FutureX
25.5K subscribers
17 photos
23 videos
15 files
54 links
The future starts here!
Download Telegram
ጀግኖች ዋናው ፈተና መስራታችሁ ከዛ መከለሳችሁ ነው‼️

የFutureX አባላት ፈተናው ላይ ባሳያችሁት አስገራሚ Performance በሁላችሁም ኮርተናል! በዚህ ከቀጠልን ኢንትራንስ የኛ ነው! ያልተፈተናችሁ ተፈተኑ፤ ሞዴል ፈተናውን ያልጨረሳችሁ እንድትጨርሱ የዛሬውን ቀን ነፃ አድረገንላችኋል። 

ሞዴል ፈተናውን የጨረሳችሁ ተማሪዎች የሚናስቸግራችሁን ት/ት ምዕራፎች ከልሱበት። ለ SAT ሁሌም የማይቀሩ Vocabularies Shortnote'ቱ ላይ አሉ፤ በደምብ እወቋቸው። ለመዝናናት፣ ፈታ ለማለት ከፈተና በኋላ ሰፊ ጊዜ አለህ! መዘናጋት የለም በትኩረት መዘጋጀት ብቻ!ጥረታችሁን ፈጣሪ ይባርክ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🙏7154🏆13👍8👏6🔥3
Audio
🛑 ነገ Pilot ፈተና እንጀምራለን‼️

የቀራችሁ 26 ቀን ብቻ ነው፤ በዚህ ድምፅ እንዴት በዚህ አጭር ጊዜ በደምብ እንደምትዘጋጁ እና ስለነገው Pilot ፈተና ያብራራል!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🏆18891👍35🙏21🔥10🎉10🕊9🤝8😍7😘7🆒6
🛑 በቀሩን ቀናት ተዓምር እንሰራለን‼️ Pilot ፈተና ተጀምሯል!

ለብዙ ጊዜ አጥንታችኋል፣ አንዳንዴም ተዘናግታችሁ ጊዜ አባክናችኋል፤ ያለፈው አልፏል! የቀረውን ቀን ግን በቃ የመጨረሻ ዕድላችሁ ነው፤ ስለዚህ በእልህና በዲስፕሊን በጣም ብዙ ፈተና ስሩ፤ በ Shortnote ከልሱ።

ዛሬ የPilot ፈተና ይኖረናል፤ Math's እና English ሰዓት ይዘህ ትፈተናለህ፣ ፈተናውን ተፈትነህ ስትጨርስ X የገባብህን፣ የከበደህን ወይም የረሳኸውን በ Shortnote ትከልሳለህ። በሙሉ አቅምህ ለኢንትራንስ ተዘጋጅ! ከዛ ውጤት ሲመጣ እንኳን ለፋው ጀግና ነኝ ትላለህ! ትያለሽ! ፈጣሪ አብሮን ነው በርቱ!

መልካም ፈተና!🙏

@Futurexapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
99🙏26🏆12🔥8🆒4
🛑 ዲሲፕሊን ብቸኛው ኢንትራንስ ማለፊያ ቁልፍ ነው‼️

አንተ ፈተና ብትሰራም ባትሰራም ጊዜው ካሰብከው በላይ በፍጥነት ይከንፋል። አንተ ጠንክረህ ከተፈተንክ እና ከከለስክ ጊዜው ቢሄድም ችግር የለውም። ዛሬ English እና Maths ፈተና  ጨርሰሃል?

በኢንትራንስ ከፍተኛ ውጤት የሚያስመዘግቡ ተማሪዎች ሁሉንም የዛሬን ዕቅድ ሙሉውን አጠናቅቀዋል። አንተም ከነሱ በምንም አታንስም! ተነስና የዛሬን ጨርስ! በርቱ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
38🔥33🙏15👍7🏆6🫡2
🛑 ቆራጥና የውሳኔ ሰው ሁን!

