ፍሬ ሀይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት (mana dilbata firee amentaa)
175 subscribers
238 photos
10 videos
23 files
44 links
በዚህ መንፈሳዊ ቻናል የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሐይማኖታችንን እንድናውቅ የሚረዱ :-

፨ ከተለያዩ መንፈሳዊ ቻናሎች የምናገኛቸውን መረጃዎች አናጋራቹሃለን።

፨ ጥያቄ አና መልስ አንጠያየቃለን።


፨ መንፈሳዊ መፃህፍትን በ አማርኛ ፣ Afaan oromoo አና English language እናካፍላቹሃለን።

ሐሳብ አስተያየት ካላቹ @ye_gebriel ላይ አሳውቁን።
Download Telegram
#የጌታ_ልደት_በቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

ቀዳማዊ አምላክ ዛሬ ተወለደ፤ ጥንቱን ገንዘቡ ባይደለ ባህርይ ተገኝ፤ እርሱ ቀዳማዊ አምላክ ነው፤ ሰው በመሆኑም ከባህርይው አልተለወጠም፡፡ የመለኮቱ መገኝትም ከእመቤታችን ከተወለደ ወዲህ አይደለም፤ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ጥበብ ነው እንጂ፤ የማይታመም እርሱ ከባህርይ መለኮቱ ሳይለወጥ ሕማም የሚስማማውን ስጋን ተዋሃደ፡፡ ዳግመኛም በልዑል ዙፋን ላይ ተቀምጦ ያለ እርሱ በበረት ተጣለ ስጋ ሳይሆን የነበረ የማይዳሰስ ወልድ ዋህድ ዛሬ ስጋን በመዋሃድ ተዳሰሰ፤ ሃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱ በጨርቅ ተጠቀለለ፡፡

መፅሃፍ እንዲህ አለ፦ ብልህ ሽክላ ሰሪ የሚሰራውን የለዘበ ጭቃ በአገኝ ጊዜ ከእርሱ መልካም እቃ እንዲሰራ እንደዚሁ ጌታችን የዚህችን ድንግል ንፁህ ስጋዋን ንፅህት ነፍሷን ባገኘ ጊዜ ነፍስ ያለችውን ስጋ ሊዋሃደው ፈጠረ፡፡ እንደወደደ ከድንግል ነፍስን ስጋን ፈጥሮ ለበሰ እርሱንም ተዋህዶ ዛሬ ተወለደ ሕፀፅ ያለበት ነው ብሎ ባህርያችንን አልተወውም ፤ ስጋን በተዋህዶ ጊዜ ቃል ከምላቱ አልተወሰነም፤ ስጋ የፈጣሪ አካል ባህርይ በሆነ ጊዜ ፍፁም አምላክነትን አገኝ እንጂ፡፡ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረ እርሱ ትንሽ ህፃን ሆኗልና፡፡

እኔ ፈፅሜ አደንቃለሁ፤ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን በዘላለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ ከስጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ ሃጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት፤ ይህን ወዷልና፡፡ ክብሩ ተለይቶት የነበረ ስጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው፤ የፀጋ ገዥነትን አጥቶ የነበረ ስጋንም የባህርይ ገዥ ሊያደርገው ወደደ፤ አዳም ከእኛ እንዳንዱ ሆነ ያለውንም ሰው በመሆን ሊገልጠው ወደደ፡፡
Forwarded from Janderebaw Media
ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋራ፡አዩት፥ወድቀውም ሰገዱለት፥ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።
ወደ ሄሮድስም እንዳይመለሱ በሕልም ተረድተው፡በሌላ መንገድ ወደ አገራቸው ሔዱ።

-የማቴዎስ ወንጌል 2:11-12
በጣም ተገርሜያለው። ቦታውን ካወቃቹት ንገሩኝ
+• ምን ይዘህ ወጥተሃል? •+

በአንድ መንደር ዝናብ ጠፍቶ ተቸገሩ አሉ። ሰው ተሰብስቦ "ምን ይሻላል? ምን እናድርግ?" ብሎ ተማከረ። ትልቁ መፍትሔ የዝናቡ ጌታ የሆነውን እግዚአብሔርን መማጸን እንደሆነ ተገንዝበው ጸሎትና ምሕላ ለማድረስ ተስማሙ።

