ግዕዝ
1.63K subscribers
41 photos
4 videos
3 files
46 links
Download Telegram
📜 ልሣነ ግእዝ 📜

የግእዝ ቋንቋን በቀላሉ መማር ፤ ማጥናት ፤ መከታተል ፤ ይፈልጋሉ ? ከታች ያለውን አድራሻ በመጫን በነጻ ይከታተሉ ፡፡
ለጥያቄ እና ለአስተያየት @eyobabebe10

ለ 15 ሰው ሼር በማድረግ ጥንታዊና ቀዳማዊ ቋንቋችንን ለእህት ወንድሞቻችን እናዳርስ ፡፡

👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat/AAAAAFYMhT_hyvIrGJPATA
አልቦ 0
አሐዱ 1
ክልኤቱ 2
ሠለስቱ 3
አርባዕቱ 4
ሐምስቱ 5
ስድስቱ 6
ስብዓቱ 7
ስመንቱ 8
ተሰዓቱ 9
አሠርቱ 10
፩ አሠርቱ ወአሐዱ 11
፪ አሠርቱ ወክልኤቱ 12
፫ አሠርቱ ወሠለስቱ 13
፬ አሠርቱ ወአርባዕቱ 14
፭ አሠርቱ ወሐምስቱ 15
፮ አሠርቱ ወስድስቱ 16
፯ አሠርቱ ወሰብዓቱ 17
፰ አሠርቱ ወስመንቱ 18
፱ አሠርቱ ወተሰዓቱ 19
እስራ 20
፩ እስራ ወአሐዱ 21
፪ እስራ ወክልኤቱ 22
፫ እስራ ወሠለስቱ 23
፬ እስራ ወአርባዕቱ 24
፭ እስራ ወሐምስቱ 25
፮ እስራ ወስድስቱ 26
፯ እስራ ወሰብዓቱ 27
፰ እስራ ወሰመንቱ 28
፱ እስራ ወተሰዓቱ 29
ሠላሳ 30
፩ ሠላሳ ወአሐዱ 31
፪ ሠላሳ ወክልኤቱ 32
፫ ሠላሳ ወሠለስቱ 33
፬ ሠላሳ ወአርባዕቱ 34
፭ ሠላሳ ወሐምስቱ 35
፮ ሠላሳ ወስድስቱ 36
፯ ሠላሳ ወሰብዓቱ 37
፰ ሠላሳ ወሰመንቱ 38
፱ ሠላሳ ወተሰዓቱ 39
አርብዓ 40
ሃምሳ 50
ስድሳ 60
ሰብዓ 70
ሰማንያ 80
ተሰዓ 90
ምዕት 100
፩ ምዕት ወአሐዱ 101
፪ ምዕት ወክልኤቱ 102
፫ ምዕት ወሠለስቱ 103
፬ ምዕት ወአርባዕቱ 104
፭ መዕት ወሐምስቱ 105
፮ ምዕት ወስድስቱ 106
፯ ምዕት ወሰብዓቱ 107
፰ ምዕት ወስመንቱ 108
፱ ምዕት ወተሰዓቱ 109
፲ ምዕት ወአሠርቱ 110
፲ወ፩ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 111
፲ወ፪ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 112
፲ወ፫ ምዕት አሠርቱ ወሠለስቱ 113
፲ወ፬ ምዕት አሠርቱ ወአርባዕቱ 114
፲ወ፭ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 115
፲ወ፮ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 116
፲ወ፯ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 117
፲ወ፰ ምዕት አሠርቱ ወስመንቱ 118
፲ወ፱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 119
፳ ምዕት ወእስራ 120
፴ ምዕት ወሠላሳ 130
፵ ምዕት ወአርብዓ 140
፶ ምዕት ወሃምሳ 150
፷ ምዕት ወስድሳ 160
፸ ምዕት ወሰብዓ 170
፹ ምዕት ወሰማንያ 180
፺ ምዕት ወተሰዓ 190
፻ ክልኤቱ ምዕት 200
፻ወ፩ ክልኤቱ ምዕት ወአሐዱ 201
፻ወ፪ ክልኤቱ ምዕት ወክልኤቱ 202
፻ወ፫ ክልኤቱ ምዕት ወሠለስቱ 203
፻ወ፬ ክልኤቱ ምዕት ወአርባዕቱ 204
፻ወ፭ ክልኤቱ ምዕት ወሐምስቱ 205
፻ወ፮ ክልኤቱ ምዕት ወስድስቱ 206
፻ወ፯ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓቱ 207
፻ወ፰ ክለኤቱ ምዕት ወስመንቱ 208
፻ወ፱ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓቱ 209
፻ወ፲ ክልኤቱ ምዕት ወአሠርቱ 210
፻፲ወ፩ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 211
፻፲ወ፪ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 212
፻፲ወ፫ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሠልስቱ 213
፻፲ወ፬ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአርባቱ 214
፻፲ወ፭ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 215
፻፲ወ፮ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 216
፻፲ወ፯ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 217
፻፲ወ፰ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰመንቱ 218
፻፲ወ፱ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 219
፻፳ ክልኤቱ ምዕት ወእስራ 220
፻፴ ክልኤቱ ምሪዕት ወሠላሳ 230
፻፵ ክልኤቱ ምዕት ወአርብዓ 240
፻፶ ክልኤቱ ምዕት ወሃምሳ 250
፻፷ ክልኤቱ ምዕት ወስድሳ 260
፻፸ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓ 270
፻፹ ክልኤቱ ምዕት ወሰማንያ 280
፻፺ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓ 290
፻ ሠለስቱ ምዕት 300
፻ አርባዕቱ ምዕት 400
፻ ሐምስቱ ምዕት 500
፻ ስድስቱ ምዕት 600
፻ ስብዓቱ ምዕት 700
፻ ስመንቱ ምዕት 800
፻ ተሰዓቱ ምዕት 900
፻ አሠርቱ ምዕት 1000
፻ እስራ ምዕት 2000
፻ ሠላሳ ምዕት 3000
፻ አርብዓ ምዕት 4000
፻ ሃምሳ ምዕት 5000
፻ ሳድስ ምዕት 6000
፻ ሰብዓ ምዕት 7000
፻ ሰማንያ ምዕት 8000
፻ ተሰዓ ምዕት 9000
፻ እልፍ 10,000
፻፻ ክልኤቱ እልፍ 20,000
፻፻ ሠለስቱ እልፍ 30,000
፻፻ አርባዕቱ እልፍ 40,000
፻፻ ሐምስቱ እልፍ 50,000
፻፻ ስድስቱ እልፍ 60,000
፻፻ ሰብዓቱ እልፍ 70,000
፻፻ ስመንቱ እልፍ 80,000
፻፻ ተሰዓቱ እልፍ 90,000
፻፻ አሠርቱ እልፍ 100,000
፻፻ እስራ እልፍ 200,000
፻፻ ሠላሳ እልፍ 300,000
፻፻ አርብዓ እልፍ 400,000
፻፻ ሃምሳ እልፍ 500,000
፻፻ ስድሳ እልፍ 600,000
፻፻ ሰብዓ እልፍ 700,000
፻፻ ሰማንያ እልፍ 800,000
፻፻ ተሰዓ እልፍ 900,000
፻፻ አእላፋት 1,000,000
፻፻፻ ትእልፊት 10,000,000
፻፻፻ ትልፊታት 100,000,000
፻፻፻፻ ምእልፊት 1,000,000,000

