አምበሶ ብርጌድ በጥምረት ከቀኑ 6:00-7:00 በተፈጸመ ድንገተኛና ፈጣን የማጥቃት አውደ ውጊያ  ጉማራ ላይ የነበረው ጭራቅ ታጣቂ ቡድን ከሐሙሲት የመጣው ኃይል እግሬ አውጭኝ ሲል ከተማዋን ለቅቆ ፈርጥጧል። በዚህ ያልታቀደ ውጊያ ጠላት አሥከሬኑን ሁሉ ትቶ ፈርጥጧል።

              አምበሶና ጣና ብርጌድ ጉማራ ላይ ጠላትን በየአቅጣጫው ሲበታትኑት የጣና ብርጌድ አካል የሆነችው ''እሸት ሻለቃ'' ደግሞ ሐሙሲት ከተማ በመግባት ተጨማሪ የአገዛዙ ታጣቂ ቡድን ወደ ጉማራ እንዳይንቀሳቀስ አድርጋዋለች። እሸት ሻለቃ ወደከተማዋ የገባው በአርሴማ በኩል ሲሆን አርሴማ ላይ የነበረውን የጠላት ሀይል ድንገተኛ ጥቃት በመክፈት መድረሻ አሳጥተዋለች።
     ድላችን በተባበረ ክንዳችን!!!
አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ!!
ከአፋብኃ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ
ጥቅምት 22/2018ዓ.ም

በቁርጠኛ ተጋድሎ እንጅ ገዳይን በመለማመጥ ነፃ የወጣ ህዝብ በዓለም ላይ የለም!!!

(በአርሲ ዞን በክርስቲያን ወገኖች ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ከአፋብኃ የተሰጠ መግለጫ)
"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
በአርሲ ዞን በጉና፣ በመርቲ፣ በሸርካ እና በሆሎንቆ ዋቢ ወረዳዎች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች እና ካህናት በተለይም አማራወች ላይ ላይ ሲፈፀም የቆዬው ግድያ እና ስቃይ እጅጉን ተባብሶ መቀጠሉን ተገንዝበናል።

የአማራ ፋኖን ወደ ጫካ የገፋው ዋናው ምክንያት አገዛዙ በአማራ ህዝብ እና በቤተ እምነቶች ላይ የሚፈፅመውን መዋቅራዊ ጥቃት እንዲያቆም በተደጋጋሚ በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያችዎችን ሲጠይቅ አረመኔው የአብይ አህመድ አገዛዝ ይህንን ጥያቄውን ከመስማት ይልቅ በጩኸት በመመሰል ወደ ሙሉ ዘር ማጥፋት ጦርነት በመግባቱ እንደሆነ መላው ህዝባችን የሚውቀው ነው፡፡

ይህ መዋቅራዊ ጥቃት የአብይ አህመድ አገዛዝ ወደ ስልጣን ከወጣበት ግዜ ጀምሮ እጅጉን ተባብሶ በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍል በካህናት እና መሻይኮች፣ በኦርቶዶክስ እና በእስልምና ምዕመናን ላይ በግልፅ እና በስውር ጭፍጨፋ ሲፈፅም ከመቆዬቱ ባሻገር በአርሲ አካባቢ የተፈፀመው ማንነት ተኮር ጭፍጨፋም የዚሁ ነፀብራቅ መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው።

ጥቃቱን ይበልጥ አስከፊ የሚያደርገው የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት ያለበት አገዛዝ ለጨፍጫፊዎች መሳሪያ ማደልን ጨምሮ በቀጥታ በግድያዎች ላይ እየተሳተፈ የሚፈፅመው መሆኑ ነው፡፡ ይህ ተግባርም አገዛዙ የአማራን ህዝብ እና ቤተ-እምነቶቹን በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ማጥፋት የእቅዱ አካል መሆኑን በቂ ማሳያ ነው።

አገዛዙ እነዚህን እና መሰል ድርጊቶች እየፈፀመ ያለው የቤተ ክርስቲያኗን መዋቅር በቁጥጥር ስር በማስገባት ጭምር በመሆኑ ኃላፊነት ያለባቸው መንፈሳዊ አባቶች አገዛዙ ድርጊቱን እንዲያቆምና እንዲያስቆም በቂ ትግል ማድረግ ቀርቶ ጥቃቱን ለማውገዝ እንኳን ዳተኝነት እንዲታይባቸው ምክንያት ሆኗል፡፡

የጥቃቱ ሰለባዎችን ማንነት የሚጋራው ህዝብም ሆነ ሌላው ኢትዮጵያዊ የጥፋት ተልዕኮ ይዞ የተነሳውን አገዛዝ ማስወገድ ላይ ከማተኮር ይልቅ ከገዳይ ፍትህን የመናፈቅ አደገኛ አስተሳሰብን በመሸከም ዛሬም እንደ ትላንቱ ሻማ በማብራት እና ፍትህ በመለመን ሞቱን የሚጠባበቅ መሆኑ መጭውን ግዜ አስከፊ ያደርገዋል፡፡

በዝምታ እያየው ያለው ሁሉ የአገዛዙ የጥፋት እቅድ እንዲቀጥል ድጋፍ እያደረግለት መሆኑም መታወቅ አለበት። በሰው ልጆች እልቂት ማዘን ሰብአዊ ባህሪ ቢሆንም በቁርጠኛ ተጋድሎ እንጅ በሀዘን እና እርግማን ነፃ የወጣ ህዝብ በዓለም ላይ የለም፡፡ በመሆኑም ሀዘንና እርግማን የሚለውጠው ነገር እንደሌለ ታውቆ በከተማም ሆነ በገጠር የሚኖረው ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደ አካባቢው ነባራዊ ሁኔታ እራሱን በማደራጀት አገዛዙን በሁሉም ረገድ ታግሎ እንዲያስወግደው ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል አመራር እና ሰራዊቱ የሽብር እና የጭካኔ ተግባራት የሚቆሙት አረመኔውን የአብይ አህመድን አገዛዝ ፍትህ በመለመን ሳይሆን በሁሉም የአገራችን አካባቢዎች በአፈሙዝ በታገዘ ሁሉን ዓቀፍ ህዝባዊ እምቢተኝነት በሚደረግ ትግል ብቻ እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ ለዚህም ድርጅታችን ሲያደርግ የቆየውን ተጋድሎ አጠናክሮ በመቀጠል የዜጎቻችንን ደም የሚያፈሰውን አገዛዝ በማስወገድ ኦርቶዶክሳዊያንን ጨምሮ ለመላው ህዝብ የሰላም አየር ይመጣ ዘንድ መስዋዕትነት መክፈሉን ይቀጥላል።

በመጨረሻም በዚህ በአገዛዙ ይሁንታ በሚደረግ አሰቃቂ ኢሰብአዊ የጭካኔ ድርጊት የወደቁ ሰማዕታትን ነፍስ ይማር እያልን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕምናን እና ለሰማዕታቱ ቤተሰቦች መጽናናትን እንመኛለን፡፡

ሕልውናችን በተባበረ ክንዳችን
አፋብኃ👊