FutureX
25.5K subscribers
17 photos
23 videos
15 files
54 links
The future starts here!
Download Telegram
ነገ 2ኛ ዙር Pilot ፈተና ይኖረናል! ተዘጋጁ‼️

የFutureX አባላት እስካሁን ባሳያችሁት አስገራሚ Performance በሁላችሁም ኮርተናል! አጨራረሳችንን ካሳመርን ኢንትራንስ የኛ ነው! ያልተፈተናችሁት ፈተና ካለ ተፈተኑ፤ ያልጨረሳችሁትን እንድትጨርሱ የዛሬውን ቀን ነፃ አድረገንላችኋል። 

እስካሁን ያሉትን ፈተናዎች የጨረሳችሁ ተማሪዎች የሚናስቸግራችሁን ት/ት ምዕራፎች ከልሱበት። ለ SAT ሁሌም የማይቀሩ Vocabularies Shortnote'ቱ ላይ አሉ፤ በደምብ እወቋቸው። በዚህ ወቅት Effectively ከተዘጋጃችሁ ውጤታችሁ በጣም ከፍ ይላል! በርቱ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
56🙏52🏆13👍8🫡7🔥2🎉2🤝2
🛑 Math's ኖት ተለቋል! ለነገው ወሳኝ ፈተና ተዘጋጁ‼️

ቃል በገባነው መሰረት የ 4 ዓመቱን ት/ት በ 10 Chapter ከፋፍለን ብሔራዊ ፈተና ላይ የማይቀሩትን ነገሮች የያዘ ኖትና በተደጋጋሚ የሚጠየቁ የኢንትራንስ ጥያቄዎችን የያዘ ፋይል FutureX አፕሊኬሽን ላይ ለቀናል። በነፃ ከፍታችሁ ተጠቀሙበት፤ ለ Math's ፈተና ማወቅ ያለባችሁን ሁሉ የያዘ ነው።

ነገ 2ኛ ዙር Pilot ፈተና ይኖረናል፤ ይሄንን ፈተና Typical ኢንትራንስ ማለት ይቻላል፤ በጥንቃቄ ፈተና ክፍል እንዳላችሁ ቆጥራችሁ ስሩት። የጊዜ አጠቃቀም፣ የማስታወስ ብቃታችሁን ፈትሹበት፤ ውጤታችሁ ምንም ቢሆን ስህተታችሁን በ Correction ማስተካከል አትርሱ። እናንተ ከጣራችሁ ፈጣሪም ይረዳችኋል!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
113🙏30👍8🔥6🏆6🤝4🆒4👏1
🛑 ሁለተኛ ዙር Pilot (2016) ፈተና ዛሬ ጀመረ‼️

ዛሬ English እና Maths ትፈተናላችሁ። የዛሬ 15 ቀን የሀገሪቱን ትልቅ ፈተና ትወስዳለህ፤ ማለፍና መውደቅ ያኔ ይወሰናል። አሁን የምትፈተነው ፈተና የሚጠቅምህ ለዛ ወሳኝ ቀን እንደሆነ አስታውስ! ስለዚህ ከልብህ ፈተናውን ስራ፤ ቀጣይ የህይወትህ ምዕራፍ ምርጥ ይሆናል!

የፈተና ሳይኮሎጂ 👉 ሁሌም ጥያቄ ስትሰራ ከቀላሉ ጀምር፤ ምክንያቱም ቀላሎቹን ቀድመህ ስትሰራ ኮንፊደንስህ ያድጋል፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ለከባድ ጥያቄዎች ብዙ ጊዜ ይተርፍሀል። 

እረፍት እያረጋችሁ ተፈተኑ!

መልካም ፈተና! 🙌
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
54🔥37🙏7👍4🏆4
🛑 ዲሲፕሊን ብቸኛው ኢንትራንስ ማለፊያ ቁልፍ ነው‼️

አንተ ፈተና ብትሰራም ባትሰራም ጊዜው ካሰብከው በላይ በፍጥነት ይከንፋል። አንተ ጠንክረህ ከተፈተንክ እና ከከለስክ ጊዜው ቢሄድም ችግር የለውም። ዛሬ English እና Maths ፈተና  ጨርሰሃል?