@geezlove @eyobabebe10
ነገረ - ነገረ
ነገረት - ነገረች
ነገርከ - ነገርክ
ነገርኪ - ነገርሽ
ነገርኩ - ነገርኩ
ነገሩ - ነገሩ
ነገራ - እነርሷ ነገሩ
ነገርክሙ - ነገራችሁ
ነገርክን - እናንቺ ነገራችሁ
ነገርነ - ነገርን
ይንግር - ይነግራል
ትንግር - ትነግራለች
ትንግር - ትነግራለህ
ትንግሪ - ትነግሪያለሽ
እንግር - እነግራለሁ
ይንግሩ - ይነግራሉ
ይንግራ - እነርሷ ይነግራሉ
ትንግሩ - ትነግራላችሁ
ትንግራ - እናንቺ ትነግራላችሁ
ንንግር - እንነግራለን
@geezlove @eyobabebe10
የግእዝ ፊደላት አካፋፈል

መጀመሪያ ጊዜ ለሄኖስ በጸፍጸፈ ሰማይ (በሰማይ ገበታነት) የተገለጹለት ፊደላት
አሁን በፊደል ገበታ ላይ በቅደም ተከተል እንደምናያቸው ሳይሆን ከዚህ በተለየ
መልኩ ተዘበራርቀውና የእብራይስጡን የቋንቋ ስልት ይዘው ነው እነሱም አሌፋት
በመባል የራሳቸው ስያሜ ነበራቸው
አ – አሌፍ ሐ – ሔት ሠ – ሣምኬት
በ – ቤት ጠ – ጤት ጸ – ጻዴ
ገ – ጋሜል የ – ዮድ ፈ – ፌ
ደ – ዳሌጥ ከ – ካፍ ዐ – ዔ
ሀ – ሄ ለ – ላሜድ ቀ – ቆፍ
ወ – ዋው መ – ሜም ተ – ታው
ዘ – ዛይ ነ – ኖን ረ – ሬስ


በማለት በእብራይስጡ አጠራር ይጠሯቸው ነበር፤ ነገር ግን እነዚህን የግእዝ ፊደላት
በኢትዮጵያ ቀዳማዊ ጳጳስ በአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን የግእዝ ፊደላትን አሻሽለው
አሁን በፊደል ገበታ ላይ የምናያቸውን በቅደም ተከተል ከማስቀመጣቸው በፊት ያሉት
ፊደላት፡-
ቀዳማዊ የግእዝ ፊደላት በሚል ስያሜ የሚጠሩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከሀ – ጀምሮ
በዝርዝር በቀደም ተከተል የምናያቸው ፊደላት ደግሞ ደኀራዊ የግእዝ ፊደላት ብለን
በሁለት እንመለከታቸዋለን፡፡

