💕 ፍቅርን በቃላት 💕
98K subscribers
1.35K photos
259 videos
15 files
881 links
💞 ፍቅርን በቃላት 💞

♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር💟 ማለት፤

|➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
|➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
|➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟
💝የፍቅር ቃላት ሁሌም አሸናፊ ናቸው💝

ለማስታወቂያ ስራ ➢ @Naolviva

ғᴏʀ sᴘᴀᴍ 👇
@fkrn_be_kalat_bot

ᴇʏᴏʙ ᴍᴇᴋᴏɴɴᴇɴ 👇
@eyoba_king_of_reggaee
Download Telegram
በ'ነሱ ቤት
----------------------

    ክፍል አራት [፬]
.
.
.

ሰመረ እንደዚ አይነት መጨናነቅ የለመደ ልጅ አይደለም እና ሁኔታዋን አይቶ'ምነው እቺን ልጅ ላናድድ ብዬ ከተቀመጥኩበት ባልተነሳው በገዛ እጄ አባባይ ልሁን እኔ ሲጀመር ምን አገባኝ !ማድረግ ያለብኝን አድርጌላታለው በቃ የራሷ ጉዳይ 'ብሎ ትቷት ወደ ጓደኞቹ ተመለሰ ። ጓደኞቹ ገና ከመምጣቱ በተረብ አላስቀምጥ አሉት።
"እኔ የምልህ ከዚች አመዳም ጋር የዚን ያክል ክርክሩ ምንድነው ?ደሞ አይደብርህም እንዴ ያንን አስቀያሚ ጫማዋን ከእጇ እየነጠክ ትወረውራለህ ሃሃሃ በል በል አሁን ሂድና እጅህን ታጠብ ሆሆሆ ሳም ሙት! አንዳንዴ ምንም አትገባኝም በላይህ ላይ ጀርም ትጋብዛለህ ሃሃሃሃ"ብሎ ጌታነህ ሳቀበት ።እንየው ቀበል አድርጎ "እኔ እኮ የገረመኝ ገንዘብ አውጥተህ መስጠትህ ምን ፈልገህ ነው ግን ኪኪኪ ለነገሩ አጥበህ አስቆንጅተህ በትበላው የሚያስከፋ አይደለም በደንብ ከተያዘች ቆንጆ ነገር ናት ግን ጓደኞቼ እየወረዳቹ ነው ዛሬ 😀ወይ ከዚ በረንዳ ወደውስጥ እንግባ 😀"አለ ሳቁን መቆጣጠር እያቃተው ።
ሰመረ እነሱ የተናገሩት ነገር ምኑም ደስአላለውም ይብስ ተከፋ ሁለቱም ባሰቡት መንገድ እንዳላሰበ ደጋግሞ አስረዳ ። ከነሱ ጋር ክርክሩ አላዋጣ ሲለው አይኖቹን መልሶ ወደ መንገዱ ወርወር አደረገ አብላካት እየተወለጋገደች ሁለቱን ጫማወቿን አንጠልጥላ በተስፋመቁረጥ ስትራመድ አያት ለምን እንደው ያላወቀው ስሜት ወረረው ልቡ አዘነ ይህቺ ልጅ ገና ታዳጊ ናት ለምንድነው የዚን ያክል መከፋት ያለባት ምን አይነት የተቸገረ ቤተሰብ ቢያሳድጋት ነው እንዲ የሆነችው አለ ለራሱ ፣ሰው በዚመጠን ደሃ ይሆናል ጫማ እስከመዋዋስ ለዛውም ጀየሚያስጠላ ጫማ ይገርማል ። በመንገዱላይ ብዙ ሰው አይታይም አብላካት ያመንገድ አላልቅ ያላት ይመስላል በራሷ በጣም ተሸማቃለች ገና ከሳምንት ጀምሮ ስትዘጋጅበት የነበረ ቀጠሮ ነው የተበላሸባት ለሷ የመጀመሪያ ቀጠሮዋ ነው ለዛውም ከችግር የምትወጣበት ቀጠሮ ነገር ግን በገዛ እጇ አበላሸችው ምነው ታምራትን ከማስከፋው የራሴን ጫማ አድርጌ በመጣው ይሄኔ እኮ አግኝቼው የምሰራበትን ቦታ አሳይቶኝ ሁሉም ነገር ተስተካክሎ እመለስ ነበር የተረገመ ጫማ ።ደሞስ ምን አጣደፈኝ ቀስ ብዬ አልሻገርም ነበር ።በራሴው ስህተት ነው ስራውን ያጣውት ።ዕድ ለቢስ ነኝ ሲጀመር ብላ ስንጥቅ የበዛባትን የሞባይል ስልኳን አየች በተስፋ ታምራት የተባለው የፌስቡክ ጓደኛዋ ይደውል ይሆናል በሚል ምኞት ።ይህችን የሞባይል ስልክ ከሰው ላይ የገዛችላት እናቷ ነች ከዘጠኝ ወደ አስር በጥሩ ውጤት ስላለፈችላት ደስታዋንና በሷ መኩራቷን ለማሳየት ።እና አብላካት የዛንቀን ከጓደኞቿ እኩል ሞባይል በመያዟ ደስታዋ ወደር አልነበረውም። ከዛን ጊዜጀምሮ ፌስቡክ ከፍታ ከተለያዩ ሰዎች ጋር ታወራለች ከአንገት በላይ ተነስታ የምትለቃቸው ፎቶዎቿ የሚስቡ በመሆናቸው ብዙ ወንዶች ኢንቦክስ እየገቡ ያወሯታል የፍቅርጥያቄ ያቀርቡላታል አብላካት ለሁሉም በየዋህነት ገና ለዛ እንዳልደረሰች ትፅፍላቸዋለች ።ብዙዎቹ ያለምጡባታል ።ከነዛ ውስጥ ግን የታምራት አቀራረብ ይመቻታል ልጅነቷን ስትነግረው መገመቱን እና እሱ እህት እንዳለው ልክ በሷ ዕድሜ መሆኗን እየነገረ አግባባት ከዛ በዋላ ስለቤተሰብ ስለትምህርት እየጠየቀ ችግሯን ሁሉ ሳትደብቅእንድትነግረው አደረገ ከዛም ነገረችው ።እናቷ እሷን በልጅነቷ ሰውቤት ሰራተኛ ሆና ከአሰሪዋ ልጅ እንዳረገዘቻትና አሰሪዎቿ ይሄንን ሲያውቁ እንዳባረሯት ከዛም እሷን ጎዳናላይ እንደወለደቻት ከዛ በዋላም እናቷ እጅ ሳትሰጥ ጉሊት እየሰራች ፍራፍሬ አትክልት እየሸጠች እንዳሳደገቻት አወራችው ።በጣም የሚያሳዝን ታሪክ እንዳላት እና እሷን ለመርዳት ሲል የአክስቱን ልጅ እንደሚያናግራት እና እሷ ፑቲክ ውስጥ እንደሚያስቀጥራት ነገራት ።ይሄንን ያላት ቀን በደስታ ነበር የሰከረችው ። በተለይ እናቷ ከቅርብ ጊዜ ወዲ እግሬን እየወጋኝ ነው እያለች ከምትሰራበት ጉሊት መመለሷ እየተለመደ መጥቷል እመም ይሰማታል ይሄን ስለምታውቅ ።እሱ ስለስራ ሲያወራት ቀጥታ የታያት እናቷን ማገዟ ነው ።አብላካት ስላረፈድሽ የማልቀርበት ጉዳይ ስላለኝ ሄጃለው ባይሆን ማታ ተገናኝተን ተጫውተሽ ትመለሻለ ሲላት አይመቸኝም ስትለው ድንገት ቅይር ብሎ ካልሆነ ይቅርብሻ ነበር ያላት በጣም ተናዳለች በፌስቡክ እንዳወራት አልሆነላትም ።ሰው በአንድጊዜ ጥፋት እንዲ ይለወጣል ያሳዝናል ።'ወይኔ እናቴ መቼ ልደርስልሽ ነው 'እያለች በአዘን ተቆራምታ በባዶእግሯ ትጓዛለች ። ሰመረ የሰጣትን ብር ጨምቃ ይዛታለች ።
*ሰመረ ተነስቶ ቆመ ጓደኞቹ እኩል ወዴት ነው አሉት መጣው ብሎ በረንዳውን በፍጥነት መውረድ ጀመረ
ጓደኞቹ ግራ በመጋባት ተያዩ ሰመረወደ አብላካት አቅጣጫ ፈጠነ,,,,,,,

ይቀጥላል........


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         

       @fkrn_be_kalat_bot
     ❥❥________⚘_______❥❥
በ'ነሱ ቤት
------------------

    ክፍል አምስት [፭]
.
.
.

አብላካት ገና በጠዋቱ ከሕይወት አስከፊ ጎን ጋር ተላትማ ፡ባልገባት የኑሮ ሁኔታ ተጠላልፋ ግራ እንደተጋባች እንድትጓዝ ማን እንደፈረደባ አሰበች ፡ማነው እንዲ እንዲሆን የሚያደርገው ፈጣሪዬ እኔና እናቴ ምን ብናረግ ነው በችግር የምንጠበሰው ። ለምን ?ለምን ? አሁንስ ማልቀስ እራሱ ሰለቸኝ ኡፍፍፍ ......
"ሚጣ ሚጣ...."ሰመረ እሮጦ ደረሰባት
"አብላካት ነው ስሜ !"አለች አብላካት። ሰመረን ዞራ እንኳ ሳታየው
"እሺ አብላካት "አላት ከፊቷ ቀደም ብሎ በመቆም
"ምን?"አለችው በግዴለሽነት
"ይሄውልሽ ቅድም ከሆነ ሰው ጋር በስልክ ስታወሪ ሰምቼሻለው እና ስለሱ ማወቅ ፈልጌ ነው "አላት
"ለምን ማወቅ ፈለክ እሱ የኔ ጉዳይ ነው?!"አለች ለመሄድ እየሞከረች። ሰመረ ከፊለፊቷ ቆሞ አገዳት
"እባክህ የታመመች እናት አለችኝ ቢያንስ ገብቼ ልያት "አለች ፍቃድ የምትጠይቅ መስላ
"እሺ ትሄጃለሽ ችግር የለም እዛችጋር መኪና አቁሜያለው እኔ ይዤሽ እሄዳለው በርሽ ድረስ ከፈለግሽ ።ግን ያ በስልክ ያናገርሽው ሰው ማነው በማታ ለምን ቀጠረሽ"አላት
"ማነወ በማታ የቀጠረኝ እንደሱ ማን አለ"አለች ደንገጥ ብላ
"ሰምቼሻለው በማታ እናቴ አትፈቅድልኝም ስትዪ "አላት እጇን ይዞ እንድታወራ እየገፋፋት
"እባክህ በቃ ተው ያበቃለት ጉዳይ ነው ፡ሁሉም ነገር ተበላሽቷል "አለች
"ምንድነው የሚበላሸው ለምን አታወሪም "አላት ቆጣ ብሎ ፡
"እሺ ይህውልህ እሱን የማውቀው በፌስቡክ ነው አግኝቼው አላውቅም ስራ ሊያስገባኝ ነበረ ፡ዛሬ የተቀጣጠርነው ታውቃለህ ለኔ ጥሩ ስራ ነበረ እናቴን ላግዛት የምችልበት ብቸኛው መንገድ ፡ስራው ቀላል ነበረ ቡቲክ ቤት ደሞ እህቱ ነበረች የምትቀጥረኝ ።አስበህዋል ግን በዚ ጫማ የተነሳ ስራውን አጣውት ።እዛ ጉሊት ላይ በፀሐይ የምትንቃቃዋ እናቴ ዕድለኛ አይደለችም ።ለኔስትል አመድ እንደወረሳት እንድትኖር የሆነ አይል ፈርዶባታል ምስኪን እናቴ በዛላይ ታማለች አቤት ስቃይዋ ።እሷ እየተቃጠለች ለኔ ብርሃን ለመሆን ትጥራለች ኡፍፍፍፍ "ብላ ተነፈሰች
ሰመረ ግራ ገባው እሱ ከአብላካት የሚሰማው የኑሮ ዓለም የተለየ ነው አይቶም ሰምቶም አያውቅም መቼስ ስለዚ ልብ የሚልበት ጊዜ ኖሮት ያውቃል
በጭንቀት ሲመለከታት ቆይቶ
"እሺ ያሰው በፌስቡክ የምታውቂው ሰው ።እንዴት ትክክለኛ ሰው ነው ብለሽ አሰብሽ ።አንቺ እንዳልሺው ጥሩ ሰው ባይሆንስ ።አንቺን ለማማለል ሲል ቢሆንስ አንቺ ስለ ወንዶች የምታውቂው ነገር የለም ስራ ላስቀጥርሽ ብለው ልጁ ነትሽን የሚጠቀሙ ስንት አብታም ሰወች አሉ መሰለሽ "አላት እንዴት ማውራት እንዳለበት ግራ እየገባው
"አይ እሱ አይደለም ጥፋተኛ እኔ ነኝ በጫማው ምክንያት ነው"
"አይ አይደለም መጀመሪያም ያሰው ስራ ሊያስቀጥርሽ ፈልጎ አይደለም ስለዚህ በጭራሽ ደግመሽ እንዳታናግሪው ። መልካም ሰው ቢሆን ማታ ካልመጣሽ አይልሽም እሺ"አላት እንዴት እንደሚያስረዳት እየጨነቀው።አብላካት ሰመረን ለመጀመሪያ ጊዜ አተኩራ ተመለከተችው እናም ገረማት እንዴት ከቅድም ጀምሮ አሳቢ ሆኖ ሊረዳኝ ፈለገ በጣም የሚያምርና ሀብታም ወጣት ወይም የሀብታም ልጅ እንደሆነ ያስታውቃል ሁሉ ነገሩ ፅድት ያለ ነው አጥብቆ የያዛት እጁ እራሱ ጠንካራ ቢሆኑም ለስላሳ ናቸው ። ቀናችበት ምንም አይነት አሳብ ያለበት አይመስልም ።
"ሲጀመር እሱም አያናግረኝም ለማንኛውም ግን አመሰግናለው ።አሁን ወደ ቤት መመለስ አለብኝ "አለችው ሰመረ እጇን እንደያዘ
"ቆይ እዛ ጋር ባንክ ይታየኛል በኤትዬም ገንዘብ አውጥቼ እሰጥሻለው ።የቅድሙ ጥሩ ጫማ ለመግዛት አይበቃም "አላት
"አይ አይ ለኔ ብዙ ነው አንተ አትቸገረ አንድ ጫማ አይደለም አራት ጫማ የሚገዛ ገንዘብ ነው የሰጠኽኝ "አለች
"ግድ የለሽም ሚጣ በዛላይ የታመመች እናት አለሽ"አላት
"ስሜ አብላካት ነው ሚጣ መባል አልፈልግም ነገርግን ለመልካም አሳብህ ምስጋና አለኝ ።ከዚ በላይ ግን ብቀበልህ አይናውጣነት ነው "አለች አብላካት ። ሰመረ ክስተር ብሎ
"አታስቸግሪኝ እባክሽ እኔ ንዴት አልችልም ካልኩ አልኩ ነው የወሰንኩበትን ነገር ከማድረግ የሚከለክለኝ ሰው ያበሳጨኛል እና ብሩን አውጥቼ እሰጥሻለው ይዘሽ ትሄጃለሽ ።እና ደሞ ከዛሰው ጋር ዳግም ላታወሪ ቃል ትገቢልኛለሽ አለቀ "አላት ።አብላካት ፊቱን ስታየው ከምሩን እንደሆነ ተሰማት ።እናም እጇን እንደያዛት ወደ ኤትኤም ማሽኑ ሲያቀና ።በዝምታ ተከተለችው ። ሁኔታውን ከርቀት ሲከታተሉ የነበሩት ጓደኞቹ ጉዱን እንየው ብለው ወደነሱ መጡ ። አብላካት በዙሪያዋ በሚገባ የለበሱና የሚያማምሩ ወጣቶች ድንገት መከበቧ ሰላም አሳጣት በተለይ የሁለቱ ወጣቶች አስተያየት አስጨነቃት ። ፍርሃት ወረራት አይኖቿን ወደ ሰመረ ተከለች ።ከነዚ የሚያስጨንቅ አስተያየት ካላቸው ጓደኞችህ አድነኝ የምትል ይመስላል .............