በኢንትራንስ ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች ሁሉንም የዛሬን ዕቅድ ሙሉውን አጠናቅቀዋል። አንተም ከነሱ በምንም አታንስም! ተነስና የዛሬን ጨርስ! በርቱ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
78🏆11🔥8🙏8🆒4💯3🤝3👍2👏1
🛑 አሁን ከለፋህ ነሀሴ መጨረሻ ውጤትህ ሲመጣ አይቆጭህም‼️

በውጤት ቀን የቤተሰቦችህን ኩራት አስብ። ያ ደስታ በዚህ ሰሞን በምትሰራው ፈተናዎችና ክለሳህ ይወሰናል። ሰበብ የለም። በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ ተፎካካሪዎችህ የምትበልጠው አቅምህን ጥግ ድረስ ስትጠቀም ነው።

በሙሉ ትኩረትና ዲስፕሊን ከልብህ ተፈተን፤ የተሳሳትከውን ሳትሰለች ከልስ፤ ዛሬ የ Pilot ፈተናችን SAT እና Phy/His ነው የምንሰራው። አሁን ከለፋህ ነሀሴ መጨረሻ ውጤትህ ሲመጣ አይቆጭህም! ዳይ ወደ ዝግጅት!💪

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
77🔥18🏆11👍7🫡7👌2🙏1
🛑 ብዙ የፈተና ጥያቄ ስራ! ከዛ ከ 500 በላይ ግድ ነው!

የዛሬው Pilot ፈተና ተጠናቋል? ውጤትህ ምንም ይሁን፤ ተፈትነህ፤ Correction አይተህ ስህተትህን እወቀው፤በደምብ ከልስ፤ ለዋናው ፈተና የዛሬውን ስህተት እንዳትደግመው! አለቀ!

ከጨረስክ እረፍት አርግ፤ ነገ ትቀጥላለህ፤ ካልጨረስክ አልጋው እንዳይነካህ! የወደፊት ህይወትህ በዚህ ጥንካሬ ላይ የተመሰረተ ነው! ተራ ጥረት ተራ ውጤት ያመጣል። ከ 500 በላይ ማምጣት ከፈለግክ አሁን ዋጋ ክፈል!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
64🙏17🔥7🏆7🫡6👍3😍2👏1🕊1
🛑 12 ቀን ለውጥ ይፈጥራል ጥረታችሁን ቀጥሉ‼️

እንዴት አደርክ የ 2019 የዩኒቨርስቲ ተማሪ? ፈተና የመስራት ሞራልና ስሜት ከፍ ዝቅ ሊል ይችላል፤ ፈተናችሁ ሲቃረብ መፍራት መደንገጥም ይኖራል፤ ይሄ የተለመደ ነው። አሁንም ቢሆን ፈተና መስራት፤ ኖት ማየት አታቁም።

ዛሬ ናቹራሎች Chem እና Bio፤ ሶሻሎች Geo እና Eco Pilot ፈተና እንፈተናለን፤ ስንጨርስ የተሳሳትነውን እንከልሳለን፤ ውጤት ከ 600 እናያለን። ነገ ማታ ስለ ፈተና ሳይኮሎጂ በድምፅ እንመካከራለን፤ በርቱ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
110🔥15🙏9🎉7🏆7🤝4👏2👍1
🛑 12 ቀን ቀረን‼️ አጭር መልዕክት‼️

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🏆13075🙏24🆒13👍6👏5🔥4🕊2👌1
🛑 ቆራጥና የውሳኔ ሰው ሁን!

አእምሮህ ቅዳሜን መዝናናት ይፈልጋል። "የዛሬን ፈተና ልምምድ እና ክለሳ ሳልጨርስ አላርፍም!" ማለት አለብህ። እንደዚህ አይነት ቆራጥ ውሳኔዎች ናቸው የሚያልፈውን እና የማያልፈውን የሚለዩት። 

ዛሬ ሁላችንም ያልጨረስነውን ፈተናዎች እንጨርሳለን፤ በዚህ ወቅት ያለህ ጠንካራ ጥረት እስከዛሬ ከነበረህ ጉብዝና በላይ ለውጤትህ ወሳኝ ነው። ሌላው ቅዳሜን ሲዘናጋ አንተ ጠንክረህ ፈተና ስራ፣ ከዛ ከልስ፤ ሽልማቱን ሰኔ 24 ብሔራዊ ፈተና ስትፈተን ታገኘዋለህ! በርታ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
115🔥16👍12🙏12💯10🏆7🆒6🫡2
Audio
🛑 የፈተና ሳይኮሎጂ ለ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ

መልካም ፈተና! ይቅናችሁ🙏
https://youtu.be/38Rx5PNm0AM?si=ErODHBr4iUkCSgoN

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
320🙏83👍32💯27🏆26🫡15🔥7🎉6👏5
🛑 ውጤት ሲመጣ ራስህን ታደንቀዋለህ‼️

ዛሬ ማንነትህን የምታስመሰክርበት ቀን ነው። የ 2011 English እና Math ፈተና ስራ፤ ልክ እንደ እውነተኛው ፈተና ቁጠረው። ከዛ የተሳሳትከውን ማስታወሻ ይዘህ ከልስ፤ አንዴ የመታህ ድንጋይ ደግሞ እንዳይመታህ ማለት ነው።