@geezlove @eyobabebe10
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ገና እንቀጥላለን ሊንኩን share በማድረግ ተባበሩን 500 ቤተሰቦቻችን እንወዳችኋለን።
Promotion ለሰራችሁልኝ እና linkun ላጋራችሁ በሙሉ ፈጣሪ ይስጣችሁ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFYMhT_hyvIrGJPATA
ነባር አንቀጽ (Verb to be)
ውእቱ , ነው፣ ነበር፣ ነሽ፣ ነህ፣ ናችሁ
ይእቲ , ናት፣ ነበረች
ውእቶሙ (ሙንቱ) , ናቸው፣ ነበሩ (ለወንዶች)
ወእቶን (እማንቱ), ናቸው፣ ነበሩ (ለሴቶች )

ምሳሌ ፡- አነ ውእቱ ፍኖተ ጽድቅ
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም
አንተ ውእቱ ቤዛ ኩሉ ዓለም
ማርያም ይእቲ መሠረተ ሕይወት
ጳውሎስ ወጴጥሮስ መምህራን ውእቶሙ
ሰሎሜ ወኤልሳቤጥ ቅዱሳት ውእቶን

@geezlove @eyobabebe10
የአበገደ ፊደላት ትርጉም

የአበገደ ፊደላት የየራሳቸው መጠሪያ ስም እና ትርጉም አላቸው፡፡ በመጀመሪያ
ፊደላቱን ከዚያም መጠሪያቸውን፤ ማለትም የሚወከሉበትና ትርጉማቸውን
እንደሚከተለው እናቀርባለን፡-
አ ፡- አልፍ፤ አሌፍ ብሂል አብ ፈጣሬ ኵሉ ዓለም፤ አ፤ አልፍ፤ አሌፍ ማለት ዓለምን
ሁሉ የፈጠረ አብ ማለት ነው፡፡
በ፡- ቤት ፡- ቤት ብሂል ባዕል እግዚአብሔር፤ በ፤ ቤት፤ ማለት ባለጸጋ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ገ፡- ጋሜል፡- ጋሜል ብሂል ግሩም እግዚአብሔር፤ ገ፤ ጋሜል ማለት የሚያስፈራ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ደ፡- ዳሌጥ፡- ዳሌጥ ብሂል ድልው እግዚአብሔር፤ ደ፤ ዳሌጥ ማለት "ዝግጁ የሆነ" እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ሀ፡- ሄ ፡- ሄ ብሂል ህልው እግዚአብሔር፤ ሀ፤ ሄ ማለት እግዚአብሔር ህልው ዘለዓለማዊ ነው ማለት ነው፡፡
ወ፡- ዋው፡- ዋው ብሂል ዋሕድ እግዚአብሔር፤ ወ፤ ዋው ማለት እግዚአብሔር አንድ ነው ማለት ነው፡፡
ዘ፡- ዛይ፡- ዛይ ብሂል ዝኩር እግዚአብሔር፤ ዘ፤ ዛይ ማለት እግዚአብሔር አሳቢ ነው ማለት ነው፡፡
ሐ፡- ሔት፡- ሔት ብሂል ሕያው እግዚአብሔር ፤ሐ፤ ሔት ማለት ሕያው፤ ዘለዓለማዊ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ጠ፡- ጤት፡- ጤት ብሂል ጠቢብ እግዚአብሔር፤ ጠ፣ ጤት ማለት ጠቢብ፤ ጥበበኛ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
የ፡- ዮድ፡- ዮድ ብሂል የማነ እግዚአብሔር፣እደ እግዚአብሔር፤ የ፤ ዮድ ማለት የእግዚአብሔር
ቀኝ ፤ የእግዚአብሔር እጅ ማለት ነው፡፡
ከ፡- ካፍ፡- ካፍ ብሂል ከሃሊ እግዚአብሔር፤ ከ፤ ካፍ ማለት ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ለ፡- ላሜድ፡- ላሜድ ብሂል ልዑል እግዚአብሔር፤ ለ፤ ላሜድ ማለት እግዚአብሔር ታላቅ ነው ማለት ነው፡፡
መ፡- ሜም፡- ሜም ብሂል ምዑዝ እግዚአብሔር፤ መ፤ ሜም ማለት ጣፋጭ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ነ፡- ኖን፡- ኖን ብሂል ንጉሥ እግዚአብሔር፤ ነ፤ ኖን ማለት እግዚአብሔር ንጉሥ ነው ማለት ነው፡፡
