ፎረም ሚዲያ ኔትዎርክ
95 subscribers
48 photos
25 videos
126 links
ዜና እና ፓለቲካዊ ጉዳዮች
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህ ወንድም እህቱን አዲደፍር የሚደረግበት የብልፅግና ስርአት ነው
👍1
ሳብስክራይብ
Forwarded from Bahir Dar WikiLeaks - BW
ለሁሉም ቀጠና ፋኖዎቻችን - አዛምቱልን!

የአረጋ ከበደ "የ3 ወራት የክተት ዘመቻ" አዋጅ በማግስቱ በፋኖዎቻችን "የዘመቻ አንድነት" ተቀልብሶ፣ የአገዛዙ መዝገብ በየቀኑ ባለሶስት ዲጅት አስክሬን መመዝገብ ከጀመረ ዛሬ 31 ቀናት ተቆጥረዋል።

ይህ ለእኛ እጅጉን ድንቅ ተጋድሎ ነው። ምክንያቱም ክረምቱን አምርሮ የፈራው አገዛዙ፣ በመጋቢት፣ ሚያዝያ እና በግንቦት መጠነሰፊ ማጥቃት ፈፅሞ "ፋኖን ማጥፋት" የሚል ዕቅድ ነበር የነበረው። ነገር ግን ባልተጠበቀ መልኩ ፋኖዎቻችን ጭራሽ ወደተቀናጀ ማጥቃት ገቡና አገዛዙን አስክሬን ያስቆጥሩት ጀመር።

በእግረኛ ኃይል ተስፋ የቆረጠው እና የከፋ ኪሳራ ያጋጠመው ፋሽስታዊው የጨቅላው አብይ አህመድ አገዛዝ በእነዚህ ወራቶች የተጠናከሩ የድሮን ጥቃቶችን ሊፈፅም እንደሚችል ግልፅ ነው። አሁንም indiscriminately ይህንን ጥቃት በንፁሐን አዛውንቶች፣ ህጻናት፣ ገብያተኞች ወዘተ እየፈፀመ ይገኛል፤ ይህንንም የአየር ሁኔታው እስኪገድበው ድረስ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መገመት ይገባል።

እኛ ደግሞ ለአገዛዙ ምቹ የተባለውን ወቅት ጭራሽ በማጥቃት እንቅስቃሴ እያገባደድን የእኛ ወቅት እየገባልን ይገኛል። እስከዚያው ግን የድሮን ጥቃትን መከላከል የሚያስችል እንቅስቃሴን መተግበር የግድ ይላል። ፋኖዎቻችን የአገዛዙን የደመነፍስ የድሮን ጥቃት ለመከላከል ማህበረሰባችንን እራሱ እንዲያነቁ ይጠበቃል (እንኳን እራሳቸውን)።

ሁኔታዎችን ልክ ባልሆነ ትንታኔ የማናናቅ እና የግድየለሽ ዝርክርክ እንቅስቃሴና መሰባሰቦችን በተለያዩ አካባቢዎች ከሰማን ተጠያቂው የቀጠናው የፋኖ አመራር መሆን አለበት፤ ዝርክርክ አመራር ዝርክርክ ከባቢን እና አደረጃጀትን እየፈጠረ እንዳለ ከተጠየቅ ጋር ማሳወቅ ያስፈልጋል።

ሌላው ልናሰምርበት የምንፈልገው ነገር ደግሞ ወታደራዊ የምርቃት ፕሮግራሞች የሚፈጥሩት ማህበረሰባዊ እና የጓዶች መነቃቃት እንዳለ ሆኖ እስከክረምቱ ድረስ ግን ጋብ ማድረግ ያስፈልጋል፤ እስካሁንም የፈጣሪ ጥበቃ ታክሎበት እንጅ ልክ ያልሆነ እንቅስቃሴ ነው። ለእኛ ከሚያስደምም ወታደራዊ የምርቃት ፕሮግራሞች እና ትዕይንቶች ይልቅ በውጊያ ወቅት ጥንቅቅ ባለ ወታደራዊ ዲሲፕሊን መስመር ሰርቶ ሲንቀሳቀስ የምናየው የፋኖ ሰራዊት ይበልጥ ይማርከናል።

ስለምታዳምጡን እናመሰግናለን!
ይህ ሁሉ ፋኖን ካለማወቅ ነው