ይቀጥላል........


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         

       @fkrn_be_kalat_bot
     ❥❥________⚘_______❥❥
በ'ነሱ ቤት
-------------------

    ክፍል ስድስት [፮]
.
.
.

ሰመረ የጓደኞቹ በአብላካት ዙሪያ ሽርጉድ ማለት አልተመቸውም ።እነሱን የራሱን ያክል ያውቃቸዋል ምን አስበው እንደሚዞሯት ያውቃል ።ያንን ሲያስብ ደሞ ስቅጥጥ አለው ።ምክንያቱም አብላካት ለሱ ያልደረሰች ልጃገረድ ፡ገና ምኑንም የማታውቅ ታዳጊ ናት እና የነሱ አቀራረብ ምቾት አልሰጠውም ።
እነሱ ደሞ የሰመረ እሳን ለመርዳት እያደረገ ያለው ጥረት ትንሽ ከተለመደው ማንነቱ ውጪ ሆኖባቸው እየቀለዱበትም ጭምር ነው ።
አብላካት ሰመረ በኤትኤም አውጥቶ ስለሰጣት የብር ኖቶች እራሱ ለማጣራት ጊዜ እስከማታገኝ ድረስ ነው የጨነቃት ።የነ ጌታነህ አነጋገር አሳሳቅ አስተያየት ብልግና እንዳለበት ልቧ ነግሯታል እናም በፍጥነት ከነሱ መራቅ ፈልጋለች ስለዚ ሰመረ የሰጣትን ብር ምንም አይነት አስተያየት ሳትሰጥ ያረጀች ቦርሳዋ ውስጥ በፍጥነት ከተተች እና ሰመረ ቶሎ እንዲሸኛት አይን አይኑን አየችው። ሰመረ ስሜቷን የተረዳ ይመስል ከእነሱ ሊያርቃት እጇን ይዞ ወደፊት ተራመደ ። ጌታነህ ተከተላቸው
"ቆይ ቆይ ከዚች ልጅ ጋርማ በደንብ ነው መተዋወቅ ያለብን ።ስምሽ ማነው ግን "አላት
"አ አብ ላካት መሳይ "አለችው ድምጿ እየተርገበገበ
"ውይይ እንዴት ደስ የሚል ስም ነው ከነ አባትሽ ጭምር !"አለ በፌዝ እያጋነነ
"በቃ ተመለሱ እኔ ሸኝቻት እመጣለው "አለ ሰመረ የጓደኛው ቀልድ ለመጀመሪያ ጊዜ እየደበረው
"ኧረ አንተ ደሞ የኔንም ስም ልንገራት ።እኔ ጌታነህ እባላለው ያኛው ጓደኛዬ ደሞ እንየው ይባላል"አላት ፈንጠር ብሎ ወደ ቆመው እንየው እያሳያት ።እንየው አብላካት ስታየው እጁን አውለበለበላት ።
አብላካት አይኗን ወደ ሰመረ መለሰች ።እናም
"እእ እኔ ብቻዬን እሄዳለው ላደረክልኝ ነገር በሙሉ አመሰግናለው ።"አለችው ።ሰመረ ጥቂትሲያያት ቆይቶ "በቃ እሺ ሂጂ እዛች ጋር ላዳዎች ታገኛለሽ ።በቀጥታ ግን ወደ ቤት ሂጂ በፍፁም እዛ ሰው ጋር እንዳትሄጂ እሺ "አላት ።አብ ላካት አንገቷን ነቀነቀች እና እንደማትሄድ አረጋገጠችለት ።ሰመረ ጥሩ ብሎ እንድትሄድ ፈቀደላት ።አብ ላካት መንገድ ስትጀምር ።ጌታነህ በሰመረ ቀለደበትና እሱን አልፎ በመሄድ አብላካትን አስቆማት ።ሰመረ ጨነቀው ለመጀመሪያ ጊዜ በጓደኛው ተማረረበት ።ምንድነው አንዲት ትንሽ ሴት ልጅ ላይ የዚን ያክል ፍላጎት ማሳየት ።
"ቆይ ቆይ አቢዬ በናትሽ ስልክሽን ስጪኝ ለሌላ ነገር አደለም ብቻ በሰላም መግባትሽን ለማወቅ ስለሚያስፈልገን ነው እሺ የኔ ውድ "አላት አብላካት አመነታች ።ጌታነህ ደጋግሞ ሰላሟን ለማረጋገጥ ስለፈለገ ብቻ መሆኑን ሲነግራት እሺ ብላ ሰጠችው ።ጌታነ ስልኳን አባብሎ ሲቀበላት ።ሰመረ ንዴቱ ጨመረ ነገር ግን እሷው ስለሰጠችው ምንም ነገር ከመናገር ተቆጠበ ። አብላካት ከጌታነህ ጋር ስልክ ከተለዋወጠች በዋላ ፈጠን ፈጠን እያለች ዞራ ሳትመለከት ሄደች ። ጌታነ በድል አድራጊነት ።ወደነሰመረ እየሳቀ ሲመጣ ።ሰመረ አንገቱን ነቀነቀበት ።ጌታነ ይበልጥ ስቆበት
"ምንድነው ዛሬ ሰሙ ሃሃሃሃሃሃ እቺን እንቡጥ በጣም አባበልሻት ሃሃሃሃሃሃ! ግን በስተመጨረሻ አላወቅሽበትም ያሁሉ ብር ሰጥተህ በነፃ ልትሸኛት እናስ እኔ ጌትሽ ከአፍሽ ላይ ሞጨለፍኩሽ ።'እሟ ቀሊጥ !' አለ ጋሼ ሃሃሃሃሃ ተበላ!"አለው ስልኩን ከፍ አድርጎ እያሳየው
"ምን አስበህ ነው ? አታረገውም ገና ትንሽ ልጅ ናት እኮ በዛላይ ችግር ውስጥ ናት አንተ ደሞ ታበዛዋለህ !ሴት አጥተህ ነው ?ያው ቅድም ስልክ ስትሰጥ አልነበረ እንዴ ለዛች ለኮስሞቲክሷ ልጅ !ምንድነው እንዲ የሚያደርግህ ?"አለው ከምሩ ተቆጥቶ
"ሃሃሃሃ ምን ፈልጌ እንደሆነ ልንገርህ ምንም ያልተነካካች እንቡጥ "
"ነው እንደዛ ከሆነ መቼም ቢሆን አትነካትም እሺ"አለው ሰመረ በእልህ። እንየው የነገሩ መቀየር አስጨነቀው ከዚ በፊት በጓደኞቹ መሃል እንዲ አይነት ፀብ የሚመስል ነገር አይቶ አያውቅም ።
"ይቅርታ ይህንን ነገር መተው አትችሉም ።ይልቅ አንድ ቦታ ሄደን ዘና እንበል ቅዳሜን በዚ መልኩ አታበላሿት "አለ
"አይ አይ ይናገር ልጅቷን አትነካትም ነው አይደል ያልከው በቃ ታየኛለህ በቅርቡ ።ታውቀኛለ የፈለኩትን ለማግኘት ምን ያክል እርሸት እንደምሄድ "አለው እያመረረ ።ሰመረ የጌታነህ የለየለት ጭካኔ ደበረው ።ከሱጋር የእልህ ወሬ ከማውራት ቢቀርብኝ ይሻላል ። ልጅቷን ይበልጥ ችግር ውስጥ መክተት ነው ብሎ እራሱን አረጋጋ እና የጌታነህን ደስ የማይል ወሬ ችላ ብሎ ከእንየው ጋር ስለሚያመሹበት ቦታ ማውራት ጀመረ ,,,,,,,,,,

ይቀጥላል........


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         

       @fkrn_be_kalat_bot
     ❥❥________⚘_______❥❥
በ'ነሱ ቤት
-------------------

    ክፍል ሰባት [፯]
.
.
.

አብላካት ከራሷ ጋር ስለችግሯ መብዛት እያወራች ከአምላኳ ጋር እየተሟገተች ረጅም መንገድ በእግሯ እንደተጓዘች እንኳ ልብ አላለችም ። በቻ ከዋላዋ አንድ ወጣት መጥቶ "እናት ጫማሽን ላሰራልሽ "ሲላት ።እንደመባነን አለች በቀጥታ ወደ እግሯ አየች መሬት ለመርገጥ የሚያሳዝኑት እግሮቿ ስቃይ የበዛባቸው መሶለው ታዩዋት ለዎትሮው ምንም የተሻለ ጫማ ባይኖራትም በእግሯ ግን ተራምዳ አታውቅም እንዲሁም መሬት ሲነካት ትንንሽ ጠጠሮች እንኳ ሲነካት እግሯን የበሳት ያህል ነው የሚያማት ። አብላካት ከዳሃዋ እናት ተገኝታ እንጂ ሁሉ ነገሯ የሚሳሳለት ነበር ። እናቷም ብትሆን ባላት አቅም ልጇ እንዳይከፋት ታግላ ነበር ።አሁን ላይ ግን ምን እንደሚያማት ባታውቅም እመም እየደቋቆሳት የለት ጉርሳቸውን ከሟሟላት የዘለለ ለማድረግ አቅቷታል ። አኪም ጋር ሄዶ ለመታየት እራሱ ልቧ ፈርቷል ።እክምናው በቀላሉ የሚታይ ባይሆንስ ገንዘብ አውጥቶ ለመታከምም የተቀመጠ ነገር ያስፈልጋል እናስ ከየት ሊመጣ ነው ። የአብላካት እናት ባይሆን የምታመሰግነው ።አንዲት በእድሜ የገፉ የነበሩ ሴት አስጠግተዋት ኖረው የቀበሌ ቤታቸውን ስላወረሷት ።የቤት ክራይ ጭንቀት ስለሌለባት ነው ። አንዳንዴ ተከራይ ብሆን ኖሮ እኔና ልጄ ጎዳና እንወጣ ነበር ።እማማን ነብሳቸውን በገነት ያኑርልኝ ትላለች።
አብላካት ያናገራትን ወጣት ቀና ብላ ስታየው ልቧ ደነገጠባት ።ቅድም ከመኪናው ጎትቶ ያወጣት ያስተናጋጅ ልብስ ለብሶ የነበረው ወጣት ።እሱ ደሞ ለምን ተከተለኝ በዛላይ ልብሱን ቀይሮ በኖርማል ልብስ ነው
"አልሰማሽኝም ሰሚር ጅላሉ እባላለው "
"እሺ ምን አልከኝ "አለች እየደበራት
"ጫማሽን ላሰራልሽ እዛ የሊስትሮ እቃ የያዘ ልጃለ አየሽው "አላት
"እንዴት እዚ ድረስ ተከተልከኝ "አለችው በጥርጣሬ እያየችው
"እሱ አስፈላጊ ነው ?"አላት
"አይ ግን ማወቅ ያለብኝ ነገር ካለ ብዬ ነው"
"አትጨነቂ ቅድም ሳይሽ ፍፁም ከራስሽ ጋር አልነበርሽም በዛላይ እነዛ የሀብታም ልጆች ሲከተሉሽ ደስ አላለኝም ምክንያቱም እነሱን እኛ እሬስቶራንት ሲመጡ አቃቸዋለውአንድም ቀን ስለሴት ልጅ መልካም የሆነ ነገር ሲያወሩ ሰምቼ አላውቅም እና ከንቺን እንዳይተናኮሉሽ ፈርቼ ነበር ። ለዛ ብዬ ሰአቴም እየደረሰ ስለነበር ከስራ ወጣው እና እየተከታተልኩሽ ነበር ።ለምን ልጅ ስለሆንሽ ብር ሲሰጥሽ በቀላሉ እንዳትሸወጂለት ለመንገር እና ልረዳሽ የምችለው
" ነገር ካለ ልጠይቅሽ ፈልጌም ነው "አላት ሰሚር
"ይቅርታ ልጅ ስለሆንሽ እንዳትለኝ እና በቀላሉ በገንዘብ ትታለያለሽ ብለህ አታስብ እና አመሰግናለው ላደረክልኝ መልካምነት ጫማውን እንድናሰራው የጠየከኝን ግን ተቀብዬዋለው እሺ"አለች ለምን እንደው ባታውቅም ሰሚርን አምናዋለች
"እሺ ነይ በቀላሉ ያስተካክሉታል አትጨነቂ እስከዛው ግን ከዛ ሱቅ ሲሊበር ጫማ እንገዛና ታደርጊያለሽ "አላት ሰሚር በአዘኔታ እያያት ።አብላካት ተስማማች ከሰሚር ጋር ጫማ ገዛች የጓደኛዋን ጫማ አሰራች አብረው እየሄዱ ብዙ አወሩ ስለራሷ ምንም ሳትደብቅ አወራችው ።ሰሚር የሰማውን ሁሉ ሰምቶ ዝም አላለም ስለራሱ አጫወታት አመጣጡ ከደቡብ ኢትዮጲያ ገጠር አካባቢ መሆኑን እዛ የሚረዳቸው እናትና ታናሽ እህት እንዳለው ።አባቱ መሞቱን የቤተሰብ አላፊነቱን እሱ መውሰዱን ። አብላካት የሱን ታሪክ ስትሰማ ትንሽ ቀለላት ። ሰሚር የሚያፅናናትን ቃላት ሁሉ እየነገረ አብሯት ሰፈሯ ድረስ ሄደ ። አብላካት ሰፈሯ ስትደርስ ያካባቢው ሰዎች ደሞ ከወንድ ጋር አየናት ብለው እንዳያወሩባት በማሰብ ።
"በቃ ሰሚር ሌላ ጊዜ እንገናኛለን ቻው አመሰግናለው አለችው"ሰሚር ስለገባው
"እሺ ብዙ አትጨነቂ እሺ ሁሉም ነገር በሰሃቱ ይስተካከላል ኢንሸሀላ እኔም ዝም አልልሽም እኛጋር መስተንግዶ እንድትሰሪ አነጋግርልሻለው እሺ "አላት እንደታናሽ እህቱ በማባበል
"እሺ እሱን ካመቻቸህልኝ ባለውታተዬ ነህ "አለችው ሲሰነባበቱ እንደታላቅ ወንድምና እንደ ታናሽ ወንድም በመተሳሰብ ነበር,,,,,,,,,

ይቀጥላል........


