የኔ ደብዳቤዎች
295 subscribers
73 photos
20 videos
3 files
101 links
This channel was dedicated for👇
Letters.💋💋💋💋
Couples goals 💑
Cozy fashions👄
Music.😻😻
Sistership goal 🙎🙎
Join as u will not
Regret with it🙏🙏🙏🙏
Download Telegram
​​🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

፨፨፨፨ የእርዳታ ጥሪ ፨፨፨፨

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#ለወገን_ደራሽ_ወገን_ነው👈👈👈
🙏🙏 🙏🙏 🙏🙏 🙏🙏 🙏

ችግር የሚገባበት አይታወቅምና ዛሬ በእኔ ላይ ደርሶ #የድረሱልኝ_ጥሪዬን ወደናንተ ወደ ወገኖቼ ዘርግቻለሁ። ፈጣሪ የሚሰጥበት መንገድ አይታወቅምና ምናልባት ፈጣሪ በእናንተ በተከበራችሁ #በኢትዮጵያ ህዝብ በኩል ከደረሰልኝ ብዬ #የአባቴን ህይወት ትታደጉልኝ ዘንድ ክብር የኢትዮጵያን ህዝብ እማፀናለሁ።
🙏
ወገኖቼ ሆይ #ሰው_ያለቤተሰብ_ያለ እናትአባትባዶነውና ቤተሰብ ያለው እናት አባት ያለው ሁሉ አይቶና ስሜቴን ተረድቶ ውድ #አባቴን እንድትታደጉልኝ ስል እማፀናለሁ።
🙏
በምስሉ ላይ የምትመለከቱት
#አባቴ አቶ ጌትዬ አሰፋ በደረሰበት የጠና #የኩላሊት\ህመም ምክንያት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል #የኩላሊት_እጥበት ሲያረግ ቆይቶ በመጨረሻም #የጥቁር_አንበሳ_ሆስፒታል የሀኪሞች ቦርድ ወደ #ውጪ ሄዶ እንዲታከምና በአጭር ጊዜ ውስጥም ወደ ውጫገር ሄዶ ህክምናውን ካላገኘ #በህይወት_የመቆየቱ ጉዳይ አጠራጣሪ በመሆኑ ዛሬ ችግሬን ችግራችሁ ህመሜን ህመማችሁ አርጋችሁ በፈጣሪ ስም #የአባቴ_ህይወት በእጃችሁ ነውና እንድትታደጉልኝ በመማፀን እጠይቃለሁ።
🙏
በዚህ መሰረት ወደ ውጪ ሄዶ ለመታከም የሚያስፈልገው ገንዘብ በአጠቃላይ ከ800,000 ብር በላይ ስለሆነና የተጠየቀውን ገንዘብ እኔ ለመሸፈን አቅሙ ስለሌለኝ ወደናንተው ክብር የሀገሬ ህዝቦች እጄን ዘርግቻለሁ።
🙏
ምንም እረዳት የሌለኝ በመሆኑ የሀገሬ ህዝብ እባካችሁ የእርዳታ እንድትዘረጉልኝ እጠይቃለሁ
🙏
እኔን መርዳት ወይም ማገዝ የሚፈልግ ከታች በተጠየሰው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር
➢➢ 1000352655655
ወይም
➢➢📞0967103695 ☎️
➢➢📞0914062986 ☎️
ማግኘንና ማናገር ይችላል።
የኔ ደብዳቤዎች pinned «​​🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 ፨፨፨፨ የእርዳታ ጥሪ ፨፨፨፨ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 ➢ #ለወገን_ደራሽ_ወገን_ነው👈👈👈 🙏🙏 🙏🙏 🙏🙏 🙏🙏 🙏 ችግር የሚገባበት አይታወቅምና ዛሬ በእኔ ላይ ደርሶ #የድረሱልኝ_ጥሪዬን ወደናንተ ወደ ወገኖቼ ዘርግቻለሁ። ፈጣሪ የሚሰጥበት መንገድ አይታወቅምና ምናልባት ፈጣሪ በእናንተ በተከበራችሁ #በኢትዮጵያ ህዝብ በኩል ከደረሰልኝ ብዬ #የአባቴን ህይወት…»
Audio
"ለወገን ደራሽ ወገን ነው"

