ግሎባል ፋኖ ሚዲያ /ግፋሚ/GFM
429 subscribers
808 photos
104 videos
6 files
1.35K links
አማራ በዚህ ልክ ሲጨፈጨፍ ማየት ያማል። ይህን ለማስቆም የበኩላችን መረጃ በመስጠትና ማሰራጨት ተገቢ ነው
Download Telegram
በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።

በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉና ወረዳ በሚገኘ ኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን መገዳላቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ማእከል ዘገባ አመልክቷል።

በቀበሌው የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን ከለሊቱ 6:00 ሰዓት አካባቢ በዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ14 አጥቢያ  ከተኙበት ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን ስድስቱ ከመገደላቸው ከአንድ ቀን በፊት ቀድመው ታፍነው ተወስደው ነበር ተብሏል።

የተገደሉት ምእመናን የዕድሜ ክልላቸው ከ2 ዓመት ጀምሮ እስከ 76 ዓመት አዛውንት እንደሚገኙበት መረጃው ይገልጻል።

በተጨማሪም ሁለት ሰዎች በጥቃቱ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ለተሻለ ሕክምና ወደ አቦምሳ  ከተማ  ሪፈር መሄዳቸውን በመረጃው ተያይዞ ተነግሯል፡፡

ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በቀበሌው ውስጥ የሚኖሩ 8 ኦርቶዶክሳውያን ሌሊት ላይ ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውም በዘገባው ተወስቷል። 

ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ 6ቱ በነገሌ በዓለወልድ ቤተ ክርስቲያን፣አንድ ደግሞ በሞዬ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እና ቀሪ ሟቾች ባሉበት አካባቢያቸው ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙ ተገልጿል።

በመረጃው እንደተመላከተው በቀበሌው በቀጣይ የባሰ ችግር እንዳይፈጠር በሚል ከፍተኛ ስጋት መኖሩ የተገለፀ ሲሆን የቤተ ክርስቲያን ፣ የምዕመናንና የንጹሃን ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ ሰዋዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ተጠይቋል። 

በሌላ ዜና
አሳዛኝ ዜና

በአማራ ላይ የሚፈፀመው ግፍ እና መከራ መገደል መታረ*ድ አሁንም እደቀጠለ ሲሆን በኦሮሚያ ወስጥ ናኖ ጃዊ ቀበሌ ጉና ወረዳ አርሲ አርባ ጉጉ ክፍለ ሀገር በቀን 13 ለቀን 14 አጥቢያ ለሊት የታረዱ አማራዎች የስም ዝርዝር ይፋ ሆኗል፦

1) ሻውል ይፍሩ ከነ ባለቤቱ
2) እታገኘው አስፍው ጋር 
3) መስቲካ ማሞ
4) አበበ አስፋው 
5) ሰርካለም ተስፋዬ
6) ፋኑሴ ዘውዴ ከ 3 ልጆቻቸው ጋር 
7) የሺ መልስ ከልጇጋር 
8) ሽብር ሸዋንግዛው
9) ሄለን ሙላቱ
10) ሚኪ ሙላቱ ሲሆኑ 2 የ4 አመት እና የ9 አመት ልጆችም ቆስለው ሕክምና ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

 @አለማቀፍ ፋኖ ሚዲያ
በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ሄላ ዘባባ ቀበሌ ከሚኖሩ ኦርቶዶክሳዊያን ሦስቱ መገደላቸው እና አራቱ መታገታቸው ተሰማ፡፡

በወረዳው ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ115 በላይ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውና ከ16 በላይ ዐብያተ ክርስቲያናት መዘጋታቸው ታውቋል።

MK TV ጥቅምት 19 2018 ዓ.ም

ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በደረሰው መረጃ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከለሊቱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ሄላ ዘባባ ቀበሌ አርሴማ አጥቢያ የሚኖሩ ምእመናን በታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሦስቱ መገደላቸው እና አራቱ ደግሞ መታገታቸው ተገልጿል።

ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ የአንዱ ሟች አባትና ወንድም መታገታቸው በመረጃው የተገለጸ ሲሆን ታፍነው የተወሰዱት ምእመናን ስለሚገኙበት ሁኔታ አይታወቅም ተብሏል፡፡

በመረጃው እንደተነገረው የሞቱት ሦስቱ ኦርቶዶክሳውያን በትላንትናው ዕለት ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡

ላለፉት ሁለት ዓመታት ማለትም ከ2016 ዓ.ም መስከረም 02 ጀምሮ እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ ያለማቋረጥ በወረዳው ከ115 በላይ ምእመናን የተገደሉ ሲሆን 27 ኦርቶዶክሳዉያን ደግሞ አሁንም ድረስ ታግተው ያሉበት እንደማይታወቅ ነዋሪዎቹ ለጣቢያችን ገልጸዋል።

በግድያ ያላበቃው መከራና ስቃይ በሽርካ ወረዳ ብቻ በዘጠኝ ቀበሌዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ኦርቶዶክሳዉያን መፈናቀላቸውንም በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በወረዳው ካሉ 37 አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ከ16 በላይ የሆኑት አገልግሎት የማይሰጡ መሆናቸውንና ከእነዚህም መካከል 3ቱ መሉ በሙሉ መዘረፋቸውን የደረሰን መረጃ ያመላክታል፡፡

የኦርቶዶክሳዉያን መገደል እንዲቆም ለሀገረ ስብከቱና ለመንግሥት አካላት በተደጋጋሚ ሪፖርት ቢደረግም ምላሽ እያገኙ አለመሆናቸውን ያነሱት ነዋሪዎቹ በዚህም አካባቢው በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ይገኛል ሲሉ ተናግርዋል፡፡

በተለይም በሀገረ ስብከት ደረጃ ለተፈናቀሉት ወገኖች ድጋፍም ሆነ ማጽናኛ ለማደረግ ጥረት ባለመደረጉ ማዘናቸውን የአካባቢው ምእመናን ገልጸዋል፡፡

እየደረሰ ያለው የሰው ሕይወት እልፈት ፣ መታገትና የንብረት ውድመት ችግር እልባት አንዲያገኝ የቅድስት ቤተ ክርሰስቲያን እና የመንግሥት ባለድርሻ አካላት አሁንም ትኩረት ሰጥተው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
በቋራ አራተኛ ቀኑን ያስቆጠረ አዉደዉጊያ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተሰማ።

በቋራ፣በሙር፣ወንበልጌ እና የወረዳዉ መቀመጫ ገለጎ ከተማ ወጣ ባሉ አካባቢዎች ጠንከር ያለ አዉደዉጊያ ሲደረግ ሰንብቷል ሲሉ የአካባቢው ኗሪዎች መረጃዉን ለግሎባል ፋኖ ሚዲያ ተናግረዋል።

ፋኖ እና የአገዛዙ ጥምር ጦር እያደረጉት ባለዉ አዉደዉጊያ በርካታ ወታደሮች የተገደሉ ሲሆን ገደል የገቡ ስለመኖራቸዉም አያይዘዉ ተናግረዋል።

አራተኛ ቀኑን ያስቆጠረዉ አዉደዉጊያ በጨበጣ፣በመካናይድ እንዲሁም በደፈጣ የተደረገ ሲሆን ፋኖ ድል ቀንቶታል ተብሏል።ጠንካራ የፋኖ ሰራዊት እንዳለ የሚነገርለት ቋራ እና አካባቢው ላለፉት ሁለት አመታት በርካታ የአገዛዙን ብልፅግና ጦር ማፈራረሱ ይታወሳል።

ከሁለት ክፍለጦር በላይ የሚሆን የብልፅግና ጦር በካሳ ምድር ቋራ ስለመደምሰሱ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ሳይቀር ምስክርነታቸዉን ሰተዋል።ከሰሞኑም ቋራ የአብይ አህመድ ወታደርን ስልጥ አድርጋ በልታለች ሲሉ ከአዉደዉጊያዉ ሾልከዉ የወጡ ወታደሮች ተናግረዋል።

በቋራ ላለፉት ሁለት አመታት በአየር ሀይል እና በሜካናይዝድ የታገዘ መደበኛ ጦርነት በማድረግ ዉጊያ የከፈተዉ ብልፅግና ከፍተኛ ሽንፈት አስተናግዷል።በዚህም የአገዛዙ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች የቋራን ፅንፈኛ ሀገሪቱ ባላት የጦር መሳሪያ ሁሉ ተጠቅማ ፅንፈኛዉን መምታት አልተቻለም ሲሉ ሪፖርት ማቅርባቸዉ ይታወሳል።

አራተኛ ቀኑን የየዛዉ አዉደዉጊያ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሁለተኛ መይሳዉ ካሳ ኮር የክፍለጦር አሀዶች በጋራ በመቀናጀት እየተፈለሙ መሆኑ ተገልጿል።
አፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ሶስት (3)ቀናትን የወሰደ የአዉደ ዉጊያ ጥልቅ ዳሰሳ:-