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         

       @fkrn_be_kalat_bot
     ❥❥________⚘_______❥❥
(ጸሐፊዎች ለሚወዷቸው ሰዎች ከጻፉት የፍቅር ቃላት)

1- ከካፍካ እስከ ሜሊና፦

“አልወድሽም! ይልቁንም በአንቺ የተገኘ የእኔን መኖር እወደዋለሁ..”

2- ከሞሪድ ባርጋውቲ እስከ ራድዋ አሹር፡-

“ ነፃ እንደወጣች ሀገር ቆንጆ ነሽ፤ እኔ ግን እንደተወረረ ሀገር ደክሞኛል!”

3- ከጓሳን ካናፋኒ እስከ ጋዳ አል-ሰምማን፡-

“ከእንግዲህ የእኔ የጭንቅ ሁኔታ ደግሞም ያንተን ሀዘን ለመደበቅ እና ለመቅበር ተነስቻለሁ ይህም በጣም ስለምወድህ ነው።”

4 - ከጁልዬት እስከ ቪክቶር ሁጎ፦

“እወድሃለሁ እውነት ነው! ያለፈቃዴ ያለምርጫዬ በዚህ አለም ላይ የተፈጠረው ነገር አንተ መውደድ ነው።”

5- ከጅብራን እስከ ዝያዳ፦

“ትንሿ ልጄን እወዳታለሁ፤ ነገር ግን ለምን እንደምወዳት በአዕምሮዬ አላውቅም፣ በነፍሴ እና በልቤ እሷን መውደድ በቂ ነው።”

6- ከሊዮ ቶልስቶይ እስከ ቫለሪያ አርሴኔቭ፡

“ውበትሽን ለረጅም ጊዜ ወድጄዋለሁ ነገር ግን በአንቺ ውስጥ የማይሞተውን እና ዘላለማዊ የሆነውን  ልብና ነፍስሽን መውደድ የጀመርኩት ገና አሁን ነው።”

7- ዶስቶይቭስኪ ለሚስቱ አና፡-

“በትዝታ እንኳን አልከዳውሽም!”

🪴🌹አሁኑኑ ሼር አድርጉ 🌹🪴

    ♥️
@fkrn_be_kalat ♥️
       🌹 ፍቅርን በቃላት 🌹
...........♥️💍••●🍃🌹🍃●•........
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌    ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
በ'ነሱ ቤት
-------------------

    ክፍል ስምንት [፰]
.
.
.

የቤቱ ድባብ የሚመች አይደለም በሰውኛ ቢሆን ቅዝዝ ብሏል ሊባል ይችላል ። አብላካት እናቷን ደጋግማ እየተጣራች ወደውስጥ ገባች በሩ ክፍት ነው መብራቱ ግን አልበራም ።ግራ እየገባት ወደ ጓዳ ዘለቀች እናም አይኖቿን በቀጥታ ወደ አልጋው ወርወር አደረገች ። በአልጋው ላይ እናቷን ጥቅልል ብላ ተኝታ አገኘቻት አብላካት እናቷ ስላለች እፎይ ብትልም ዳግም እንዳመማት ስለገባት ጭንቅ አላት እና ተጠግታ ትንፋሿን አዳመጠች ቶሎ ቶሎ ትተነፍሳለች ። ፊቷን ከጉንጯ ጋር አገናኝታ አሻሸቻት ።እናቷ ግን ጭልጥ ያለ እንቅልፍ ውስጥ ገብታለች ።ቀስብላ ተነሳችና ሄዳ የቤቱን በር በመዝጋት ተመልሳ መጣች ያደረገቻትን ሲልፐር ጫማ በማውለቅ ከእናቷ ጎን ተኛች ምን አልባትም በርዷት ሊሆን ይችላል ብላ በማሰብ አቀፈቻት ። እናም ስለ እናቷ አሰበች 'አንድ ነገር ብትሆንብኝስ ምንድነው የምሆነው? ያለ እሷ ማን አለኝ ? ያለሷ ፍቅር እንዴት እኖራለው ሲከፋኝ ስጨነቅ ሳዝን ማን አለው ብሎ ያፅናናኛል ኡኡፍፍፍ እናቴ ምንም አትሁኚብኝ ፈጣሪዬ አደራህን ' ብላ ይበልጥ በእናቷ ዙሪያ የጠመጠመችውን እጇን ይበልጥ አጠበቀች ። በዚ ጊዜ እናቷ በረጅሙ ተንፍሳ አይኗን ቀስበቀስ ገልጣ አየቻት እናም ፈገግ አለች ።አብ ላካት እንባ ባቀረሩ አይኖቿ እያየቻት
"እናቴ የኔ ውድ እናት ነቃሽልኝ "አለቻት
"ምነው አቢ ?ፊትሽ ልክ አይደለም ?ተኝቼ ስለጠበኩሽ ነው ? ይቅርታ የኔ ቆንጆ ልጅ አሁን ተነስቼ ቤቱን ሞቅ ሞቅ አደርገዋለው ። ቅድም እኮ ጉሊት ወጥቼ ብታይ ፀሐዩ አናት አናቴን ሲለኝ እራሴን አመመኝና ከተወኝ ብዬ ወደቤት መጥቼ ጋደም አልኩ በሩን እንኳ አልዘጋውትም እኮ ቶሎ እነሳለው ብዬ ሆሆሆ "እያለች የአብላካትን ግንባር ሳም ሳም አደረገች ።አብላካት እናቷ ህመሟ ከዛም በላይ መሆኑን ታውቃለች ።ስለዚ እራሷ ከተኛችበት በመነሳት ።
"እማ አንቺ ተኚ እረፍት አድርጊ እኔ ቆንጆ ቡና አፈላልሻለው "አለቻት
"አይ አብዬ እኔ ነኝ እንጂ ልጄን መንከባከብ ያለብኝ ደሞ በዛላይ ለአራት ሰአት ያህል የት እንደነበርሽ ትነግሪኛለሽ እሺ "አለቻት ልጇን መጫን ባትወድም አንዳንዴ እሷ ስራስራ ስትል ከቁጥጥር ውጭ እንዳትሆንባት ትሰጋለች
"ውይ እናቴ አሁንስ ይበቃል ስለኔ የምትጨነቂበት ጊዜ አልፏል ትልቅ ሆኛለው እኮ እንዴዴዴ ከዚ በዋላ ስራ ፈልጌ መግባት አለብኝ እራሴንም መቻል እንዲሁም ላንቺም መትረፍ አለብኝ እስከመቼ ነው የምታባብይኝ !"አለቻት አሳቧን እንዳትቃወማት እያስጠነቀቀችም ጭምር
"ወይ ስራ ወይ ትልቅ ሰው አብዬ አንቺ መቼ ከስራ ተለይተሽ ታውቂና ነው ይኽው ከኔጋር ከእፃንነትሽ ጀምሮ ጉሊት ስትሰሪ አልነበር ።የኔ ውድ አንቺ እኮ ልህልት ነበርሽ ምን ዋጋ አለው ከኔ ተፈጥረሽ ተሰቃየሽ አሂሂሂሂ"ብላ በቁጭት እጇን ጨበጠች
አብላካት እናቷ በዛመልኩ እንዳታስብ እያፅናናች ሳመቻት እናም ከቤት ምን አስባ እንደሄደች አንዳችም ነገር ሳደብቃት አወራቻት ።ስለ ሰመረ ስለ ጓደኞቹ ስላደረገላት ነገር ስለ ሰሚር ሁሉንም ።
የአብላካት እናት ፊቷ ላይ ምንም ነገር ባታሳይም በልጇ ገጠመኝ ተጨንቃለች ።በተለይ ሰመረ የሰጣት አምስት ሺ ብር ያለነገር አይደለም ብላ ፈርታለች ። የምትፈራው ነገር ሊደርስ እንደሆነ ተሰማት በተለይ የልጇ ውበት እያደገች በሄደች ቁጥር ሲጨምር አንድ ቀን በጨካኝና ደንታ በሌለው ወንድ እጅ ትወድቅብኛለች ብላ ትፈራ ነበር ።ያጊዜ የደረሰ መሰላት ። አንድ ልጇን ልክ እንደሷ ሕይወቷን እንዲያበለሻሹት አትፈልግም ።ልጇን ደሞ እንዲእያለች ፍርሃት መልቀቅ የባስ እንድትደናበር ማድረግ እንደሆን ተሰማት ድንገት ያደገችውን ልጇን በስስት እያየች በረጅሙ ተነፈሰች ኡፍፍፍፍፍ,,,,,,,,

ይቀጥላል........


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         

       @fkrn_be_kalat_bot
     ❥❥________⚘_______❥❥
በ'ነሱ ቤት
-------------------

    ክፍል ዘጠኝ [፱]
.
.
.