ሠ፡- ሣምኬት፡- ሣምኬት ብሂል ሰፋኒ እግዚአብሔር፤ ሠ፤ ሣምኬት ማለት ገዥ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡
ዐ፡- ዔ፡- ዔ ብሂል ዐቢይ እግዚአብሔር፤ ዐ፤ ዔ ማለት እግዚአብሔር ታላቅ ነው ማለት ነው፡፡
ፈ፡- ፌ ፡- ፌ ብሂል ፍቁር እግዚአብሔር፤ ፈ፤ ፌ ማለት እግዚአብሔር የሚወደድ ነው ማለት ነው፡፡
ጸ፡- ጻዴ፡- ጻዴ ብሂል ጻድቅ እግዚአብሔር፤ ጸ፤ ጻዴ ማለት እግዚአብሔር እውነተኛ ነው ማለት ነው፡፡
ቀ፡- ቆፍ፡- ቆፍ ብሂል ቅሩብ እግዚአብሔር ፤ ቀ፤ ቆፍ ማለት እግዚአብሔር ቅርብ ነው ማለት ነው፡፡
ረ፡- ሬስ ፡- ሬስ ብሂል ርኡስ እግዚአብሔር፤ ረ፤ ሬስ ማለት እግዚአብሔር አለቃ ነው ማለት ነው፡፡
ሰ፡- ሳን፡- ሳን ብሂል ስቡሕ እግዚአብሔር፤ ሰ፤ ሳን ማለት እግዚአብሔር ምስጉን ነው ማለት ነው፡፡
ተ፡- ታው፡- ታው ብሂል ትጉህ እግዚአብሔር፤ ተ፤ ታው ማለት እግዚአብሔር ትጉህ ነው ማለት ነው፡፡
ኀ የሐ፤ እና ፀ የጸ ድርቦች ተደርገው የግእዝ ፊደል በቊጥር ፳፪ እንደሆኑ የሚገልጹ
ሊቃውንት አሉ፡፡ ለምሳሌ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ኀ የሐ እና ፀ የጸ ድርቦች እንደሆኑ
ሁለቱ ፊደላት ፐ እና ጰ ደግሞ ከጊዜ በኋላ እንደተጨመሩ ይገልጻሉ፡፡
የተጨመሩበትንም ምክንያት ሲያስረዱ ሁለቱ ፊደላት በጽርእ፣ በቅብጥና
በሮማይስጥ ያሉ ፊደሎች ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ መጻሕፍት ደግሞ የተተረጎሙት
ከእነዚህ ነውና መጻሕፍቱ ከተተረጎሙበት ቋንቋ ጋር ለማስማማት እንደሆነ
ያስረዳሉ፡፡
ፊደላት ነገረ እግዚአብሔርን እንደሚያስረዱ በሀለሐመ እንዲሁም በአበገደ
አስረድተናል፡፡ የጥንቱ የግእዝ ፊደል የአበገደ እንደሆነ በአለፈውም ገልጸናል፡፡ ይህ
የአበገደ የፊደል ቊጥር ፳፪ ነው ይህም የ፳፪ቱ ሥነ ፍጥረት ምሳሌ ነው፡፡ ስለዚህ
ፊደል የዕውቀት ሁሉ መሠረት፤ የጥበብ ምንጭ ነውና ምርምራችንን ከፊደል
እንድንጀምር ከሚል እሳቤ ይህን አቅርበናል፡፡
ማስታወሻ፡- ኀ የሐ፣ ፀ የጸ ድርቦች ናቸው ስለተባለ ግን የትርጉም ልዩነት አያመጡም
ወይም ተመሳሳይ ድምፆች ( ዘረ ድምፆች) ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ሠረቀ፡- ወጣ፤
ተወለደ፤ ሰረቀ፡- ሰረቀ፤ በንጉሡ «ሠ» እና በእሳቱ «ሰ» ሲጻፍ የትርጉም ልዩነት
እንደሚያመጣ ሁሉ ኀ እና ፀም የትርጉም ልዩነት ያመጣሉ፡፡ ለምሳሌ፡- ፈፀመ በፀሐዩ
“ፀ” ሲጻፍ አሰረ፤ ለጎመ፤ የሚል ትርጉም ሲሰጥ፤ ፈጸመ በጸሎቱ «ጸ» ሲጻፍ ደግሞ
ጨረሰ የሚል ትርጉም ይሰጣል፡፡ እንዲሁም ነስሐ በሐመሩ «ሐ» ሲጻፍ ተጸጸተ፣
ተመለሰ የሚል ትርጉም የሚሰጥ ሲሆን ነስኀ በብዙኃን «ኀ» ሲጻፍ ደግሞ ሸተተ፤
ከረፋ የሚል ትርጉም ይሰጣል፡፡ ስለዚህ በቋንቋ ሥርዓት አንድ ድምፅ የፍች
(የትርጉም) ለውጥ ካመጣ ሞክሼ ወይም ዘረ ድምፅ ሊባል አይችልም፡፡ በመሆኑም
ራሳቸውን የቻሉ የግእዝ ድምፆች እንደሆኑ ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡
@geezlove @eyobabebe10
የዛሬውን ትምህርት ጨርሻለሁ ደህና እደሩልኝ 👋
ለአስተያየት እና ጥያቄ @eyobabebe10
ዛሬ በግል ምክንያት የዛሬው ትምህርት ለነገ ተላልፏል ።
ለተፈጠረው ችግርም ይቅርታ እጠይቃለሁ ።
ለጥያቄና አስተያየት @eyobabebe10
እፎ ሐለውክሙ ሰላም ኩልክሙ 👋
ኢዮብ ነኝ
1ዐ.4 ቦ / አለ/ በመራሕያን ሲረባ/ Verb to have/

