First priority Ethiopia
227 subscribers
1.93K photos
249 videos
159 files
60 links
First Priority Youth and school Ministries!
Download Telegram
🩸 በጋምቤላ ስናካሄድ የነበረው የክረምት በጎ ፈቃድ ሰብአዊ የደም ልገሳ መርሃ ግብር በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ! 🩸
የጋምቤላ ከተማ አመራሮች፣ የፌዴራል ሰላም ሚኒስቴር ተወካይ፣ የ“ፈርስት ፕራዮሪቲ” ጋምቤላ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እና የአካባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት ደማቅ የደም ልገሳ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
📌 ከመድረኩ የተደመጡ ዋና ዋና መልዕክቶች፦
• አቶ ማርቆስ ጉደታ (የከተማው ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ)፦
"የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የህብረተሰቡን የእርስ በእርስ መረዳዳትና አብሮነት ከማጠናከሩ ባለፈ የወጣቶችን በጎ ፈቃደኝነት ባህል ለማሳደግ ትልቅ ሚና አለው። ህብረተሰቡን ያሳተፉ መሰል የበጎ አድራጎት ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ።"ሲሉ በመድረኩ ተናግረው
• አቶ የማነ ተስፋዬ (የከተማው ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ)፦
"በጎ ፈቃደኝነት የሰዎችን ህይወት ከመታደግ ባሻገር ማህበራዊ አንድነትን ለማጠናከር የሚያስችል ትልቅ በጎ ተግባር ነው።"በማለት መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
📊 የደም ልገሳው አጠቃላይ አሃዛዊ መረጃ፦
• 📍 በዋናው ማጠቃለያ መርሃ ግብር፦ 11 በጎ ፈቃደኞች (10 ወንድ እና 1 ሴት)
• 📍 በኤም ኤስ ኤፍ (MSF) ኩሌ፦ 15 በጎ ፈቃደኞች (13 ወንድ እና 2 ሴት)
• 📉 አጠቃላይ ድምር፦ 26 በጎ ፈቃደኞች (23 ወንድ እና 3 ሴት) ደም በመለገስ ህይወት የመታደግ አጋርነታቸውን አሳይተዋል።
የማጠቃለያ መርሃ ግብሩ በእለቱ በደም ልገሳው ላይ በመሳተፍ ሰብአዊነታቸውን ላስመሰከሩ በጎ ፈቃደኞች በሙሉ ምስጋና በማቅረብ በሰላም ተጠናቋል።
ለሰጡት ህይወት ሰጪ ስጦታ እናመሰግናለን! 🙏✨
❤3