ፎረም ሚዲያ ኔትዎርክ
95 subscribers
48 photos
25 videos
126 links
ዜና እና ፓለቲካዊ ጉዳዮች
Download Telegram
ይህ ሁሉ ፋኖን ካለማወቅ ነው
አማራነት እንደ ንጋት ጮራ እየደመቀ ይበራል!

"አማራነት ምሉዕነት እና ስምረት ያለው ማንነት ነው"
================================

አማራነት የትኛውንም ሀይማኖት እና ጠቅላይ ግዛት የሚቀድም እና የሚበልጥ በማንነቱ ግንጥል ጌጥ ተነጥሎ የማይበየን፣ በመገለጫ አላባውያኑ ተገጣጣሚነት ምሉዕ እና ስምረት ያለው ዘውጋዊ፣ ታሪካዊ እና ፖለቲካዊ ማንነት ነው።
አማራነትን ከሀይማኖታዊ ማንነት ነጥሎ አለማየት አንድም አማራነትን መክፈል፣ ከታሪካዊነቱ መቁረስ እና ፖለቲካዊ እሱነቱን መበረዝ/መከለስ ነው። እንዲሁም ከአማራነት ጋር በተለዋጭነት ለሚቀርበው ሀይማኖታዊ ማንነትም ማሳነስ እና በእምነት አስተምህሮት ላይ የቆመውን ማንነት በዘውግ ፈርጅ በመነጠል ከአለማአቀፋዊነቱ ማጉደል ነው። ይህ ዕሳቤ ለአማራነትም ለሀይማኖታዊ ማንነቱም እኩል ጠላት ነው።

አማራነት ከአላባውያኑ ተነጥሎ የማይገለጽ ቢሆንም አላባውያኑ ወይም መገለጫዎቹ ጋር የሚወዳደር ሳይሆን መገለጫዎቹን አስተሳስሮ እና አገጣጥሞ የሚነብር እኛነት ነው።

አማራ በጥንታዊ የነገድ መሠረት ትውልድ፣ በርስት እና አጽመ-ርስት፣ በቋንቋ፣ የኑሮ ልማዶች ውርስና ተራክቦ፣ በተመሳሳይ መሻት ላይ የተመሠረተ አንድ የጋራ እጣ ፈንታ ያለው ህዝብ ነው።

ከዚህ ባነሰም ሆነ በተለዬ መልኩ የሚገለጽ እኛነት የለንም።
አማራነት በየትኛውም ግንጥል ጌጥ ወስኖ ማጥበብ እንዲሁም ግንጥል ጌጡን ወስዶ በሌላ የማንነት ጎራ ካሉ ጋር አጣምሮ የአማራነት ልዩትነቱን ማጥፋት/ማጓደል እኩል የአማራነት ጠላትነት ነው። ይህንም ታግለን እናሸንፈዋለን።

አማራነት እንደ ንጋት ጮራ እየደመቀ ይበራል።
እናሸንፋለን!

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ !አዲስ ተስፋ
1
ስቦ ማስከዳት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡
የመሪያችንን የአርበኛ ዘመነ ካሴን ጥሪ የተቀበሉ የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ አራዊት ሠራዊት በየቀኑ ስርዓቱን እየከዳ ወደ አማራ ፋኖ በገፍ እየተቀለቀለ ይገኛል። ዛሬም የመሪያችንን ጥሪ የተቀበለው ራሱን ሰላም አስከባሪ ብሎ ከሚጠራው ተላላኪ አጥቦ አይለብሴ ሚሊሻ አባል የነበረዉ ሀብታሙ አታላይ ወደ አፋጎ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ፮ኛ ክፍለ ጦር ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ ከነሙሉ ትጥቁ ተቀላቅሏል፡፡ ለሌሎች የስርዓቱ አገልጋይ ሠራዊት ደግሞ እንደ እኔ የአብይን ሴራ እወቁበትና ራሳችሁን ከሞት ታደጉ ታሪካችሁንም በወርቅ ቀለም ፃፋ ሲል ወንድማዊ መልዕክቱን አስተላልፏል::
እኛም ለሁለት እግር አሳማ ካድሬዎች፣ ለአጥቦ አይለብሴ ሚሊሻዎች ፣ ለተላላኪ ፖሊስ እና የአጎረሰ ነካሽ ሆድ አደር አድማ በትን እንደዚህ እንላለን:  የአብይ አህመድን ስልጣን ለማራዘም ብላችሁ አይተኬ ወድ ህይወታችሁን አትቅጠፉ ታሪካችሁንም በጥቁር ቀለም አትፃፉ  አሁንም ረፈደ እንጂ አልመሸምና ኑ! ወደ ወገናችሁ ተቀለቀሉ።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!
የንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
ፋኖ ባዬ ሽፈራው (ቀኜ)