ግሎባል ፋኖ ሚዲያ /ግፋሚ/GFM
429 subscribers
808 photos
104 videos
6 files
1.35K links
አማራ በዚህ ልክ ሲጨፈጨፍ ማየት ያማል። ይህን ለማስቆም የበኩላችን መረጃ በመስጠትና ማሰራጨት ተገቢ ነው
Download Telegram
ብልፅግና በአዲስአበባ ከተማ አፈሳ ማካሄዱ ተገለፀ።

አገዛዙ በአዲስ አበባ ከተማ የወጣቶችን አፈሳ አጠናክሮ ቀጥሏል ሲሉ ኗሪዎች ተናገሩ።

ዛሬ ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በአዲስአበባ ከተማ በርካታ ወጣቶች ታፍሰዉ ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መወሰዳቸዉ ታዉቋል።

በ11 ክፍለከተማ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ታፍሰዉ በሶስት መሰረታዊ ዉትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መወሰዳቸዉን ከአዲስአበባ  ከተማ ኗሪዎች ለግሎባል ፋኖ ሚዲያ ተናግረዋል።

በተለይ እድሚያቸው ከ18 አመት በታች የሆኑ ታዳጊ ወጣቶች ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለዉ ስለመወሰዳቸዉ ጭምር ኗሪዎች ተናግረዋል።አፈሳዉ በናዝሬት፣በደብረዘይት፣በሞጆ፣በሀዋሳ፣በይርጋለም፣በኦሮሚያ ክልል በሁሉም አካባቢዎች እንዲሁም በጋሞ እና ወላይታ ብዛት ያላቸዉ ወጣቶች ታፍስዉ በእየ አዳራሹ ታጉረዉ ይገኛሉ።

በተለይ በኦሮሚያ ክልል የሚታፈሱ ወጣቶች ቁጥር ከወትሮው በተለየ መልኩ መጨመሩ የተገለፀ ሲሆን የብልግና ኦህዴድ ብልፅግና አገዛዝ የኦሮሞን ስልጣን እንጠብቅ እንዲሁም የፕሮቴስታንት እምነትን ሊያጠፉ ነዉ በሚል ስብከት ወጣቱ እየታፈሰ ነዉ ተብሏል።

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!!
የፋኖ ድምፅ!!!
👍1
ከዓለም አቀፍ የአማራ ግብረኃይል የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ 
 
የአረመኔው የአብይ አህመድ ፋሽስት ሰራዊት በወጣት አርበኛ ሴቶቻችን ላይ የፈጸመውን የጭካኔ ጥግ መላው ዓለም ሊያውቀውና ሊያወግዘው ይገባል!!!

ፋኒት በዓለም ዋሴ : ፋኒት ትግስት ወዳጅ ይመርና ፋኒት መቅደስ ተስፋዬ የፋኖ አርበኞች የብልፅግና ሥልጣን አስጠባቂ ሰራዊትን ቁስለኛና ምርኮኛን በቅድሚያ የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ አድርገው በምህረት ወደ የቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ አድርገዋል፡ እያደረጉም ነው። ምርኮኞች ቁጥራቸው በርከት ሲሉም ለዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ያስረክባሉ። የታወቀውን የዓለም አቀፍ ምርኮኛ አያያዝን ህግ ያከብራሉ። ይህ በፋኖ ዘንድ የተለመደ አሰራር ነው።