ብዙ ልጆች እሁድን እየተዝናኑ ሲሆን አንተ ግን ቤተሰብህ በኩራት እንዲያለቅሱ የሚያደርግ ህይወት እየገነባህ ነው። ጀግና! ጊዜህን በደምብ  ተጠቀምበት! "ውጤት ሲመጣ እንኳን ለፋው" ብለህ በጣም ትደሰታለህ። በርታ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
110🫡23🏆8👍6🔥5
🛑 ሲያልፍ እንዳይቆጭህ በፅናት ቀጥል‼️

የዛሬ ፈተና እንዴት ነው? ጨረሳችሁ? ጥሩ ነው? ቆራጥ የሆነ ተማሪ በፕሮግራም ይፈተናል ከዛ ይከልሳል፤ ዲስፕሊን እና ትከረት አለው!! ስልካችንን ከትምህርት ውጪ ለምንም ነገር አንጠቀምም! ⭐️ "ይሄ ወቅት ለህይወታችን በጣም ወሳኝ ነው!" ይሄንን መቼም እንዳትረሱ።

ጊዜያዊ ስሜትህን ተቆጣጥረህ ለኢንትራንስ ዋጋ ከከፈልክ ዕድሜ ልክህን በራስህ ትኮራለህ! አይቆጭህም! ሁላችሁም የሚገርም ጥረት እያረጋችሁ ነው፤ ጀግኖች በርቱ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
👍5635🙏11🏆9🔥8🫡5🆒3
🛑 ጊዜህን ተጠቀምበት 10 ቀን አለህ‼️

ከ 10 ቀን በኋላ ግማሽ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ኢንትራንስን ይፈተናሉ። አብዛኞቹ ትንሽ ሞክረው ተስፋ ቆርጠዋል። አንተ ግን በቻልከው አቅም በየቀኑ ፈተና እየሰራህና እየከለስክ ነው፤ ጀግና ነህ‼️ ፈተናውን ማለፍህ ግድ ነው!

ዛሬ የ 2011 ኢንትራንስ SAT እና Phy/His እንፈተናለን፤ የተሳሳትነውን ማስታወሻ ይዘን እንከልሳለን። በቀረህ 10 ቀን በሚገርም ሞራል እንደጀመርክ መጨረስ አለብህ፤ ከፈጣሪ ጋር ታሪክ እንሰራለን!🙌

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
97🙏15🏆7👍6🔥5😘3🫡2🆒1
🛑 ሳትጨርስ መተኛት አይቻልም!

"ነገ እፈተናለው፣ ነገ እሰራለሁ" ህልሞችን የሚያጠፋ የሰነፍ ዓረፍተ ነገር ነው። የዛሬን ለነገ ካሳደርክ ፀፀት ይቆጣጠርሀል! የቀሩህ ቀናት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው፤ ከተጠቀምክባቸው ግን ልዩነት ይፈጥራሉ።

እንቅልፍ የድካም ውጤት ሳይሆን ከጥናት በኋላ ሽልማት ነው። ለራስህ ታማኝ ሁን። ሰበብ የለም! የዛሬ ፈተና እስኪያልቅ ድረስ ማቆም አይቻልም! የተሳሳትከውን በደምብ ከልሰው።

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
82🎉11🆒8👍5🔥5🙏5🏆5🤝3👏1
🛑 በዚህ ጥረታችሁ ኢንትራንስ ማለፍ ትችላላችሁ‼️

አብዛኞቻችሁ ከልባችሁ ጥያቄ ሰርታችሁ፤ የተሳሳታችሁን ከልሳችኋል፤ አሁን ያ ጥያቄ ደግሞ ቢመጣ ትመልሱታላችሁ? መልሳችሁ አዎ ከሆነ ኢንትራንስን ማለፍ ብቻ ሳይሆን ምርጥ ውጤት ታመጣላችሁ።

9 ቀን ለተጠቀመበት ታሪክ ይቀይራል፤ ዩኒቨርስቲ ያስገባል። ዛሬ Bio እና Chem/Geo እና ECo2011 ኢንትራንስን ጥንቅቅ አድርገን ሰርተን የከበደንን ማስታወሻ ይዘን በደምብ እንከልሳለን። ማታ ውጤታችሁን ከ 600 ትነግሩናላችሁ እንጠብቃለን፤ ዳይ ወደ ፈተና!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
55🔥14🙏8🏆6👍4
🛑 መፍራት መደንገጥ የለም! መዘጋጀት ብቻ‼️

የ 2011 ፈተና 6ቱንም ተፈትነህ ጨርሰሃል? ያልጨረስከው ካለ አሁኑኑ ፈጽመው። "መፍራት፣ መደንገጥ የለብህም፤ ካንተ የሚጠበቀው መዘጋጀት ብቻ ነው። የለፋችሁትን ልታገኙ ከጫፍ ደርሳችኋል!