ማንም ሰው ሳያዳምጠው ሊያልፍ የማይገባ!
📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌
@poimfitsae @poimfitsae

በየትኛውም ሁነት ላይ ግጥም ለማፃፍ
> ለፍቅረኛዎ
>ለወዳጅ ዘመድ
>ለሀዘን ወዘተ

የፈለጉትን መፅሀፍ ለማስላክ
የምግብ አሰራር
ፈረንሳይኛ ቋንቋ መማሪያ
ልብ ወለድ
ታሪክ...ወዘተ
@ft2194 👈 ይህንን ሊንክ ተጭነው ያናግሩኝ!!

@poimfitsae @poimfitsae
📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌📌
ሀገር እንደ ሀገር ስታነባ አምርራ
የወገንን ስጋ ሲበላው አሞራ
መግደልና መሞት
የለት ተእለት ዜና ሆኖ እየተወራ
ሰላም ወዴት አለች
ወዴት ኮበለለች ወዴት ሄደች ሸሽታ
ሰብአዊነታችን
ከምን ተቀበረ ወርዶ ከከፍታ
ሀበሻነታችን
መለያ ስማችን
የዋህነታችን ስለምን ተፋቀ
ስለምን የሰው ልጅ
ከእንስሳነት ወርዶ ከክፋት ወደቀ
ሀገርን እንደ ሀገር
ሞገስ ያለበሰው የሀገር ጠባቂ
ለምን ተሰቃየ
ተፈተነ ክንዱ በወገን ሰባቂ
ለሀገር አንገቱን
ሰቶ ለሚሰዋ መስውአት ወታደር
ሞቱ ለህይወት ነው
ለሀገር ህልውና ለመለዮ ክብር
ዛሬም ወገን አለህ
የሞትክለት ህዝብህ ክብርህን አይረሳም
ስጋህ ቢቀበርም
አላማህ ትልቅ ነው ከግቡ አይገታም
ለሀገር የሞተ
ከኗሪ በላይ ነው የሰውነት ልኩ
ሞተ አይባልም
እሬሳ አይባልም የአንበሳ ነው መልኩ
አበሻነት ስሙእንታቀፍ
ከምግባሩ ራቀ ከፋ መሰይጠኑ
ስለምን ይወጋ
ስለምን ይታመስ ወገን በወገኑ
ይበቃል ይገታ
የመከራው ዝናብ ከጣራችን ይንጠፍ
ፅልመቱን ገርስሰን
በሀበሻነት እቅፍ ዛሬም እንታቀፍ
ከ ፍፁም ጥበበ
@poimfitsae @poimfitsae
ይህን ያውቁ ኖሯል

👉ሻርኮች ማንኛውንም በሽታ የመቋቋም ከፍተኛ ብቃት አላቸው። በጣም ገዳይ የሆነው ካንሰር እንኳን ለነሱ ምንም አይደለም
@poimfitsae
🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧🎧
ልዩ ልዩ ግጥሞችን!!
🖊በ ፅሁፍ
🎙በ ድምፅ
🎥በ ቪዲዮ አሰርተው
ለወዳጅዎ
ለፍቅረኛዎ
ለልጅዎ
ለእህት/ወንድም
ለፈለጉት ሰው ልደት ፣ የፍቅር መግለጫ ፣ የይቅርታ መጠየቂያ ፣ የሀዘን መግለጫ የሆኑ፤
ሀሳብን የሚገልፁ አንጀትን የሚያርሱ ግጥሞችን ለማሰራት 👉 @ft2194 ላይ ያናግሩኝ!!

@poimfitsae @poimfitsae

🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
ቻናላችንን ይቀላቀሉ!! በፅሁፎቻችን ይደሰቱ!! @poimfitsae
Forwarded from  የፍቅር ስሜት 💕((በግጥም)) (👻Makbale🐼)
​​፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