የ19 ዓመትዋ ወጣት በዓለም ዋሴ እንደማንኛውም ወጣት የራሷን ኑሮ አመቻችታ ተመሳስላ አስመስላ መኖር ትችል ነበር፤ ሆኖም ግን በአማራው ሕዝብ ላይ የሚደርሰው ሰቃይና መከራ፣ ሰደትና መፈናቀል፣ መገደልና መጨፍጨፍ አንገብግቧት ይህን አረመኔ የአብይ አህመድ ፋሽስት አገዛዝን ለመፋለምና ነጻነቷን ለማስከበር ቆርጣ ወስና የህልውና
ትግል ከሚያደርገው ፋኖ ጋር በአርበኝነት ተቀላቀለች። በፋኖም ውስጥ የመደበኛና የኮማንዶ ስልጠናዎችን ጨርሳ የአፋብኃ ቲዎድሮስ እዝ 5ኛ ክፍለ ጦር አባል ሆና ከሌሎች ጓዶቿ ጋር ለቅኝት ሰራ ተሰማርታ እያለ ድንገት በአረመኔው የአብይ አገዛዝ ወታደሮች ቀለበት ውስጥ ወደቀች። ጥቂት አርበኞች ሆነው የሚችሉትን ያህል ቢዋጉም የአብይ አህመድ ወታደሮች በርካታ ነበሩና ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ/ም በጥይት ቆስላ ተማረከች። 
የአረመኔው አብይ አህመድ አገዛዝ ወታደሮች ግን በጥላቻና በሰለጠኑበት የሃሰት ትርክት ስለሚመሩ ይህችን የ19 ዓመት ወጣት ፋኒት በዓለም ዋሴ ቆስላ ስትማረክ የፈጸሙባት ተግባር ግን ተሰምቶና ታይቶ የማያውቅ አስቃቂ የጭካኔ ጥግ ነው። ቁስለኛዋን ምርኮኛ ልብሷን አወላልቀው “አማራ” የሚለውን እጇ ላይ የተነቀሰችውን ንቅሳት በጩቤ ገፈው፤ ሁለቱንም ጡቶቿን በሳንጃ ቆራርጠው፣ መላ ሰውነቷን በሳንጃ ስለት ወጋግተው በኢስብዓዊነትና እጅግ በሚዘገንን ሁኔታ አስከሬኗን ማንኩሳ ከተማ መሀል አስፋልት ላይ ጥለው የአረመኔነታቸውን ጥግ ለሕዝብ አሳይተዋል። ይህ ነው የአብይ አህመድ ሰራዊት መለያ!

ከዚያ በፊት መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ/ም በወገራ የበላይ ዘለቀ እዝ 3ኛ ኮር አምባራስ ክፍለ ጦር አባል የሆነችው አርበኛ ፋኒት መቅደስ ተስፋዬን በመግደል ሬሳዋን በመኪና በመጎተት አስፋልት ላይ ጥለው እንዳትቀበርም አስከሬኗን በጸሀይና በዝናብ እንዲበላሽ በማድረግ ዘግናኝ ድርጊት በመፈጸም የአብይ ሰራዊት የተካነበትን የኢሰብዓዊ ባሕሪውን ለሕዝብ አሳይቷል።

ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ/ም ደግሞ በራያ በጮቢ በር ግንባር ተጋድሎ እያደረገች የተሰዋችው የምሥራቅ አማራ ኮር አንድ
ሀውጃኖ ክፍለጦር 3ኛ ሻለቃ አባል የሆነችው አርበኛ ፋኒት ትግሥት ወዳጅ ይመር ከአስከሬኗ ላይ አንደኛውን ጡቷን ቆርጦ እርቃኗን ሜዳ ላይ ጥሎ ሰቅጣጭና አረመኔያው ድርጊት የፈጸመው በጥላቻ የተሞላው የአብይ አህመድ ሰራዊት ነው።

አማራ ሆኖ በአማራው ላይ ይህንን የመሰለ የጭካኔ ተግባር ተፈጽሞ እያየንና እየሰማን ልባችንን አደንድነን መቀመጥ አለብን ወይ? ብለን መጠየቅና የህልውና ትግሉን በውስጥም በውጭም ያለን ሁሉ መርዳት ካልቻልን በእያንዳንዳችን ቤተሰብ ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ሊፈጸም እንደሚችል መገንዘብና ሁላችንም በጭንቀትና በተሰፋ መቁረጥ ከምንቀመጥ በምንችለው አቅምና መንገድ በተግባር የህልውና ትግሉን መደገፍና መርዳት ይኖርብናል። ይህን አስከፊ የጭካኔ ወንጀልንም መላው ዓለም እንዲያወቀውና እንዲያወግዘው ለተለያዩ የዜና አውታሮች ማድረስ፣ ለዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ ለመንግስታት፣ ለኮንግረስና ለፓርላማ አባላት በዘመቻ መልክ ማሳወቅ ይኖርብናል።

በወጣት የሴት አርበኞቻችን ፋኒት በዓለም ዋሴ፣ ፋኒት መቅደስ ተስፋዬና ፋኒት ትእግሥት ወዳጅ ይመር ላይ የደረሰው አስቃቂ አረመኔያዊ ተግባር የፈጸሙት ወንጀለኞችም በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ሰራ መሰራት ይኖርበታል።