ጸሎቱ በሚጸለይበት ዕለት አንዲት እናት ከቤት ለመውጣት እየተዘጋጀች እያለ፥ ልጇ "እማዬ የት ልንሄድ ነው?" ብላ ጠየቀቻት። እናትም "እግዚአብሔር ዝናብ እንዲሰጠን ልንጠይቅ ወደ ቤተክርስቲያን ልንሄድ ነው" ብላ መለሰች።

ዝግጅታቸውን ጨርሰው ሲወጡ፥ ልጅቷ መለስ ብላ "እማዬ፥ ጥላ አንይዝም እንዴ?" ብላ ጠየቀች። እናት በመገረም "ለምንድር ነው ጥላ የምንይዘው ደግሞ?" አለች። ልጅም "እግዚአብሔርን ከጠየቅነው ስለሚሰጠን፥ ስንመለስ ዝናብ እንዳይመታን ነው።" ብላ መለሰች። እናት የልጇን ንጹሕ እምነት ልብ ማለት ቢያቅታትም፥ እግዚአብሔር ግን ይህንን ፍጹም መታመን አይቶት ነበር።

ጸሎታቸውን ጨርሰው ሲመለሱ፥ ድንገተኛ ዝናብ መጥቶ በመንደሪቷ ላይ ዶፍ ዝናብ ጣለ። ጥላ ሳይይዙ የሄዱ እናትና ልጅም በዝናብ ርሰው ወደ ቤታቸው ገቡ። ማመን መታመን እንዲህ ነው! ሰው እምነትን ከሞኝነት ቢቆጥረው፥ እግዚአብሔር ግን ከተግባር ያደርሰዋል። ሰው ከቅርብ ማየት የማይችለውን እምነት፥ እግዚአብሔር ግን ከሩቅ ያየዋል።

በሕይወትህ እግዚአብሔርን ብዙ ጠይቀኸው ሊሆን ይችላል፥ ግን ይሰጠኛል ብለህ ምን ይዘህ ወጥተሃል?
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"ከንቱ ውዳሴ በመንገድ ሁሉ የሚከተልህ የተሸሸገና ጭንብል ያጠለቀ ሌባ ነው። አሳዳጅ በመሆኑ በጣም ደኅንነት በሚሰማህ አሳቻ ሰዓት ሳታውቀው ይዘርፈሀል፤ ይገድልህማል። "

ቅዱስ ጎርጎርዮስ
#EOTC

ዛሬ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

ብፁዕነታቸው በመግለጫቸው ፤ " በዚህ ወቅት ቤተክርስቲያኗ የተለያዩ ፈተናዎች ገጥመዋታል ፤ በየግል በተለያዩ አባቶች፣ በተለያዩ መንገዶች በሚሰበኩ ስብከቶች ፣ በሚፈጠሩ ሁኔታዎች ፣ ለምን ? እንዴት ? ዝም አልሽ ቤተክርስቲያን በሚልም ትልቅ ፈተና ላይ ነች " ብለዋል።

ቤተክርስቲያን ፈተናዋን እንዴት ማለፍ እንዳለባት በጸሎት እግዚአብሔርን እንጠይቀዋለን ሲሉ ገልጸዋል።

" ባለፈው የተለያዩ አባቶች በተለያየ መንገድ ተናገሯቸው ስለተባሉት ጉዳዮች ተነስቶ መንግስት ቀየሜታውን ገልጾ ቤተክርስቲያን መልስ እንድትሠጥበት አሳስቧል " ያሉት ብፁዕነታቸው " ቤተክርስቲያንም በስፋት፣ በትኩረት ተወያይታበታለች (ቅዱስ ቋሚ ሲኖዶስ) ይሁን እንጂ የብፁዓን ሊቃነጳጳሳት ጉዳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳይ ነው የሚሆነው ፣ ምክንያቱም አንድ ሊቀ ጳጳስ ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ስለሆነ፤ ቀርቦ ተጠይቆ አውንታዊ መልስ ሰጥቶ ስህተት ነው ? እውነት ነው ? ብሎ የሚወሰን እንጂ ብግድ ተብሎ በቋሚ ሲኖዶስ ወይም በሌላ የተለያየ መልኩ እንዲህ ነው እንዲያነው ብሎ መናገር ህገ ቤተክርስቲያናችን አፈቅድም " ብለዋል።

" ቤተክርስቲያን ሰላምን መፈለግ ፣ መሻት ፣ መልካም ነገር ማድረግ ነው ከዚህ ውጭ ሌላ አቋም የላትም " ያሉት ብፁዕነታቸው ፤ " እንደ ህግ እና ስርዓታችን በአባቶች ደረጃ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚወስነውን ይወስናል። ይህ ቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ ሲኖዶስ ተወያይቶ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚለውን እንዲል አልፎታል " ሲሉ አሳውቀዋል።

