ፎረም ሚዲያ ኔትዎርክ
94 subscribers
48 photos
25 videos
126 links
ዜና እና ፓለቲካዊ ጉዳዮች
Download Telegram
ዘመነ ካሴን ይዘነዋል ? ሲያምርህ ይቅር 🤣

ከየወረዳው የተውጣጣው ተሰብሳቢ ወደ ስብሰባ አዳራሹ ይገባና ቦታ ቦታውን ይዟል። መድረኩን  ተመስገን ጥሩነህ እና አረጋ ከበደ ተሰይመውበታል።

ተሰብሳቢዎች መንግስት መከላከያ አስፓልት አስፓልቱን ብቻ ይዞ ሁሉንም ቀበሌዎች ለፋኖ አስረክቦ ነው ያለው። በተለይ ጎጃም ትላልቅ ከተሞችን እያስለቀቁት ነው። መልቀቁ ብቻ ሳይሆን እኛን ለፋኖ አሳልፎ ሰጦ እያስፈጀን ስለሆነ ወደመጣንበት ስንመለስ ከህዝባችን እና ከፋኖ ታርቀን በሰላም መኖር ይሻለናል የሚል ሀሳብ ቀረበ።

መድረኩን ይመሩት የነበሩት ተመስገን ጥሩነህ እና አረጋ ከበደ በብስጭት ጠረጴዛ ሲደበድቡ ቆይተው ለጥቂት ሰከንድ በጆሮ ከተንሾካሾኩ በኋላ "እንኳን ደስ አላችሁ ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን የፅንፈኛውን ቡድን መሪ ዘመነ ካሴን ይዞታል" አላቸው ተመስገን ጥሩነህ። መድረኩ በጭብጫቦ ተደበላለቀ  በተለይ ራቅ ላለ አካባቢ የመጡ ካድሬዎች ፉከራ ቢጤም ሞከሩ። ምክክሩ እስከ ምሳ ሰዓት በደስታ ታጅቦ ቆይቶ ምሳ ወጡ።

ለምሳ ከአዳራሽ የወጣው 2ሺ ካድሬ ወደየመጣበት አካባቢ እየደወለ ሁኔታውን ሲያጣራ ወፍ የለችም። ዘመነ ካሴን ያዘ የተባለው መከላከያ በጎንደር፣ በወሎ ፣በሸዋ እና በጎጃም በፋኖ እየተገረፈ መሆኑን ሲሰሙ  በብስጭት የጥፋት ምክክሩን ጨርሰው አበላቸውን አፍነው መመለሻ ጠፍቶ ባህርዳር ስራ አመራር ጊቢ ታሽገዋል።

ድሃ በህልሙ ቂቤ ይውጣል ነው የሚባለው?

Tilahun Abeje