በእየጊዜዉ ሽንፈትን እየተከናነበ ያለዉ አረመኔዉ የአገዛዙ ስርዓት ከተለያዩ ቦታዎች በብዛት የሰበሰባቸዉን ወንበሩን ጠባቂ እረኛ ወታደሮች በመያዝ ወደ ጃዊ ወረዳ ማቡልክ ቀበሌ የተንቀሳቀሰ ቢሆንም ከባድ ሰባዊ እና ቁሳዊ ኪሳራን አስተናግዶ ወደ መጣበት ለመመለስ ቢሞክርም የበረሃ መብረቆቹ የጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ከበባ ዉስጥ በማስገባት እየቀጠቀጡት ይገኛሉ።

ከ 16/02/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ 18/02/2017 ዓ.ም ለሶስት ቀናት በተደረገ ፍልሚያ በጃዊ መተከል ቀጠናዎች የተደረጉ ዉጊያዎች:-
1. በ 16/02/2018 ዓ.ም :-
_ብሔራዊ ቀጠና ፍልዉሃ (አባሆይ ድንግራ)ተብሎ ከሚጠራዉ ቦታ ላይ በተደረገ ዉጊያ በርካታ የጠላት ሀይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል።
_ጃዊ ፈንድቃ ከተማ ሞሰቢት ከተባለ የጠላት ካምፕ ላይ በጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት ማድረስ ተችሏል።
_ወርቅ ሜዳ እና ደቅ ላይ በተደረገ ዉጊያ የጠላት ሃይልን ማሽመድመድ ተችሏል።
2.በ17/02/2018 ዓ.ም:-
_ማቡልክ ቀጠና የጀግኖች አምባ ተራራ ላይ በተደረገ ከባድ ተጋድሎ አንድ ኦራል ሙሉ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። አንድ ኦራል መኪናም ከጥቅም ዉጭ ማድረግ ተችሏል።
_በተመሳሳይ ወርቅ ሜዳ እና ደቅ ላይ የወገን ጦር በወሰደዉ የሰርጎ ገብ ድንገተኛ ጥቃት በጠላት ላይ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።
3.በ18/02/2018 ዓ.ም:-
_ደረቅ ወንዝ ከተባለ ቦታ ላይ በተደረገ ትንቅንቅ በርካታ የጠላት ኃይል ሙትና ቁስለኛ ማድረግ ተችሏል። እንደ እብድ ዉሻ እየተክለፈለፈ የገባዉ የጠላት ኃይል እንደ ቅጠል ረግፏል።
_ይህንን የተከበበ የጠላት ኃይል ለማዉጣት ተጨማሪ ኃይል የተጨመረ ቢሆንም ቦታዉ ላይ ሳይደርስ በመንገድ ላይ ተቀጥቅጧል።
_በተመሳሳይ ጃዊ ፈንድቃ ከተማ ሞሰቢት ከተባለ የጠላት ካምፕ ላይ በድጋሜ በተደረገ ድንገተኛ ጥቃት ጠላትን መግደል እና ማብረክረክ ተችሏል።
_ወርቅ ሜዳ፣ ደቅ፣ መንደር 11፣ መንደር 12፣ መንደር 14፣ መንደር 26 ከተባሉ የፓዊ ወረዳ ቀበሌዎች ላይ በተደረጉ ድንገተኛ ተመሳሳይ የሰርጎ ገብ ጥቃት በጠላት ላይ ድል መቀዳጀት ተችሏል። በተለይ መንደር 11 ከተባለ ቦታ ላይ ሰባት(7) የሚሊሻ አባላት እስከ ትጥቃቸዉ ተማርከዋል።

ዉጊያዉ ዛሬም ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን የጠለት ኃይል ለመዉጣት እየተፍጨረጨረ ይገኛል።

"አዲስ ትዉልድ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ተስፋ"
        