ብፁዕነታቸው ፤ " አሁን ግራ የሚያጋባው ትላንት ለበዓለ ጥምቀቱ የተሰየመው አብይ ኮሚቴ ከከተማ አስተዳደሩ፣  ከሚመለከታቸው የፀጥታ ኃላፊዎች ጋር ፣ከታላላቅ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርጎ ነበር። በውይይቱ ይህ ከባድ ፈተና እየተነሳ እንዳለና አሁንም በዓለ ጥምቀቱን ለማክበር ቅድመ ዝግጅት ቤተክርስቲያኒቱ እንዲህ አይነቱን ለይታ እንድታወግዝ ፣ የራሷን መልዕክት እንድታስተላልፍ በመንግሥት አቋም ተይዞ ለአብይ ኮሚቴው ተነግሯል " ብለዋል።

" ቤተክርስቲያን ያራሷ ነፃነት አላት ፣ የራሷ ክብር አላት ፣ የራሷ ነፃ መድረክ ፈላጊ ናት ሁሉም እየተነሳ ያም ይሄን አድርጊ፣ ይሄም ይሄን አድርጊ ስላላት እየተጎተተች የተባለችውን አታስተናግድም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ክፉውን ክፉ፣ በጎውን በጎ፣ መልካሙን መልካም ፤ መልካም ያልሆነውን መልካም አይደለም ብላ ለማስተላለፍ የራሷ ህግ ስርዓት አላት " ብለዋል።

" የፈለገ የሚያዛት ፣ የፈለገ የሚያሽከረክራት ፣ ያልወደደ እንደ ወደደ ፍላጎቱን ምኞቱን እንድትፈፅምለት የሚጎትታት ቤተክርስቲያንን ኖራም አታውቅም ወደፊትም ልትኖር አይገባም " ሲሉ ተናግረዋል።

" ቤተክርስቲያን በራሷ ነፃ መድረክ ቆማ ችግሩን ችግር ነው ብላ መናገር አለባት እያደረገችም ነው። " ያሉት ብፁዕነታቸው " ይሄ በፍፅሙ አይመጥነኝም። እንዲህ አይነቱ የኔ ቃል አይደለም ብላ #ታውጃለች ግን በግልፅ መጠየቅ ያለባትን ጠይቃ መናገር ያለበትን እንዲናገር ፈቅዳ ሁሉን ነገር በአግባቡ ታደርጋለች እንጂ በኩርፊያ በአላስፈላጊ ብሂል ይሄን ካላደረግሽ በዓል ለማክበር አልችልም ፣ ከናተ ጋር ግንኙነት የለንም እስከሚባል ድረስ የሚኖረው ነገር ከማንም ከምንም በፍፁም አይጠበቅም " ሲሉ አሳውቀዋል።
#ጥር_4

#ሐዋርያው_ቅዱስ_ዮሐንስ_ወልደ_ነጎድጓድ

ጥር አራት በዚህች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደው የከበረና የተመሰገነ ወንጌልን የጻፈ የሐዋርያው ዮሐንስ የፍልሰቱ መታሰቢያ ሆነ።

ለዚህም ቅዱስ ወደ እስያ ሀገር ይሔድ ዘንድ ዕጣው በወጣ ጊዜ እጅግ አዝኖ አለቀሰ እነርሱ ክፉዎች ከሀዲዎች ልባቸው የደነደነ መሆናቸውን አውቋልና ግን ከጌታችን ኃይልን መጽናናትን አግኝቶ ከደቀ መዝሙሩ ከአብሮኮሮስ ጋር ወጥቶ ወደ ክፍሉ ሔደ።

ወደ ኤፌሶንም ሊሔድ ወዶ በመርከብ ላይ ተሳፈረ መርከቡም ተሰበረ እየአንዳንዱ በመርከብ ስባሪ ሠሌዳ ላይ ተንጠለጠለ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስንም የባሕሩ ማዕበል ወደአንዲት ደሴት አደረሰው ቅዱስ ዮሐንስ ግን በባሕሩ ማዕበል መካከል አርባ መዓልት አርባ ሌሊት ኖረ።