ብየ= አለኝ ምሳሌ ምንት ብየ ምስሌኪ ካንቺ ጋር ምን አለኝ
ብከ= አለህ ምንት ብከ ምስሌሃ ከርሷ ጋር ምን አለህ
ብኪ = አለሽ ምንት ብኪ ምስሌሃ ከርሷ ጋር ምን አለሽ
ብነ = አለን ምንት ብነ ምስሌክሙ ከእናንተ ጋር ምን አለን
ብክሙ=አላችሁ ምንት ብክሙ ምስሌሆሙ ከእነርሱ/ ከወንዶች/
ጋር ምን አላችሁ
ብክን= አላችሁ / ለሴት/ ምንት ብክን ምስሌየ ከእኔ ጋር ምን አላቸው
ቦሙ= አላቸው ምንት ቦሙ ምስሌየ ከእኔ ጋር ምን አላቸው
ቦን = አላቸው / ለሴት/ ምንት ቦን ምስሌኪ ከአንቺ ጋር ምን አላቸው
ከላይ ለጠቀስናቸው አፍራሻቸው አል ነው፡፡
ለምሳሌ:-
አልብየ = የለኝም
አልብከ = የለህም
አልብኪ = የለሽም
አልብነ = የለንም
አልቦ = የለንም፣ የሉም፣ የለም
ቦ = አለ ፣አለው
ዘቦ = ያለው
1ዐ.5 ባለቤት ተውላጠ ስም (Subjective Pronoun)
እግዚአብሔር ለሊሁ ፈጠረ ዓለመ / እግዚአብሔር እርሱ ራሱ ዓለምን ፈጠረ/
ለሊሁ የአምር
ለሊከ እግዚኦ ተአምር እበድየ
ለሊከ እግዚኦ ተአምር ጽእለትየ
ለሊከሰ ሕይወተ ታሐዩ
ለሊኪ አውሰብኪ
ለሊሃ ትበልዕ ኩሎ ዘትረክብ
ትአምሩ ለሊክሙ ኩሎ ነገረ ዘኮነ በይሁዳ
ለሊሁሰ እግዚእ ኢየሱስ ኢያጥመቀ ዳእሙ አርዳኢሁ/ ዳእሙ — እንጂ/
ነጠላ ብዙ
ለሊሁ = እርሱ እራሱ / Himself/ ለሊሆሙ = እነርሱ እራሳቸው
(Themselves)
ለሊሃ = እርሷ እራሷ (Herself) ለሊሆን = እነርሱ / ለሴቶች/
(Themselves)
ለሊከ = አንተ እራስህ (Yourself) ለሊክሙ = እናንተ እራሳችሁ
( Yourselves)
ለሊኪ = አንቺ እራስሽ (Yourself) ለሊክን = እናንተ እራሳችሁ /ለሴቶች/
( Yourselves)
ለሊየ /ለልየ = እኔ እራሴ/ ( My self) ለሊነ = እኛ እራሳችን
( 0urselves)
1ዐ.6 ተሳቢ ተውላጠ ስሞች ( Objective Pronouns)
ነጠላ ብዙ
ኪያየ = እኔን ( Me) ኪያነ = እኛን (Us)
ኪያከ = አንተን ( You) ኪያክሙ = እናንተን (You)
ኪያኪ = አንቺን ( You) ኪያክን = እናንተን ( You) ለሴቶች
ኪያሁ = እሱን ( Him) ኪያሆሙ = እነርሱን ( Them)
ኪያሃ = እሷን ( Her) ኪያሆን = እነርሱን ( Them ለሴቶች/
ምሳሌ
ዘርእየ ኪያየ ርእየ አቡየ
መኑ ይጼውእ ኪያከ
ኪያኪ ሰናይተ ዘፈጠረ እግዚአብሔር ይትባረክ
ቀድሱ ኪያሁ ወባርኩ ስሞ
አምላክነ አድኀነ ኪያነ እሞት
ዘተወክፈ ኪያክሙ ተወክፈ ኪያየ
ፈኑ ኪያሆሙ ኀበ አሕዛብ
ርእየ ኪያክን ወተፈስሐ ብክን
® ስለዚህ ተሳቢ ማለት “ን” የሚለውን ቃል ወይም ፊደል
የሚያመጣ ማለት ነው፡፡
የሚያበዙ ፊደላት
አ፡-
ነጠላ ብዙ የብዙ ብዙ
ደብር አድባር አድባራት
ርእስ አርእስት
ከዚህ ላይ የቃላቱን መጨረሻ ሁለት ፊደላት ማስተዋል ነው፡፡
ብር፣ እስ / ሳድስ ናቸው፡፡/
ን፡- ሀ. ደራሲ + ያን = ደራስያን
ሠዓሊ + ያን = ሠዓልያን
ለ. ኢትዮጵያዊ +ያን = ኢትዮጵያውያን
ሐ. ቅዱስ = ቅዱሳን
ብፁዕ = ብፁዓን
መዘምር = መዘምራን
ከዚህ ላይ የቃላቱ የመጨረሻው ሁለት ፊደላት ራብዕና ሣልስ ናቸው፡፡
ራሲ፣ ዓሊ፣ እንደገና የመጨረሻዎቹ ሁለት ፊደላት ፁዕና ዱስ ይላል፡፡
ት፡- ኢትዮጵያዊት+ ያት – ኢትዮጵያውያት
ሰማይ = ሰማያት
ቅድስት = ቅዱሳት
ሠናይት = ሠናያት
v አሁንም ቢሆን የቃላቱን ሁኔታ ማስተዋል ነው፡፡
መ፡- ኩሉ — ኩሎሙ ለሊሁ — ለሊሆሙ
አንተ —አንትሙ ለሊከ —ለሊክሙ
እ፡- ኃጢአት — ኃጣውእ
ይ ፡- መርዔት= መራዕይ ል ፡- ኪሩብ = ኪሩቤል
ሌሊት = ለያልይ ሱራፊ = ሱራፌል
ው ፡- ዕፅ = ዕፀው
አብ = አበው
እድ = እደው
የጸያፍ አበዛዝ ምሳሌ
መምህራን፡ መምህራኖች
ደራሲያን ፡ ደራስያኖች
ቅዱሳን ፡ ቅዱሳኖች
ማስታወሻ፡- የጸያፍ አበዛዝ ማለት ፈጽሞ
ግእዝም አማርኛም ያልሆነና ከሕግ
ውጭ የሆነ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ
ከላይ የተጠቀሱት ቃላት
አላዋቂነት ካልሆነ በቀር ፈጽሞ
አይባሉም፡፡