         ፋኖ ያዕቆብ ጌታሁን
የአፋብኃ ቴዎድሮስ ዕዝ ጃዊ መተከል 4ኛ ክ/ጦር ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ
በቋራ ወረዳ በበራየ 504 ኮር 96 ክፍለ ጦር ም/ል አዛዥ ኮኔርል ታከለ ቁስለኛ መሆኑ ተረጋግጧል!!!
በዝርዝር እንመለስበታለን!!
@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!
👍3
በምስራቅ ደንቢያ ወረዳ አገዛዙ የአርሶ አደር  ትጥቆችን በኃይል መንጠቁ ታወቀ።
     ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም በምስራቅ ደንቢያ ወረዳ በተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች ነዋሪዎችን ህጋዊ ጠመንጃዎች በሃይል መንጠቅ ጀምሯል።
    ብልጽግና የአማራ ፋኖን የኃይል እርምጃ መቋቋም ሲያቅተው በንጹሃን የአማራ ተወላጆች ላይ በተለይም በአርሶ አደሮች ላይ የበቀል በትሩን ማሳረፍ ከጀመረ ውሎ አድሯል።
   የበቀል በትሩ በህይወት ብቻ የሚቆም ሳይሆን በኢኮኖሚ ላይም ጭምር ነው።
   በትላንትናው እለት በሱፍቃራና በሌሎች ቀበሌዎች
   ከ15 በላይ የንጹሃን አርሶ አደሮችን ነብስ ወከፍ መሳሪያዎችን በየቤታቸው ገብቶ በመፈተሽ ዘርፈው ወስደዋል።
    በመከላከያና ሚሊሻ ዝርፊያ ተፈጸመበት አርሶ አደሩ ከፍተኛ ቁጣ ላይ መሆኑም ታውቋል። ዝርፊያው ቀጣይም በሌሎች የምስራቅ ደንቢያ ቀበሌዎችና በሌሎች በሁሉም የደንቢያ አባቢዎች እንደሚቀጥል የመረጃ ምንጫችን ያስረዳል።
    በዚህም መሠረት ሁሉም ትጥቅ ያለው የአማራ ተወላጅ በተጠንቀቅ እንዲቆም መልእክት ተላልፏል።
       በሌላ በኩል ደግሞ በአማራ ላይ ጭፍን ጥላቻ ያለበት እና አማራን ለአንዴና ለመጨረሻ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት አበክሮ እየሰራ ያለዉ የእናት ጡት ነካሹ እና ቆራጩ ብልፅግና በአማራ ምድር ላይ ያለ የሌለ ሀይሉን እያሰማራ እና እያሰፈረ ይገኛል።
   የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ፫ኛ ኮር ተቆጣጥሯቸዉ እና እያስተዳደራቸዉ ባሉ ቀጠናወች ላይ ይህ ወራሪ ሀይል ይዞት እና እንደቀበሮ ተደብቆበት ከነበረዉ ጥቁር አስፓልት እና የወረዳ ብሎም የዞን ከተሞች ወጥቶ እንቅስቃሴ ሊያደርግ ሲል የ፫ኛ ኮር አካል ክ/ጦሮች እየገደቡትና እያሽመደመዱት ይገኛሉ።በዘሪማ ወደ ጥራይና ለመግባት ሙከራ አድርጎ ጭና እና ድብ ጠለምት ክ/ጦር በተቀናጀ መልኩ መብረቃዊ ጥቃት ሲያደርሱበት ወደ ደባርቅ ከተማ ተሠልሶ ገብቷል።በዚህም የተጠና እና ቅንጅታዊ የ2ቱ ክ/ጦር ሰራዊት በአደረሱበት ከፍተኛ በትር መጠነ ሰፊ ሙትና ቁስለኛ አስተናግዶ ተመልሷል።በጭና በኩል እንቅስቃሴ ያደረገዉ ገዳይ ሰራዊት አያሌዉ ብሩ ክ/ጦር በአደረሰበት ከፍተኛ ምት አፍሮና ተሸማቆ ተመልሶ ወደ ወቀን እንዲገባ ተድርጎ እና ተገዷል።
    ሌላዉ ገዳዩ እና አራጁ ስርአት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲል የፋኖ ጭንብል ለባሾችን በየቀጠናዉ  በማሰማራት ህዝብን
     በማገት
     በመዝረፍ
     በመግደል  እና በማሰር ፋኖ ሰራቸዉ በማለት ፋኖን ከህዝብ ለመነጠል ታላቅ ጥረት እያደረገ ነዉ።ይህን እኮይ ሴራቸዉን የነቃባቸዉ የአማራ የቁርጥ ቀን አናብስቶች ማፈን እና እርምጃ መዉሰድ ሲጀምር የፋኖ ትግል አላማ የሌለዉ መሆኑን ተገንዝበን እጅ ሰጥተናል ብሎ በገዳዩ ስርአት የሚዲያ መስኮት በመዉጣት መግለጫ ሲሰጡ ተመልክተናል።
     ታዲያ ገዳዩ ማን ነዉ?እጅ የሰጠዉ ማን ነዉ?
ፋኖ ወይስ ጡት ቆራጩ ስርአት።
         
         ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን።
         አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ
          ጥቅምት 22/2018ዓ.ም