ምድር ላይ ሚዛናዊ ሚባል ህግ የለም ፤ ሰው ያወጣው ህግ እንጂ
ያላቹበትን ደረጃ ከፍ አድርጋቹ ህጉን እራሳቹ ማውጣት ትችላላቹ
ምን እያልከን ነው? እራሳቸው በማይተገብሩት ህግ ውስጥ ነው ያለነው። የራስህን ህግ ለማውጣት ጠንክረ መስራት ፣ መማር እና በቶሎ ብዙ ነገር ማወቅ አለብህ እያልኩ ነው !!!!
https://t.me/ethiocs
Getch✍️

👍35😁12❤4🌚2👏1
የባዶነት ስሜት
ይሄ ስሜት አለማችን ላይ ካሉ በጣም ከባዱ ስሜት መካከል አንዱ ነው። የባዶነት ስሜት ብዙ ነገር እያለን ምንም እንደሌለን የሚሰማን ፤እንዲሁም ጊዜው የሶሻል ሚዲያ ዘመን እንደመሆኑ አምሮአችን በቀን ብዙ ነገሮችን ያስተናግዳል። ይሄ ነገር በኖረኝ አምሮትን ተከትሎ ምንም እንደሌለን ይሰማናል ። በዚህ ጊዜ በሌሎች ሃገሮች በብዛት ፤ በእኛ ሃገር ደግሞ በተወሰነ ደረጃ እራሱን በራሱ የሚያጠፋ ሰው በዝቷል። ምክንያቱ ደግሞ የባዶነት ስሜት ይዞት የሚመጣው ጭንቀት ፣ ዲፕሬሽን ፣ እራስን አለመውደድ ፣ ትግስትን ማጣት ሁሉ ነገር በአንድ ጊዜ እንዲሆን መመኘት ይሄን ሁሉ ነገር ይዞ ይመጣል ። ይሄ ስሜት ደግሞ ሁሉ ነገር ያለውንም ፣ የሌለውንም ያጠቃል ። ሰው የባዶነት ስሜት ሲሰማው እራሱን መንከባከብ ያቆማል ፣ የተዛባ አመጋገብ ይኖረዋል ፣ ቤት ውስጥ ሚውል ከሆነ የተዝረከረከ አኗኗር ልብስ አለማጠብ፣ ፅዱ አከባቢ አለፍጠር ይከተላል ። ስለዚህ ይህን ያህል ካወራን ወደ መፍትሄው እና እኔ ወደማግዛቹ ነገር እንለፍ 👌 መጀመርያ ከዚህ ስሜት መውጣት ያስፈልጋል ፤ ከዛም ሁሉ ነገር ተከትሎ ይመጣል ። ከዚህ ስሜት ለመውጣት የመጀመርያው ሁሉም ሰው ስልክ አለው እኔ እንደሌላው ከሶሻል ሚዲያ ጥፉ አልላቹም 😂 ነገር ግን ስልካቹ ላይ ያሉትን ሁሉንም ሶሻል ሚዲያዎች እናንተ ምን እንደምትፈልጉ እንዲያውቁ አድርጓቸው ። እንደሱ ለማድረግ ደግሞ ሁሉም ሶሻል ሚዲያዎች የራሳቸው የሆነ ስርዓት(System) አላቸው ። እሱን እንዴት ማድረግ እችላለው ? ጥሩ ጥያቄ ነው ።
✅ መጀመርያ እናንተ መሆን ምትፈልጉትን ነገር ምረጡ የልብስ ዲዛይነር፣ ዩትዩበር ፣ ግራፊክስ ዲዛይነር ፣ ሽያጭ ፣ ገጣሚ ፣ ደራሲ ፣ ወዘተ
✅ ወደ ሁሉም ሶሻል ሚዲያ ግቡና እናንተ ምትፈልጉትን ቪዲዮ ሰርች አድርጋቹ ማየት ጀምሩ በተከታታይ አምስት ቪዲዮ ካያቹ ስልካቹ እናንተን ማወቅ ይጀምራል ፤ ትምርታዊ ነገር እንደምትወዱ ፣ መንፈሳዊ ነገር እንደምትወዱ ማወቅ ይጀምራል ። ከዛ መጥፎ ነገር ከስልካቹ እየጠፋ ሚጠቅሙ ነገሮች ደግሞ በተቃራኒው በይበልጥ ወደናንተ መምጣት ይጀምራል ። ከዛም ለጠቃሚ ቪዲዮዎች ፎልደር ስሩለት ፤ Save ያደረጋቹትን ቪዲዮ ደግማቹ ለማየት ሞክሩ። ምክንያቱም ጠበብቶችን ጠቢብ ያደረጋቸው ሁሉት ጊዜ ማየታቸው እና ሁለት ጊዜ መስማታቸው ነው ይባላል ።
✅ ያላቹበትን ቦታ ንፁህ ማድረግ ንፁህ ልብስ ፣ ንፁህ ቤት የተስተካከለ ማድረግ