በጀግንነት የተሰዉትን የነፋኒት በዓለም ዋሴንና ጓዶቿ ምስልና ታሪክ በሁላችንም ልብ ተቀርጾ እንዲቀመጥ በየአገሩ ያለን ሁሉ የተለያዩ የፈጠራ ሰራዎች በመስራት ለምሳሌ ምስሎቻቸው ያለበትን ቲሸርት በመልበስ፣ የሻማ ምሽቶች በማዘጋጀት በስማቸው ዝግጅት በማዘጋጀትና የመሳሰሉትን ቢያንስ ማከናወን ይኖርብናል።

የዚህ ፋሽስት ሰራዊት መሪ የሆነው የአብይ አህመድ አገዛዝን ዘመን እንዲያበቃ የማያቆም ዘመቻ መካሄድ ይኖርበታል። በአገርም ሆነ በውጭው ዓለም የሕዝብን ትኩረት ወደ ሌላ አቅጣጫ በማስቀየር የዘረኛውና አረመኔው አብይ አህመድ አገዛዝን እድሜ ለማስቀጠል ፕሮፓጋንዳ በመስራት የሚዳክሩ የሚዲያ ክፍሎች፣ የኢንቨስትመንት ደላላዎች፣ አገር
ለአረብ እየተሸጠች “አዲስ አበባ አሽበረቀች አማረች” እያሉ ከንቱ ስብከታቸውን የሚያሰሙና በውስጥም በውጭም ሕዝብን ማዘናጊያ በርካታ የመዝናኛ እና የተለያዩ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ሀገር ሰላም የሆነች ይመስል ሕዝብን ዳንኪራ የሚያስረግጡና ገንዘቡን በአልባሌና ጭፈራ እንዲያባክን ሰራ የሚሰሩ ግለሰቦችም ሆኑ ተላላኪዎች እንዲሁም ማንኛውም ሰው ከዚህ የሆዳምና የባንዳ ሰራቸው እንዲታቀቡ እንመክራለን።

ሀብት ለመሰብሰብ በመሯሯጥና የጨለማና የሀዘን ዘመንን በጭፈራና በደስታ ለማሳለፍ የሚዳክሩትን ሁሉ እግዚአበሔር ልቦና ይስጣችሁ፣ ነገ ይህች አገር ሰትጠፋ
ተመልሳችሁ አገር አልባና ጨለማ ውስጥ የምትወድቁ መሆናችሁን እንድታወቁት፤ በታሪክም በሕዝብም ተወቃሽና ተጠያቂ መሆናችሁንም አትዘንጉ እንላለን!

የነፋኒት በዓለም ዋሴ ጀግንነት አርዓያ ሊሆነን፣ የተፈጸመባቸው አስቃቂ ድርጊትና እንዲዘገንነን እንዲቆጠቁጠን ነግ ተነግወዲያ በሌሎችም ጀግና እህቶችና ወንድሞቻችን ላይም እንዳይደገም ማድረግ የሁላችንም የህሊና ግዴታ ነውና በየከተማው በተለያዩ ምክንያቶች ተዳክመን፣ ፈዘንና ደንዝዘን በተለያዩ ምክንያቶች ተስፋ ቆርጠን የቆየን ሁሉ፤ የባሰ
እየመጣ ነውና ወጣት አርበኞቻችንን ወገኖቻችንን ተጋድሎ ስቃይና ግፍን በማስታወስ እንደገና እንነሳ! እንበረታታ!

እግዚአብሄር ለተሰዉት አርበኞቻችን ቤተሰቦችና ጓዶች መጽናናቱን ይስጥልን። ፈጣሪ ነፍሳቸውን በገነት ያኑርልን። 
እግዚአብሔር የአማራውን የህልውና ትግል ይባርክ! 
ድል ለአማራ የህልውና ትግል! 
የአማራው ህልውና የኢትዮጵያም ህልውና ነው!!!
የአረመኔው አብይ አህመድ አገዛዝ ያብቃ! ወንጀለኞችም ለፍርድ ይቅረቡ!!!

ዓለም አቀፍ የአምራ ግብረኃይል (ዓ/አ/አ/ግ/ኃ)
ዓለም አቀፍ የአምሓራ ግብረኃይል (ዓ/አ/አ/ግ/ኃ)  / International Amhara Task Force (IATF)

Official Call to Action: United Global Mobilization for Amhara Advocacy 
IN OPPOSITION TO MUTILIZATION OF FEMALES and DRONE አጥታችክስ

Dear Leaders and Representatives of Amhara Associations and Organisations, The International Amhara Task Force (IATF) extends its heartfelt greetings and deep appreciation for your continued commitment to the Amhara people and our shared cause of justice, peace, and Survivals.