ከዚህም በኃላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮሮስ ወዳለበት ወደ የብስ ባሕሩ ተፋው ስለ መገናኘታቸውም እግዚአብሔርን አመሰገኑት በዚያን ጊዜም ተነሥተው ወደ ኤፌሶን ከተማ ገቡ ግን በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሰብኩ ዘንድ አልተቻላቸውም እነዚያ ያገር ሰዎች እጅግ የከፉ ናቸውና።

ስለዚህም ምክንያት ፈጥረው ዮሐንስ ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤት እሳትን የሚያነድ ሆነ ረድኡ አብሮኮ ሮስም አጣቢ ሆነ ያቺ ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ነበር መጻተኞችም ስለሆኑ ታጉሳቁላቸዋለች ትደበድባቸዋለች ትረግማቸዋለች ባሮቿም እንደሆኑ ጽፈውላታልና ለእርሷ ባሮች አደረገቻቸው በዚህ በታላቅ ጒስቊልና ውስጥ ኖሩ።

ከዚህም በኃላ በአንዲት ዕለት ይታጠብ ዘንድ የአገረ ገዥው ልጅ ገባ በዚያም የውሽባ ቤት ከተሠራ ጀምሮ የሰይጣን ኃይል አለ የመኰንኑንም ልጅ አንቆ ገደለው በዚያንም ጊዜ የአገር ሰዎች ለዚያ ለሞተው ሊያለቅሱለት ተሰበሰቡ የከበረ ዮሐንስም ከእርሳቸው ጋር መጥቶ እንደ ሰው ሁሉ ሊያይ በዚያ ቆመ።

ሮምናም በአየችው ጊዜ ረገመችው አንተስ በጌታዬ ልጅ ሞት ደስ ብሎህ ልትዝትብኝ መጣህ አለችው ቅዱሱ ግን በቅንነት አይዞሽ አትዘኝ አላት ይህንንም ብሎ ወደ ሞተው ቀረብ ብሎ በመስቀል ምልክት አማተበበት በፊቱም ላይ እፍ አለበት። በዚያንም ጊዜ ያ ሞተው ድኖ ተነሣ የአገር ሰዎችም ደነገጡ ሮምናም ወዮልኝ እግዚአብሔር የሚሉት አምላክ አንተ ነህን አለች። እርሱም አይደለሁም እኔ አገልጋይ ሐዋርያው ነኝ እንጂ አላት በእነርሱ ላይ የሠራችውን በደል ሁሉ ይቅር ይሏት ዘንድ መሪር ልቅሶ በማልቀስ ሐዋርያትን ለመነቻቸው እነርሱም አረጋጓት አጽናኗትም።

ከሀገሩም ሰዎች ብዙዎቹ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው በፊታቸውም ብዙዎች የሆኑ ድንቆች ተአምራትን አደረገ ይህንንም አይተው የሀገሩ ሰዎች ሁሉም በጌታችን አመኑ። ከጣዖታቱ አገልጋዮች በቀር እነርሱም ሰይጣን በእርሱ ላይ ስለሚያነሣሣቸው ሊገድሉት ይሹ ነበር ነገር ግን ምርጦቹን እግዚአብሔር ጠበቃቸው።

የከበረ ዮሐንስም ሁሉንም እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ እስከመለሳቸው ድረስ ታላቅ ድካምና ጭንቅ የሆነ መከራ ደረሰበት። የከበረ ሐዋርያ ጳውሎስም ስለ ልቡናቸው ደንዳናነት ጣዖታትን ስለመውደዳቸውም ስለ እነርሱ መስክሮአል። እርሱም ዮሐንስ በታላቅ ድካም ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው። ከዚህም በኋላ ኤጲስቆጶሳትን ቀሳውስትን ዲያቆናትን ሾመላቸው።

ከዚህም በኃላ ከእስያ በዙርያዋ ወዳሉ አገሮች ሁሉ ወጥቶ አስተማረ እግዙአብሔርንም ወደማወቅ መለሳቸው። ይህም የከበረና የተመሰገነ ዮሐንስ በዚህ ዓለም ዘጠና ዓመት ኖረ እጅግም ሸመገለ ግን እንደ ባልንጀሮቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አልቀመሰም። ስለ ድንግልናውና ስለ ንጽሕናው ይህ ሆነ ሁሉም በክብር ይስተካከሉ ዘንድ እርሱም ወንጌልን ቀለም ሲስ የሙባለውን ራእይ ሦስት መልእክታትን የጻፈ ነው። ራት ሲበሉ በጌታ ኢየሱስ አጠገብ የተቀመጠውና አቤቱ የሚያሲዝህ ማነው ያለው ይህ እርሱ ነው።