✅ በቀን አንድ ግዜ መፅሃፈ ወይም ከዩትዩብ ላይ አውዲዮ ቡክ መስማት
ይሄ ለምን ይጠቅማቹዋል ንግግራቹ ላይ ትሰራላቹ ፤ እናንተ ጋር ብዙ ምታወሩት ሃሳብ ፤ ለሰው ሚተርፍ ነገር እንዳለ እንዲሰማቹ ያደርጋል ። ማታነቡ ከሆነ የማያገባቹን ታወራላቹ ፤ ለዛ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ አንባቢ ስለሌለ ሃሜተኛ የበዛው ይባላል 🤣 ስለዚህ አንብቡ
✅ በቀን 1% ብቻ ለማደግ ሞክሩ የሆነ ነገር ለማወቅ ፣ ዩትዩብ ላይ ገብታቹ አንድ ነገር ብቻ በቀን ካወቃቹ በቂ ነው ሂደትን ልመዱ
✅ ሌላ ደግሞ ዩትዩብ ላይ መስራት የምትፈልጉ ዩትዩብ ላይ 53 ቪዲዮ በነፃ ለቀናል በቀን 1 ቪዲዮ ብቻ በማየት በ 2 ወር ውስጥ የማንም እርዳታ ሳያስፈልጋቹ በራሳቹ መስራት ትችላላቹ
ስለዚህ በርቱ ተስፋ እንዳትቆርጡ ፀልዩ
Getabalew Taidwos
ጌች✍️
ይሄ ስሜት አለማችን ላይ ካሉ በጣም ከባዱ ስሜት መካከል አንዱ ነው። የባዶነት ስሜት ብዙ ነገር እያለን ምንም እንደሌለን የሚሰማን ፤እንዲሁም ጊዜው የሶሻል ሚዲያ ዘመን እንደመሆኑ አምሮአችን በቀን ብዙ ነገሮችን ያስተናግዳል። ይሄ ነገር በኖረኝ አምሮትን ተከትሎ ምንም እንደሌለን ይሰማናል ። በዚህ ጊዜ በሌሎች ሃገሮች በብዛት ፤ በእኛ ሃገር ደግሞ በተወሰነ ደረጃ እራሱን በራሱ የሚያጠፋ ሰው በዝቷል። ምክንያቱ ደግሞ የባዶነት ስሜት ይዞት የሚመጣው ጭንቀት ፣ ዲፕሬሽን ፣ እራስን አለመውደድ ፣ ትግስትን ማጣት ሁሉ ነገር በአንድ ጊዜ እንዲሆን መመኘት ይሄን ሁሉ ነገር ይዞ ይመጣል ። ይሄ ስሜት ደግሞ ሁሉ ነገር ያለውንም ፣ የሌለውንም ያጠቃል ። ሰው የባዶነት ስሜት ሲሰማው እራሱን መንከባከብ ያቆማል ፣ የተዛባ አመጋገብ ይኖረዋል ፣ ቤት ውስጥ ሚውል ከሆነ የተዝረከረከ አኗኗር ልብስ አለማጠብ፣ ፅዱ አከባቢ አለፍጠር ይከተላል ። ስለዚህ ይህን ያህል ካወራን ወደ መፍትሄው እና እኔ ወደማግዛቹ ነገር እንለፍ 👌 መጀመርያ ከዚህ ስሜት መውጣት ያስፈልጋል ፤ ከዛም ሁሉ ነገር ተከትሎ ይመጣል ። ከዚህ ስሜት ለመውጣት የመጀመርያው ሁሉም ሰው ስልክ አለው እኔ እንደሌላው ከሶሻል ሚዲያ ጥፉ አልላቹም 😂 ነገር ግን ስልካቹ ላይ ያሉትን ሁሉንም ሶሻል ሚዲያዎች እናንተ ምን እንደምትፈልጉ እንዲያውቁ አድርጓቸው ። እንደሱ ለማድረግ ደግሞ ሁሉም ሶሻል ሚዲያዎች የራሳቸው የሆነ ስርዓት(System) አላቸው ። እሱን እንዴት ማድረግ እችላለው ? ጥሩ ጥያቄ ነው ።
ይሄ ለምን ይጠቅማቹዋል ንግግራቹ ላይ ትሰራላቹ ፤ እናንተ ጋር ብዙ ምታወሩት ሃሳብ ፤ ለሰው ሚተርፍ ነገር እንዳለ እንዲሰማቹ ያደርጋል ። ማታነቡ ከሆነ የማያገባቹን ታወራላቹ ፤ ለዛ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ አንባቢ ስለሌለ ሃሜተኛ የበዛው ይባላል 🤣 ስለዚህ አንብቡ