ቦሌ አካባቢ የምትገኝ አነስተኛ ናይት ክለብ ውስጥ እነ ሰመረ በሞቅታ ጮክ ብለው እኩል በሚባል ደረጃ ያወራሉ ። አልፎ አልፎ ባልተግባቡበትም በተግባቡበትም ጉዳይ ላይ እኩል ጮክ ብለው ይስቃሉ ። በናይት ክለቡ ውስጥ ደጋግሞ በመምጣትና ገንዘባቸውንም ያለስስት ስለሚረጩት እዛቤት ያሉ ቆነጃጂት አስተናጋጆች በነሱ መምጣት ደስተኞች ናቸው ። ስለዚህም በሳቃቸው ይስቃሉ ምቾታቸውን ይጠብቃሉ ። ሰመረና ጓደኞቹ ደሞ ከሌሎች ደረጃቸውን ከጠበቁ ትላልቅ ክለቦች ይበልጥ ይህንን ቤት ይወዱታል ። ምክንያቱም እዛቤት ያሉት ሴቶች ውበታቸው ይለያል በዚያላይ እነሰመረ ለሚጠይቁት ጥያቄ ሁሉ መልሱ አላቸው ።ሲፈልጉ የፈለጓትን ሴት ይዘው ይወጣሉ ገንዘባቸው ይጨነቅ ይህንን ቤት ግን ይበልጥ የሚወደው ጌታነህ ነው ። ሌላ ስም ያላቸው ናይት ክለቦች ለሱ ምቹ አይደሉም ምክንያቱም የታላቅ ወንድሙ መስፍን መኖር ሊረብሸው ይችላል ።ወንድሙ መስፍን እድሜው ወደ ሠላሳ ስድስት ቢገመትም ትዳር አልያዘም በዛላይ ጭፈራና መዝናናት እንደ ታዳጊ ጎረምሳ ነው የሚወደው ። እሱም እንደ ጌታነህ ከአንድ ሴት ጋር የመርጋት ችግር አለበት ። ይህንን አመሉን ደሞ ቤተሰቦቹ ጥግ ድረስ ነው የሚያውቁት ።ከበፊት ጀምሮ የቤት ሰራተኞቻቸውን ጭምር ሲያስቸግር ያውቃሉ ። ቤተሰቦቹ አመሉን ችለው ነው የሚኖሩት ።የመስፍንን የስራ ብቃት ግን ማንም የቤተሰቡ አካል አይወዳደር ።አባቱ አቶ ጀንበር የሚወዱትም በዚ ምክንያት ነው ።ብዙ ሴቶችን በተመለከተ ስሞታ ቢደርሳቸውም ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ያልፉታል። ጌታነህ ወንድምየው ያለበት መገኘት በጭራሽ አይፈልግም ።ምክንያቱም ልክ እንደ ቆፍጣና ወንድም ልቆጣጠርህ የሚል ፀባይ አለው ።ጌታነህ ደሞ አይዋጥለትም ስለዚ ከዚ ሁሉ ድብቅ ቦታ መርጦ መዝናናትን ያዘወትራል ።እነ ሰመረም የጓደኛቸውን ስሜት ተረድተው በሱ መንገድ መዝናናትን መርጠዋል ።
ሰመረ ሞቅ እያለው ሲመጣ ወሬው ተቀየረ ።'ልጅቷ ያቺ ልጅ በናታቹ በጣም ታሳዝናለች 'ማለት ጀመረ ። እንየው የዘወትር አስተናጋጃቸው እና ሁለት ጊዜ አብሯት ያደረውን ንግስት የተባለች እድሜዋ ከሃያ የማይዘላትን ወጣት ጠርቶ መነካካት ጀመረ ። ጌታነህ ሰመረ ሞቅ ሲለው እንደልቡ እንደሚያወራ ስለሚያውቅ እንደ ቀኑ አልተከራከረውም ።
"ስማ በጠይም ፊቷላይ የሚነበበውን የተጠራቀመ አዘን እንደኔ ተጠግተህ ብታየው እኮ ! ታውቃለህ በዛላይ እንደዛ እንካን ሆና የልጅነት ውበቷ ለየት ይላል መቼም እድሜዋ ሲጨምር እና ራሷን ስትጠብቅ ታየኝ ምን እንደምትመስል "አለ ወደ ጌታነህ እያየ ።ጌታነህ አልተዋጠለትም በግዴለሽነት ጭንቅላቱን ነቀነቀለት ። የሰመረ ሁኔታ ምቾት አልሰጠውም 'ምንድነው ለአንዲት የደሃ ልጅ የምጨነቀው 'ብሎ ለራሱ ፈገግ አለ ። ልጅቷ ቆንጆ ታዳጊ ናት ነገርግን ደረጃቸው አይደለችም እንደሷ ያሉ ልጆችን በጊዜ አስተናግዶ መሸኘት ነው የሚፈልገው።
"ስማ እሷን ተዋትና ቤት ደውል እና ዛሬን እነ እንየው ቤት እንደምናድር ንገር እንዳያስቡ ።እኔም ለዳድ እደውላለው "አለው
"ለምን እንዴ ገናነው ሰአቱ "አለ ሰመረ
"ኧረ በናትህ የችኮቹ እቅፍ አልናፈቀህም እኑ እያበሰለ ነው እኔም ወደ ቤቲ ልዘምት ነው በቃ ዛሬ ያማረኝ ቤቲን እያስጮሁ ማንጋት ነው ኪኪኪኪ "ብሎ ሳቀ ።ሰመረ አብሮት ሲስቅ ቆይቶ ።
"እሺ እኔ ግን ማደር ካለብኝ ማፊን መጥራት ይኖርብኛል "አለ በቅርቡ የተዋወቃትን ቅንጦት ያንገላታትን ልጅ ።
"አትለኝም ያችን ሞዛዛ እኔማ እሷ ነገርየው ላይ እያለህ እራሱ አንዴ ሜካፔን ልየው ሳትልህ አትቀርም ኪኪኪኪኪ "ብሎ አሽካካበት
"እሱን ለኔ ተወው ሰው ያለ አመል መች ይፈጠራል በጊዜ ሂደት አስተካክላታለው "አለው አብሮት ስቆ
"ምን አስጨነቀ ዘና የሚያደርግህን ሰው አትፈልግም ተመልከታት እዛጋር አዲስ ልጅናት መሰለኘ የዋላው ደሞ የሰጠ ነው እሱላይ ውረድበት ኪኪኪ የምን ማፊ ነው "አለው ወደ አንዲት አስተናጋጅ እየጠቆመው። ሰመረ የጌታነህን ጥቆማ ወደጎን በመተው ከራሱ ጋር መማከር ጀመረ አወጣ አወረደ እና በመጨረሻ ወሰነ እነሱን እዛው ባሉበት ትቶ ወደቤቱ ሄዶ የሰላም እንቅልፉን ለመተኛት ። አሳቡን ሲነግራየው ትንሽ ተከራከሩትና ደየማይረታ ሲሆንባቸው ። እንደፈለክ አሉት በቅሬታ ።ሰመረ ቀን ላይ ካያት ትንሽዬልጅ ጀምሮ ፀባዩ ተቀይሮባቸዋል ።አዲስ ሰመረ ሆኗል ለነሱ ። ሰመረ ደሞ ድንገት ከጓደኞቹ ጋር የሚያሳልፈው ምሽት ስሜት አልሰጥ ብሎታል ። ስለዚ ተነስቶ ተሰነባብቷቸው ከናይት ክለቡ ወጥቶ ወደ መኪናው አመራ,,,,,,,,,,,

ይቀጥላል........


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን🧣
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         

       @fkrn_be_kalat_bot
     ❥❥__⚘_❥❥
በ'ነሱ ቤት
-------------------

    ክፍል አሥር [፲]
.
.
.

መሸት ሸት ብሏል በመንገዱ ላይ ሽው እያሉ ከሚያልፉ መኪኖች በስተቀር ምንም ሰው አይንቀሳቀስም።ጌታነህ ሰአቱን ገመተ 'ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ይሆናል' በቃ ይሁና ምን ችግር አለው የሰው ቤት አይደለ የምገባው ያ ሆዳም ዘበኛ እንደው ገንዘብ ከሰጠውት አንዳች ነገር አይናገር ፣ አለ ለራሱ።መኪናውን ወደ ቤቱ አቅጣጫ እየነዳ፣በዛቻ አይነት ከጎኑ የተቀመጠችዋን የናይት ክለብ አስተናጋጇን ተመለከታት። የሰከረች ትመስላለች የተለያዩ ዘፈኖች ትዘፍናለች በመሃል"ኡኡኡኡኡ "እያች የዘፈን ማድመቂያ የሚሆን ጩኽት ታሰማለች።እንደዛ ስትሆን ሞቅታውስጥ ያለው ጌታነህ ከትከት ብሎ የውሸት ይስቃል እራሱ የሚያውቀውን የተንኮል ሳቅ።ይህችን ልጅ ወደቤት ይዞ መሄድ እሪስክ እንዳለው ቢያውቅም ለቤተሰቦቹ ያለው አክብሮት እየቀነሰ በመምጣቱ ግድ አጥቷል። አባቱ አቶ ጀንበርም ሆኑ እናቱ ወይዘሮ ፅጌ ያን ያክል ጠንከር ያለ እርምጃ የማይወስዱ።ልጆቻቸው የሚያደርጉት ነገር ከማስገረምና ከማሳቅ ያለፈ የሚያብሰለስላቸው ሆነው አያውቁም።ጌታነህ ወንድሙ መስፍን ሰራተኛ ሁሉ አስረግዞ ጉዳዩ እንዳይታወቅባቸው እሷን ከማባረር በስተቀር እሱ ላይ አንዳች አይነት ወቀሳ እንዳላደረሱበት።እራሱ መስፍን በስካር መንፈስ ነግሮታል 'ያቺ በረሮ ሰራተኛ እኔን ለማጥመድ ብላ አረገዘች።ዝቅ ብዬ ባጫውታት ከፍ ብላ በልጅ ሰበብ ልትጫወትብኝ ስትል የኔ ውድ አባት ከላዬላይ አርቆ ጣላት የታባቷ "እያለ ያለፈ የጉርምስና ታሪኩን ዘክዝኮለታል።እሱም ካልሆነሰው ጋር እንዳይወድቅ ሊመክረው ሞክሯል።ጌታነህ እቺን ወሬ መቼም አይረሳትም እንዲሁም ከዛ ጊዜ ጀምሮ ለቤተሰቡ የነበረው ፍራቻ ቀንሶለታል።
*ቤት ሲደርስ እንደተለመደው የጊቢውን በር የከፈተለት ዘበኛ እንደማቅማማት እያለ አንዴ እሱን አንዴ ያመጣትን ሴት ሲያይ ከኪሱ ብር አውጥቶ እጁ ላይ አደረገለት።በዚ ጊዜ እየተቅለሰለሰ መንገድ ለቀቀ ጌታነህ 'ሆዶ ኪኪኪኪ'ብሎ አሹፎበት ልጅቷን ይዟት ገባ።እናም በቀስታ እየተራመደ እና እንዳትጮኽ አፋን እየያዘ ወደ መኝታ ክፍሉ ይዟት ገባ ውስጥ ከገቡ በዋላ በሩን እንደነገሩ ዘጋውና ተሸክሞ አልጋው ላይ ጣላት ልጅቷ እንደመጮህ ስትል አፏን ግጥም አድርጎ ይዞ እላይዋላይ ተከመረ ያወፍራም ሰውነቱ ከላይዋ ሲወድቅ ትንፋሽ አጠራት ከስሩ ለመውጣት ታገለች አርፋ እንድትመቻች በቁጣ ነገራት ልጅቷ ሁኔታው ፍፁም ሲቀያየርባት መጮኽ ፈለገች ምንም እንኳ ገንዘብ ፈልጋ በተጨማሪ ከወንዶች ጋር ብትወጣም ግዴታ ያለበት ግንኙነት ደስ አይላትም ግን ዛሬ በዚ ወፍራም እና ጉረኛ ደፋር ወጣት እጅ ገብታ ለዛውም በናት ባባቱ ቤት እንዴት ታምልጥ ስካሩ በድንገት ለቀቃት ከስሩ ሆና ተንፈራፈረች አለቅ አላት ልብሷን ከላይዋላይ የመቅደድ ያህል ከፍ አደረገባት ልትከላከለው ብላ እንደመቧጨር ስትይዘው በጥፊ አጮላት ፣በዚጊዜ እሪታዋን አቀለጠችው አፏን ለመያዝ ቢታገላት አልሰማ አለችው በፍጥነት ልብሷን ገፎ በላይዋ ዳግም ተከመረ ጩኽቷን አስነካችው ይህን የምታደርገው ልምዱ ስለሌላት ሳይሆን ሰላማዊ ያልሆነ ግንኙነት ስለሚያስጠላት ነው።ጌታነህ አንቆ ይዞ ሲገፋፋት።እሷ ስትጮህ የሚሯሯጥ ኮቴ ተሰማና የጌታነህ ክፍል ብርግድ ብሎ ተከፈተ።የጌታነህ እናት አባት በድንጋጤ የሚይዙትን አጡ ,,
👁አብላካት ለእናቷ ቡና እያፈላች ስለውሎዋ እየነገረች ልታስገርማት ብትጥርም የአብላካት እናት ግን ከመገረም ይልቅ ፍርሃት ነገሰባት።ትንሿ ልጇ አድጋ የወንዶች ፍላጎት መወጣጫ እንዳትሆን የሁልጊዜ ፀሎቷ ነበር።ዛሬ ያ የምትፈራው ጊዜ እንደደረሰ ተሰማት ልጇን የምትሳሳላትን ወዴት እንደምትሰውራት ምን እንደምታረጋት ግራ ገባት አብላካት የእናቷ ጭንቀት አልገባትም እሷ ዋነኛ ጭንቀቷ የሷ ጤንነት ነው ታክማ እንድትድን ፈልጋለች ሰመረ የሰጣትን አምስት ሺ ብር ለዚሁ አላማ መጠቀም ነው አሳቧ።
"እናቴ እባክሽ አትጨናነቂ እኔ የምፈልገው ደና እንድትሆኚልኝ ብቻ ነው እሺ! እና ነገ በጠዋት ተነስተን ሀኪም ቤት እንሄዳለን ከዛ ትታከሚያለሽ ከዛ የኔ ውድ እናት እንደበፊቱ ሮጥ እሮጥ እያለች ትሄዳለች በቃ😀" ፈገግ ፈገግ አለች አብላካት እናቷ ዘና እንድትልላት
"የኔ ትንሿ አበባ የኔ አሳቢ ልጅ ስለኔ አትጨነቂ ድካም ብቻ ነው ህመሜ ሰላም እሆናለው ቀስ በቀስ ይተወኛል እሺ "ብላ በጭንቀት አየቻት።'እኔ በሌለውበት ልጄ ምንድነው የምትሆነው እኔ ዘመድ የለኝ ብቸኛ ከማን ጋርስ ወስጄ አስተዋውቃታለው ማንስ አለኘ።ወይ ይህ ክፉ ዕድሌ በሷም ላይ ተጋባ 'ብላ ከራሷ ጋር አወራች
"እማ ድካም ነው ካልሺኝ ቆየሽ ነገር ግን እየባሰ ነው የሄደው እናቴ እኔ አሁን አሁን አጣሻለው ብዬ እየፈራው ነው እባክሽ ሀኪም ጋር እንሂድ እባክሽ ሳህሉም በርትቶብሻል አንቺ ቢያንስ እንኳ ጤናጣቢያ የመሄድ ፍላጎት የለሽም።ለኔ ስትዪ እንኳ አታደርጊውም "ብላ እንደማልቀስ አለች
"ነይልኝ የኔ ትንሽ አበባ ነይ ልቀፍሽ እኔ ምንም አልሆንብሽም እሺ ነይ ልቀፍሽ "ብላ እጇን ዘረጋች።አብ ላካት ተነስታ በመሄድ የእናቷ እቅፍ ውስጥ ገባች ፀጉሯን ስታሻሻት ደስ የሚል ስሜት ተሰማት
"የኔ ትንሽዬ አበባ ይሄውልሽ አሁን የሚያሳስበው የኔ ጉዳይ ሳይሆን ያንቺ ነው እእእ ምን መሰለሽ ውዴ ሕይወት ለአንዳንድ ሴቶች ቀላል አደለችም በተለይ ደሞ በችግር ላደገች ሴት የኔን ሕይወት ነግሬሻለው መቼም አትረሺውም አይደል?አዎ ለቤተሰቦቼ አንድ ነበርኩ እንደ አይን ብሌናቸውም ነበርኩ ነገር ግን በጦርነት ምክንያት አባቴን አጣው ቀጥሎ እናቴም በሱ መሞት ስታዝን አዘኗ ልክ በማጣቱ እሷም ተከተለችው እና እኔም የተወለድኩበትን አገር ጥዬ አዲስ አበባ ገባው በደላላ አማካኝነትም የቤት ሰራተኝነት ስራን አገኘው የገባውት አብታም ቤት ነበር።ቀሪውን ታውቂዋለሽ ከላይ ጀምሮ እየተከተለኝ ያለ እጣፋንተ አንቺላይ ሲደገም ማየት አልፈልግም። ምን መሰለሽ ዛሬ የነገርሺኝ ነገር አሳስቦኛል ማለቴ አምስት ሺብር ወንድ ልጅ ያለምክንያት አንስቶ አይሰጥሽም።እእእ ላስፈራራሽ ፈልጌ አይደለም ነገር ግን ወንዶች አብዛኞቹ በችግርሽ በደካማ ጎንሽ ነው የሚገቡት እና ዛሬ ለሰጠሽ ነገር ሊያስከፍልሽ ብሎ በደንብ ሊያቀርብሽ ያስብ ይሆናል እና ከዚ በዋላ በምንም አይነት ጉዳይ ላይ አግኝቶ ሊያወራሽ ቢፈልግ ለኔ እንዳትደብቂኝ ሚስጢር የሚባል ነገር የለም።እሱን ብቻ ሳይሆን ሌሎች ወንዶችም ቢሆኑ እሺ "አለቻት ጣቶቿን በፀጉሯ ውስጥ እያንሸራሸረች
"እማ እናቴ ሰመረን ብታይው እንዲ አትይም ነበር እሱ እውነተኛ ሰው ነው ማለቴ እንደ ታላቅ ወንድም ነበር እየተቆጣ ያወራኝ ደሞ ስልክ እንኳ አልጠየቀኝም ቀጥ ብዬ ላዳ ይዤ ወደቤት እንድሄድ እና ያስራ አስገባሻለው ያለሽ ሰውዬጋር እንዳትሄጂ ብሎ አስጠንቅቆኝ ነው የሄደው ባይሆን ጓደኞቹ ደስአላሉኝም ሰሚር ደሞ አስተናጋጅ ነው ስራም ሊፈልግልኝ ቃል ገብቷል እሱም ሊረዳኝ ነው የፈለገው።በዛላይ ቀለል ያለ ነው እንደ ቤተሰብ እዚድስረ ነው የሸኘኝ እንደ ነገርኩሽ እንደውም እሱን አስተዋውቅሻለው "አለቻት
"እሺ የኔ ውድ እያስፈራራውሽ አይደለም እንድትጠነቀቂ ብቻ ነው"አለቻት ይበልጥ አስጠግታ እያቀፈቻት።ውስጧ ፈርቷል ልጇን ከጉያዋእየፈለቀቁ ሊወስዱባት የቋመጡ ጅቦች የከበቧት ያህል ተሰማት የእናትነት ዕንባዋ ጉንጮቿን አቋርጠው ሲወርዱ ይበልጥ ብቸኝነት ተሰማት,

ይቀጥላል......


