Genius Tutorial Service
139 subscribers
191 photos
5 videos
51 links
Empowering Genius Mind
Download Telegram
Channel created
Genius Tutorial Service -Tutorial service by teachers. -K.g up to post graduate(Including Degree,Masters,Phd). -Based on your teacher choice. -Everywhere. -Home to home or online. Contact us: -Telephone-+251118676489 -Telegram- https://www.t.me/@geniustutorialservice DIRECT REGISTRATION: genius.novahnm.com Empowering Genius Mind Genius Tutorial Service
👍1
ሰላም ለሁላችሁም

በቅድሚያ ሰላምታን አቅርበን ከዚህ በታች ያሉትን የድርጅታችንን ማህበራዊ ሚዲያ ገፆችን ይከተሉ፣ያጋሩ እያልን ጥሪ እናቀርባለን።

              Telegram: https://t.me/geniustutorialservice

              Facebook:     https://facebook.com/geniustutorialservice

              Instagram: https://www.instagram.com/geniustutorialservice
  
              Twitter: https://www.twitter.com/geniustservice
   
              Tiktok: https://www.tiktok.com/@geniustutorialservice
  
              Linkedin: https://www.linkedin.com/in/geniustutorialservice
❤2
Channel photo updated
#ZENA
#ATTENTION የትምህርት ሚኒስቴር የብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ ፦

(ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ - የትምህርት ሚኒስትር)

- የፈተና ንክኪው በእጅጉ ተቀንሷል።

- ከዚህ በፊት በፈተና አሰጣጥ ወቅት የነበረውን " የኔ አካባቢ ሰው ፣ የኔ ዘመድ " የሚለውን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ማንኛውም የአንድ አካባቢ ተወላጅ እዛው አካባቢ ያሉ ተማሪዎችን አይፈትንም። ማንኛውም የአንድ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ እራሱ የሚያስተምርበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አይፈትንም።

- ተማሪዎች አንዴ ዩኒቨርሲቲ (ካምፓስ) ከገቡ በኃላ ከሌለው የውጪ ማህበረሰብ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አይኖራቸውም። ምንም ስልክ ወይም ሌላ የግንኙነት ነገር ይዘው አይገቡም።

- ተፈታኝ ተማሪዎች ለ4 ቀናት ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ እናበላቸዋለን ፣ እናጠጣቸዋል፣ እንከባከባቸዋለን ነገር ግን በፍፁም ከሌላው ዓለም ጋር አይገናኙንም።

- ተማሪዎች ከሚነሱበት ቦታ የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው እንዳይሄዱ የክልል የፀጥታ ኃላፊዎች የፍተሻ ስራ ይሰራሉ፤ የክልል የፀጥታ አከላት ስራ ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲ በር ላይ እስኪደርሱ ብቻ ነው ከዛ በኃላ ያለውን የፍተሻ እና ጥበቃ ስራ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ይሆናሉ።

- ስልክ ይዞ አንድ ተማሪ ቢገኝ ስልክ ይቀማል ሳይሆን ሙሉ በሙሉ ፈተናውን እንዳይወስድ ይደረጋል።

- ተማሪዎች በምንም ሁኔታ ፈተና ከሚወስዱበት ግቢያቸው ውጭ መውጣት አይችሉም፤ ከማንም ጋር መገናኘት አይችሉም።

- ከፍተኛ ዝግጅት እያደረግን ስለቆየን ችግር ይኖራል ብለን አናምንም።

- በእስር ላይ ላሉ፣ በውጭ ላሉ የኮሚኒቲ ት/ቤቶች ፣ በፀጥታ ምክንያት ፈተናውን ለመውሰድ ለማይችሉ ሌላ ሁለተኛ ፈተና ተዘጋጅቶላቸዋል። በአንድ ወር ውስጥ ይሰጣቸዋል።

የተፈጥሮ እና ሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች በተለያየ ጊዜ መፈተናቸውን ተከትሎ ተመሳሳይ የሆኑ ትምህርቶች እንዴት ይሰጣሉ ?

በትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ ላይ እንደተገለፀው የፈተና ስርቆትን ለማስቀረት እና ኩረጃን ለመከላከል በ2ቱ ዙር ተፈታኞች መካከል ምንም አይነት ግኝኑነት አይኖርም።

የመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች ፈተናቸውን ጨርሰው ከወጡ ከቀናት በኃላ ነው ሁለተኛው ዙር ተፈታኞች የሚፈተኑት።

ሁለቱም የሚወስዷቸው (የናቹራል እና ሶሻል) አንድ አይነት ትምህርቶች ላይ ጥንቃቄ ተደርጎ የተለያዩ ፈተናዎች ናቸው የተዘጋጁት።

ተማሪዎች ስልክ ይዘው ባለመሄዳቸው ከወላጆቻቸው ጋር እንዴት ይገናኛሉ ?