At this critical time, our collective voice is needed more than ever. The global Amhara community is facing immense humanitarian and human rights challenges, and silence is no longer an option. LTo strengthen our advocacy and amplify our global impact, the IATF is calling upon all Amhara associations, unions, community organizations, and advocacy networks to unite in a coordinated international rally and digital campaign.

Global Campaign Period
From November 1 until November 30, 2025
During this one-month global action, IATF calls for unified participation across all Amhara organizations and allies worldwide.

Objectives of the Mobilization

1. To stop drone attacks and all forms of violence against civilians in the Amhara region.
2. To raise global awareness about the ongoing atrocities and humanitarian crisis facing the Amhara people.
3. To draw international attention to recent crimes against Amhara women and civilians, demanding an  independent international investigation and accountability.
4. To demonstrate unified Amhara solidarity across continents in defence of justice and human dignity.
5. To engage international media, human rights institutions, and policymakers to act against hate-driven  policies and impunity.

Planned Global Activities

• Worldwide Rallies: Local chapters are encouraged to organize peaceful rallies in their respective cities during  the campaign period.

• Digital Advocacy: Participate in coordinated Twitter campaigns, email outreach, and global petitions initiated and organized by IATF.

• Media and Outreach: Amplify the Amhara voice through public statements, coordinated press 
releases, and engagement with local and international media.

Your Role

We call upon your association to:
• Mobilize your members and partners to actively participate in the global campaign from November 1 to November 30.

• Coordinate locally with IATF liaisons for unified messaging, scheduling, and logistics.

• Share updates, photos, and media coverage from your activities to strengthen the global narrative

Next Steps
 
Please confirm your participation and designate a contact person from your organisation by replying to this  email: iatf@amharataskforce.org
hashtags, visuals, and petition links — will be shared upon confirmation.

Together, let us stand firm in defence of our people and speak with one voice for justice, dignity, and  survival.
👍1
በአርሲ ሀገረ ስብከት በኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።

በአርሲ ሀገረ ስብከት ጉና ወረዳ በሚገኘ ኖኖ ጃዊ ቀበሌ የሚኖሩ ኦርቶዶክሳውያን መገዳላቸውን የማኅበረ ቅዱሳን ማእከል ዘገባ አመልክቷል።

በቀበሌው የሚኖሩ 14 ኦርቶዶክሳውያን ከለሊቱ 6:00 ሰዓት አካባቢ በዕለተ ረቡዕ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለ14 አጥቢያ  ከተኙበት ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በከፈቱት ተኩስ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ሲሆን ስድስቱ ከመገደላቸው ከአንድ ቀን በፊት ቀድመው ታፍነው ተወስደው ነበር ተብሏል።

የተገደሉት ምእመናን የዕድሜ ክልላቸው ከ2 ዓመት ጀምሮ እስከ 76 ዓመት አዛውንት እንደሚገኙበት መረጃው ይገልጻል።

በተጨማሪም ሁለት ሰዎች በጥቃቱ ምክንያት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ለተሻለ ሕክምና ወደ አቦምሳ  ከተማ  ሪፈር መሄዳቸውን በመረጃው ተያይዞ ተነግሯል፡፡

ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ሁኔታ በቀበሌው ውስጥ የሚኖሩ 8 ኦርቶዶክሳውያን ሌሊት ላይ ከቤታቸው አስወጥተው የታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸውም በዘገባው ተወስቷል። 

ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ 6ቱ በነገሌ በዓለወልድ ቤተ ክርስቲያን፣አንድ ደግሞ በሞዬ ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን እና ቀሪ ሟቾች ባሉበት አካባቢያቸው ሥርዓተ ቀብራቸው መፈጸሙ ተገልጿል።

በመረጃው እንደተመላከተው በቀበሌው በቀጣይ የባሰ ችግር እንዳይፈጠር በሚል ከፍተኛ ስጋት መኖሩ የተገለፀ ሲሆን የቤተ ክርስቲያን ፣ የምዕመናንና የንጹሃን ጉዳይ ያገባኛል የሚል ሁሉ ሰዋዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ተጠይቋል። 