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
     @fkrn_be_kalat
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
በ'ነሱ ቤት
-------------------

    ክፍል አሥራ አንድ [፲፩]
.
.
.

ሦስቱ ጓደኛሞች በስራ ተወጥረው ከርመው በሚጠብቋትና በምትመቻቸው ቅዳሜ ቀን በተለመደው ሰአት የለመዷት ሬስቶራንት ተገናኝተዋል ።ቦሌ አካባቢ የምትገኛዋ ብዙም ሰው የማይበዛባት ጥራቷ የተመሰከረላት ቬነስ እሬስቶራንት እንግዶቿን በፍቅር ማስተናገድ ታውቅበታለች ።ለዚህም ነው ጓደኛማቾቹ ሁሌም ምሳ ለመብላት ወደዚ የሚመጡት ። ሰመረ ቦታ መርጦ ወደ ጥግ ሲሄድ ጌታነህም በምርጫው በመስማማት ተከተለው እንየው በሁለቱ ምርጫ ተቃውሞ አቅርቦ አያውቅም እሱ ሰላም ብቻ ነው የሚፈልገው እነሱ የመረጡለትን ልብስ ይለብሳል እነሱ የመረጡትን ማንኛውንም ምርጫ ተቃውሞ ሳያቀርብ ይከተላል ። ከርቀት እነሰመረ ቦታ ሲይዙ አይቶ ሰሚር ፈጠን ብሎ ሊታዘዛቸው መጣ ።ሲያዩት ፈገግ አሉ ።እናም የተለመደውን ምግብ አዘው መጫወት ጀመሩ።
"እሺ ባካቹ ሳምንቱ እንዴት አለፈ "አላቸው ፈገግ ብሎ
ጌታነህ ።ሁለቱም ተያይተው ምንም አዲስ ነገር የለም በሚል መልሰው ፈገግ ብለው አዩት።
"አሃ ሳምንቱን ሙሉ መቼም አልተኛችሁም !የሰውልጅ ደሞ ከተንቀሳቀሰ የሆነ ነገር ሳያጋጥመው አይቀርም "አላቸው ፈገግ ፈገግ እያለ።ከሁኔታው አንዳች ነገር ሊነግራቸው እንደሆነ አወቁ
" ምነው አንተ በግድ ነው እንዴ እኔን በተመለከተ ከስራ ወደቤት ከቤት ወደስራ ነበር ሌላ የለም እንግዲ ያንተን እንስማዋ "አለው ሰመረ ።እንየው ፈገግ ፈገግ እያለ "እንዴ የዛንለት ማለቴ ቅዳሜ ኪኪኪኪ "ብሎ መሳቅ ጀመረ እንየው ሁሌም የሚያስቅ የመሰለውን ወሬ ሊናገር ሲል ቀድሞ የመሳቅ ልምድ አለው
"ምንድነው እሱ ?ምን ተፈጠረ ?ለካ እዛው ጥለንህ ነበረ የሄድነው ጓደኛዬ "አለው ጌታነህ ወሬውን ለመስማት እየጓጓ
"ኧረ በናትህ ሳይቸግረኝ ሁለት ቺክ ይዤ ወጥቼ አላበላሹኝም ኪኪኪኪ "ብሎ ሳቀ ።ሁለቱም ተያይተው 'ምን'አሉ እኩል ።በዚ ጊዜ አስተናጋጁ ሰሚር ምግባቸውን ይዞ መጥቶ ጠረጴዛው ላይ ማስተካከል ጀመረ ። እናም የሳምንቱን አጢያታቸውን ለመስማት ጓጓ ።እነ ሰመረ አስተካክሎ እስኪጨርስ ጠበቁትና ጨርሶ ፈንጠር ብሎ ሲቆም ወደወሬ አቸው ተመለሱ ።
"እሺ ባክህ ?"አለው ጌታነህ እንደጀብደኛ እየተመለከተው ። ሰመረ ውስጡ የሚያቅለሸልሽ ስሜት ተሰማው የእንየው ወሬ አልተመቸውም የለየለት ብልግና ውስጥ እንዳሉ እየተሰማው ነው ሰሞኑን ቸልተኝነቱ እና ግድ የለሽነቱ ጥለውት ጠፍተዋል ።ምን አልባት በቅርቡ የተዋወቃት ሞልቃቃዋና ቆንጆዋ ማፊ ቀልቡን ስባው ይሆናል ።
"ከዛላቹ አገላብጣቸዋለው ያልኩት ሰውዬ አገላበጡኛ ኪኪኪኪኪ አንዷ ተወችኝ ስል አንዷ እንደ ቴኒስ ኳስ ተቀባበሉኝ ኪኪኪኪኪ ዋውው ለየት ያለ ለሊት ነበር ኪኪኪ የሚገርመው ግን ጠዋት ስነቃ ሁለቱም ሄደዋል የሉም ኪኪኪኪኪ"ብሎ ወሬውን በሳቅ አጅቦ ጨረሰ። ጌታነህ ተነስቶ አጨበጨበ እና
"ወንድ ነህ አባቴ አሳምነህ ነው የሸኘሃቸው እንድገመው ማለታቸው አይቀርም "ብሎ አብሮት ሳቀ
"በህልምህ እንዳይሆን ጠዋት ላይ አብረውህ ያደሩት ሴቶች ገንዘብ መጠየቅ ነበረባቸው ።በዛላይ ወንድነህ የሚያስብል ወሬ አልነገረንም የሰማውት ተቀባበሉኝ ስትል ነው !እእእ እርግጠኛ ነህ ግን በውንህ ነው እንዴት ገንዘባቸውን ሳይወስዱ "አለው ሰመረ ሳይዋጥለት ።እንየው ትንሽ ሲያስብ ቆይቶ።
"እሱማ በኪሴ ውስጥ ከስልኬእና ከኤቴሜ ውጪ ምንም አላስቀሩልኝም"ብሎ ዝም አለ ።በተራው ሰመረ ጮክ ብሎ መሳቅ ጀመረ ። ሰሚር ወሬውን በመጠኑም ቢሆን አገጣጥሞ ተረድቶት ስለነበረ በቆመበት እያያቸው የተረገሙ ይላል በሆዱ ።ብቻ ያችን ታዳጊ ልጅ ወደዚ ክፋታቸው እንዳይጨምሯት ።መቼም ለአንደኛው ስልኬን ሰጥቼዋለው ብላለች ብሎ ተከዘ ,,,,,,,,,,,,,,,,,

ይቀጥላል........


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         

       @fkrn_be_kalat_bot
     ❥❥________⚘_______❥❥
በ'ነሱ ቤት
-------------------

    ክፍል አሥራ ሁለት [፲፪]
.
.
.

ጌታነህ በእንየው ሁኔታ ሳቁን መቆጣጠር አቅቶት ነበር ።ምክንያቱም አገኘዋቸው ብሎ ቢያወራም ሁለቱም ሴቶች አግኝተውታል ።መስከሩን ስላወቁ የሚፈልገውን ነገር ካደረጉ በዋላ ኪሱን እጥብ አድርገው ነው የሄዱት ። ግን ደሞ በእንየው ቢስቅም እንዲ ያደረጉትን ሴቶች ያውቃቸዋልና በልቡ ቂም አሳድሮባቸዋል ።እዛ ናይት ክለብ የሁልጊዜ ደንበኛ ሳሉ እንዴት እንዲ ያደርጉታል እነሱንማ እሰራላቸዋለው ብሎ ዛተ ። እንየው ብዙም ብልጣብልጥ እንዳልሆነ ጓደኞቹ ያውቃሉ ስለዚህም ነው አንድ ነገር ሰራው ብሎ አዳንቆ ሲያወራ በተለይ ሰመረ ነገሩን ከስሩ አጣርቶ እንዲነግረው ይገፋፋዋል እንጂ ያወራውን ወሬ አምኖ ተቀብሎ ዝም አይልም ። ጌታነህ ደሞ ሴቶች ላይ የሚደረጉ ነገሮች ሁሉ ያስቀዋል ያዝናናዋል ስለዚህም ስለሴት ልጅ ሽንፈት ሲሰማ የነገሩን እውነት ከማጣራት ይልቅ መሳቅ ይቀናዋል ።
አስተናጋጁ ሰሚር ተጠግቶ ጌታነህን እያየ ምን ልጨምር ብሎ ጠየቀ ።ጌታነህ መልስ ሳይሰጠው በእጁ ብቻ ምልክት በመስጠት ወደነበረበት እንዲመለስ አሳየው ።ሰሚር እንዲ በንቀት ያየኛል ብሎ ስላልጠበቀ ተናደደበት ።በልቡ መቼም ይሄ ገንዘብ አያሳየን ጉድ የለም ። እንጂማ እኔ በምንም ቢሆን ከሱ አላንስም ።ወይ ገንዘብ ከፍዝቅ የምታደርግ አንተ አለ ወደቦታው እየተመለሰ ።ጌታነህ ፈገግ ፈገግ እያለ ጉሮረውን ሲያፀዳ ።ሁለቱም ጓደኞቹ ሊያወራ የፈለገው ነገር እንዳለ በመረዳት ጠበቁ።
"የኔን ነገር በናታቹ ለወሬም አይመችም ግን ይሄን የወጣትነት ሞቅታ ዕድሜ ከገፋ በዋላ የሚገኝ ስላይደለ ምንም ማረግ አይቻልም መሟሟቅ ነው ክክክክሃሃሃ ታውቃላቹ ሴት ይዤ ገባው ያቺን በቀቀን የናይት ክለቧን ።ከዛላቹ እንደተለመደው ላስጨፍራት ስል በክብር ቤት ድረስ ስለወሰድኳት ነው መሰል እንዴት እንዳረጋት ።በቃ ምን ልንገራቹ በነካዋት ቁጥር እንደ ልጃገረድ አገር ይያዝልኝ አላለችም በጣም ተናድጄ እኔስ ልለቃት ነው የራስሽ ጉዳይ ብዬ ወረድኩባታ ።ከዛስ እላይዋላይ ወጥቼ ስጨፍር በሩን አልቆለፍኩት ኖሮ ማምና ዳድ ዘው ብለው ቢገቡስ "
"ከዛስ"አለ እንየው
"ከዛ ይቀጥላል "አለ ጌታነህ,,,,,,,,,,,,,

ይቀጥላል........


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         

       @fkrn_be_kalat_bot
     ❥❥________⚘_______❥❥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በ'ነሱ ቤት
-------------------

    ክፍል አሥራ ሦስት [፲፫]
.
.
.