...ፍቅር........
...
ያኔ አንቺን ሳገኝሽ
ልቤም አዝኖ ነበር.....
ተስፍዬ ተሟጦ
ባዶ ሆኔ ነበር....
ያኔ ስንገናኝ
የህይወቴ ምእራፍ
አእላፍ ገፆቹ....
ተሞልተው ነበረ
በዝብርቅርቅ ስሜት
ሙሉ መስመሮቹ.....
....
አዎን የኔ ሀዊ
ተስፋዬን አብርተሽ
አዲስ አርገሽኛል....
ክፍተቶቼን ሞልቶ
ፍቅርሽ ከልሎኛል
የረጠበው አይኔ
ያዘሉትን እንባ
በፍቅርሽ አብሰሽ...
ይኸውልሽ ልቤ
ዛሬ ላለሁበት
ለደስተኛው ፍቅርሽ
ማንነትን ሰጠሽ..
..
..ውዴ.....
እስኪ መልሽልኝ
በእኔና ባንቺ ቃል
ለፍቅራችን እምነት
ቃልኪዳን ስናስር
እስኪ ማን ነበሩ?.....
ከከዋክብት ውጪ
ያዩ ከነበሩ
አምጪ ይጠየቁ
የፍቅራችንን ጥግ
ያቁ ከነበሩ....
........
አዎ አስከፋሻለሁ
ይህንን አውቃለሁ
ብትቀየሚኝም
ጨክነሽ አይደለም

..ሚስቴ....
ፍቅርሽ ያፈቅርሻል....
በውስጡ አስፍሮ
ሁሌም ሳትወጪ
ንግስቱ አድርጎ
በልቡ ሾሞሻል.....
ፍቅርሽ እንዳይጠፋ
በትልቅ ሸራ ላይ
በደማቁ ብእር
ስምሽን አስፍሮታል...
...
እናም ይኸውልሽ
በፍቅሬ አትወላውይ
ጥርጥር አይግባሽ
አወድሻለሁኝ.....
ይህ ስለማይገባሽ
ቃሉም ደስ አይልም
አፈቅርሻለሁኝ

ለ ፍቅር
ከ አፍቃሪሽ

ተፃፈ በ @Mak_bale
21.3.2013

@joftdav
@joftdav
@joftdav
Forwarded from  የፍቅር ስሜት 💕((በግጥም)) (👻Makbale🐼)
▣▣▣▣▣▣▣▣▣▣▣▤▤▣▣▣▣▣▣▣▣▣

.....የጷጉሜ ገፃቼ.....

በፀጥታዬ ውስጥ ትልቅ ጩኸት ይሰማኛል። ባለመናገሬ መሀል ሀያል ቃላትን አምቄያለሁ። የምር ውዴ የምነግረው አጥቼ ሰሚ ሲጠፋብኝ ለአንዲት ጨረቃና ለአእላፍ ከዋክብቶች ሁላ ሳይቀር ለፍልፌያለሁ።


ህይወት ግን ምን አይነት ናት.........
እሷ ባለችው እንጂ እኛ ባሰብነው፤ አይናችን እንደሚመለከተው
እንጂ ልባችን
እንደሚያስበው አናስኬዳትም.... እኔም ለዚህ ነበር
የእኔ አንቺን
ማፍቀር ብቻ
ደስታዬን ሙሉ ያደርገዋል፤ የእኔ ፍቅር ለሁለታችንም ይበቃል ብዬ አስብ የነበረው....
ነገር ግን ውዴ ለካ ሁሉም ስህተት ነበር ያንዱ
ማፍቀር የሁለቱንም
ፍቅር
አይተካምና.....


..ህይወቴ.........

ዝም ብለሽ ትሄጃለሽ ብዬ አላሰብኩም ነበር, ደግሞም አንቺ ነበርሽ
ተናግሮ ከሄደ ይልቅ
ዝም ብሎ የሄደን ሰው
መጠበቅ እጅጉን
ይጎዳል ያልሽኝ...
ደግሞሞ በበፊቱ ፍቅርሽ የተሰራብሽን በደል ህመሙን እያወቅሽ
በስቃዩ ውስጥ እየኖርሽ
ለሌላው ታጋሪዋለሽ ብዬ
አላስብም ነበር....

ውዴ በመሄድሽ አላዘንኩም
ቂምም አልያዝኩም
ምክንያቱም
ምናልባት ከኔ ያጣሽውን ከሌላው ለማግኘት ልብሽ ከጅሎ ይሆናል የማዝነው
........................................................................................................................................................................................................ ይቀጥላል........

