8.71K subscribers
14 photos
4 videos
9 files
12 links
The future starts here!
Download Telegram
"ሁሉም ሰው ጂኒየስ ነው፤ ግን አሳ ከዛፍ ዛፍ በመዝለል ችሎታው ከተመዘነ እድሜ ልኩን የማይረባ እንደሆነ ያምናል" ይለናል አልበርት አንስታይን

ድክመታችንን ከሌሎች ጥንካሬ ጋር ካወዳደርነውማ ሁሌም የበታችነት ይሰማናል፤ ከሌሎች ዝቅ ያልን ይመስለናል። አንተ ጂኒየስ የምትሆንበትን የህይወት አላማህን እወቀው! ሌላው አያሳስብህ!

ደስ የሚል ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ከአንተ የሚጠበቀው!

በተግባር የምትገልጠው ማንነት ያስፈልግሀል፤ ከ 5 ዓመት ወይ ከ 10 ዓመት በኋላ መሆን የምትፈልገውን ሰው አሁን መሆን መጀመር አለብህ!

በቃ ካንተ የሚጠበቀውን ሁሉ አድርግ! በየቀኑ በጥረትህ የሚገነባ እንጂ ከሰማይ የሚወርድ ማንነት የለም!

የተለየ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ዳይ ማጥናት ጀምር!

ለእራት ሲያስቡን ለምሳ አረግናቸው እንደሚባለው የትም አይደርስም ብለው ለሚያስቡህ እንደተሳሳቱ ማሳየት አለብህ!

ያ የሚሆነው ደግሞ ማንም ሳይነግርህ ማጥናት ከጀመርክና ከበረታህ ብቻ ነው።

የለውጥ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ማትሪክን ከ 500 በላይ እናመጣለን!

የ 4 ዓመት ልፋትህን የሚወስነው የ 2 ሰዓት ፈተና ነው። ፈተና ክፍል ስትሆን የምታደርገው ነገር፤ ተረጋግተህ መስራትህ ወይ መደናበርህ ውጤትህን ይወስነዋል።

በዚህ ሰዓት በጣም ወሳኙ ነገር መረጋጋት ነው፤ በተለይ ፈተና አጭር ቀን ስለቀረው ያወጣሀቸውን ኖቶች ገለጥ ገለጥ እያደረክ እያቸው፤ በጣም ብዙ የማትሪክ ጥያቄ ስራ።

ስለ ፈተና ሳይኮሎጂ ይበልጥ ለማወቅ ኮርሳችንን ከፍተህ ማየት ነው። ከ 500 በላይ ታመጣለህ! ታመጫለሽ!

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑 እነዚህን 3 ነገሮች ሁሌም አስባቸው

1. አላማ ይኑርህ አለበለዚያ ጊዜው ሲገፋ በዘፈቀደ የሚኖር ከንቱ ሰው እንደሆንክ ማሰብህ አይቀርም፤

2. ወደ አላማህ አንድ እርምጃም ቢሆን የሚያስጠጋህን ነገር በየቀኑ አድርግ፤ ስለዚህ በየቀኑ አጥና፣ ጥያቄ ስራ

3. በፈጣሪህ ታመን ከዛ ልበሙሉነት ፀባይህ ይሆናል ግን ሲሳካልህ አመስጋኝ እንጂ ጀብደኛ አትሁን!

ግሩም ምሸት ተመኘንላችሁ🙏
@futureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
የዘራኸውን ታጭዳለህ!

አይምሮህ ውስጥ ምንድነው የምትዘራው? መልካም ሀሳብ ወይ መጥፎ ሀሳብ? አንድ ነገር ግን እርግጠኛ ነኝ፤ የዘራኸውን ታጭዳለህ! ደጋግመህ ያሰብከው ሀሳብ በህይወትህ ውስጥ በተግባር ይገለጣል።

ከሚያበረታቱህ ሰዎች ጋር ብቻ ዋል፤ በጎ ነገር ብቻ ስማ፤ ብቻህን ስትሆን ራስህን አድንቅ፤ እንደምትችል ለራስህ ንገረው፤ አየህ ጠንካራ ስብዕና የሚገነባው እንደዚህ ነው።

ግሩም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ደስ ይበልህ!