በሞዴል ፈተናችን ኪሩቤልእሙሽ ተፈሪ 541/600 አምጥቶ ከፊት እየመራ ነው፤ ስህተቱን አውቆ የሚያስተካክል የትኛውም ተማሪ በብሔራዊ ፈተና ይሄን ውጤት ማምጣት ይችላል! በርቱ አላማችን ዋናው ብሔራዊ ፈተናን በምርጥ ውጤት ማለፍ ነው!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
58🆒12🔥8🙏8👍5🫡5
ታልፋለህ አትጠራጠር‼️ 8 ቀን አለህ ሳትሰለች ፀጥ ብለህ ቀጥል!

ለምን እንደጀመርክ አስታውስ፣ በአንተ ስኬት የሚወዱህ ሁሉ ምን ያህል ደስ እንደሚላቸው፣ እንደሚረኩ አትርሳ! ተራ ተማሪዎች ሲደክማቸው ያቆማሉ፤ ቆራጦች ግን ማቆም ቢፈልጉም ይቀጥላሉ።

ዛሬ በዕቅዳችን መሰረት ሁላችሁም የ 2010 English እና Math's ትፈተናላችሁ። ስትጨርሱ የከበዳችሁን/የተሳሳታችሁትን መዝግቡ፤ ከዛ በደምብ ከልሱ። ዲሲፕሊን ማለት እያስጠላህም ቢሆን ማድረግ ያለብህን ማድረግ ነው። ዳይ ወደ ልምምድ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
95👏13👌8👍6🏆6🙏5💯5🔥3
🛑 8 ቀን ለተጠቀመበት ብዙ ነገር ይቀይራል!

ውጤታችሁ ምንም ይሁን የዛሬውን ፈተና ተፈትናችሁ ጨርሱ!  የዛሬ ስህተታችሁን ካወቃችሁ ለኢንትራንስ አትደግሙትም፤ አላማችን ይሄ ነው! ያልተፈተናችሁ ልጆች ለነገ ማሳደር አይቻልም አሁኑኑ ተፈተኑ! ከዛ ስህተታችሁን በክለሳ እወቁት።

ሁለቱንም ትምህርቶች የተፈተናችሁ ተማሪዎች፤ ስህተታችሁን ለይታችሁ ክለሳ ካደረጋችሁ አሁን እረፍት አድርጉ። ነገ ደግሞ የቀሯችሁን ትቀጥላላችሁ።  በርቱልን የኛ ጠንካሮች!👏👏👏

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
94🔥20🙏16🏆11🕊10🫡1
🛑 የመጨረሻና ወሳኙን ፈተና ነገ እንፈትናችኋለን‼️

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
👍16266🆒52🔥18🏆18🫡14💯11🎉10🙏9🕊8👌5
🛑 የመጨረሻው ሞዴል ፈተናችን ዛሬ ጀመረ‼️

የዛሬ 5 ቀን የሀገሪቱን ትልቅ ፈተና ትወስዳለህ፤ ማለፍና መውደቅ ያኔ ይወሰናል። አሁን የምትፈተነው ፈተና የሚጠቅምህ ለዛ ወሳኝ ቀን እንደሆነ አስታውስ! ስለዚህ ከልብህ ፈተናውን ስራ፤ ቀጣይ የህይወትህ ምዕራፍ ምርጥ ይሆናል! Maths እና English ፈተና ስራ ዛሬ!

የፈተና ሳይኮሎጂ 👉 ሁሌም ጥያቄ ስትሰራ ከቀላሉ ጀምር፤ ምክንያቱም ቀላሎቹን ቀድመህ ስትሰራ ኮንፊደንስህ ያድጋል፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ለከባድ ጥያቄዎች ብዙ ጊዜ ይተርፍሀል። 

እረፍት እያረጋችሁ ተፈተኑ!

መልካም ፈተና! 🙌
@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
99🙏15👍8🏆8🤝5👏3🔥1🕊1🆒1
🛑 ዲሲፕሊን ብቸኛው ኢንትራንስ ማለፊያ ቁልፍ ነው‼️

አንተ ፈተና ብትሰራም ባትሰራም ወሳኙ ፈተና ደርሷል። አንተ ጠንክረህ ከተፈተንክ እና ከከለስክ ጊዜው ቢሄድም ችግር የለውም። ዛሬ English እና Maths ፈተና  ጨርሰሃል? የሚባክን ጊዜ መኖር የለበትም!

በኢንትራንስ ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች ሁሉንም የዛሬን ዕቅድ ሙሉውን አጠናቅቀዋል። አንተም ከነሱ በምንም አታንስም! ተነስና የዛሬን ጨርስ! በርቱ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
51🔥35🙏10🤝8🏆6👍5🆒3👏2