ግሎባል ፋኖ ሚዲያ /ግፋሚ/GFM
432 subscribers
808 photos
104 videos
6 files
1.35K links
አማራ በዚህ ልክ ሲጨፈጨፍ ማየት ያማል። ይህን ለማስቆም የበኩላችን መረጃ በመስጠትና ማሰራጨት ተገቢ ነው
Download Telegram
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ አንደኛ ኮር ጉና ክፍለጦር እስቴ ዴንሳ ብርጌድ በጠላት ላይ ድል ተቀደጅቷል።

በእስቴ መካነየሱስ ዳጉት እና አበርጉት መሳለሚያ በተደረገ አዉደዉጊያ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ ሌጆች የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ ሻለቃ አራት በጠላት ላይ ሰራዊት ላይ እርምጃ ተወስዷል።ድልድይ ለማስመረቅ በሚል የእስቴ ወረዳ እና የመካነየሱስ ከተማ ካድሬዎች በአገዛዙ ጥምር ጦር ታጅበዉ ወደ ዳጉት እየሱስ ቢጓዙም የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ ሻለቃ አራት በአገዛዙን ሰራዊት እና ካድሬዎቹ ላይ በወሰዱት እርምጃ የጠላት አብይ አህመድ ሰራዊት ወደ መጣበት ተመልሷል።

ከአበርጉት መሳለሚያ ሰፍሮ የነበረዉ የአገዛዙ ብሌፄግና ሰራዊት በተወሰደበት ጠንከር ያለ እርምጃ ከአበርጉት መሳለሚያ ወደ ዳጉት እየሱስ አሯሩጠዉ መልሰዉታል።ድልድዩ አንድ ሚሊዮን ባልሙላ ገንዘብ ቢጠናቀቅም የአገዛዙ ካድሬዎች አስር ሚሊዮን ብር በላይ አወራርደዉበታል ተብሏል።

ባልተሰራ መሰረተ ልማት ፕሮፓጋንዳ ለመስራት ያሰበዉ አገዛዙ ብልፅግና በጀግኖቹ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ታማኝ ልጆች ከሽፏል።

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!
የፋኖ ድምፅ!!!
ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም.

በሰብዓዊነት ላይ የሸፈተውን አገዛዝ መታገል የሰው ልጅ ሁሉ ግዴታ ነው!!

የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ዛሬ ካለበት ደረጃ ይደርስ ዘንድ በርካታ መስዋዕትነት ተከፍሎበታል። አገዛዙ አረመኔነትን፣ አውሬነትን እና ዓለም አቀፍ አሸባሪነትን ተላብሶ ባካሄደው የዘር ማጥፋት ወንጀል ንፁሃንን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል። የሟቾችን አስከሬን በእሳት አቃጥሏል፣ አካላቸውን ቆራርጧል። የሐይማኖት ተቋማትን ምሽግ በማድረግ አራክሷል።
በአጠቃላይ የአማራ ህዝብ ላይ የሽብር ተግባራትን መፈፀም አንደኛው የጦርነት ስልት አድርጎት ቆይቷል።

ጥቅምት 02 ቀን 2018 ዓ.ም ምዕራብ ጎጃም ማንኩሳ አካባቢ ከጠላት ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ቀላል ጉዳት ደርሶባት የአገዛዙ ሰራዊት እጅ የወደቀችው የ19 ዓመቷ ፋኒት በዓለም ዋሴ ላይም ተመሳሳይ ድርጊት ተፈፅሞባታል። ፋኒት በዓለምን ከነ ህይወቷ በእጁ የያዘው ሰራዊት ከበላይ ኃላፊወቹ በተሰጠው መመሪያ መሰረት የፋኖዋን ሁለት ጡቶች በመቁረጥ አስፋልት ላይ ከመጣሉም ባሻገር "አማራ" የሚል ንቅሳት ያለበትን የቆዳዋን አካል በመግፈፍ ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥላቻ አሳይቷል።

አገዛዙ ለመደበኛ ሰራዊቱ ከሚሰጠው የጥፋት ተልዕኮ ባሻገር መሰል የሽብር ድርጊቶችን የሚፈፅም ኃይል በየ አሃዶቹ በመመደብ በሽብር ተግባር ህዝቡን ሊያሸንፍ በመጣር ላይ ይገኛል።