#እንዲቀጥል_vote_ሰጠት_ሰጠት

^ከ~ጷጉሜ ገፃቼ ውስጥ የተቀነጨበ
4ተኛው ገፅ የመጀመሪያው ክፍል^


ተፃፈ በ @Mak_bale
4,13,2012


@joftdav
@joftdav
@joftdav
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ሰውነት ስንት ነው" ገጣሚ ፍፁም ጥበበ በ "እሁድን በ ኢቢ ኤስ" @poimfitsae
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"ዛሬ ቢሆን ገና" ገጣሚ ፍፁም ጥበበ ከ "እሁድን በ ኢቢኤስ" ጋር በግጥም ስራ @ft2194 @poimfitsae
አንቺ ከሄድሽ ወዲ
.
.
አንቺ ከሄድሽ ወዲ
ናፍቆት በሹል መርፌው እየጠቀጠቀ
ለየዋሁ ልቤ ስቃይ እያረቀቀ
እማላገኝሽን
እማላገኝሽን
አንቺን አምጣት አለኝ
እሷን አምጣት አለኝ
ቆራርጦ አፈራርሶ ካፈር ሊያዳቅለኝ
እስትንፋሴን ነጥቆ ከጉድጓድ ሊጥለኝ

አንቺ ከሄድሽ ወዲህ
መሰለኝ መቃብር
ያለሁበት ሰፈር
ዘልዬ ቦርቄ
ያደኩበት መንደር

ደሞም ባከባቢው
የሚወጣው ድምፀት
የሚሰማው ጩኸት
መሰለኝ የሲኦል
ጫጫታ'ና ሁካታ፥
የአጋንንት ፉጨት
የሐጣን ዋይዋይታ፥
የሐጥአን እሪታ...

እንዲም አስባለሁ
ሰፈርተኛው ሁሉ
ሞልቶለት ሲዘክር
ይመስለኛል የኔ
የአርባዬ ተስካር
የሰማንያ ተስካር
ሙት አመቴን ማውሻ
እኔን ማስታወሻ
ደግሶ ማልቀሻ...

አንቺ ከሄድሽ ወዲ
አለሜ በሙሉ ተመሰቃቀለ
ሁሉ በኔ አየለ
ህሊናዬ ዛለ
ዋለለ ቆሰለ
መላው ሰውነቴም
ነደደ ከሰለ
ከሰለ
.
.
እንደው ባጠቃላይ
አንቺ ከሄድሽ ወዲ

ምናለ ያልሆንኩት ምናል ያላረግሽኝ
አንድ ጊዜ ሄደሽ አስሬ ገደልሽኝ!!!

ማይክል ሰለሞን
(የቡዜ ልጅ)

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
የጨለመ ጊዜ
""""""""""""""""
ለምን?
ጊዜ ዘመን ሰዓት እያዋጀን፤
ለብርሃን ስንሮጥ
እንደ እሳት እራት ብርሃኑ ፈጀን?

ለምን?
እያደር ሰቆቃ እያደር ጭካኔ፤
ለአዘቅዝቆ ኗሪው
መትረየስ ነበረ የሚገባው ለኔ?

ለምን?
በሚስቴ አስክሬን ሀዘን 'ምቆራመድ
በልጆቼ እሬሳ በቁጭት የምነድ
ከሀገሬ ቆሜ በሀገሬ የምሰደድ

ለምን?
ብለን ስንጠይቅ

እሳት ሲለቁብህ
አንተ ምጣድ ሆነህ ዝምብለህ ተጋገር፤
በነገር ቢጠብሱህ
አንተ ምድር ሆነህ በሆድ ችለህ እደር፤
እንረድህ ሲሉህ
ትንፋሽህን ውጠህ ከአንገትህ በል ሰበር፤
በጨለመ ጊዜ
ጠይም ፀሀይ አስብ ደም ያለበት ጀንበር፤
እውትና ንጋት ይፈካል እያደር!

የሚል መልስ አለ እንዴ?
ልክ ያጣ ቀን ሲኖር
ለካም ቤተ መቅደስ ይኖራል ወንበዴ!


አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
ናፈቀኝ ሀገሬ
"""""""""""""""
ብዕሬን ሸክፌ
ሀሳብ አጠንፍፌ
ቃላት አጣልፌ
ሄድኩኝ ከወረቀት፤

ቅኔ ልደረድር
ግጥሜን ልሰድር
ከመድብሌ ልከት!

ሀገር ብዬ ጀመርኩ
ሀገሬን ላልጨርስ
ጦማሬን ከትቤ፤

ዋ ብሎ አስፈራራኝ
ከራሴ እያጣላ
አመንትቶ ቀልቤ!
.
.
ለምን አልሽ አለሜ?
.
.
እንደምን ይፃፋል
ስለሀገር ግጥም
ጦቢያ ይሉት ቅኔ፤

ሁሉም አስሮ ይዞት
ዘር የሚሉት ብሂል
የአስተሳሰብ ጠኔ፤

የአባ ጃርሶ ቁጣ
የአቶ መርዕድ ዱላ
የት አለና? ዛሬ፤

የፅዮን ስፍስፍ ልብ
የከድጃ ገር ነፍስ
ርቆ ሄዶ ከኔ፤

የትርንጎ ውበት
የአለሚቱ ምክር
ጠፍቶ ከዘመኔ፤

እንደምን ይፃፋል
ሀገር ይሉት ግጥም
ሀገር ይሉት ቅኔ!
.
.
ጉድ አለ በሀገሬ
.
.
አዬ ጉድ ነው መርዶ
ሰው ከራስ ተሰዶ
ከእምነቱ እረክሶ፤

እሩቅ እሩቅ ሲሄድ
እሳትን ሲላመድ
እያደር ተናንሶ፤

ስክነት ይሉት ጠፍቶ
ሰው እብሪትን ሽቶ
እሳትን ተላብሶ፤

አባት አንገት ደፍቶ
እናትን ሆድ ብሷት
አይኖቿ አልቅሶ፤

እህት በእህቷ
ወንድም በወንድሙ
ጦር ሰይፍ ተማዞ፤

መከባበር ጠፍቶ
ልጂት እናት ንቃ
ልጅ አባቱን አ'ዞ!

ሰው በቁም ታርዞ
ሲሄድ ሲፈረጥጥ
ቁልቁሉን እሩጫ
የእውር ድንብር፤

እንዴት ከግጥሜ ላይ
ጎላ ብላ ትፃፍ
ቅኔ ያላት ሀገር?
.
.
እንዴት? .....እንዴት?
.
.
ወገን ተከፋፍሎ
እገደል ተምሎ
በዘርና በጎጥ፤

በነጮች ሰበካ
ከሀገር ተሰዶ
በድኑን ሲቀመጥ፤

በዳንኪራ ፈዞ
ቁሙን ተገንዞ
ከሀገር ሲፈረጥጥ፤

እና እንዴት ተብሎ
ስለ ሀገር ይፃፍ
ሀገር ትቆላመጥ?
.
.
ተመልከች ዓለሜ
.
.
ሀገር ማለት ሰው ነው
ሰው ነው
ሰው ነው ሀገር፤

ሰው ከሌለ የለም
ሀገር ይሉት ወሬ
ሀገር ይሉት ነገር!

ሰብዕና ጎድሎ
በሌላ ተደልሎ
በቁም ተቀምጦ እሩቅ ከከነፈ፤

ምን ተብሎ ቅኔ
ምን ተብሎ ግጥም
ስለ ሀገር ተፃፈ?
.
.
(እናማ)
.
.
ስለሀገር ያሰብኩት
ብዙ የተለምኩት
ባሸተው ሰንፍጦ
ብቀምስ ጎመዘዘኝ፤

ከእውነቱ ተውኩና
ከተስፋ አጠቀስኩኝ
ብዕሬን አነሳሁ ከወረቀት ልቀኝ፤

ሀሳቤን ሳሰፍር
የሚል ግጥም ፃፍኩኝ
ሀገሬ ላይ ቆሜ ሀገሬ ናፈቀኝ!