@geezlove @eyobabebe10
ትክክልኛ promoter ከፈለጋችሁ @btbabi አናግሩት
ወንድሜ ፈጣሪ ይስጥህ።
ንግግር ፨
ከቻላችሁ ለሁለት ሁናችሁ ተለማመዱት አርድዕተ ግዕዝ
#ኢዮብ ፡ ሰላም ላኪ (ሰላም ላንቺ !!!ይሁን)
#ገነት፡ ወሰላም ለከ እኁየ (ሰላም ላንተም ይሁን ወንድሜ)
#ኢዮብ ፡ ቡሩክ ሀሎ (ቡሩክ አለ)
#ገነት ፡ ናሁ ወጽአ እምነ ማኅደሩ (አሁን ከቤት ወጣ)
#ኢዮብ ፡ እምአይቴ ሖረ ይመስለኪ (የት የሄደ ይስልሻል)
#ገነት፡ ኀበ ቅድስት ማርያም (ወደ ቅድስት ማርያም)
#ኢዮብ ፡ ዮም ቀዳሲ ውእቱ (ዛሬ ቀዳሽ ነው)
#ገነት ፡ አኮ (አይደለም)
#ኢዮብ፡ ማእዜ ይትመየጥ (መቼ ይመለሳል)
#ገነት ፡ ዐሠርቱ ሰዓት ይመጽእ (አሥር ሰዓት ይመጣል)
#ገነት ፡ በድኅር ነዓ አው ንስቲት ጽንአ እስከ ፲ቱ ሰዓት (በኋላና ወይም አስከ አሥር ሰዓት ቆይ)
#ኢዮብ፡ ኦሆ እምዝንቱ እነብር (እሺ ከዚህ እቀመጣለሁ)
#ኢዮብ ፡ ኵለሄ ቤተክርስቲያን ውእቱ (ሁል ጊዜ ቤተክርስቲያን ነዉ)
#ገነት፡ ውእቱሰ ኀረየ መክፈልተ ሠናየ (እሱስ መልካም/በጎ/እድልን መረጠ)
#ኢዮብ : ምንት ነሲኦ ውእቱ ዘሖረ (ምን ይዞ ነው የሄደው)
#ገነት ፡ መጽሐፍ ቅዱስ
#ኢዮብ ፡ አንሰ አሌሊተ አልብየ ተስፋ(እኔስ ወዮልኝ ተስፋም የለኝ)
#ገነት ፡ ዮኒከ ዘወድቀ ይትነሣእ (አይዞህ የወደቀ ይነሣል)
#ኢዮብ፡ ወኀልቀ ዘመንየ በከንቱ (ዘመኔ በከንቱ አለቀ)
#ገነት፡ ኢታማስን ተስፋከ ባሕቱ ጽንአ በሃይማኖት ወግበር ሠናየ (ተስፋህን አታጥፋ ነገር
ግን በሃይማኖትህ ጽና መልካምን አድርግ)
#ኢዮብ ፡ ይኲነኒ በከመ ትቤለኒ (ይሁንልኝ ይደረግልኝ)
#ገነት ፡ አሜን (ይሁንልን)
@geezlove @eyobabebe10
ልሳነ-ግዕዝ!!!
ትርጓሜ ዕለታት ወአውራህ !!!
የዕለታት እና የወራት ፍቺና ስርዎ ቃላቸው!!! በዝንቱ ዕለት ንሬኢ ትርጓሜ ዕለታት!!!
#የዕለታት_ፍቺና_ስርዎ_ቃላቸው!!!
ግዕዝ አማርኛ ፍቺ
እሑድ እሑድ አሐደ - አንድ አደረገ ፡ አንደኛ ፡ የቀን መጀመሪያ
ሰኑይ ሰኞ ሰነየ- ሁለት ሆነ ሁለተኛ ቀን
ሠሉስ ማክሰኞ ሠለሰ - ሦስት አደረገ ፡ ፫ኛ ቀን ፡ ማግስተ ሰኞ
ረቡዕ ሮብ ረብዐ - አራት አደረገ ፡፡ ፬ኛ ቀን ማለት ነው፡፡
ኃሙስ ኃሙስ ኀመሰ - አምስት አደረገ ፡፡ ፭ኛ ቀን
ዓርብ ዓርብ ዐርበ - ገባ መሸ ፡፡የስራ ወይም የምግብ መካተቻ የሰንበት መግቢያ/ዋዜማ
ቀዳሚት ቅዳሜ ቀደመ - ቀደመ የመጀመሪያ ሰንበት!!!
@geezlove @eyobabebe10
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ #ደብረ_ታቦር (ቡሄ) በዓል በሰላም አደረሣችሁ፡፡ #መልካም_በዓል!
@geezlove @eyobabebe10
እፎ ሐለውክሙ ሰላም ኩልክሙ 👋
አርድእተ ግእዝ ንህነ ዮም ንነጽር ተሰሐቢ መራህያን ምስለ ትርጓሜሆን
የባለቤት መራህያን የተሳቢ
ትርጉም መራህያን
አነ = እኔ ኪያየ = እኔን
ንሕነ =እኛ ኪያነ = እኛን
አንተ = አንተ ኪያከ =አንተን
አንትሙ = እናንተ(ለወንድ) ኪያክሙ = እናንተን
አንቲ = አንቺ ኪያኪ =አንችን
አንትን = እናንተ(ለሴት) ኪያክን = እናንተን
ውእቱ = እሱ ኪያሁ = እሱን
ውእቶሙ = እነሱ(ለወንድ) ኪያሆሙ = እነሱን
ይእቲ = እሷ ኪያሃ = እሷን
ውእቶን = እነሱ(ለሴት) ኪያሆን = እነሱን
እነዚህ የግእዝ መሰረቶች ናቸው በመሆኑም አንድ የግእዝ ተማሪ የግድ እነዚህን ማዎቅ አለበት።
ኢዮብ ነበርኩ ደህና እደሩልኝ
@geezlove @geezlove