ትምህርት ሚኒስቴር ኩረጃን እና ስርቆት ለመከላከል ሲባል ተማሪዎች ወደ ሚፈተኑበት ተቋም ስልክ ይዘው መግባት እንደማይችሉ አሳውቋል።

ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ፈታኞችም የፈተና ክፍሎች አቅራቢያ እና ፈተናው የሚሰጥበት አካባቢ ስልክ ይዘው መገኘት አይችሉም።

በየዩኒቨርሲቲዎቹ አንድ አንድ ተወካይ የሚኖር ሲሆን በተወካዩ አማካኝነት ወላጆች ልጆቻቸውን ያሉበትን ሁኔታ ለማወቅ ይችላሉ።

የህትመት ዝግጅቱ ምን ይመስላል ? የፈተናው ኮዶች ስንት ናቸው ?

በአጠቃላይ የህትመት ዝግጅቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ እና ጥንቃቄ የተደረገበት ሲሆን የፈተናው ኮዶች በፊት ከነበረው " 4 ኮድ " ወደ " 12 ኮድ " ከፍ ተደርጓል።

ለወላጆች የተላለፈ መልዕክት ፦

ወላጆች ተማሪዎች ይዘው መሄድ የሌለባቸው ፣ እና ስለሚጠበቅባቸው ግዴታቸው አስገንዝበው መላክ አለባቸው።
#ZENA #ATTENTION ስልክ ይዞ የተገኘ ተማሪ ስልኩ አይቀማም በቀጥታ ከፈተናው ይወገዳል ፤ ፈተና አይፈተንም ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

- ሶሻል እና ናቹራል ላይ ላሉ ተመሳሳይ የትምህርት ዓይነቶች የተለያዩ ፈተናዎች ተዘጋጅተዋል

- ተማሪዎች ከግቢ በምንም ዓይነት ምክንያት መውጣት አይችሉም

- በስህተት እንኳን ስልክ ይዞ የተገኘ ተማሪ ከፈተናው ይወገዳል ፤ ከግቢውም እንዲርቅ ይደረጋል

- ተማሪዎቹ አንዴ ካምፓስ ውስጥ ከገቡ በኋላ ከሌላው ዓለም ጋር ግኑኝነት አይኖራቸውም

- ግቢ ከገቡ በኋላ ፈተናው ቢወጣ እንኳን ተማሪዎች ሊጠቀሙ የማይችሉበት ሁኔታ ተፈጥሯል

- ተፈታኞች በግቢ ቆይታቸው እናበላቸዋለን፣እናጠጣቸዋለን፣እንከባከባቸዋለን፣... ከሌላው ዓለም ግን ግንኙነት የላቸውም

- የአንድ አካባቢ ተወላጅ አካባቢው ላይ ያሉ ተማሪዎችን አይፈትንም

- ማንኛውም የአንድ ዩንቨርሲቲ አስተማሪ የሚያስተምርበት ዩንቨርሲቲ ውስጥ አይፈትንም

source-@Temhert_Minister
#ZENA
#ATTENTION የፈታኝ መምህራን ጉዳይ !

የትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚፈትኑ መምህራንን ምደባ አካሂዷል።

መምህራኑ ወደ ተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ወዳሉ የመፈተኛ ማዕከላት የተመደቡ ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ሚቀርቡ ማንኛውም አይነት ጥያቄዎችን እንደማያስተናግዱ ዩኒቨርሲቲዎች እያሳወቁ ይገኛሉ።

በሚኒስተሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 260/2004 አንቀፅ 9(2) በተሰጠው ሥልጣንና እንዲሁም በሀገር አቀፍ የፈተና አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 1/2012 መሰረት ፈተና ለመፈተን ወደ ሌላ መፈተኛ ማዕከል የተመደበ መምህር በተዘጋጀው የፈተና አሰጣጥ እና አፋጻጸም ማንዋል 01/2014 መሰረት የፌደራል ት/ሚ/ር እና ፈተናዎች አገልግሎት ኤጄንሲ ወደ ተመደበበት ቦታ የመገኘት ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ይገልጻል፡፡

በመመሪያው መሰረት የዩኒቨርሲቲ መምህራን ወደ ተመደቡበት አካባቢ ሄደው የተጣለባቸው #ሀገራዊ_ኃላፊነት የመወጣት ግዴታ ያለባቸው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ከጉዞ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ማንኛውንም ጥያቄ እንደማያስተናግዱ ከወዲሁ እያሳወቁ ይገኛሉ።

ትላንት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሰጡት መግለጫ ፤ " ከዚህ በፊት የነበረውን የኔ አካባቢ ሰው ፣ የኔ ዘመድ የሚለውን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ማንኛውም የአንድ አካባቢ ተወላጅ እዛው አካባቢ ያሉ ተማሪዎችን አይፈትንም። ማንኛውም የአንድ ዩኒቨርሲቲ አስተማሪ እራሱ የሚያስተምርበት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አይፈትንም " ሲሉ አሳውቀዋል።

(ከላይ የተያያዘው ደብዳቤ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከፈታኝ መምህራን ምደባ ጋር በተያያዘ ማንኛውም አይነት ጥያቄ እንደማያስተናግድ ያሳወቀበት ነው)

source-@Temhert_Minister