እንየው አንድ ወሬ ተጀምሮ ካልተጨረሰ ደስ አይለውም ።ጌታነህ ደሞ ማጓጓት እና ትኩረት ማግኘት ይወዳል ስለዚ አንድ ወሬ ጀምሮ ቶሎ ተናግሮ አይጨርስም ። አጭሯን ነገር መጎተት ልማዱ ነው ። ሰመረ የጌታነህ ወሬ የተለመደ ስለሆነ ብዙምስሜት አይሰጠውም እንዲሁም አንዳንዴ የሚስቀው በነገሩ ተገርሞ ሳይሆን በጌታነህ በሚረባውም በማይረባውም ጉዳይ መደነቅና በዛ ደሞ እራሱን እንደጀብደኛ አድርጎ በማውራቱ ነው ።
"ስሙ ማሚና ዳዲ እንዴት ክው እንዳሉ "አለና ሳቀ እንየው አብሮ ሳቀ ግን ከልቡ አይደለም ጓደኛው እንዳይቀየመው እንጂ በእናትና በአባት ፊት ነውር ስራ መስራት ተገቢ ነው ብሎ አያምንም ። ሰመረ በጓደኛው ወሬ ብዙም ደስተኛ ባለመሆኑ እንደሌላው ጊዜ በሳቅ ከማጀብ ይልቅ ኮስተር ብሏል ። ጌታነህ እረጅም ሳቅ ከሳቀ በዋላ ።
"ከዛ ልክ እንደ በደለኛ ተነስቼ ሁለቱም ላይ ብጮኽባቸውስ !" አለ እንየውን እያየ
"ምንብለህ ደሞ ሆሆሆ ካንተም ብሶ!?"አለው እንየው
"እንዴ ለምን ክፍሌ ዘው ብላቹ ትገባላቹ ።እኔ እናንተ ክፍል ዘው ብዬ እገባለው ወይ?ቢያንስ አታንኳኩም ብዬ ነው ኪኪኪ ከዛ ዳድ ሙድ የገባው ነው እኮ ድንጋጤውን እንደያዘ ይቅርታ ጩኽት ስንሰማ ጊዜ ነው ብሎ ተጨማሪ ነገር ሳይናገር ተመለሰ ።ማም ግን እንዴት በንቀት ሁለታችንንም እንዳየችን ።ያቺ በቀቀን እኔን አስበልታኝ ልክ እንደ ቤቷ ብርድልብሱን ተጠቅልላ ፀጥ ብላ ተጋድማለች እናቷን ደግሜ ላግኛት እራቅ ያለ ቦታ ወስጄ እሷንማ ካልሰራውላት ። በሷ የተነሳ እስካሁን ከማም ጋር አናወራም ፊቴን እንኳ ዞራ አታየኝም ። ዳድ ግን በነጋታው ቁርስ ልጋብዝህ ብሎ ወስዶኝ ብዙ ምክር መከረኝ ኪኪኪኪ ወይ ዳድ ጉርምስናዬን እንደሚረዳ ነገር ግን ቤት ድረስ ሴት ይዞ መምጣት ቤተሰቡንመናቅ እንደሆነ በመንገር የእናቴንም ክብር ዝቅ እንደማድረግ እንደሚቆጠር ,,,,ብቻ ብዙ ብዙ አለኝ እና ላቹ ምክሬን ተቀብዬ ይቅርታ ጠይቄ ከዳድ ጋር ችግሩን በዚሁ ፈታነው ።ከማም ጋር ግን እንደተኮራረፍን ነው ጋይስ እናትህ ስትቆጣ ከባድ ነው ኪኪኪኪኪ ግን ይሄን ነገር ምን እናርገው ኪኪኪኪ"ብሎ ወደታች እያሳየ ሳቀ ።እንየው አጀበው
"በነገራችን ላይ እስካሁን የነገርከን ነገር የሚያስቅ አይደለም በጣም የወረደ ተግባር ነው የፈፀምከው ።ለቤተሰብህ ንቀት ካለብህ በሌላ መልኩ ብታደርገው ይመረጣል ።በእናትና በአባት ፊት ግን ሽርሙጥና ማካሄድ ይበል የሚያስብል ጉዳይ አይደለም ጓደኛዬ ።ስለዚህ ዛሬ መሳቅ ሳይሆን ያለብህ መፀፀት ነው ላደረከው ነገር አላፊነቱን ወስደህ ማስተካከል አለብህ ። በምን? በመጀመሪያ እናትህን ይቅርታ መጠየቅ አለብህ የሰራኽው ሁሉ በመጠጥ ተገፋፍተህ መሆኑን ! በመንገር በመቀጠል ያቺ በቀቀን ያልካት ልጅ ምን አልባት አንተን ተከትላ የሄደችው ደካማጎን ስላላት ነው ወይ ቤተሰብ ታሞባት ገንዘብ አስፈልጓት ይሆናል ክብሯን የምታጣው ስለዚህ እንደ ባለጌ ብቻ ባታያት እና ይቅርታ ብትጠይቃት ይሻላል እንጂ እሷላይ ዳግም መዛት አያስፈልግም ። "አለው ሰመረ በአዋቂነት ።ጌታነህ ሰመረን በመገረም ሲያየው ቆይቶ የለበጣ ሳቅ ሳቀ "ስማ ደሞ መካሪም ሆነህልኛል ዘንድሮእንደው ለየት እያልክ ነው ። በመጀመሪያ ማም በራሷ ሰአት ነገሩ ሲገባት ትተወዋለች ትልቁ ቤት እንደው ለምዶበታል ሴትልጅን አስደስቶ መላክ ኪኪኪኪኪ ምን ልላቹ ነው ማም አዲሷ አይደለም ከዚ በፊት የወንድሜ መስፍንን ዕፀፅ እየሸፈነች ኖራለች ሰራተኛ አስረግዞ ከቤት አባራት ታውቃለች ስለዚ ታሪክ ነግሬአቹሃለው አይደል መቼም ከእናንተ ከጓደኞቼ ሚስጥር መደበቅ አልችልም ። እና እናቴ የኔ እንዲማድረግ ለጊዜው ቢያናድዳት እንጂ ቂም አትይዝብኝም ። መስፍን ያንን ሁሉ አድርጎ እንዴት ከኔ አስበልጣ እንደምትንከባከበው ።አይታችዋል ለኔ እንኳ የመጨረሻ ልጄ ነው ብላ ቦታ ሰጥታኝ አታውቅም ሳምንቱን ሙሉ እሷ እንዳትጎዳ ብዬ ጠብ እርግፍ እያልኩ ድርጅታችን ወስጥ ብሰራም ትኩረቷን ስቤ አላውቅም የፈለገውን ለሚያደርገው ለጡረተኛ ልጇ ታደላለች እና የማም ውለታ የለብኝም ባይዘዌ"ብሎ ወደዋላው ለጠጥ ብሎ ተቀመጠ ።ሰመረ የጓደኛው ቂመኝነት እና ግዴሌሽነት እያሳሰበው ። በራሱመንገድ ሊያስረዳው አፉን ከፈት ሲያደርግ ።ጌታነህ "በቃ በቃ አፍህን ዝጋው እኔን ለመምከር እንዳትሞክር እኔ ህይወቴን በራሴ መንገድ ነው የማስኬደው የግድ አንተን ወይም እንየውን መምሰል አይጠበቅብኝም ።እሺ ይሄንን እርዕስ ዘግቼዋለው ።አለው ሰመረ በምንቸገረኝ ትከሻውን ነቅንቆ ዝም አለ እንየው ሁለቱ ሲነጋገሩ አቅጣጫው መቀየር ስለጀመረ ለማንም ሳይወግን የቀረበውን እየበላ ዝም ብሏል ። ጌታነህ ሰመረ ከቅርብ ጊዜ ወዲ በንግግሩ ሁሉ ከመዝናናት ውጪ ልክ አይደለህም የሚል ሙግት ስለጀመረው አካሄዱን አልወደደለትም ። ወደዋላው ለጠጥ ብሎ ማሰብ ጀመረ ምንአልባት ልቡ የሻከረበት ባለፈው የእህቱ ቬሮኒካ አስራ ስድስተኛ አመት ሲከበር አብሯት በጣም ሲዝናና ነብር ያሁኔታ አስከፍቶት ይሆን ብሎ አሰበ ። ሰመረ ታናሽ እህቱ ቬሮኒካ ገና ከአሁኑ ቀውጢ ልጅ ናት ማንንም አትሰማም የመሰላትን ነው የምታደርገው ።ስለዚ በቀላሉ ችግር ውስጥ ልትገባ ትችላለች ተብሎ በሰመረ አማካኝነት እሷ በማታውቀው መልኩ ጠባቂ ተቀጥሮላታል ።ጓደኞቿበሚደግሱት ድግስ ሳይቀር በቅርብ ሆኖ ነው የሚከታተላት ጠባቂዋ ዳዊት ። ሰመረ ለዳዊት ሁሌም ትህዛዝእንደሰጠው ነው ከአይንህ አትራቅ ይለዋል ።እሱም ትህዛዙን በሚገባ እየተወጣ ነው እስካሁን የተለየነገር አላየባትም ከእብደቷ በቀር ችግሯ አጥብቆ መዝናናትን መውደድ ነው ።
ጌታነህ ልጥጥ ብሎ እንደተቀመጠ ወደ ባሻገር ሲመለከት ቆይቶ የሆነ ነገር ያስታወሰ ይመስል ድንገት ወደ አስተናጋጁ ሰሚር በምልክት ተጣራ
"አቤት ምን ይምጣ "አለው አስተናጋጁ ሰሚር
"አንተ ለዛች ለክስሞቲክሷ ልጅ ስልኬን በትክክል ሰጥተሃታል የዛን ለት "አለው ቆጣ ብሎ
"አዎ እንዴ አልደወለችም"አለ ሰሚር ።በልቡ ባትደውል ደስ እንደሚለው እየተናገረ
"አልደወለችም ይላል እንዴ ሂድና አሁን እሷ ካልቻለች እኔ ልደውልላት ስለምችል ስልኳን ተቀብለሃት ና "አለው በትህዛዝ መልክ ።
"እሺ እሺ "አለና በፍጥነት ተንቀሳቀሰ ።ሰመረ አንገቱን ነቀነቀ እንየው ፈገግ አለ ። ጌታነህ የሰሚርን አሯሯጥ ሲያይ ሊስቅ ከጀለው ,,,,,,,,,,,,,


ይቀጥላል........


የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         

       @fkrn_be_kalat_bot
     ❥❥________⚘_______❥❥
    🌹 ፍቅርን በቃላት 🌹

.....ስለሌለሽ አይደል?

ሌሊት ስድስት ሰዓት
የመናፈቅ መዓት
በድቅድቅ ጨለማ
እቅፍሽ የለማ
ቢኖርማ ኖሮ
የማንም ድሪቶ ባልመጣ ከኔ በር
ንፋስ ጌታ ሆኖ ባላዘዘኝ ነበር
ስለሌለሽ አይደል?

እንዲህ ባልነበርኩኝ
የፌስታል ሽወታ ደጄ ድረስ መጥቶ
እንዴት ቤቴ ገባ ውርጭ አቅም አጊንቶ?
ስለሌለሽ አይደል?

ነፍሴን ብቸኝነት አልምዶ ቢያፀናኝ
የሴተኛ አዳሪ ጩኸት ባላስቀናኝ::
ስለሌለሽ አይደል?


ኤልያስ ሽታኹን

           ᴊᴏɪɴ ᴀɴᴅ sʜᴀʀᴇ
         🌹 ፍቅርን በቃላት 🌹
┄┄┄┄┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄┄
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በ'ነሱ ቤት
-------------------

    ክፍል አሥራ አራት [፲፬]
.
.
.

አብላካት የእናቷን እመም ካወቀች በዋላ ትንሽም ቢሆን ቀለል ብሏታል ቢያንስ ህመሟ መዳኒት ያለው መሆኑ አንድ መፍትሄ ነው ብላ አምናለች ።ዶክተሩ አንደኛው ሳንባሽ በከፊል ተጎድቷል ነገርግን እክምናሽን በትክክል ከተከታተልሽና እራስሽን ከተንከባከብሽ መዳን ይችላል ሲላት ።በጆሮዋ ሰምታለች ። የዚህን መፍቴሄም ነግሯቸዋል ከብርድ መጠንቅ እንዳለባት ትንሽ እረፍት እንደሚያስፈልጋት መመገብ ስላለባት ጭምር ሁሉንም አብራት ዶክተሩ ጋር ገብታ ሰምታለች ።ስለዚህም እናቷን ለጊዜው ጤናዋ እስኪመለስ ልታሳርፋት ወስና ። ጉሊት መሄዱን የሷ ድርሻ አድርጋዋለች ። ምንም እንኳ እንደ እናቷ ከደንበኞቿጋር ለመግባባት ቢከብዳትም ። ይህንን መወጣት እንዳለባት አምናለች ። በጠዋት ተነስታ አትክልት ተራ በመሄድ የተለያዩ አትክልቶችን በማምጣት ያቅሟን ትግሏን ጀምራለች ።እናቷ መሳይ የልጇ ድካም ስሜቷን ቢነካውም ።ተይ ብትላት ደሞ ከልጇ ጋር መጣላት እንደሚሆን ስለገባት ተሳቃ የልጇን ድካም ከማየት በቀር ምንም የማለት ጉልበት አጣች ።አብላካት የራሷ ድካም አልታያትም የሷ ፍላጎት እናቷ በፍጥነት ድና ማየት ብቻ ነው ።
አልፎ አልፎ ከአስተናጋጁ ሰሚር ጋር ይደዋወላሉ ።ሰሚር ስራ እንዳገኘላት በተደጋጋሚ ቢነግራትም ።ለጊዜው የእናቷን መደብ ጥሎ መምጣት ስለማትችል ስራው እንደማያስፈልጋት ነግራዋለች ። አስተናጋጁ ሰሚርም ተረድቷት በሀሳብ ግን እያገዛት ነው ያለው ። በወሬ አቸው መሃል ስለነ ሰመረ ይነግራታል እንዴት ያሉ ስርሃተ ቢስ እንደሆኑ ለሴት ልጅ ያላቸውን ንቀት ደሃ እንደማይወዱ በተለይ ደሞ ወፍራሙ ልጅ ጌታነህ ስልክሽን የተቀበለሽ ልጅ ጥሩ ልጅአይደለም አደራ እንዳያታልልሽ ይላታል ሰሚር እንደ ወንድም ። አብላካት ማንም አያታልለኝም የኔ ትልቁ ፍላጎቴ እናቴን መርዳት ብቻ ነው ። ብላዋለች እናም እሱም ይህን ጥንካሬዋን ማስቀጠል እንዳለባት ይመክራታል ።
*አብላካት የጉሊት ስራዋን ጨርሳ የሸጠቻትን ብር ቦርሳዋ ውስጥ ጨምራ ።ለእናቷ ወተት ገዝታ ወደቤቷ እየተጣደፈች ሳለ ስልኳ ጮኽ
"አቤት "አለች በእጇ የያዘችውን እቃ መሬት ላይ አስቀምጣ
"አቢ እንዴት ነሽ አስታወሺኝ የኔ ቆንጆ"አለ ድምፁ
"አላወቅኩህም ማን ልበል "አለችው እየተጠራጠረች
"እንዴ ይሄ ድምፅ ይረሳል በይ በይ ጌታነህ ነኝ ከሳምንት በፊት መንገድ ላይ ጫማሽ ተበላሽቶ እንዲሁም ጓደኛዬ የረዳሽ ጊዜ ኪኪኪኪ "አላት። አብላካት አወቀችው ነገር ግን አነጋገሩ አልተመቻትም
"እእ አወቁኩ ሰላም ነው"አለችው ተረጋግታ
"ጎበዝ እንደሱነው የሚባለው ።እኔ መረሳት የማልወድ ልጅ ነኝ እሺ የኔ ቆንጆ "አላት ለማግባባት እየሞከረ
"እሺ ለማንኛውም ስለደወልክልኝ አመሰግናለው መንገድ ላይ ነኝ ብዙእቃ ይዣለው ስለዚ ቆይቼ ልደውልልህ "አለችው ፍላጎት ባጣ ስሜት
"እውነት ደክሞሻላ !እኔን ይድከመኝ አቢዬ የኔ ቆንጆ በቃ በዋላ መደወልሽን እንዳትረሺ ።እሺ አቢዬ በጣም ነው ካየውሽ ጀምሮ ትናፍቂኝ ነበር "አላት ተለሳልሶ
"እሺ እደውላለው "አለች አብ ላካት ለመገላገል
"እሺ እወድሻለው እሺ "አላት ።አብ ላካት ሳቋ ልትለቅ ምንም አልቀራትም ድንገት ተነስቶ እወድሻለው ዕፃን አደረገኝእንዴ የሚያታልለኝ አለች ለራሷ
"ለማንኛውም አመሰግናለው መልካም ምሽት "ብላ መልስ ሳትጠብቅ ስልኩን ዘጋችው ። እናእቃዋን ሰብስባ እየፈጠነች ወደቤቷ ሄደች ,,,,,,,
👁ጌታነህ አስተናጋጁ ሰሚር መጥቶ ሲፈራ ሲቸር
"ይቅርታ የኮስሞቲክሷ ልጅ ስልክ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለችም"ሲለው በመገረም አየው ።ሰመረ እና እንየው ተያይተው ተሳሳቁ ።ጌታነ ሽንፈት ስለማይወድ በንዴት አስተናጋጁ ሰሚር ላይ አፍጥጦ
"ማነኝ ነው የምትለው ?!ደሞስ ባለፈው ተቀብላ እደውላለው ብላለች አላልክም "አለው
"አዎ ባለፈው ብላ ነበር "አለው ሰሚር
"እና ዛሬ ምን ብለሃት ነው?"አለው ሽንፈቱ እየቆጨው
"አይ እንደውም ስላንተ አግባብቼ ነግሬያት ነበር ።ነገርግን ባለ ትዳር እና የሁለት ልጆች እናት ነኝ ይቅርታ ደግመህ እንዳትመጣ ።አለመደወሌ እኮ አለመፈለጌን ያሳያል ለምን ይጨቃጨቃል አለችኝ "አለው ሰሚር በውስጡ እየሳቀ
"ምን እንደዛ ነው እንዴ ውይ እኔም አልፈልጋትም አሮጊት "አለ ጌታነህ ።አለመሸነፉን ለራሱ እየነገረ ።ሰመረ ከት ብሎ ሲስቅበት ነበር ሰመረን የሚያናድደው ነገር ሲፈልግ ።የአብላካት ስልክ ትዝ አለው እናም በፍጥነት ወደ አብላካት ደወለ የሰመረ ፊት ሲቀያየር ሲያይ ደስ እያለው ነበር ,,,,,,,,,,