የአፋብኃ ሰራዊት እና አመራር ይህንን የአገዛዙን ዋነኛ ባህሪ አስቀድሞ በመረዳት የአገዛዙን ሰራዊት በመተናነቅ የመጨረሻው ህቅታ ላይ እንዳደረሰው ሁሉ የአብይን ቡድን ሙሉ በማስወገድ የአማራን ህዝብ ማህበራዊ እረፍት ማምጣት ልዩ ተልዕኮው አድርጎ የሚሰራ ይሆናል።

ፋኒት በዓለም ዋሴ ላይ የተፈፀመው አውሬያዊ ተግባር በመላው የአማራ ህዝብ ላይ የተፈፀመ ጥቃት እንደመሆኑ ይህንን እና መሰል ስምሪት የሚሰጠውን አረመኔ አገዛዝ ከነ መዋቅሩ ነቃቅለን ለመጣል ለምናደርገው የፍትህ ተጋድሎ መላው ኢትዮጵያዊ እና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከጎናችን እንዲቆም እንጠይቃለን።

በሰብዓዊነት ላይ የሸፈተውን አገዛዝ መታገል የሰው ልጅ ሁሉ ግዴታ መሆን ይገባዋል።

ሕልውናችን በተባበረ በክንዳችን!
የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከአፋብኃ ደቡብ አማራ ቀጠና አሳምነው ዕዝ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ
4
ሰበር ዜና !
የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ የዲያቆን ሸጋውን አጃቢ ጭምሮ በርካታ የአገዛዙ ሚኒሻ መከላከያ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት ከበየዳ ወረዳ፤ከጠለምት ወረዳ ከቤተአማራ ዋግህምራ ዞን አበርጌሌ ወረዳ ካለ የአገዛዙ ጥምር ሰራዊት በየአቅጣጫው በመክዳት እስከ ሙሉ ትጥቃቸው የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዘለቀ ዕዝ የራስ አሞራው ውብነህ 3ኛ ኮር የሰሜን ብርቅየ ክፍለጦርን ተቀላቅለዋል ።
የክፍለጦሩ ዋና አዛዥ አርበኛ አስፋው ሰርጸ እና ምክትል አዛዡ አርበኛ አድኖ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ሙሉ ቁጥራዊ መረጃ እና vedio ሲደርሰን የምናጋራ ይሆናል።
በተለይ አማራ ሁነህ ከአገዛዙ ጋር የተሰለፍክ አማራ ወዮልህ ከማለቅህ በፊት እየወጣህ ፋኖን ተቀላቀል።
ምስል :ከተቀላቀሉት መካከል በከፊል!
ድል ለአማራ ፋኖ
4
ሰላም ቤተሰብ ይህ የግሎባል ፋኖ ሚዲያ ተጨማሪ ዩቱዩብ ቻናል ነው። የተለያዩ ፕሮግራሞችና ዜናዎችን እናቀርባለን። ሸር፣ ላይክ እና ሳብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑን።
https://www.youtube.com/@GLOBALFANOMEDIA-27
አብይ አህመድ በራያ ግንባር ጦርነቱን ከሜካናይዝድ በመውጣት በአየር ሃይል አድርጎታል::

ከቡድን መሳሪያ ብሬን : ድሽቃና ላውንቸር አልፎ የሜካናይዝድ ክፍሉን ዙ -23 : ፔምፔ (ብረት ለበስ ) ታንክ : መድፍ : ሞርታር : ቢኤም :... ቢያሰልፍም ማፈግፈግ ይሉት ነገር ቀርቶ ምሽግ እየደረማመሱ የጦር ሰፈሩን በማስለቀቅ የሬሳ ከምር ሲያስቆጥሩት : የቆቦ ሆስፒታልና ጤናጣቢያ አልበቃ ብሎ ግዝያዊ ሕክምና ማአከል እንዲከፍቱ ያስገደደ የቁስለኛ ነዶ ያስመዘገቡት የዋርካው ምሬ ወዳጆ ልጆች : የአሳምነው ፅጌ መንፈስ ወራሾች : የምንሊክ እዝ አባላት ለጠላት የማይቀመሱ ሆነው ከርመዋል::

ይህን ተከትሎ አዲስ ወደቀጠናው የገባው የደቡብ እዝና ሰሜንምሥራቅ እዝ አባላት የአየርሃይል ጦር እንድገባለት ጠይቆ በ 1 ቀን አውደውጊያ 19 የድሮን ጥቃት ፈፅሟል : መድፍና ታንክ ሲያጉአራ : ሞርተርና ዙ -23 ሲያሽካካ ቢውል ከመጤፍ አልቆጠሩትም : ዳሩ ግን በርካታ ንፁሃን ተ ጨፍጭፈዋል : ቤቶቻቸውና የዓመት አዝመራቸው እንዳልነበር ሆኖ ወድሟል : ከብቶቻቸው ተገድለዋል::