በሌላ ዜና
አሳዛኝ ዜና

በአማራ ላይ የሚፈፀመው ግፍ እና መከራ መገደል መታረ*ድ አሁንም እደቀጠለ ሲሆን በኦሮሚያ ወስጥ ናኖ ጃዊ ቀበሌ ጉና ወረዳ አርሲ አርባ ጉጉ ክፍለ ሀገር በቀን 13 ለቀን 14 አጥቢያ ለሊት የታረዱ አማራዎች የስም ዝርዝር ይፋ ሆኗል፦

1) ሻውል ይፍሩ ከነ ባለቤቱ
2) እታገኘው አስፍው ጋር 
3) መስቲካ ማሞ
4) አበበ አስፋው 
5) ሰርካለም ተስፋዬ
6) ፋኑሴ ዘውዴ ከ 3 ልጆቻቸው ጋር 
7) የሺ መልስ ከልጇጋር 
8) ሽብር ሸዋንግዛው
9) ሄለን ሙላቱ
10) ሚኪ ሙላቱ ሲሆኑ 2 የ4 አመት እና የ9 አመት ልጆችም ቆስለው ሕክምና ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

 @አለማቀፍ ፋኖ ሚዲያ
በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ሄላ ዘባባ ቀበሌ ከሚኖሩ ኦርቶዶክሳዊያን ሦስቱ መገደላቸው እና አራቱ መታገታቸው ተሰማ፡፡

በወረዳው ባለፉት ሁለት ዓመታት ከ115 በላይ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውና ከ16 በላይ ዐብያተ ክርስቲያናት መዘጋታቸው ታውቋል።

MK TV ጥቅምት 19 2018 ዓ.ም

ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን በደረሰው መረጃ ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከለሊቱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በምሥራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ሄላ ዘባባ ቀበሌ አርሴማ አጥቢያ የሚኖሩ ምእመናን በታጠቁ ኃይሎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሦስቱ መገደላቸው እና አራቱ ደግሞ መታገታቸው ተገልጿል።

ከተገደሉት ምእመናን ውስጥ የአንዱ ሟች አባትና ወንድም መታገታቸው በመረጃው የተገለጸ ሲሆን ታፍነው የተወሰዱት ምእመናን ስለሚገኙበት ሁኔታ አይታወቅም ተብሏል፡፡

በመረጃው እንደተነገረው የሞቱት ሦስቱ ኦርቶዶክሳውያን በትላንትናው ዕለት ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡

ላለፉት ሁለት ዓመታት ማለትም ከ2016 ዓ.ም መስከረም 02 ጀምሮ እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ ያለማቋረጥ በወረዳው ከ115 በላይ ምእመናን የተገደሉ ሲሆን 27 ኦርቶዶክሳዉያን ደግሞ አሁንም ድረስ ታግተው ያሉበት እንደማይታወቅ ነዋሪዎቹ ለጣቢያችን ገልጸዋል።

በግድያ ያላበቃው መከራና ስቃይ በሽርካ ወረዳ ብቻ በዘጠኝ ቀበሌዎች በሺዎች የሚቆጠሩ ኦርቶዶክሳዉያን መፈናቀላቸውንም በመረጃው ተጠቅሷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በወረዳው ካሉ 37 አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ከ16 በላይ የሆኑት አገልግሎት የማይሰጡ መሆናቸውንና ከእነዚህም መካከል 3ቱ መሉ በሙሉ መዘረፋቸውን የደረሰን መረጃ ያመላክታል፡፡

የኦርቶዶክሳዉያን መገደል እንዲቆም ለሀገረ ስብከቱና ለመንግሥት አካላት በተደጋጋሚ ሪፖርት ቢደረግም ምላሽ እያገኙ አለመሆናቸውን ያነሱት ነዋሪዎቹ በዚህም አካባቢው በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ይገኛል ሲሉ ተናግርዋል፡፡

በተለይም በሀገረ ስብከት ደረጃ ለተፈናቀሉት ወገኖች ድጋፍም ሆነ ማጽናኛ ለማደረግ ጥረት ባለመደረጉ ማዘናቸውን የአካባቢው ምእመናን ገልጸዋል፡፡

እየደረሰ ያለው የሰው ሕይወት እልፈት ፣ መታገትና የንብረት ውድመት ችግር እልባት አንዲያገኝ የቅድስት ቤተ ክርሰስቲያን እና የመንግሥት ባለድርሻ አካላት አሁንም ትኩረት ሰጥተው ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።