ስለዚህ በርቱ ተስፋ እንዳትቆርጡ ፀልዩ
Getabalew Taidwos
ጌች✍️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
👍21👏3🫡3💯2🔥1🏆1
የሃሳብ አረም
በዚህ ጊዜ ትውልዱ ላይ በብዛት እየታየ ያለ ችግር ነው። የሃሳብ አረም ማለት አረም በተፈጥሮ እኛ ከምንፈልገው ዘር ጋር አብሮ ሚያድግ አላስፈላጊ ነገር ነው። አረም በጊዜ ካልተነቀለ አስፈላጊ እና ዋና ነገርን ያቀጭጫል ፤ ፍሬ ያሳጣል። የሃሳብ አረም ማለት የፀና አቋም ይዞ አለመገኘት ማለት ነው። ከሁሉም ቦታ የተሰበሰበ ከትክክለኛውም ፣ ትክክል ካልሆነውም፣ ከተማረውም ፣ ካልተማረውም የዚህ ሁሉ ክምችት የሃሳብ አረም ሊፈጥር ይችላል። የሃሳብ አረም መንስኤው ጨርሶ አለመማር እና ነገሮችን ከግማሽ ማቋረጥ ያቋረጥነውን ነገር ደግሞ ከሆነ ጊዜ ቡሃላ ደግሞ ለመስራት መሞከር ከዛ እንደገና ማቋረጥ ነው ። አንድን ነገር ከጀመርን ትክክለኛ አቋም እና እውነት ላይ እስክንደርስ ድረስ በራሳችን ጥረት ለማወቅ መጣጣር እና መማር አስፈላጊ ነው።
https://t.me/getabalewt
Getabalew Tadiwos

👍35❤12🔥6👌2🫡2
ዝም ብሎ ደስታ
ሰው በምድር ላይ ይሄን ደስታ ከተለማመደ ከስኬትም ሆነ ከምንም ነገር ማንም አያስቆመውም ይሄም ዝም ብሎ ደስታ ይባላል። ይሄ ደስታ የሚፈጠረው ሰው በአምላኩ ላይ ባለው እምነት ብቻ የሚፈጠር ነው። ሰው በምድር ላይ በሚኖረው ጉዞ ስለነገው በአምላኩ ተማምኖ ፣ ስለዛሬው ቀን አመስግኖ በቀን ውስጥ በሚሄድበት ሁሉ አምላኩን እያሰበ ደስ መሰኘትን መለማመድ አለበት ። በዚህ ዘመን አብዛኛው ሰው ለምን ደስታ እራቀው? ያለውም ቢሆን ለምን የነፍስ እርካታ አላገኝም ? ምክንያቱም ደስታን ውጭ ላይ በሚያገኛቸው ነገር ፣ በገንዘብ ፣ በሰው አጀብታ አገኛለው ብሎ ስላሰበ ነው። ይሄን ቃል ክርስቲያኖች ያቁታል ፊልጵስዩስ ላይ ያለውን ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ። ሰው በምድር ላይ ሲኖር እውነተኛ ደስታን እና እርካታን ማግኘት የሚችለው በአምላኩ ብቻ ነው ። ዝም ብሎ ደስተኛ መሆንን ተለማመዱ ይሄ ደግሞ ወደ አምላካቹ ስትጠጉ ወደሱ ስትቀርቡ ይመጣል ። ውስጣቹ ላይ ቀድሞም ደስታ ካለ ምንም ቢመጣ አያስደንቃቹም ። አሁን ላይ ሰው ደስታን ፍለጋ ሶሻል ሚዲያ ለይ በሚኳትንበት ዘመን ሚለቀቁ ፎቶዎች ሳይቀሩ ሚስጥራትን ያጋልጣሉ ፤ ደስታን ፍለጋ እንደሆነ ያሳብቃሉ ። ምክንያት አልባ ፎቶዎች በዝተዋል እራሳችንን ብንሸውደውም ህሊናችን ግን ይጠይቀናል ይሄን ነገር ግን ለምን እያረክ ነው ይለናል ። ከገገንዘቡም በፊት፣ ከምግቡም ፣ ከመኪናውም ፣ ከመዝናናቱም በፊት ሰው ዝም ብሎ በአምላኩ መደሰትን መለማመድ አለበት ባይ ነኝ

👍33❤11❤🔥2🔥2🍌1
This is what the wise Solomon said.