ጌታችንም በተሰቀለ ጊዜ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በመስቀሉ አጠገብ የቆመ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው።

ጴጥሮስም እርሱን ሲከተለው በአየው ጊዜ ስለርሱ ጌታ ኢየሱስን አቤቱ ይህስ እንዴት ነው ብሎ የተናገረ ጌታ ኢየሱስም እስክመጣ ድረስ ይኖር ዘንድ ከወደዱኩ አንተ ምን አለህ አንተ ግን ተከተለኝ ያለለት ይህ ነው።

የተመሰገነ ዮሐንስም ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ሰዓት እንደ ቀረበ በአወቀ ጊዜ ሕዝቡን ጠራቸው ጸሎትንም ጸለየና ኅብስቱን ባርኮ ቆረሰ ይህም የጌታችን ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ባረካቸው አጽናናቸውም።

ከዚህም በኃላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ። ከኤፌሶንም ከተማ ውጭ ወጣ ጐድጓድ እንዲቆፍሩም አዘዘ ከውስጥዋም ወርዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ ከአንድ የበፍታ ቀሚስ በቀር አላስቀረም። እጆቹንም አንሥቶ ጸለየና ወደ ከተማ ይመለሱ ዘንድ አሰናበታቸው በክርስቶስም ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝቡ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዛቸው በጎ ሥራዎችንም ይሠሩ ዘንድ ጌታችን ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፈለው ዘንድ አለውና።

ሁለተኛም እንዲህ አላቸው እኔ ከሁላችሁም ደም ንጹሕ ነኝ ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራችሁ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩኝም።

ይህንንም በተናገረ ጊዜ አለቀሱ እጆቹንና እግሮቹን ስመው በጒድጓዱ ውስጥ ትተውት ወደ መንገድ ተመለሱና የሆነውን ሁሉ ለሰዎች ነገሩዋቸው ሁሉም ደንግጠው መጡ ግን ልብስና ጫማ እንጂ መቃብሩን አላገኙም እጅግም አደነቁ ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስን በዚህ በጎ ዕረፍት ያሳረፈው እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ አባት በሐዋርያ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥር)
"አብ ከእኔ ይበልጣል " ዮሐንስ 14፥28

ክፍል-፩

"አብ ከእኔ ይበልጣል " ዮሐንስ 14፥28 እንዴት ? ይህን ቃል የተናገረው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ። የጻፈልን ደግሞ ከአሥራ ሁለቱ የጌታ ደቀመዛሙርት መካከል አንዱ የሆነው ወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ ነው ። ቅዱስ ዮሐንስ አስቀድሞ "እኔና አብ አንድ ነን" " እኔን ያየ አብን አይቷል" የተባሉትን የጻፈልን ወንጌላዊ ነው ። ስለዚህ ምክንያቱን ካልመረመርነው "አብ ከእኔ ይበልጣል" የሚለው ሐሳብ መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በራሱ ይጋጫል እንዴ ያስብላል ።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን ቃል የተናገረበት ምክንያት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ ምሥጢሩን በገለጠላቸው መጠን በብዙ አቅጣጫ አብራርተውልናል ። ነገር ግን በዚህ ርዕስ ኢየሱስ ክርስቶስ "ከእኔ አብ ይበልጣል" ካለበት ምክንያቶች ሁለቱን ብቻ ብንመለከት በቂያችን ነው ። ይኸውም ፦ አንደኛ "ከእኔ ተማሩ እኔ የዋኅ በልቤ ትሑት ነኝና " እንዳለሁ ሁሉ፦ እኛን ትሕትና ለማስተማር ነው ። ዮሐ 11፥29 ሁለተኛ ደግሞ በለበስኩት ሥጋ ከእኔ አብ ይበልጣል / ሰው በመሆኔ ከእኔ አብ ይበልጣል / ማለቱ ነው ።  ምክንያቱም አብ ሰው አልሆነምና ይህ ሲባል ግን ክርስቶስ በመለኮቱ ከአብ እኩል መሆኑን መዘንጋት አይገባንም ። ክርስቶስ አምላክ መሆኑን ከጎኑ ትቶ ሰው መሆኑን አጉልቶ ወይም በሰው ቦታ ገብቶ መናገሩ ነው እንጂ ። ይህም ለተወሰነ ጊዜ ነው ፦ ማለትም ዘመነ ሥጋዌውን ይኸውም ሰው ሆኖ ከተወለደበት ሞትን ድል አድርጎ ወደቀደመው ክብሩ እስኪመለስ ድረስ ያለው ጊዜ ነው ። በዚያን ጊዜ በለበሰው ሥጋ ፍጹም ሰው በመሆኑ ከአብ ሳይሆን ከመላእክት እንኳ አንሶ መገኘቱን ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን መልእክቱ በምዕራፍ 2 ከቁጥር 9 ላይ ጽፎልናል ። "በእግዚአብሔር ጸጋ ስለሰው ሁሉ ሞትን ይቀምስ ዘንድ ከመላእክት ይልቅ ጥቂት አንሶ የነበረውን ኢየሱስን ከሞት መከራ የተነሳ የክብርና የምስጋና ዘውድ ተጭኖ እናየዋለን ። " ይህ የሚያስረዳን ኢየሱስ በሥጋ ወራት በለበሰው ሥጋ እንኳን ከመላእክት አንሶ እንደነበር ነው ።