(ሀገሬ ናፈቀኝ)

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
🍃 የጎረቤትፍቅር ●🍃
,,,,,,,,


ተሳስሮ አንደበቴ ድፍረቱን አጥቼ
አልነግርሽም እጂ የልቤን አውጥቼ
ደጅሽ እመጣለው በፀሀይ አሳብቤ
አይኔ እንዲያጣምርሽ ከምስኪኑ ልቤ
እርቀት አይባል የገደበን ድንበር
አንድ ላይ ያለነው ያውም አንድ ሰፈር
ከቤቴ ስወጣ ይታየኛል ቤትሽ
መዋያቸው እዚ እናትና አባትሽ
ሀይሉ ሲበረታ የጎሮቤት ፍቅር
ሰርቄ አይሻለው በቤታቹ አጥር

እናትሽ ተጫዋች ፍቅር አዋቂ ናቸው
ደግ ደጉን እንጂ ክፋም አይወጣቸው
አባትሽ ወገኛ ወግ አጥባቂ ናቸው
አያውቁት ዘመኑን ፍቅር አይገባቸው
ታዲያ እንዴት አድርጌ ፍቅሬን ልንገራቸው

እናልሽ ሀሳቤ፤
ምስኪኗ ሰበቤ፤
በሾህ ታጥረሽብኝ እንደ ፅጌሬዳ
መአዛሽ ይመጣል አልፎ ካንቺ ጓዳ
አያገኝሽ ነገር ልቤ አንቺን ሽቶ
አወደኝ መአዛሽ እንደ ናርዶስ ሽቶ
አንቺስ ባወቅሽኝልኝ ቀርቶብኝ የነሱ
ልቤ ከሚጣላ ከገዛ እራሱ
ነገር በአይን ይገባል አይደለ ተረቱ
ምነው የኔ ጊዜ አልገባሽም እቱ
እራብ ጥማት ሲሆን ግድ እንኳ አይሰጠኝ
ማወቅ ይሳነዋል ቀርቦ ሚጠይቀኝ
ናፍቆትሽ ሲመጣ ወቶ ላይደበቅ
ማንም አይቸግረው ስሜቴን ለማወቅ
ስናፍቅሽ ውዬ ስባዝን በቁሜ
ትመጪያለሽ ደግሞ ለሊቱን በህልሜ
እስኪነጋ ሌቱ አቅፌሽ በክንዴ
ቻው እንኳ ሳትይኝ ትሄጂያለሽ ባንዴ
ውለታ የረሱ የዛሬን ለማደር
ወርቅ ላበደረ ተመልሰ ጠጠር
ሲፈለጉ ታተው ቀን ቀን እየሸሹ
ለሊት እየመጡ ሰው ለሚረብሹ
ህልም ላበደሩስ ምንድነው ምላሹ?

አባ ይፍቱኝ ተብሎ አይኬድ ከቄሱ
እኔስ ቸግሮኛል ለጥያቄው መልሱ
እንከን ባይኖራቸው ውበት ቢላበሱ
ፍቅር አይገነቡም ሰው እያፈረሱ።


ቶፊቅ መሀመድ
(@Tufawmuhe)


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae
Forwarded from የፍፄ ግጥሞች (Fitsae T)
#እዬዬ
.
.
ከሩቅ ይታየኛል
'ካድማስ ወዲያ ማዶ
አይመሽ ወይ አይነጋ፤
ጭጋግ የወረሰው ያልታደለ ቀንሽ፣
ገብቶሽ እንደው እንጃ፤
በለቅሶ ሲታጀብ የታፈነው ሳቅሽ፡፡

በትላንት ጀምበር
እንባሽ ላይታበስ ፀዳሉ ላይፈካ፣
ጥምሽን ላይቆረጠው ረሃብሽ ላይረካ፣
የፊትሽ ወጋገን በሀዘን ሲታረስ፣
"እዬዬ"ሽን ሳቂው፤
ወትሮም ቤተኛሽ ነው እየሳቁ ማልቀስ፡፡

እየሳቁ ማልቀስ እየሞቱ መኖር፣
ላንቃ እያኘከ እያከኩ ማደር፣
የኋሊት መዘመን ሲተልቁ ማነስ፣
ሰብስቦ መበተን ደምሮ መቀነስ፡፡
ነው እና ያንቺ እጣ፤
በሆነብሽ ሁሉ ብዙ አትከፊ፣
በእንባ ጎርፍ አለም እየሳቅሽ እለፊ፡፡


abiye12

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@poimfitsae @poimfitsae
@poimfitsae @poimfitsae