እውነተኛ ለውጥ በፈተናና በችግር የተሞላ ነው፤ ከንብ ማር መውሰድ የሚፈልግ ሰው ንድፊያዋን መታገስ አለበት።

ወዳጄ ነገሮች ከባድ ሲሆኑ ብታዝን፣ ብታማርር ወይ ራስህን ብትጎዳ ምንም አትፈጥርም! በፈተና ደስ ይበልህ ምክንያቱም ጠንካሮች ናቸው የሚፈተኑት! 

ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ማቆም የለም!

ነገሮች ከፍ ዝቅ እያሉ ይሆናል፣ ከመቀጠል ይልቅ ማቆም የተሻለ የሚመስልበት ሁኔታ ውስጥ ልትገባ ትችላለህ ግን ሁሉንም እርግፍ አርጎ መተው ቀላል ነው፤ ሀይል ሰብስቦ መቀጠል ነው ከባዱ!

ወዳጄ ለራስህ የምትሆነው ከዛ ለምትወዳቸው የምትደርሰው ተስፋ ሳትቆርጥ ከቀጠልክ ብቻ ነው። ለዛ ነው መበርታት ያለብህ፤ ዳይ ያቆምከውን ቀጥል አሁኑኑ!

ተስፋ የሞላው ህይወት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
የተግባር ሰው መሆን አለብህ!

የሆነ ነገር ካሳመነህ ለማድረግ መወሰን አለብህ፤ ውጤታማ ለመሆን በደምብ ማጥናት ብዙ ጥያቄ መስራት እንዳለብህ ካወክ ወደ ተግባር መግባት አለብህ!

ፈጣን ለውጥ የምታየው በማወቅ ብቻ አይደለም፣ በማድረግ ነው! የተግባር ሰው በመሆን ነው።

@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ተመስገን በል!

የዛሬ ሳምንት እንደምትሞት ቢነገርህ አሁን ያስጨነቀህ ነገር ሁሉ ተራ እንደሆነ ይገባሀል! ከጎደለህ ይልቅ የተደረገልህ ይበልጣል! ስለዚህ ተመስገን በል ወዳጄ!

የምስጋና ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
የስኬት Formula 👉 እምነት + ጥረት = ውጤት

ፈጣን ለውጥ ከፈለክ የፈለከውን ማሳካት እንደምትችል እመን፤ ከዛ ውጤታማ ለመሆን ካንተ የሚጠበቀውን ጥረት አድርግ! አለቀ በቅርቡ ለውጡን ታየዋለህ።

ፈጣሪ የሚያስገርም አቅም ሰቶሀል!ከማንም አታንስም! ከለፋህ እንደሚሳካልህ 100% እመን፤ ከዛ ከአሁን ጀምረህ አጥና፣ ጥያቄ ስራ፣ ለነገ ስኬትህ አሁን ዋጋ ክፈል!

@Futurexethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
አሁንም ታገስ!

የምትችለውን እያደረክ ይሆናል ግን የፈለከውን ውጤት ማየት አልቻልክም፤ "ለምን እባክናለው? እንደውም አቆመዋለው!" ልትልም ትችላለህ፤ እውነት አለህ ወዳጄ።

ግን አቁመህስ ምን ትፈጥራለህ? ማቆም መፍትሄ ሆኖ አያውቅም፤ ስለዚህ ታገስ! ካልታገስክ ተዓምር አታይም። ደግሞ አትጓጓ! ከጓጓህ ከመንገድ ትቀራለህ።

የሚደንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@futureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
አሁን ጀምር!

ከአሁን ጀምሮ ራስህ ላይ ብትሰራ በዚህ አለም የሚኖርህን ቀሪ ቆይታ ማሳመር ትችላለህ፤ ስለማትቀይራቸው ነገሮች አብዝተህ ማሰብ አቁም!