አንድም ከመላእክት አነሰ ማለት ሰው ሆነ ማለት ነው ። ሰው ከመላእክት በጥቂት ያንሳል "ታስበው ዘንድ ሰው ምንድ ነው ? ከመላእክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸው በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው " በማለት ዳዊት ሰው ከመላእከት በጥቂት ያነሰ መሆኑን ጽፎልናል ። መዝ 8-6 ሰው ከመላእክት በጥቂት ያንሳል የተባለውም ሕመምና ሞት የሚስማማ ሥጋ በመልበሱ ብቻ ነው። ምክንያቱም መላእክት ሕመምና ሞት የለባቸውምና ። በአዲስ ኪዳን ግን አምላክ ሰው ሲሆን ሰው ደግሞ አምላክ በመሆኑ ምክንያት ሰው መላእክትን በልጧል ። ስለዚህ ጌታችን ከእኔ አብ ይበልጣል ያለው አብ ሕመምና  ሞት የሚስማማው የሰው ሥጋ ያልለበሰ መሆኑ ለማስገንዘብ ነው ። እንጂ በመለኮቱ ከአብ እኩል መሆኑን " እኔና አብ አንድ ነን " ሲል ነግሮናል ። ዮሐ 10፥30 ( እውነተኛ ክርስትና ገጽ 162-163 ተስፍዬ ምትኩ )

በሚቀጥለው " አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ" ሜቴ 27-46  ያለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እናያለን ።

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ የቴሌግራም ቻናል ይከታተሉን ።

  (ዲያቆን ፍፁም ከበደ)
" አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ" ሜቴ 27፥46 ምን ማለት ነው ?

ክፍል-2

ክርስቶስ መከራ መስቀልን የተቀበለው በኃጢያቱ ተፈርዶበት አሊያም ከእግዚአብሔር ምህረት ለማግኘት አይደለም ። ስለ እኛ ኃጢያትና በደል ራሱን ካሳ አድርግ አቀረበ እንጂ ማንም አስገድዶት አይደለም ። "ነፍሴን ስለበጎቼ አኖራለሁ እኔ በፍቃዴ አኖራለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም ። ላኖራትም ላነሳትም ስልጣን አለኝ" እንዲል ዮሐ 1.፥17

ጌታችን ይህን ቃል የተናገረው ከእርሱ ሌላ አምላክ ኖሮት ወደ እርሱ ለመማጸን ሳይሆን የተሰቀለው ስለ አዳምና ልጆቹ ስለሆነ አዳምና ነቢያቱም በመከራው ዘመን አምላኬ አምላኬ ለምን ተውኸኝ ብለው ይጮኹ ስለነበር የሰው ልጅን እዳ በደል ተሸክሞ ስለ ሰው ጮኸ እንጂ ። "አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና" እንዲል ሮሜ 5፥14 ። አንድም ትንቢቱ ይፈፀም ዘንድ ጮኸ ። "አምላኬ አምላኬ ተውኸኝ እኔን ከማዳን ከጩኸቴ ቃል ሩቅ ነህን ? " በማለት አስቀድሞ ነብዩ ዳዊት ትንቢት ተናግሮ ነበርና ። መዝ 21-1