በውጤት ቀን የቤተሰቦችህን ኩራት አስብ። ያ ደስታ በዛሬው ጥረትህ ይወሰናል። ሰበብ የለም። በመቶ ሺዎች ከሚቆጠሩ ተፎካካሪዎችህ የምትበልጠው እሁድን ጥግ ድረስ ስትጠቀም ነው። በሙሉ ትኩረት አጥና።

ዛሬ ሁላችንም የPilot ፈተና SAT እና Phy/His እንፈተናለን። ወጥ አቋም (Consistency) ከጉብዝና ይበልጣል። ሌላው እሁድን ሲዘናጋ አንተ ጠንክረህ ፈተና ስራ፣ ከዛ ከልስ፤ ሽልማቱን ሰኔ 24 ብሔራዊ ፈተና ስትፈተን ታገኘዋለህ! በርታ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
66🙏10🔥5👏5🏆3👍1😍1
🛑 ብዙ የፈተና ጥያቄ ስራ! ከዛ ከ 500 በላይ ግድ ነው!

የዛሬው Pilot ፈተና ተጠናቋል? ውጤትህ ምንም ይሁን፤ ተፈትነህ፤ Correction አይተህ ስህተትህን እወቀው፤በደምብ ከልስ፤ ለዋናው ፈተና የዛሬውን ስህተት እንዳትደግመው! አለቀ!

ከጨረስክ እረፍት አርግ፤ ነገ ትቀጥላለህ፤ ካልጨረስክ አልጋው እንዳይነካህ! የወደፊት ህይወትህ በዚህ ጥንካሬ ላይ የተመሰረተ ነው! ተራ ጥረት ተራ ውጤት ያመጣል። ከ 500 በላይ ማምጣት ከፈለግክ አሁን ዋጋ ክፈል!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
64🔥7🏆6🙏5👍2🤝2🫡2👏1
🛑 መዘናጋት የለም! በቆራጥነት እንቀጥላለን‼️

እንዴት አደርክ የነገው የዩኒቨርስቲ ተማሪ? ፈተና የመስራት ሞራልና ስሜት ከፍ ዝቅ ሊል ይችላል፤ ዲሲፕሊን ግን ዘላቂ ነው። ዛሬ ወደ ዩኒቨርሲቲ የምትገባበትን ዝግጅት ታደርጋለህ፤ ስለዚህ የሚያዘናጉህን ነገሮች በሙሉ አስወግድ።

ዛሬ ናቹራሎች Chem እና Bio፤ ሶሻሎች Geo እና Eco ሞዴል ፈተና እንፈተናለን፤ ስንጨርስ የተሳሳትነውን እንከልሳለን፤ ውጤት ከ 600 እናያለን። የቤተሰብህ መስዋዕትነት ምርጥ ብቃትህን ይፈልጋል። በቆራጥነት ጥረትህን ቀጥል!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
👍5749🙏27🔥10🏆9🫡6👏4💯2😘2
🛑አጭር መልዕክት‼️

@FutureXapp
👍18775🔥22🙏20🏆11🆒9💯8🤝8🕊6🫡4
🛑 አትዘናጋ ቤተሰብ ውጤትህን ይጠብቃል!

22 ቀናት ቀርቶናል። ለሰበብ ጊዜ የለም። ሰበቦች የዩኒቨርሲቲ ወንበርህን ያስነጥቁሃል። ክለሳህን፣ ፈተና መስራትህን አቋርጠህ መዝናናት ብትፈልግ እንኳን ለምን እንደጀመርክ አስብ።

የቤተሰብህ ተስፋ ካንተ ድካም በላይ ይከብዳል። በእነዚህ ጥቂት ቀናት የምታደርገው ነገር ውጤትህን ይቀይረዋል። ዲሲፕሊን ማለት እያስጠላህም ቢሆን ማድረግ ያለብህን ማድረግ ነው። ማረፍ ከፈለክ ከብሔራዊ ፈተና በኋላ 4 ወር አለህ፤ ያኔ ከልብህ ትዝናናለህ፤ አሁን ግን በትኩረት ተዘጋጅ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
114🙏17👍8🏆8🔥7🫡7🕊5😍2🎉1🆒1
🛑 ሳትጨርስ መተኛት አይቻልም!

