የፍ/ሰ/ሰ/ት/ቤት መዝሙር ክፍል
1.48K subscribers
108 photos
14 videos
226 files
30 links
ይህ ገፅ የፍኖተ ሰላም ሰ/ት/ቤት የመዝሙር ክፍል ገፅ ነው
# መዝሙሮች
# የበዓላት ወረብ
# መልዕክቶች
ይለቀቁበታል።
Download Telegram
ቡሄ በሉ
ቡሄ በሉ ሆ /2/ ልጆች ሁሉ ሆ
የኛማ ጌታ ሆ የአለም ፈጣሪ ሆ
የሰላም አምላክ ሆ ትሁት መሃሪ ሆ
በደብረ ታቦር ሆ የተገለጠው ሆ
ፊቱ እንደ ፀሀይ ሆ በርቶ የታየው ሆ
ልብሱ እንደ ብርሀን ሆ ያንጸባረቀው
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና /2/
የቡሄው ብርሀን ለኛ አበራልን /2/
ያዕቆብ ዮሀንስ ሆ እንዲሁም ጴጥሮስ ሆ
አምላክን አዩት ሆ ሙሴ ኤልያስ ሆ
አባትም አለ ሆ ልጄን ስሙት ሆ
ቃሌ ነውና ሆ የወለድኩት ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና /2/
የቡሄው ብርሀን ለኛ አበራልን /2
ታቦር አርሞንኤም ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ
በቅዱስ ተራራ ሆ ስሙ ደስ አላቸው ሆ
ሰላም ሰላም ሆ የታቦር ተራራ ሆ
ብርሀነ መለኮት ሆ በአንቺ ላይ አበራ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና /2/
የቡሄው ብርሀን ለኛ አበራልን /2/
በተዋህዶ ሆ ወልድ የከበረ ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ ሆ ወልደ ማርያም ነው ሆ
ቡሄ በሉ ሆ /2/ የአዳም ልጆች ሆ
ብርሀን ተቀበሉ ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና /2/
የቡሄው ብርሀን ለኛ አበራልን /2/
አባቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
እናቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
አጎቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
አክስቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
ተከምሯል ሆ እንደ ኩበት ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና /2/
የቡሄው ብርሀን ለኛ አበራልን /2/
የዓመት ልምዳችን ሆ ከጥንት የመጣ ሆ
ከተከመረው ሆ ከመሶብ ይውጣ ሆ
ከደብረ ታቦር ሆ ጌታ ስለመጣ ሆ
የተጋገረው ሆ ሙልሙሉ ይምጣ ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና /2/
የቡሄው ብርሀን ለኛ አበራልን /2/
ኢትዮጵያውያን ሆ ታሪክ ያላችሁ ሆ
ባህላችሁን ሆ ያዙ አጥብቃችሁ ሆ
ችቦውን አብሩ ሆ እንደ አባቶቻችሁ ሆ
ምስጢር ስላለው ሆ ደስ ይበላችሁ ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና /2/
የቡሄው ብርሀን ለኛ አበራልን /2/
አባቶቻችን ሆ ያወረሱን ሆ
የቡሄን ትርጉም ሆ ሲያሳውቁን ሆ
እንድንጠብቀው ሆ ለኛ የሰጡን ሆ
ይህን ነውና ሆ ያስረከቡን ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና /2/
የቡሄው ብርሀን ለኛ አበራልን /2/
ለድንግል ማርያም ሆ አስራት የሆንሽ ሆ
ቅዱሳን ጻድቃን ሆ የሞሉብሽ ሆ
በረከታቸው ሆ ያደረብሽ ሆ
ሁሌም እንግዶች ሆ የሚያርፉብሽ ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና /2/
የቡሄው ብርሀን ለኛ አበራልን /2/
ለሐዋርያት ሆ የላከ መንፈስ ሆ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ
በበጎ ምግባር ሆ እንድንታደስ ሆ
ለቅን ልቦና ሆ ለጥሩ መንፈስ ሆ
በረከተ ቡሄ ሆ ለሁላችን ይድረስ ሆ
ድምፅህን ሰማና በብሩህ ደመና /2/
የቡሄው ብርሀን ለኛ አበራልን /2/
ዓመት አውደ ዓመት ድገምና ዓመት ድገምና
በጋሽዬ ቤት ›› ›› ››
ያውርድ በረከት ›› ›› ››
ወርቅ ይፍሰስበት ›› ›› ››
በእማምዬ ቤት ›› ›› ››
ይግባ በረከት ›› ›› ››
ማርና ወተት ›› ›› ››
ይትረፍረፍ በእውነት ›› ›› ››
እንዲሁ እንዳላችሁ በእውነት
አይለያችሁ አሜን
ለአመቱ በሰላም በእውነት
ያድርሳችሁ አሜን
ክርስቶስ በቀኙ በእውነት
ያቁማችሁ አሜን
የመንግስቱ ወራሽ በእውነት
ያድርጋችሁ አሜን
እንዲሁ እንዳለን በእውነት
አይለየን አሜን
ለአመቱ በሰላም በእውነት
ያድርሠን አሜን
አማኑኤል በቀኙ በእውነት
ያቁመን አሜን
የመንግስቱ ወራሽ በእውነት
ያድርገን አሜን
የቅዱሳን መላእክት የጻድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በዚህ ቤት
በዚህ ቤት /2/ ይግባ በረከት /2/
6
ሆያ ሆዬ
የደብረታቦር መዝሙር
ሆያ ሆዬ
ሆያ ሆዬ /4/
እዛ ማዶ        ሆ
ምን ይታያል
ታቦር ተራራ
ብርሃን ለብሷል
ጌታ ቀሚሱ
ያንፀባርቃል 
በክብር ውበት
በግርማው ቆሟል
ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ /2/
ሆያ ሆዬ /4/
ጴጥሮስ በግርማ       ሆ
እጅግ ደንግጦ
መሬት ወደቀ
እራሱን ስቶ
ኤልያስ ሙሴ
መጡ ከፊቱ
የእግዚአብሔርን ልጅ
ኑ ተመልከቱ
ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ /2/
ሆያ ሆዬ /4/
አብ በሰማያት        ሆ
ድምፁን አሰማ
ልጁን እንመን
እርሱን እንስማ
በፍቅር ብርሀን
እንዲያደምቀን
እንቅረብ ፊቱ
ስሙን አውቀን
ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ /2/
ሆያ ሆዬ /4/
ከደብረ ፅዮን          ሆ
ህዝቡን ይጠራል
በዚህ በግርማው
ዳግም ይመጣል
ከሙሴ ጋራ
ከኤልያስ
ሊያቆመን ቀኙ
እኛን በነፍስ
ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ /2/
ሆያ ሆዬ /4/
የሙሴን ጌታ         ሆ
ሙሴ ነው ሲሉ
እንደ ኤልያስ
ነቢይ እያሉ
አይሁድ ቢስቱ
ቢነሱበት
ኤልያስ ሙሴ
መሰከሩለት
ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ /2/
ሆያ ሆዬ /4/
የአመት ልምዳችን        ሆ
ከጥንት የመጣ
የቡሄ ለታ
ችቦ ሲወጣ
ከእማምዬ ቤት
ሙልሙሉ ይምጣ
ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ /2/
አመት አውደዓመት ድገምና አመት ድገምና /2/
የአባብዬን ቤት                "           "
ሰላም ይሙላበት
የእማምዬን ቤት
ፍቅር ይሙላበት
ክበር በንስሐ ክበር በፀሎት የነአባብዬን ቤት ጌታ ይግባበት
ክበር በንስሐ ክበር በፀሎት የነእማምዬን ቤት ጌታ ይግባበት
4
🔶 ቅዳሜ 9/12/2018 ዓ.ም መዝሙር እና ዝማሜ ጥናት ይቀጥላል ሁላችንም በሰዓት እንገኝ።