ትናንትን መቀየር አትችልም፤ ዛሬን መጠንከር ከዛ ነገህን ማሳመር ትችላለህ። ወዳጄ ለምንም ነገር አልዘገየህም አጥብቀህ የምትፈልገውን ነገር አሁን ጀምረው!

የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ተዓምር ትሰራለህ!

አሸናፊ የሆንከው በፈጣሪ መመካት ስትጀምር ነው፤ ስለዚህ ምንም ነገር ብትሞክር ወይ ታሳካዋለህ ወይ የሚገርም የህይወት ትምህርት ትማርበታለህ። ምንም ነገር ለመጀመር አትፍራ!

ወዳጄ ህልም ካለህ፣ ጥረት ብትጨምርበት እና የአላማ ፅናት ብታዳብር ካሰብከው በላይ ተዓምር ትሰራለህ! አሸናፊ መሆን የሚፈልግ ሰው ይሄን ማድረግ ነው የሚጠበቅበት።

ተዓምረኛ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
በከንቱ አትጨነቅ!

አንዳንዴ አንተ ስለተጨነክ ብቻ የማትቀይራቸው ነገሮች አሉ፤ ሸክላው ራሱን ከሚያውቀው በላይ ጠፍጥፎ የሰራው ሸክላ ሰሪው ጠንቅቆ ያውቀዋል፤ ካንተ በላይ የሚያውቅህና የሚያስብልህ አምላክ አለህ! በከንቱ መጨነቅ አቁም!

የምትችለውን ሁሉ አድርግ፤ ከዛ የሚገጥምህን መራራ ይሁን ጣፋጭ ነገር ለመቀበል ተዘጋጅ፤ ወዳጄ ጀግና እንዲህ ነው የሚያደርገው!

ብርታት የሞላው ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ጥረትህን አታቁም!

ከጓደኞችህ ወይ በዙሪያህ ካሉ ሁሉ ኋላ መቅረትህን አትጥላው፤ ምክንያቱም ረጅም ርቀት ለመወርወር ወደ ኋላ በደምብ መንደርደር ወሳኝ ነው።

እየታሸህ ያለኸው በደምብ እንድትበስል ነው፤ እድል ጓዟን ጠቅልላ እጅህ እስክትገባ ጥረትህን እንዳታቆም! የዚህ አለም እድለኞች አብዝተው የሚለፉ እንጂ አብዝተው የሚመኙ አይደሉም።

ሰናይ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
እችላለሁ በል!

ለትልቅ አላማ ነው ወደዚህ ምድር የመጣኸው ግን የምትፈልገውን ሁሉ ማሳካት እንደማትችል እያመንክ ስለሆነ ከአብዛኛው ሰው ጋር ለመመሳሰል እየጣርክ ነው። እንደ ንስር ከፍ ብለህ መብረር እየቻልክ ለምን እንደ ዶሮ መሬት ትጭራለህ?

ትልቅ ነገር የምታሳካው መጀመሪያ በነፃነት ትልቅ ማሰብ ከቻልክ ነው፤ አየህ መጀመሪያ ሀሳብ ትዘራለህ ከዛ ወደ ተግባር ትገባለህ። ወዳጄ አልችልም የሚለውን ትብታብ በጥሰህ የፈለከውን ሁሉ ለማሳካት ፈጣሪ እንደፈቀደልህ ራስህን አሳምነው! አሁን ለራስህ እችላለሁ ከማለት ጀምር!💪

የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ
@futureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🛑ለ 12 ክፍል ኢንትራንስ ተፈታኞች በሙሉ ለፈተና ማድረግ ያለባችሁ 3 ወሳኝ ነገሮች

(ይሄን ወሳኝ መረጃ ለተፈታኞች በሙሉ ሼር አድርጉት በጣም ይጠቅማቸዋል)

1. ተረጋጋ!