"ነገ እፈተናለው፣ ነገ እሰራለሁ" ህልሞችን የሚያጠፋ የሰነፍ ዓረፍተ ነገር ነው። የዛሬን ለነገ ካሳደርክ ፀፀት ይቆጣጠርሀል! የዛሬን ዛሬ ጨርስ።

የPilot ፈተና 6ቱንም ተፈትነህ ጨርሰሃል? ያልጨረስከው ካለ አሁኑኑ ፈጽመው። በረከት ሀይሉ 587/600 (Math's = 100) አምጥቶ ከፊት እየመራ ነው፤ እንቅልፍ የድካም ውጤት ሳይሆን ከጥናት በኋላ ሽልማት ነው። ለራስህ ታማኝ ሁን። ሰበብ የለም! የዛሬ ፈተና እስኪያልቅ ድረስ ማቆም አይቻልም!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
65👍20🙏7🔥6🤝6🏆4👌2
ታልፋለህ አትጠራጠር‼️ 21 ቀን አለህ ሳትሰለች ፀጥ ብለህ ቀጥል!

ለምን እንደጀመርክ አስታውስ፣ በአንተ ስኬት የሚወዱህ ሁሉ ምን ያህል ደስ እንደሚላቸው፣ እንደሚረኩ አትርሳ! ተራ ተማሪዎች ሲደክማቸው ያቆማሉ፤ ቆራጦች ግን ማቆም ቢፈልጉም ይቀጥላሉ።

Pilot ፈተና ውጤትህ ምንም ቢሆን አሁን ወደ 2013 ብሔራዊ ፈተና እንቀጥላለን። ዛሬ በዕቅዳችን መሰረት ሁላችሁም የ 2013 English እና Math's ትፈተናላችሁ። ስትጨርሱ የከበዳችሁን/የተሳሳታችሁትን መዝግቡ፤ ከዛ በደምብ ከልሱ። ዲሲፕሊን ማለት እያስጠላህም ቢሆን ማድረግ ያለብህን ማድረግ ነው። ዳይ ወደ ልምምድ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
106🙏29🔥9🏆7🆒7👍1
Audio
🛑 የMath's Concert ቀኑ ተወስኗል‼️

በአንድ ቀን ማትስ ከልሰን ጥያቄ ሰርተን እንጨርሳለን፤ ለምታውቁት የ 12ኛ ክፍል ተማሪ በሙሉ Share ለማድረግ አድርጉ።

ያልተመዘገባችሁ ልጆች ቦታ ለመያዝ ፈጥናችሁ ከታች ባለው ሊንክ ተመዝገቡ(ደግሞመመዝገብ አይቻልም!)👇
https://forms.gle/QPnfZb7veYetQquB9

@Futurexapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
🏆7566🔥13🆒12👏9🎉2👍1🤝1
🛑 20 ቀናት ቀሩን! በትኩረት ከተጠቀምክበት ታሪክ ትሰራለህ‼️

ህይወትህን ለሚቀይር ነገር ቀጠሮ አትስጥ! አሁን አድርገው! በየቀኑ ፈተና ለመፈተን፣ ለመከለስ አትሰልች! ብዙ ተማሪዎች ውጤት ሲመጣ የሚቆጫቸው "ወይኔ ብዙ ጥያቄ ብሰራ ኖሮ ኢንትራንስን አሎድቅም ነበር" ብለው ነው።