@fnotesmk
3
🔔ማስታወቂያ

🟠 ነገ 11/12/2018 ዓ.ም መዝሙር እና ዝማሜ ጥናት ይቀጥላል 12:00 ሰዓት እንገኝ።

🟠 በ12እና13 የቡሄ አገልግሎት እንዳለ ይታወቃል ሁላችሁም ወንድሞች 10:00 ሰዓት ተገኙ።

🟠 በ12እና13 የደብረ ታቦር ስራ ስለሚኖር አባላት እንድትሳተፉ እንጠይቃለን።


@fnotesmk
👍2
ዝማሜ👆🏼
🔘 ምትረተ ርእሱ ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ "መስከረም 2"

ሃሌ ሉያ እምኄሶ ለሄሮድስ ይብላዕ መሐላሁ እምያምትር ርእሶ ለዮሐንስ : ዓቢይ ነብይ ሰባኬ ጥምቀት :ለንሥሐ ከመይመኑ ህዝብ በብርሃኑ።
2
🔸ነገ 14/12/2018 ዓ.ም መዝሙር እና ዝማሜ ጥናት ይቀጥላል 12:00 ሰዓት እንገኝ።

@fnotesmk
@fnotesmk
@fnotesmk
የፍ/ሰ/ሰ/ት/ቤት መዝሙር ክፍል pinned «🔸ነገ 14/12/2018 ዓ.ም መዝሙር እና ዝማሜ ጥናት ይቀጥላል 12:00 ሰዓት እንገኝ። @fnotesmk @fnotesmk @fnotesmk»
📣 ማስታወቂያ
🔸ነገ 16/12/2018 ዓ.ም አገልግሎት ስለተጠራን 2:00 ሰዓት መጥታችሁ ልብሰ ስብሐት ውሰዱ።
▫️ቅዳሜ መዝሙር ጥናት አለ 12:00 ሰዓት እንገኝ።

@fnotesmk
@fnotesmk
የፍ/ሰ/ሰ/ት/ቤት መዝሙር ክፍል pinned «📣 ማስታወቂያ 🔸ነገ 16/12/2018 ዓ.ም አገልግሎት ስለተጠራን 2:00 ሰዓት መጥታችሁ ልብሰ ስብሐት ውሰዱ። ▫️ቅዳሜ መዝሙር ጥናት አለ 12:00 ሰዓት እንገኝ። @fnotesmk @fnotesmk»
▫️ነገ 17/12/2018 ዓ.ም መዝሙር እና ዝማሜ ጥናት አለን ያለን ጊዜ ትንሽ ስለሆነ እባካችሁ በጊዜ 12:00 ሰዓት ተገኝተን እናጥና።


@fnotesmk
@fnotesmk
@fnotesmk
3
የፍ/ሰ/ሰ/ት/ቤት መዝሙር ክፍል pinned «▫️ነገ 17/12/2018 ዓ.ም መዝሙር እና ዝማሜ ጥናት አለን ያለን ጊዜ ትንሽ ስለሆነ እባካችሁ በጊዜ 12:00 ሰዓት ተገኝተን እናጥና። @fnotesmk @fnotesmk @fnotesmk»