ይቀጥላል........

ክፍል አሥራ አምስት ከ #100 Vote ❤️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like❤️ ማድረግ አይርሱ።

Don't forget to react on our posts😊

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን!
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         

       @fkrn_be_kalat_bot
     ❥❥________⚘_______❥❥
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በ'ነሱ ቤት
-------------------

    ክፍል አሥራ አምስት [፲፭]
.
.
.

እንየው የጌታነህ ፍጥነትና በቀላሉ ያለመሸነፍ ስሜት ሁሌም ስለሚያስገርመው ምነው እሱን ቢያረገኝ ይላል በውስጡ ። እሱ ከሴቶች ጋር የማውራቱ ነገር ላይ ብዙም አይደለም ።ምንም እንኳ አቋሙ የተስተካከለ አይነግቡ ቢሆንም ተናግሮ የማሳመን ነገር ላይ የለበትም ። እንዲሁ ከጓደኞቹ ጋር በየ ናይት ክለቡ የሚያገኛትን ሴት በገንዘቡ ከመቃረም ውጪ ።በትክክለኛው መንገድ ሴትን ልጅ አግባብቶ ወደራሱ አምጥቶ አያውቅም እንደተራራ ነው የሚከብደው ። ጌታነህ ሴቶቹን ከቤት ልጅ እስከ ...... በሚባል ደረጃ በቀላሉ አግባብቶ የፈለገውን ማድረግ ሲችል ሲያይ ይቀናበታል ። ሰመረ ደሞ መናገርም ሳይጠበቅበት የተለያዩ ሴቶች የፍቅር ጥያቄ እንደሚያቀርቡለት ያውቃል ሰመረ ግን ፍላጎት የለውም እኔ ሳልወድ የሚከተሉኝ ሴቶች አይመቹኝም ይላል ።እንየው በሰመረ አይቀናም ምክንያቱም ሰመረ ግድ የለውም ።ጌታነህ ግን ነፃ ሰው ነው ብሎ የሰው ስባል ።በተቃራኒው ደሞ ጌታነህ በሰመረ ይቀናል ። ሰመረ መልከመልካም ስለሆነ ሴቶቹ በቀላሉ ይጠመዱለታል ሳይለፋ እና ጌታነህ እሱን ባረገኝ ከላይ እስከታች ነበር ማሯሩጣቸው ብሎ ያስባል ።
ጌታነህ ለአብላካት ደውሎ አውርቶ ስልኩን ሲዘጋው ። እንየው መገረሙ እንዳለ ሆኖ
"እንዴ ለዛች ትንሽ ልጅ እየደወልክ ነው እንዴ?"አለው
"እና እንዴ እኔ እኮ ነኝ "ብሎ ሳቀ
"ገራሚ ነህ ኪኪኪኪ "አለ እንየው
"ትቀልዳለህ ቆንጆ በቀቀን እኮ ናት"አለው ጌታነህ
"ስማ በየናይት ክለቡ እንደምታገኛቸው ሴቶች በቀቀን እያልክ ልትጠራት አይገባም በጣም ልጅ እኮ ናት "አለው ሰመረ እየደበረው
"ተው እንጂ !ታዲያ ምን ችግር አለው ሁሌም እሷ ስትመጣ በአንድ እጄ ጡጦ ይዤ በሌላኛው ደሞ ......እንትን ይዤ አጫውታታለዋ "አለው እየሳቀ
"መቀለድህ ነው ! ቆይ እኔን ለመቃረን ፈልገህ ነው ወይስ የእውነት በዛች ትንሽ ልጅ ላይ ፍላጎት አሳድረህ ነው ?"አለው ሰመረ ፊቱን አጨፍግጎ
"ኧረ በናታቹ እንዴ ስለዝች ልጅ ሲነሳ ሁለታቹ መናቆር ጀምራችዋል እንዴ ሰሙ ምንድነው ይቺን ልጅ ፈልገሃታል እንዴ "አለው ለጌታነህ በመቆርቆር
"አንተም እንዲ ታወራለህ? ልክ ነው እያልክ ነው ?ለነገሩ አንተ ምን ታውቃለህ መከተል ብቻ የራስህ አቋም የለህ ። "አለው ሰመረ ብልጭ ብሎበት
"ኧረ አብርድ እንዴ ይህውልህ ምንም አልክ ምንም በቅርቡ ታየኛለህ የሷን ጉዳይ ሳፋጥነው "ብሎ የሚያናድድ ረጅም ሳቅ ሳቀ ጌታነህ ።ሰመረ በንዴት መልስ ሊሰጥ ሲል ። የጌታነህ ስልክ ጮኽች ። ጌታነህ ስልኩን አየና ሳቀ ወደ ሰመረ እያየ "ተመልከት ሴቶች ቀልብ የላቸውም የኔቆንጆ ማለት ብቻ ነው የሚጠበቅብህ ኪኪኪ "ብሎ ስቆ ስልኩን አንስቶ ማውራት ጀመረ ።ሰመረ ልቡ ተሸበረበት እንዴ የእውነት ያቺ ልጅ ደውላለት ነው ።ኤጭ እንዴት ያናድዳል ። በቃ ችግር ውስጥ መግባቷ ነው ለዚ ደሞ እኔ ነኝ ተጠያቂው ።ምን አለ የዛን ለት ባላወራዋት አለ። እንየው የጌታነ የጅንጀና ወሬ ይጠቅመው ይመስል አፉን ከፍቶ ያዳምጠዋል ።ጌታነህ ብዙ የፍቅር የሚመስሉ ወሬዎችን ካወራ በዋላ ቀጠሮ ይዞ ስልኩን ዘጋው እናም እንደተለመደው እረጅም ሳቅ ሳቀ ።
"ታውቃላቹ ባለፈው ሐሙስ ለት ገቢዎች ሄጄ ነበር ዳድ ስላልተመቸው አመታዊ ግብር እንድከፍል ። ከዛ አንዷ እንደኔው ክፍያዋን ልትፈፅም የመጣች ተለቅ ያለች ሴት አይኗን ብትጥልብኝስ ኪኪኪ እኔስ ምኔ ሞኝ ስርስ ብዬ ተጠግቼ ያዋቂ ወሬ እያወራው ልባን አልነሳዋትም መሰላቹ ኪኪኪ ከዛስ ጉዳይዋን ፈፅማ ስትጨርስ ።በጣም ስለተመቸኽኝ እንደዋወል ብላ ከአንዳንድ ስልኬን አልተቀበለችኝም ዋው ተለቅ ብትልም ለየት ያሉ ነገሮች አሏት መደበቂያ የሚሆኑ ኪኪኪኪኪ እና ከሷ ጋር ነው ያወራውት ።እኔ እረስቻት ነበር እንግዲ ከመጣች ምን ይደረጋል ኪኪኪኪ"ብሎ የሰመረን ሁኔታ መከታተል ጀመረ
"እና እሺ ከአንዱ ወዳንዱ ሆነብህ እኮ ፈንድተህ እንዳትሞት ተረጋጋ "አለው ሰመረ ።በውስጡ እፎይ ብሏል አብላካት የደወለች መስሎት አሳስባው ነበር
"ይመችህ ጌቾ እሱን እርሳው እንጫወት ካሉ አጫውታቸው ላንተ የዘነበው ለኛም ያካፋልን "አለው እንየው እየሳቀ
"ሰሙ ሰሞኑን ለየት ብለሃል ወይ ማፊ አወዛግባሃለች ወይ ወይ አንድ የደረሰብህ ነገር ይኖራል አይዞህ እንግዲ ወደጤናህ እንድትመለስ እንፀልያለን "አለው
"ለራስህ ፀልይ ባክህ አሁን ለምን አንወጣም "አለ ሰመረ እየሰለቸው
"እእ የት ነን ዛሬ "አለ እንየው በጉጉት
"እህ የተለመደው ቦታ ነዋ ያችን በቀቀንማ ማግኘት አለብኝ እንደዛ በነ ማሚ ፊት አዋርዳኝማ አለቃትም ዛሬ አግባብቼ ይዣት ወጥቼ ልክ ነው የማስገባት "አለ ጌታነህ ።እንየው ሳቀ ።ሰመረ የራስህ ጉዳይ ቀሚል ተሰላችቶ ቆመ እናም"ይቅርታ ዛሬ የክለብ ነገር ይቅርብኝ በጊዜ መተኛት እፈልጋለው ። በዛላይ ማፊም ሰፈር እንገናኝ ብላኛለች ።እሷን ካገኘው በዋላ በቀጥታ ወደቤት ነኝ "አላቸው ።ሁለቱም ተያይተው በመከፋት ስሜት አዩት ።የሰመረ አካሄድ ደስ አላላቸውም ።ከዚ በፊት እንዲ ተለያይተው አያውቁም ።ምን ተፈጠረ ብለው አሰቡ ። ማፊ ናት ፀባዩን የቀየረችው ወይስ ያቺ ትንሽ ልጅ,,,,,,,,,,,,,,


ይቀጥላል........

ክፍል አሥራ ስድስት ከ #100 Vote ❤️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like❤️ ማድረግ አይርሱ።

Don't forget to react on our posts😊

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን!
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         

       @fkrn_be_kalat_bot
     ❥❥________⚘_______❥❥
በ'ነሱ ቤት
-------------------

    ክፍል አሥራ ስድስት [፲፮]
.
.
.