ጥያቄ እንደመስራት ውጤታማ የሚያደርግ ነገር የለም፤  ዛሬ ሁላችንም የ 2013 ኢንትራንስ SAT እና Phy/His እንፈተናለን።  ሳትሰለች የተሳሳትከውን አስተካክል፤ Shortnote ተጠቀም። እየበላህ ወይ እየተራመድክ ወይ ተኝተህ ካልሆነ በስተቀር እየተዘጋጀህ መሆን አለበት። መዘናጋት የለም በሙሉ በትኩረት ጥንቅቅ አርገህ ጨርስ !ጥረታችሁን ፈጣሪ ይባርክ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
100🙏24🏆10🫡6👍5🔥2👏2🤝2😘2👌1
🛑 ዲስፕሊን + ትኩረት = ምርጥ ውጤት‼️

የዛሬ ፈተና እንዴት ነው? ጥሩ ነው? ቆራጥ የሆነ ተማሪ በፕሮግራም ይፈተናል ከዛ ይከልሳል፤ ዲስፕሊን እና ትከረት አለው!! ስልካችንን ከትምህርት ውጪ ለምንም ነገር አንጠቀምም! ⭐️ "ይሄ ወቅት ለህይወታችን በጣም ወሳኝ ነው!" ይሄንን መቼም እንዳትረሱ።

ፈተና ሰርተህም፤ ከልሰህም ከጨረስክ እረፍት አርግ፤ ነገ ትቀጥላለህ፤ ካልጨረስክ አልጋው እንዳይነካህ! የወደፊት ህይወትህ በዚህ ጥንካሬ ላይ የተመሰረተ ነው! ተራ ጥረት ተራ ውጤት ያመጣል። ከ 500 በላይ ማምጣት ከፈለግክ አሁን ዋጋ ክፈል!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
67👍12🏆9🆒8🙏3🎉2🕊1
🛑 መፍራት መጨነቅ የለም! መዘጋጀት ብቻ‼️

ጊዜው እየሮጠ ነው፤ አንተም በፕሮግራም እየተፈተንክና እየከለስክ ነው፤ ስለዚህ መፍራት፣ መጨነቅ የለም! እነዚህ ቀናት በምርጥ ውጤት ሊያሳልፉህ ወይም ሊጥሉህ ይችላሉ።

ዛሬ ናቹራሎች የ2013 Chem እና Bio፤ ሶሻሎች Geo እና Eco ትፈተናላችሁ። በሙሉ ትኩረት ጥያቄ ስሩ፤ ስትጨርሱ የከበዳችሁን/የተሳሳታችሁትን መዝግቡ፤ ከዛ በደምብ ከልሱ። ዛሬ ከፍተኛ ጥረት ይፈለጋል፤ እያንዳንዱን ሰከንድ ተጠቀም። የሚባክን ጊዜ የለም!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
48🤝14🙏11🏆8🔥6👍3🆒3🫡2👌1
🛑 ሳትጨርስ መተኛት አይቻልም!

"ነገ እፈተናለው፣ ነገ እሰራለሁ" ህልሞችን የሚያጠፋ የሰነፍ ዓረፍተ ነገር ነው። የዛሬን ለነገ ካሳደርክ ፀፀት ይቆጣጠርሀል! የዛሬን ዛሬ ጨርስ።

የ2013 ብሔራዊ ፈተና 6ቱንም ተፈትነህ ጨርሰሃል? ያልጨረስከው ካለ አሁኑኑ ፈጽመው። በረከት ሀይሉ 594/600 (Math's, SAT, Chem = 100) አምጥቶ ከፊት እየመራ ነው፤ እንቅልፍ የድካም ውጤት ሳይሆን ከጥናት በኋላ ሽልማት ነው። ለራስህ ታማኝ ሁን። ሰበብ የለም! የዛሬ ፈተና እስኪያልቅ ድረስ ማቆም አይቻልም!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
75🔥15🙏10🏆10🆒4🫡3😍2🎉1🤝1
🛑 ውጤት ሲመጣ ራስህን ታደንቀዋለህ‼️

ዛሬ ማንነትህን የምታስመሰክርበት ቀን ነው። የ 2012 English እና Math ፈተና ስራ፤ ልክ እንደ እውነተኛው ፈተና ቁጠረው። ከዛ የተሳሳትከውን ማስታወሻ ይዘህ ከልስ፤ አንዴ የመታህ ድንጋይ ደግሞ እንዳይመታህ ማለት ነው።

ብዙ ልጆች ቅዳሜን እየተዝናኑ ሲሆን አንተ ግን ቤተሰብህ በኩራት እንዲያለቅሱ የሚያደርግ ህይወት እየገነባህ ነው። ጀግና! ጊዜህን በደምብ  ተጠቀምበት! "ውጤት ሲመጣ እንኳን ለፋው" ብለህ በጣም ትደሰታለህ። በርታ!