እዝነት ይሉት ነገር : ይሉኚታ ባልነበር
እንኩአን ብሬን ታጥቆ
ራያን ለጩቤ : መርሳን ለጥልቆ : የጁን ለመዋጣ ማን ይችለው ነበር:: ነው የአበው ብሂሉ::

የራያ ማሽላ : ማኛ ነጭ ጤፉ ውስጣውስጡ በጁላ ሠራዊት አስከሬን ተሞልቷል : ምሺግ : ውድማው የጣር ድምፅ በሚያሰሙ የጠላት ሃይል ተጨንቁአል:: 3ኛ ቀኑን በያዘው ትንቅንቅ የወንድሞቻቸውን ደም ሳይውል ሳያድር እየመለሱት ነው : የህታቸውን ቁስል ልያሽሩ ለሕይወታቸው ሳይሰሱ ደረታቸውን ለጥይት አረረ ሰተው እየተዋደቁ ነው::

ድል ለአማራ ፋኖ : ድል ለአማራ ሕዝብ!
@አለማቀፍ ፋኖ ሚዲያ
      የፋኖ ድምፅ!
የድል ዜና

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ)
ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ

የልጅ እያሱ ኮር አካል የሆኑት የራስ አሊ ክፍለ ጦር እና የራምቦ ክፍለ ጦር  ጥቅምት 8/2018 ዓ.ም በሰሜን ወሎ ዞን  ሀብሩ ወረዳ በውርጌሳ እና አካባቢው በተደረገ እልህ አስጨራሽ ውጊያ በራስ አሊ ክፍለ ጦር ስር ያሉ ሻለቃዎች  እና በራምቦ ክፍለ ጦር ስር ያሉ ሻለቃዎች ጥምረት በመፍጠር የመጣውን ጡት ቆራጭ ወንበር አስጠባቂ ወታደር አብዘሀኛው በየ ጥሻው የጥይት ሲሳይ ሲሆን በለስ የቀናው ጡት ቆጭራ ወንበር አስጠባቂ ወታደር እጅ እንድሰጥ ተገዷል።

የደረሰውን ቁሳዊ እና ሰበአዊ  ኪሳራ ዝርዝሩ እንደደረሰን የምናሳውቅ ይሆናል።

መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል!

አፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ሚኒሊክ ዕዝ ልጅ እያሱ ኮር  ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት 8/2018 አ.ም
የነውረኛው ዐቢይ አሕመድ ቡድን በባሕር ዳር ዙሪያ ደህና ማሪያም ቀበሌ ላይ በፈጸመው የድሮን ጥቃት የተገደሉና የቆሰሉ ንፁኋኖች እንዲሁም የወደመ ሀብት ንብረት።
ጉና ክፍለጦር የእስቴ ወረዳ ዋና ከተማ የሆችውን መካነ እየሱስ ከተማን ተቆጣጠረ::

የአፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ ሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ጉና ክ/ጦር እስቴ ዴንሳ ብርጌድ እና ስማዳ ሀገረ ቢዝን ብርጌድ በእስቴ መካነ እየሱስ ከተማን ሙሉበሙሉ  ተቆጣጥሯል።

ከባድ ውጊያ እየተደረገ ሲሆን ጠላት ወደ ደብረታቦር እግሬ አውጭኝ ሩጫውን ተያይዞታል። በአገዛዙ ፋኖ ናችሁ እየተባሉ የታጎሩ እስረኞች ተለቀዋል።

በርካታ የአገዛዙ አራጅ ሰራዊት የተደመሰሰ ሲሆን በርካቶች ተማርከዋል። እስካሁን በርከት ያሉ የቡድን መሳሪያና የነፍስ ወከፍ ክላሽ ገቢ ተደርጎል።

ውጊያው እንደቀጠለ ሲሆን በደቡባዊ ጎንደር ቀጠና ያለው ሁሉም የፋኖ መዋቅር በተናበበ መልኩ በአገዛዙ ላይ እርምጃ መውሰዱን አጠናክሮ ይቀጥላል።
 
ድል ለአማራ ፋኖ
ነፃነታችን በክንዳችን !
ጥቅምት 9/2018 ዓም