የ 12 ዓመት ልፋትህ በእነዚህ 3 ቀናት ፈተና ይወሰናል፤ ስለዚህ መጀመሪያ በጣም የሚያስፈልግህ መረጋጋት ነው። የፈተና ወረቀቱ እስኪሰጥህ ድረስ ራስህን አረጋግተህ መልካም ነገር አስብ፣ ከቻልክ አጭር ፀሎት አድርግ።

2. ከቀላሉ ጀምር

ጥያቄዎቹን መስራት ስትጀምር አስቀድመህ ቀላሉን ስራ፣ ከባድና ጊዜ የሚወስዱ ጥያቄዎችን ቀላሉን ሰርተህ ስትጨርስ ተረጋግተህ ትሰራቸዋለህ። ቀላሎቹን ቀድመህ መስራትህ ኮንፊደንስህን ይጨምረዋል፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ለከባድ ጥያቄዎች ብዙ ጊዜ ይተርፍሀል። ( የብዙ ተማሪዎች ችግር ቀድመው ከባድ ጥያቄዎችን ይሰሩና ጊዜ ያባክናሉ፣ ቀላሎቹን ሳይሰሩ ሰዓት አልቋል ይባላሉ፤ ይሄን ስህተት አንተ እንዳትሰራ!)

3. አታካብድ! የዓለም ፍፃሜ አይደለም!

የምታቀውን ተረጋግተህ ስራ፤ የማታቀው ብዙ ቢሆን እንኳን አትጨናነቅ፤ አንተ በሙሉ አቅምህ መስራትህን እርግጠኛ ሁን ሌላውን ለፈጣሪ ተወው። ካንተ በላይ የሚያስፈልግህን እሱ ያውቃል፤ ተጨንቀህ ምንም አታመጣም! የ 12ኛ ክፍል ፈተና የዓለም ፍፃሜ አይደለም፤ ፈተና ወድቀው የሚፈልጉትን ያሳኩ ሰዎች ብዙ ናቸው! አንተ ግን የምትችለውን ስራ! አትኮርጅ! ላንተ ካለው የሰራኸውን ፈጣሪ ባርኮልህ ታልፋለህ! አለቀ!

ለ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ መልካሙን ሁሉ እመኛለው! ይቅናችሁ! ፈጣሪ የልባችሁን ያሳካላችሁ!
ስነወርቅ ታዬ (FutureX CEO)

@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
እምነት!

ወዳጄ ልፋትህ መና የሚቀር ከመሰለህ ተሸውደሀል፤ ፀሎትህ ደመና ላይ የሚንሳፈፍ ከመሰለህ የፈጣሪ አሰራር አልገባህም ማለት ነው።

ከጠየክ የማይሰጥህ ነገር የለም፤ ወዳጄ ተስፋ ቆርጠህ ልታቆም ስትል ይሄንን ሀሳብ አስታውስ 'አንተ ስትጨርስ እሱ ይጀምራል!' ከልፋት በኋላ ደስታ....ከመጨነቅ በኋላ እርካታ እንዳለ አማኞች ምስክር ናቸው!

የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ🙏
@FutureXethiopia
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
ሰላም የ FutureX ቤተሰቦች 🙌

ለትምህርታችሁና ለነገ ህይወታችሁ ውጤታማ እንድትሆኑ በጣም ጎበዝና በብዙ ነገር ስኬታማ የሆኑ ተማሪዎችን ይዘንላችሁ እንቀርባለን።

የዛሬው እንግዳችን የ 12ኛ ክፍል ፈተናውን 607 በማምጣት ያለፈና ብዙ አይነት ፈጠራዎችን ሮቦቶችን ጨምሮ የሚሰራ ተማሪ ነው። ብዙ የሚጠቅም ነገር እንደምታገኙበት እምነታችን ነው!

🛑ቪዲዮውን ለማየት ከታች ያለውን ሊንክ መጫን ብቻ ነው👇👇

https://youtu.be/wa2ZGLX28a0