28 ነፍሴ እስከ ዛሬ ድረስ ትሻታለች፥ ነገር ግን አላገኘሁም፤ ከሺህ ወንዶች አንድ አገኘሁ፥ ከእነዚያ ሁሉ መካከል ግን አንዲት ሴት አላገኘሁም።
ወንድ 1/1000
ሴት 0/1000
🙆♂️🙆♂️🙆♂️
https://t.me/getabalewt
Getabalew Tadiwos
ጌች

😁11❤1🤔1💅1🙉1😎1
ምክንያታዊነት
ሶሻል ሚዲያ ላይ ከቅርብ አመታት ጀምሮ የመጣው ነገር ቢኖር ያለ ምክንያት ሁሉንም ነገር ወደሚዲያ ማውጣት ከጀመርን ሰነባብተናል ። ስንበላም ፣ ከሃገር ስንወጣም ፣ መኪና ስንገዛም ፣ ቤት ስንገዛም ፣ ስናገባም ፣ ሽምግልና ስንልክም ፣ ከቤተክርስቲያን ስራት ውጭ ቃልኪዳን ስናስርም ፣ ልደት ስናከብርም ሁሉንም ከራስ ይልቅ ለሚዲያ ተኮር ማድረግ ከጀመርን ሰነባብተናል። ፕሮግራሞች ሲዘጋጁ ጭምር አሁን ላይ ለሶሻል ሚዲያ እና ለይሉኝታ ሆኗል። አንድ ያልገባን ነገር ቢኖር የእኛ ደስታ የሚያስደስታቸው ሰዎች እጅግ በጣም ጥቂት እና በእጅ እንኳን ልንቆጥራቸው የምንችላቸው ሰዎች መሆናቸውን አለመገንዘባችን ነው። የሰው ደስታ የሚያስደስተው መልካም መንፈስ ያለበት ሰው ብቻ ነው ። ደግሞ አስቡት ምን ያህል ሰው በአቅራቢያቹ መልካም መንፈስ አለው ? ይሄን መልሱን ለእናንተ ትቼዋለው
መላ ምቶች እና ጥናቶች እንደሚያሳዩት የሰው ደስታ የሚያስደስታቸው ቁጥር በፐርሰንት ሲሰላ ከ10-20% ይሆናል የሚል ግምት አስቀምጠዋል ። በተቃራኒው ደግሞ የሰው ደስታ በተለያዩ ምክንያቶች ሊያስደስታቸው አይችልም በማለት ከ 80-90%
በቅናት፣ ግዴለሽነት፣ ወይም የራስ ጥቅም ተኮርነት እና በሌሎች ደስታ ላይደሰቱ ወይም ግድየሌላቸው ሊሆኑ ይችላሉ ይላል። ስለዚህ በማወቅም ሆነ ባለማወቅም እኛ በምናደርገው ነገር ሁሉም ሰው ደስ ይለዋል ብለን መጠበቃችንን አቁመን ማድረግ ምንፈልጋቸውን ነገሮች ሁሉ ለራሳችን እና ለራሳችን ደስታ ብቻ እናድርግ።
ምናደርገውን ሁሉ እሩቅ እንደሚጓዝ ሰው አስበን በማስተዋል ማድረግ መልካም ነው ።

❤42👍14💯4👏1
Forwarded from Ethio Computer School
የተሻለ ህይወት ለመኖር ግዴታ ድግሪ አያስፈልግም - ትምርት ሚኒስተራችን ካለው
አዎ አያስፈልግም !!!!!
🚩ዩንቨርስቲ ለመጨረስ ከ4-7 አመት
🚩ኮስት ሼሪንግ ከ200 ሺህ ብር በላይ
🚩ተመርቀ ስራ ለመያዝ የስራ ልምድ
🚩ተመርቀ ስትወጣ ካንተ ቤተስብ ብዙ ነገር ሲጠብቅ
🚩እድሜ ፣ ትዳር ፣ ገንዘብ በእና ወዘተ ነገሮች ይጠብቁሃል
ጊዜው ሳይረፍድ አሁኑኑ ጀምር አምስት አመት የኮስት ሼሪግ ብር እዳህን በ 1 ወር መስራት ያስችልሃል
ቲክቶክ ክሬተር ሪዋርድ አከፋፈቱን ማየት ከፈለክ ከታች ባለው ሊንክ አሁኑኑ ጀምር
https://www.youtube.com/watch?v=JeQNgCtKf_0&feature=youtu.be
በተጨማሪ 5ተኛ ዙር የቲክቶክ ክሬተር ሪዋርድ ኮርስ ሰኞ ይጀምራል ፤
📩 ለመመዝገብ ከታች ያለውን ሊንክ በመንካት 'ኮርስ' ብለው ይላኩ።
👇👇👇👇
@elearning15

❤4🥰3👏2🔥1
You cannot undo the moves but you can make the next step better. #ethiocomputerschool #getabalew #chess #chessmaster
👍4🏆2❤1