ለአስተያየት እና ጥያቄ @eyobabebe10
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ገና እንቀጥላለን ሊንኩን share በማድረግ ተባበሩን 700 ቤተሰቦቻችን እንወዳችኋለን።

https://t.me/joinchat/AAAAAFYMhT_hyvIrGJPATA
#አጋፋሪ_ይደግሳል_፡፡
፩ኛ ትርጕም አጋፋሪ፤ አሁን በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ደረጃ የማኅሌቱን ሥርዐት ፥ የዝክር ሁኔታን የሚያስተባብር አጋፋሪ ሲባል፤ ምክትሉ መጨኔ ይባላል፡፡
፪ኛ ትርጕሙ፤ አጋፋሪ፤ በቀድሞ ዘመን በሃገራችን በተለይም በቤተ መንግሥት ያለ ሹመት ሲሆን፤ (በጎንደር ፥ በሸዋ ፥ በትግሬ ፥ በወለጋ፥ በአሊባቡር፥ በሐረርጌ፥ በጅማ፥ በወሎ አጋፋሪ ተብሎ ሲጠራ በጎጃም መጨኔ ይባላል/
ሁለቱንም በቀድሞ ዘመንም ሆነ አሁን ባለው ሁኔታ ትርጕሙን እናያለን ፤
፠፠፩ኛ ፠፠ አሁን ካለው የቤ/ክን አገልግሎት አንጻር፤ አጋፋሪ ማለት የማኅሌቱን ሥርዐት ፥ የዝክር ሁኔታን የሚያስተባብር ሲሆን ምክትሉ መጨኔ ይባላል፡፡ ይህ አጋፋሪ በደብረ ታቦር በዓል ላይም በቅዱስ ሚካኤል ተመስሎ፤ ‹‹ሆያ ሆዬ›› ይባላል፡፡ ይኸውም
‹‹#ሆያ_ሆዬ_ሆ_››፤ ማለት ጌታው ሆዬ ፥ እሜቴ ሆዬ ለማለት ነው፡፡
‹‹#እዚያ_ማዶ_ጢስ_ይጤሳል_›› የተባለው፤ እስራኤላውያን በበረሃ ለ40 ዓመታት ሲጓዙ ደመና እየጋረዳቸው (እየጤሰ) ስለመራቸው ነው፡፡
‹‹#አጋፋሪ_ይደግሳል_››፤ የተባለው አጋፋሪው /አለቃው/ ቅዱስ ሚካኤል ሲሆን፤ ይደግሳል መባሉ እስራኤላውያንን ‹‹በዕደ መልአኩ ይዕቀበነ ፥ ሰላመ ዚአሁ የኀበነ›› እንዲል፤ በአምላክ ትዕዛዝ ቅዱስ ሚካኤል መናን ከደመናን ፥ ውኃን ከጭንጫ ዓለት እያፈለቀ (እየደገሰ) መርቷቸዋልና ነው፡፡
****እንዲሁም የአብነት (የቆሎ) ተማሪዎች በክረምት ሲለምኑ የቆዩትን አጠራቅመው፤ የደብረ ታቦር ዕለት ብርሃነ መለኮቱን የገለጠ ጌታ ለኛም እንዲገልጥልን ብለው፤ ደግሰው ለሕዝቡ ያበላሉ ፥ ያጠጣሉ፡፡ /ይህ ሥርዐት በደብራችንም የሚከናወን ድርጊት ነው፡፡/
‹‹#ያችን_ድግስ_ውጬ_ውጬ_››፤ የተባለውና በድግስ የተመሰለው መና ሲሆን፤ በደጋሹ ቅዱስ ሚካኤል አማካይነት እስራኤል 40 ዓመታት መመገባቸውን (መና መዋጣቸውን) መናገር ነው፡፡
‹‹#ከድንክ_አልጋ_ተገልብጬ_›› ፤ ድንክ አልጋ የምትመች እንደሆነች ሁሉ ፥ በድንክ የምትመሰለውንና የምትመቻቸውን ተስፋዪቱ ምድር ኢየሩሳሌምን መውረሳቸው መናገር ነው፡፡
‹‹#ያቺ_ድንክ_አልጋ_አመለኛ_#ያለአንድ_ሰው_አታስተኛ_››፤ መባሉ እስራኤል ከግብጽ ሲወጡ 600,000 ሆነው ሲሆን፤ ሁሉም በምድረ በዳ አልቀው ኢየሩሳሌምን የወረሳት ሴትና ሕፃናት ሳይቈጠሩ፤ አንድ ኢያሱና አንድ ካሌብ ናቸው ለማለት ነው፡፡