አንድም ለአቅርቦተ ሰይጣን ጮኸ ። ጌታ ይህን አስቀድሞ በምሳሌ ሲያስተምር በማቴ 12-29"...ሰው አስቀድሞ ኃይለኛውን ሳያስር ወደ ኃይለኛው ቤት ገብቶ እቃውን ሊነጥቅ እንዴት ይችላል ? ከዚያ ወዲያ ቤቱን ይበዘብዛል ። " ሲል ተናግሮ ነበር ። በዚህ ላይ ኃይለኛው የተባለው ዲያብሎስ ከአዳም በደል የተነሳ ከአዳም እስከ ክርስቶስ ያለውን ዘመን በሰው ሰጋና ነፍስ ስልጣን አግኝቶ ስለነበር ሰውን ከማኅፀን ጀምሮ እየተቆራኘ ሰው ሲሞት ነፍስን ወደ ሲዖል ስጋውን ወደ መቃብር ያውርድ ነበር ። ጌታችንም በመስቀል ተሰቅሎ "አምላኬ አምላኬ " ሲል ሰምቶ ይህስ ፍጡር ነው ነፍሱን ከስጋው ለይቼ ስጋውን ወደ መቃብር ነፍሱን ወደ ሲዖል አወርደዋለሁ ብሎ እንዲቀርበው አምላኬ አምላኬ ብሏል። ዲያብሎስ ይህን ጩኸት ሰምቶ ወደ ጌታ ቀርቧል ። ጌታ ደግሞ "ከመጣሽ ማርያም ታምጣሽ" እንዲሉ በኃይል ስቦ በነፍስ አውታር ወጥሮ በማስጨነቅ በፈቃዱ በሲኦል ያሉትን ነፍሳት አሳልፎ አዲሰጠው አድርጎታል ። በዚህም እርሱ ራሱ ድንቅ መካር ኃይል የተባለ አምላክ ሆኖ ሳለ  አምላኬ አምላኬ ብሏል ኢሳ 9፥6 ። አንድም መከራው የተቀበለው ሰውን ለማዳን በለበሰው ስጋ ነውና ስለለበሰው ስጋ ደግሞ አምላክ አለውና አምላኬ አምላኬ አለ ። አንድም "ከእኔ ተማሩ" እንዳለ እኛም መከራ ሲገጥመን ወደ አምላካችን እንድንጸልይ አምላኬ አምላኬ ብሏል ማለት ነው ማቴ 11፥29 ።  (አውነተኛ ክርስትና ተስፍዬ ምትኩ ገጽ 163-164)


በቀጣይ "ወደ አምላኬና አምላካቹ ወደ አባቴና አባታቹ አርጋለሁ" ። ዮሐ 20፥17 የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እናያለን ።

       (ዲያቆን ፍፁም ከበደ)


ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ የቴሌግራም ቻናል ይከታተሉን ።

https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
"ወደ አምላኬና አምላካቹሁ ወደ አባቴና አባታቹሁ አርጋለሁ" ዮሐ 20፥17

አምላኩ አባቱ ማን ነው? ፦ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል ነሥቶ በተነሳ ዕለት ከሁሉ ቀድማ ያገኘችው መግደላዊት ማርያም ነበረች። እርሷም የጌታን ሰውነት ልትነካው በቀረበች ጊዜ "ገና ወደ አባቴ አላረግሁም አትንኪኝ፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ እኔ ወደ አባቴ ወደ አባታቹሁ ወደ አምላኬ ወደ አምላካቹሁ ዐርጋለሁ ብለሽ ንገሪያቸው " እንዳላት ቅዱስ ዮሐንስ ጽፎልናል ። የዚህ ሐሳብ ትርጉም ከፍ ብለን ካየነው "አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ" ካለው ጋር ተመሳሳይ ነው ። አባቴ ያለው አብን ነው ። ቅደመ ዓለም ያለ እናት ከአብ አብን አህሎ ፤ አብን መስሎ /ሆኖ/ ተወልዷልና የባሕርይ አባቱ መሆኑን ሲያጠይቅ አባቴ አለ። አምላኬ ያለው ግን ለሰውነቱ ነው። ሰውነቱ ስንል ሰው መሆኑን አዳማዊ መሆኑን አንድም የአዳምን ሥጋ መልበሱን ለመናገር ነው ። ለሰው አምላክ መኖሩ የታወቀ ነውና ። ክርስቶስ ፍፁም ሰው መሆኑን ሲያጠይቅ አምላኬ አለ። አንድ ነገር መጠንቀቅ ያለብን ወደ አምላካችንና ወደ አባታችን አለማለቱን ነው ። ምክንያቱም አብ /ለኢየሱስ ክርስቶስ/ የባሕርይ አባቱ ሲሆን ለእኛ ግን የጸጋ አምላክ ነውና ። አምላኬ ያለውም ፍጡር ስለሆነ ሳይሆን የተፈጠረውን ነብስፍና ሥጋ ስለተዋሐደ ነው ። ያ ነፍስና ሥጋም ቢሆን በእርሱ የተፈጠ ነውና ። ሁሉ በእርሱ ሆነ ፥ ከሆነውም አንዳች እንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።" እንዲል ዮሐ 1፥3 ። ስለዚህ ወደ አምላኬ ና አባቴ አርጋለሁ ማለቱ ወደ ቀደመው ክብሬ እመለሳለሁ ማለቱ እንጂ ሌላ አምላክ ኖሮት አይደለም ። አምላኬ ያለው አብን ስለሆነ አምላኩ አብ ነው ከተባለም "እኔና አብ አንድ ነን ብለዋልና እርሱም አምላክ ነው ።