የአብላካት እናት መሳይ ጤንነቷ እየተመለሰ ሲመጣ ልጇን ለማሳረፍ ብላ ወደስራ ለመመለስ ወሰነች ።አብላካት በእናቷ አሳብ አልተስማማችም ።ምክንያቱም ዶክተሩ አስጠንቅቋታል ። እራሷን ከቅዝቃዜ እና ከሆነ ላስፈላጊ ድካም እንድትጠብቅ ።ስራው ደሞ በጠዋት ተነስቶ መንቀሳቀስን ይጠይቃል ማምሸትም ጭምር ። ስለዚ ከእናቷ ጋር ክርክር ገጠመች ።
"እናቴ ለምን ታስቸግሪኛለሽ ? የእኔ እናት ሆነሽ መኖር አትፈልጊም ?"አለቻት ምርር ብላ ።መሳይ ጨነቃት እንዲ ትከፋለች ብላ አላሰበችም ።የሷ ዋነኛ አላማ ልጇ የማይገባትን ስራ እየሰራች እንዳትደክምባት ነው በተጨማሪ ደሞ እኩዮቿ በተለያየ የትምህርት ስልጠናውስጥ ገብተው እሷ ግን በኑሮ ተቸግራ ገሊት ላይ አትክልት ደርድራ ከአሁን አሁን ገዢ መጣ እያለች ስትጨነቅ ማየት ስላላስቻላት ነው ። ጤንነት ሲሰማት ካላሳረፍኩሽ ያለቻት።
"የኔ ትንሽዬ አበባ እኔ እኮ ብቻሽን ስትለፊ ማየት ስለጨነቀኝ ነው ።በዛላይ በጣም ደና ነኝ "አለቻት እቅፍ አድርጋት ።
"ተይ እናቴ ለኔ ካንቺ ጤንነት በላይ የሚያሳስበኝ ነገር የለም ።ለኔ ሞራል መጠንቀቅ ፈልገሽ ነው ይገባኛል ነገር ግን እኔ ማንነቴን ጠንቅቄ የማቅ ሰው ነኝ ሌሎችን ለመሆን አይደለም አላማዬ እራሴን በሁለት እግሮቼ ማቆም እና ያንቺን የኑሮ ጫና መቀነስ ነው ። የሰፈር ጓደኞቼ ስላሉበትና ስለሆኑት ነገር እያሰብሽ ለኔም ተመኝተሽልኝ ይሆናል ነገር ግን እኔ እራሴን ከማንም ጋር አላወዳድርም እኔ ማድረግ ያለብኝ የምችለውን ነው ። እና ደሞ ታያለሽ ሁሉም ነገር አንቺ ደና ሁኚልኝ እንጂ ይቀየራል እሺ እናቴ "አለቻት እናቷ ላይ ልጥፍ ብላ ።መሳይ የልጇ አዋቂነት ሁሌም እንዳስገረማት ነው ። ልዩ ናት አብ ላካት ምንም ነገር ባልተሟላላት ሁኔታ ላይ ብትሆንም ። ቅሬታ አቅርባ አታውቅም ። እሷ የምታዝነው እናቷ ስታዝን ስታይ ነው የምታለቅሰው እናቷ ያለቀሰች ቀን ነው ። መሳይ በልጇ እንደኮራች ነው ።ነገርግን የሁሌም ጭንቀቷ አንድ ወንድ ልጇን እንዳያሰናክልባት ነው ።
*ቀን በቀን እየተተካ ጊዜው ወደፊት ገሰገሰ የአብላካትም እናት ተሽሏት ወደስራዋ ተመለሰች አብላካትም አንዲት አነስተኛ ፑቲክ ቤት ተቀጥራ መስራት ጀመረች ። በዚ አሳብ እናቷ ባትስማማም አብላካት ግን ትምህርቷን በማታው ክፍለጊዜ እንደምትማር በጭራሽ እንደማታቋርጥ ነገረቻት በስንት ጉትጎታ አመነችላት ። ይህንን ስራ ያገኘላት አስተናጋጁ ሰሚር ነበር ። መጀመሪያ ላይ እሱ የሚሰራበት ሬስቶራንት ሊያስቀጥራት ነበር በዋላላይ ግን አሳቡን ቀየረ ።ሰሚር አሳቡን ያስቀየረው ምክንያት ።ጌታነህ በስልክ እንደሚያወራት ስትነግረው ነበር ። አስተናጋጁ ሰሚር አብላካትን እሬስቶራንቱ ማስቀጠር ።ለጌታነህ አሳልፎ እንደመስጠት ነው የቆጠረው ስለዚ ተወው ።
አንድ ቀን አስተናጋጁ ሰሚር ከስራ እንደወጣ አብላካት የምትሰራበት ፑቲክ ቤት በቀጥታ ሄደ ። አሳቡ የሷም ሰአት ስለደረስ በዛው ስለ ጌታነህ እያወራት ሊሸኛት በማሰብ ነው ቀኑም ቅዳሜ ስለሆነ ትምህርት እንደማትገባም ያውቃል ።
አብላካት ሰሚርን ስታየው ደስ አላት መንገድ ስትሄድ ከሰው ጋር ብትሆን ትመርጣለች በተለይ አሁን ላይ እራሷን መጠበቅና አለባበሷም ስለተቀየረ ቁንጅናዋ ይበልጥ ስለጨመረ ። የወንዶቹ ለከፋ ምቾት ይነሳታል ስለዚ አብዛኛውን ጊዜ ከጎኗ ከምትሰራ ልጅ ጋር ነው የምትሄደው ። በእርግጥ የመጣባትን ጥያቄ ሁሉ በአግባቡ መመለስ የሚከብዳት አልነበረችም ። እሷ የሚረብሻት ጥግ ጥግ ተቀምጠው እያፏጩ የሚላከፉ ወንዶች ሁኔታ ነው ። ዛሬ አስተናጋጁ ሰሚር ስለመጣላት ተደሰተች። እናም አብረዋት የሚሰሩትን የስራ ባልደረቦቿን ቻዎ ብላ ከሰሚር ጋር እያወራች ወደ ሰፈሯ በእግር ወክ እያረጉ ሄዱ ። አስተናጋጁ ሰሚር ጥቂት እንደተጓዙ "አቢ እኔ የምልሽ እነዛ ልጆች አሁንም ይደውሉልሻል እንዴ?"ብሎ ጠየቃት
"እ እነዛ?.."
"እማለት ይሄ ጌታነህ "አላት
"እእ አዎ ኧረ ትላንት ደውሎ ምን ቢለኝ ጥሩ ነው ለዛሬ ማታ ላግኝሽ ኪኪኪ የሚገርም ምላሳም ነው "አለች
"እና አንቺ ምን አልሺው"አላት ሰሚር
"በሆዴ እያማረህ ይቅር ኪኪኪ በአፌ ደሞ በማታ አይፈቀድልኝም ከስራ የምወጣው ደሞ አስራ አንድ ተኩል ነው አልኩት "አለችው
"ጎበዝ በፍፁም አንዳቸውንም እንዳታገኛቸው "አላት
"እሺ ግን ምን ድነው የፈራኽው"አለችው
"ልክ አይደሉም ይጎዱሻል "አላት ጭንቅ እያለው አብላካት ቀና ብላ አይታው ሳቅ አለች ። በዚጊዜ አንዲት መኪና አጠገባቸው ደርሳ ሲጢጥ ብላ ቆመች ሁለቱም ደንግጠው ፈንጠር አሉ,,,,,,,

ይቀጥላል........

ክፍል አሥራ ሰባት ከ #100 Vote ❤️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like❤️ ማድረግ አይርሱ።

Don't forget to react on our posts😊

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን!
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         

       @fkrn_be_kalat_bot
     ❥❥________⚘_______❥❥
የኢድ አል አድሃ (አረፋ)

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ተኛው የኢድ-አል-አድሃ (አረፋ)  በዓል በሠላም አደረሳችሁ አደረሰን!

# EID AL ADHA
በ'ነሱ ቤት
-------------------

    ክፍል አሥራ ሰባት [፲፯]
.
.
.

አስተናጋጁ ሰሚር አጠገባቸው ድንገት የቆመችውን መኪና ሲያይ ደነገጠ።እናም ወደውስጥ አይኑን ወረወረ እንደ ጠበቀው ነው ። ከመኪናው ውስጥ ሰመረ በመገረም ሲያየው የሚገባበት ጠፋው ። አብላካት ቆጣ ብላ ወደመኪናው እያየች "በሽተኛ ነህ እንዴ ገጭተኽን ነበር እኮ ! ማን ሰቶክ ነው መኪናውን!"ብላ ተንጣጣችበት ። ሰሚር ዝም እንድትል ምልክት እያሳያት ነበር ። ሰመረ መኪናውን ከፍቶ ሲወጣ አብላካት ለማስታወስ ሞከረች ።
"እሺ አንተ ጉደኛ አስተናጋጅ እቺን ልጅ ከየት አገኘሃት ? ባክህ "አለው ፊቱን ቅጭም አድርጎ እያየው
"እእ እኔ ,,,"ብሎ ሲንተባተብ
"እንዴ ይመለከትሃል ሰሚር ጓደኛዬ ነው "አለች ለማስታወስ እየሞከረች
"ምን እሺ እኔን አስታወሺኝ ሰመረ እባላለው አንድ ወቅት መንገድ ዳር ችግር......"ብሎ ሊያስታውሳት ሲጥር
"እንዴ በፈጣሪ አስታወስኩህ በጣም ይቅርታ ሰመረ መቼም ያንተ ውለታ የሚረሳ አይደለም !"አለችው እጇን እየዘረጋች
"ያን ያክል የሚካበድ ባይሆንም ስላስታወሺኝ ግን ደስ ብሎኛል እንዴት ነሽ ግን ?"አላት አስተናጋጁ ሰሚርን እየገላመጠው ። ሰሚር ምንም እንኳ ሰመረ ስላገኘው ቢደነግጥም ።የአብ ላካት ሁኔታ ግን አላስደሰተውም ።ሰመረን የምታናግረው በጣም ተደስታ ነው ሰሚር ደሞ እነሰመረን በጣም ነው የሚፈራቸው ልክ አይደሉም ብሎ ነው የሚያስበው ሲሰበሰቡ የሚያወሩት ስለሴት ብቻ ነው በዛላይ እያወራረዱ ።በተለይ ጌታነህ ።ከሰመረ ብዙ መጥፎ ነገር ባይሰማም ነገር ግን አብሮአቸው እስካለ ።ከነሱ የተሻለ ነገር እንደማያስብ ነው የሚሰማው ። እናም አብላካት ከነሱ መራቅ አለባት ብሎ ያምናል ።
"ደና ነኝ አካበድሽ ላልከው ነገር ደሞ ሲያንስ ነው። አንተ በሰጠኸኝ ገንዘብ ተጠቅሜ የእናቴን ጤንነት መልሼበታለው ።እናቴን አትርፈህልኛል ይህ ለኔ ትልቅ ነገር ነው "አለችው ።ሰመረ እንዲ ከፍያለ ችግር ውስጥ በዚ ዕድሜዋ ትገኛለች ብሎ አላሰበም ።ስለዚ ከበፊቱ በባሰ አዘነላት ።
"እኔ ግን እንዲ አገኝሻለው ብዬ አላሰብኩም ይገርማል "አላት
"እንዴ እኔም ሁሌም ሳስብህ እንዳመሰገንኩ ነው ። "አለችው ስታናግረው ትላልቅ አይኖቿን ከአይኖቹ ሳትነቅል ነበር ። ሰመረ ውስጡ አንዳች ነገር ሲነካካው ተሰማው እና ያንን ስሜት ላለማዳመጥ ጥረት አደረገ ።በል በል ልቤ ተው ።ገና ታዳጊ ናት በዛላይ በጣም ምስኪን ይችን ልጅ ንፁ ጓደኛ አድርጎ ከጎኗ በመቆም ከክፉ አሳቢ ሁሉ መጠበቅ ነው የሚያስፈልገው አለ በውስጡ።
"ግን አንድ ነገር ቅር ብሎኛል ጓደኛዬ አንድ ሁለቴ ሲደውልልሽ ሰምቻለው እና ግን በዛ መሃል ስለኔ አንስተሽ አታውቂም "አላት በቅሬታ
"ኧረ እኔ ስለ አንተ ጠይቄው አውቃለው ነገር ግን እንደማያገኝህ ነው የነገረኝ "አለችው
"በእውነት ?!"አላት
"እውነት ስለሰሚር ደሞ ተገርመሃል አውቃለው እሱም ያው እንዳንተ እየረዳኝ ነበር እና ረጅም ጊዜ ሆነን ።አሁን እማ በጣም ተግባብተን እንደ ታላቅ ወንድሜ ሆኗል ሰሚር ወንድሜ ነው እሱ ከጎኔ ባይኖር እንዲ ጠንክሬ ባልቆምኩ በርግጥ ያን ያክል ሰነፍ ባልሆንም የሚመክር ሰው ግን ያስፈልገኝ ነበር "አለችው ።ሰሚር አንገቱን ወዝውዞ አረጋገጠ
"ይሁን እሺ ታዲያ ለምን እራት አልጋብዛችሁም "አላቸው ሰሚር "አይ እናቷ ስትቆይ ታስባለች "አለው
ሰመረ ኮስተር አለበት
"አዎ ሰመረ ሌላ ጊዜ ይሻላል "አለችው
"እሺ ካልሽ በቃ እ ለማንኛውም ግን መልሰን ስንገናኝ አንቺ ትጋብዢኛለሽ መቼም አሁን ስራ ገብተሻል አይደል "አላት ቅር እያለው
"ችግር የለውም ግን ስራ መጀመሬን በምን አወቅክ "አለችው ፈገግ ብላ
"ያስታውቃል ትልቅ ሴት ሆነሻል በዛላይ በዚሰአት ከስራ ነው መቼም የምትመለሺው እና ደሞ በስልክ ለጊታነህ ስትነግሪው ሰምቻለው "አላት
"አዎ እሱስ ልክ ነህ ጓደኛህ እየደወለ ያደርቀኛል ኪኪኪ "ብላ ሳቀች ።አስተናጋጁ ሰሚር ቅር አለው ለነዚ ሀብታሞች መሳቅ ትርፉ ችግር ነው ።ብሎ ያስባል
"በነገራችን ላይ እራስሽን ጠብቂ በፍፁም ለማንም እራስሽን አሳልፈሽ እንዳትሰጪ የፈለገ ቢሆን በይሉንታ በውለታ እንዳትሸነፊ እሺ "አላት
"እሺ አታስብ ሰመረ በድጋሚ አመሰግናለው "አለችው
"ችግር የለም እ በሉ እንግዲ ሰላም አምሹ " ብሎ ሁለቱንም ጨብጦ ከተሰናበተ በዋላ ወደ መኪናው ተራመደ ።አብላካት ሰመረን ከዋላው እያየችው በቅሬታ ቆመች ሰሚር እንሂድ እስከሚላት ድረስ ።ሰመረ መኪናው ውስጥ ከገባ በዋላ እጁን አውለብልቦላት ነንገድ ጀመረ ። እሷ ፈዛ ቀረች ።ሰሚር እጇን ጎተት ሲያደርጋት እንደመባነን አለች
"ምነው ወሬው ከምር ተመቸሽ እንዴ?"አላት እያለመጠ
"እእ አይ ገርሞኝ ነው ማለት ለምንድነውእንዲ እየተጨነቀልኝ ነገርግን ስልኬን የማይጠይቀኝ "አለችው በቅሬታ
"እንዴ እሱም እንዲነተርክሽ ፈልገሽ ነው እንዴ ?!"አላት ሰሚር ።
"አይ እሱ ይለያል ሰሚር እንደዛ እብድ ልጅ አይደለም ላደረገልኝ ነገር እንኳ ውለታ አልፈለገም "አለችው ተክዛ ሰሚር በዝምታ ስለ ሰመረ እና ስለጓደኞቹ ልዩነት እያሰበ ከአብላካት ጎን መሄድ ጀመረ ።አብላካት ጭንቅላቷን የሰመረ አነጋገር እርጋታ ቁጣ ሁሉ ነገር ሞላው ።አሰበችው ,,,,,,,,

ይቀጥላል........

ክፍል አሥራ ስምንት ከ #100 Vote ❤️ በኋላ ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like❤️ ማድረግ አይርሱ።

Don't forget to react on our posts😊

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን!
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group


╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
    
@fkrn_be_kalat
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴏᴍᴍᴇɴᴛ         

       @fkrn_be_kalat_bot
     ❥❥________⚘_______❥❥