ግሎባል ፋኖ ሚዲያ /ግፋሚ/GFM
431 subscribers
809 photos
104 videos
6 files
1.35K links
አማራ በዚህ ልክ ሲጨፈጨፍ ማየት ያማል። ይህን ለማስቆም የበኩላችን መረጃ በመስጠትና ማሰራጨት ተገቢ ነው
Download Telegram
በርካታ የብልፅግናው ሚሊሻ አባላት ፋኖን ተቀላቀሉ።

በሸዋ መርሀቤቴ አውራጃ በሚዳና ሬማ ከተማ ዙሪያ በብልፅግናው ፕሮፖጋንዳ ተታለው ከፋሽስቱ አገዛዝ ጋር ተሰልፈው በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ህዝባቸውን ሲበድሉ ቢቆዩም በቀጠናው ከተሰማራው የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ አፄ አምደ ጽዮን ኮር አፄ ዳዊት ክፍለጦር ያቀረበላቸውን ጥሪ ተቀብለው ፋኖን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።

ሁለተኛ ሳምንቱን ባስቆጠረው በቀጠናው እየተካሔደ ባለው ተከታታይ አውደ ውጊያ የብልፅግናው ዙፋን አስጠባቂ ከመቸውም ጊዜ በላይ ያለ የሌለ ሀይሉን በሬማ ቀጠና ዙሪያ እያሰለፈ ይገኛል።

ከለሚ፣ ከመርሀቤቴ አለም ከተማ፣ ከመንዝ ግሼራቤል እና ከሚዳ መራኛ ከተማ በርካታ ሜካናይዝድ ሀይሉን ወደ ሬማ ከተማ በማንቀሳቀስ ሙሉ አቅሙን የተጠቀመ ሲሆን ጀግናው አፄ ዳዊት ክፍለጦር እልሕ አስጨራሽ ተጋድሎ እያደረገች መሆኑን ክፍለጦሩ አስታውቋል።

ይሕ በእንዲሕ እንዳለ ሰራዊቱ በገፍ እየፈረሰበት ፣በአይበገሬው ሰራዊታችን ጠንካራ ክንድ እረፍት ያጣው የአማራ ጠሉ የብልፅግናው ወራሪ ሰራዊት በዝሕ ሰዓት በሬማ አጎራባች ወረዳ በሆነችው በደራ አማራዎች ላይ ከሚዳና ደራ ከሁለት አቅጣጫ ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ የደረሰውን የገበሬዎችን አዝመራ እና ቤቶችን እየተቃጠለ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
1
ሰበር አዲስ ቅዳም‼️

19 ተመክሮ አይድን በጥዋቱ ተሸኝቷል!

ዛሬ ጥቅምት 4/2018 ዓ/ም ከለሊቱ 12:00 ስዓት ጀምሮ የአፋብኃ ምዕራብ አማራ ቀጠና ቴዎድሮስ እዝ ፫ኛ ጎጃም አገዉ ምድር ፲/አ ኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ አዲስ ቅዳም ከተማ ዉስጥ በመግባት ባደረገችዉ የእጅ በእጅ ዉጊያ የታገዘ  ድንገተኛ ኦፕሬሽን በጠላት ላይ ከፍ ያለ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ ተችሏል።

በዚህ ከለሊቱ 12:00 ስዓት እስከ እረፋድ 5:00 ስዓት ድረስ ለተከታታይ 5 ስዓታት በቆየ ልዩ ኦፕሬሽን
አዲስ ቅዳም ስላሴ  ፣ አባ አይናለም   ፣ከብት ገበያ እና ባታ ቤተክርስቲያን መሽጎ የነበረዉ ከሞት የተረፈ ጠላት በፋኖዎች አረር የተሸኙ 19 እድለቢስ  ጓዶቹን ሳያነሳ ቁስለኛ እና ቁሳቁሱን በእየ ሜዳዉ እያንጠባጠበ ሙሉ በሙሉ ምሽጉን በመልቀቅ ወደ አድጓሚ ተራራ ፈርጥጧል።

አጠቃላይ በዛሬዉ የአዲስ ቅዳም ከተማ ልዩ ኦፕሬሽን
_19 የብልፅግና ታጣቂ ሲወገድ
_27 ቁስለኛ ሁኖ
_16 ክላሽንኮቭ  መሳሪያ  ብዛት ካለዉ ተተኳሽ ጋር  በምርኮ ገቢ ተደርጓል።

ፋኖነት አሸናፊነት‼️
Estibel A Zerihun
3
[ ከአርበኛ ሸጋ ጌታቸው/ ቋረኛው የተላለፈ መልዕክት ]

ጠላቶቻችን አጠፋናቸው ሲሉ በዝተን የምናድር  ባልዋልንበት ሲያውሉን በእውነት የቆምን።

እንደ ወርቅ የነጠርን እደ ብረት የተነከርን የግዜው የነጻነት ምጽአት ነን በእውነት የቆምነን የነጻነት ምሳሌ ነን።

ብቻ እንጠንክር የዘመኑ ነጻነት እኛው ነን።
ለመከራ የተፈጠርን ሳይሆን
ለነጻነት የታደልን ልጆች ነን።

አፋብኃ ሰሜን አማራ ቀጠና በለይ ዘለቀ እዝ
ም /ክ/ ወታደራዊ አዛዠ አርበኛ ሸጋ ጌታቸው !

ህልውናችን በተባበረ ክዳችን !
3
እንኳን ደስ አላችሁ የመይሳው ልጆች !
ድል ለአማራ ፋኖ
👍3
የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል ሰሜን አማራ ቀጠና በላይ ዕዝ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ አንደኛ ኮር ጉና ክፍለጦር እስቴ ዴንሳ ብርጌድ በጠላት ላይ ድል ተቀደጅቷል።

በእስቴ መካነየሱስ ዳጉት እና አበርጉት መሳለሚያ በተደረገ አዉደዉጊያ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ ሌጆች የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ ሻለቃ አራት በጠላት ላይ ሰራዊት ላይ እርምጃ ተወስዷል።ድልድይ ለማስመረቅ በሚል የእስቴ ወረዳ እና የመካነየሱስ ከተማ ካድሬዎች በአገዛዙ ጥምር ጦር ታጅበዉ ወደ ዳጉት እየሱስ ቢጓዙም የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ ሻለቃ አራት በአገዛዙን ሰራዊት እና ካድሬዎቹ ላይ በወሰዱት እርምጃ የጠላት አብይ አህመድ ሰራዊት ወደ መጣበት ተመልሷል።

ከአበርጉት መሳለሚያ ሰፍሮ የነበረዉ የአገዛዙ ብሌፄግና ሰራዊት በተወሰደበት ጠንከር ያለ እርምጃ ከአበርጉት መሳለሚያ ወደ ዳጉት እየሱስ አሯሩጠዉ መልሰዉታል።ድልድዩ አንድ ሚሊዮን ባልሙላ ገንዘብ ቢጠናቀቅም የአገዛዙ ካድሬዎች አስር ሚሊዮን ብር በላይ አወራርደዉበታል ተብሏል።

ባልተሰራ መሰረተ ልማት ፕሮፓጋንዳ ለመስራት ያሰበዉ አገዛዙ ብልፅግና በጀግኖቹ የሜጀር ጀኔራል ዉባንተ አባተ ታማኝ ልጆች ከሽፏል።

@ግሎባል ፋኖ ሚዲያ!!
የፋኖ ድምፅ!!!