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
70👍24🏆10🙏7🔥6🫡5😍1😘1
⭐️ 18 ቀን ለተጠቀመበት ብዙ ነገር ይቀይራል!

ውጤታችሁ ምንም ይሁን የዛሬውን ሞዴል ፈተና መፈተናችሁ በራሱ በቂ ነው!  የዛሬ ስህተታችሁን ካወቃችሁ ለኢንትራንስ አትደግሙትም፤ አላማችን ይሄ ነው! ያልተፈተናችሁ ልጆች ለነገ ማሳደር አይቻልም አሁኑኑ ተፈተኑ!

ሁለቱንም ትምህርቶች የተፈተናችሁ ተማሪዎች፤ ስህተታችሁን ለይታችሁ ክለሳ ካደረጋችሁ አሁን እረፍት አድርጉ። ነገ ደግሞ የቀሯችሁን ትቀጥላላችሁ።  በርቱልን የኛ ጠንካሮች!👏👏👏

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
👍5640🏆7🤝7🫡6🎉3🙏2🆒2🔥1
🛑 የምትችለውን ሁሉ አድርግ፤ የቀረውን ለፈጣሪ ተወው‼️

በየቀኑ ከልባችሁ የምታደርጉት ጥረት የኢንትራንስ ውጤታችሁን በጣም ከፍ ያደርገዋል። በሙሉ ትኩረት ጥያቄ ስሩ፤ ስትጨርሱ የከበዳችሁን/የተሳሳታችሁትን መዝግቡ፤ ከዛ በደምብ ከልሱ

ዛሬ በፕሮግራማችን መሰረት 2012 SAT እና Phy/His ብሔራዊ ፈተናን በጥንቃቄ እንሰራለን፤ የተሳሳትነውን ማስታወሻ እንይዛለን፤ ከዛ የከበደንን በደምብ እንከልሳለን። መዘጋጀት ማለት ይሄ ነው! በርቱልን!! መልካም ዝግጅት🙏

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
👍6050🫡9🙏7🔥6👏6🏆6😍1
Audio
🛑 18 ቀን ቀረን‼️ ወሳኝ መልዕክት‼️

በቀረን 18 ቀን ለወሳኙ ፈተና እንዴት እንደምንዘጋጅ ያብራራል።

FutureX

ለውጥ አሁን ይጀምራል!
239🔥33🙏26🫡22🏆17🆒11👏4👍3🎉3
🛑 ጊዜህን ተጠቀምበት 17 ቀን አለህ‼️

ከ 2 ሳምንት በኋላ ግማሽ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ኢንትራንስን ይፈተናሉ። አብዛኞቹ ትንሽ ሞክረው ተስፋ ቆርጠዋል። አንተ ግን በቻልከው አቅም በየቀኑ ፈተና እየሰራህና እየከለስክ ነው፤ ጀግና ነህ‼️ ፈተናውን ማለፍህ ግድ ነው!

ዛሬ የ 2012 ኢንትራንስ Chem/Geo እና Bio/Eco እንፈተናለን፤ የተሳሳትነውን ማስታወሻ ይዘን እንከልሳለን። 17 ቀን ቀርቶሀል በሚገርም ሞራል እንደጀመርክ መጨረስ አለብህ፤ ከፈጣሪ ጋር ታሪክ እንሰራለን!🙌

@FutureXapp
ለውጥ አሁን ይጀምራል!
80🙏30🏆10🫡6🔥3