፠፠፪ኛ ፠፠ አጋፈረ፤ግስ ሲሆን በቤተ መንግሥት ፥ በግብዣ ቦታ፥ …. በር ላይ ቆሞ የሚገባውንና የሚወጣውን ሰው አስተናበረ አስተናገደ፡፡
*አጋፋሪ፤ ቅጽል ሲሆን፤ ቃሉ የቀድሞ አማርኛ ሲሆን አስተናባሪ (ብዙውን ጊዜ በግብዣ ወይም በቤተ መንግሥት በር ላይ በመቆም ሥርዐት የሚያስከብር ማለት ነው፡፡
*አጋፋሪ፤ የድግስ አለቃ ፥ አስተናጋጅ ነገሥታት ግብር ሲያገቡ (ግብዣ ሲጋብዙ ፥ ድግስ ሲደግሱ) ወደ አዳራሹ (ወደ ድግሱ) እንዲገቡ የሚፈቅድ ፥ የማይገባቸውንም የሚከለክል፤ ከገቡም በኋላ እንደ የክብራቸውና እንደየማዕርጋቸው አንተ በዚህ ሁን ፥ አንተ በዚህ ተቀመጥ እያለ የሚያስቀምጥ፤ ኋላ የድግሱ ምግብና መጠጥ መታደል ሲጀምርም፤ እንጀራና ጠጅ አሳላፊዎችን የሚያዝና የሚቈጣጠር ትልቅ ሹም ነው፡፡
* አጋፋሪ፤ የሚለው መጠሪያ በ17ኛወና በ18ኛው ክፍለ ዘመን የታወቀ የቤተ መንግሥት ሹም መጠሪያ ነው፡፡ ‹‹ህዱግ ራስ›› በመባል የሚታወቅም ነው፤ በቤተመንግሥት የሚካሄዱ ሥራዎችንና የፍርድ ሂደቶች ያስተባብራል፤ አንዳንዴ ደግሞ የክፍላተ ሃገር የፍርድ ሰጪ ሰዎች ስም ሆኖም ያገለግላል፤ የስሜን (ከጎንደር በስተሰሜን የሚገኝ ግዛት ነው) አስተዳደር የሚገዛ ሰው ደግሞ የሰሜን አጋፋሪ እየተባለም ይጠራል፤ (ለምሳሌም አፄ ሱስንዮስ ልጃቸውን ፋሲለደስን የስሜን አጋፋሪ ብለው ሹመወት ነበር፤ ይህ የስሜን አጋፋሪ የሚለው ሹመትም እስከ 20ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ቆይቶ ነበር፡፡

#ቡሄ_
ቡሄ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጸበት የነሐሴ 13 ቀን መጠሪያ ስሙ ነው የሚሉ ሊቃውንት እንዳሉ ሁሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፤
ቡሄ የሚባለው፤ ከነሐሴ 13 በኋላ እስከ መስከረም 17 መስቀል ድረስ ሲሆን፤ በተለይም ይህ በዓል የሚታወቀው በሸዋና ወሎ /እስከ ጋይንት ጫፍ መጋጠሚያ) ድረስ ሲሆን፤ በዚህ ወቅትም ክርስትና አባት ለክርስትና ልጁ ተማሪ ከሆነ መጻሕፍትን (ዳዊት፣ …)፣ እንዲሁም አልባሳትን፣ በግና ሙክት ፍየልን የሚሰጥበት ነው፡፡ ሕፃናትና ወጣቱም ‹‹ቡሄ ፥ ሆ ….. ›› እያለ ይጨፍራል ፤ የሚሰጠውንም ሙክትና በግ እስከ መሰቅል ድረስ ሲያጠራቅም ከርሞ ለመስቀል ዕለት አርዶ ይበላል ፥ ደስታን ያደርጋል፡፡
ምንጭ፤ የቃል ትምህርት
/የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

@geezlove @eyobabebe10
እፎ ሐደርክሙ ሰላም ኩልክሙ 👋
የግዕዝ መርሐግብሩ ሰሞኑን ሲቆራረጥ ስለነበር በጣም ይቅርታ!!!
ከዚህ በኋላ የግዕዝ መርሐግብሩ በሳምንት 3 ቀን እንማማራላን ።
ቀኖቹም
እሁድ ማክሰኞ እና አርብ
የሚስማማ
ይቀየር የምትሉ ደግሞ
የማትስማሙ ቀኖቹን በ @eyobabebe10 ላይ ገብታችሁ መምረጥ ትችላላችሁ።