አትንኪኝ ማለቱማ ገና አላመንሽብኝ ብሎ ሲገስጻት ነው ። አንድም የመነካ የሚዳሰስ ስጋ መልበሱን ሲያጠይቅ ነው ። መነካት /መዳሰስ/ የሰው ባሕርይ ነው ። ለሰው ደግሞ አምላክ አለውና እርሱም ፍጹም ሰው መሆኑን ሲናገር ወደ አምላኬ ዐርጋለሁ አንድም ወደ አምላካዊ ክብሬ እመለሳለሁ አለ ። እርሱ ግን ፍጡር ሳይሆን ለአዳም ቃል የገባለት ነቢያትን ትንቢት ያናገረ ያለማንም አስገዳጅነት በፍቃዱ ሰው ሆኖ በፈቃዱ መከራ መስቀልን ተቀብሎ ያዳነን አምላክ ነው ። ያለእርሱ አምላክ የለም ነገር ግን በፍቃዱ ሰው ሆነ ። ሰው መሆኑም አምላክነቱን አላስቀረውም ። አምላክ መሆኑም ሰው እንዳይሆን ሊከለክለው አልቻለውም ። ሁሉ በእርሱ ሁሉ ለእርሱ ሁሉም ስለእርሱ ነውና። ነገር ግን ሁሉ በእጁ ተይዞ እያለ ወዶ ፈቅዶ ስለ እኛ ራሱን ደሃ አደረገ ተራበ ተጠማ ከእናቱም ጡት ወተት እየለመነ እንደ ሕፃናት ሥርዓት አደገ ማርና ወተትን በምታፈልቅ ምድር እኛን ሊያኖርን ሽቶ እርሱ በመስቀል ላይ ውኃ ጠማኝ አለ ፣ መራራውን ተጎነጨ ፣ ነገር ግን ሁሉ በፈቃዱ ነው ። ሁሉ በእርሱ ነውና ። ወዶ ፈቅዶ የፈለገውን ሁሉ መሆን የሚችል ደግሞ አምላክ እንጂ ሰው አይደለም ። ሰው ግን እንኳን ሞትን ድል አድርጎ መነሳትና ወደ ሰማይ ማረግ ቀርቶ በፈቃዱ መሞትን ወደ መቃብር መውረድን ቢሆን አይቻለውም። (አውነተኛ ክርስትና ተስፍዬ ምትኩ )


በቀጣይ ክፍል "ኢየሱስ አማላጅ ወይስ ፈራጅ" እናያለን ።


(ዲያቆን ፍፁም ከበደ)

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ የቴሌግራም ቻናል ይከታተሉን ።

https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
ሰይጣን ያደረባት አገር

ዛሬ፥ ሥላሴን የካደች ባቢሎን በሥላሴ የተቀጣችበት ዕለት ነው።
በሰናዖር ሜዳ 43 ዐመታትን የፈጀ፥ 4533 ክንድ የረዘመ ግንብ ተገንብቶ ነበር። ባለመግባባት ፈራረሰ።
ሰዎቹ ትልቅ ግንብ የመገንባት የጋራ ዕቅድ ቢኖራቸውም፥
የጋራ መግባቢያ ግን አልነበራቸውምና።

  ሳይግባቡ ከመዋደድ ተግባብቶ መኳረፍ የተሻለ የሚሆንበት ጊዜ አለ። ቢያንስ ባለመግባባት ተግባብተው በሰላም ይኖራሉና።

ሕንጻው ከፈረሰ በኋላ ሰዎቹም ተበታተኑ።
የአገሪቱም ስም ባቢሎን ኾነ። 'ዝሩት' ማለት ነው። የተበታተነች የፈራረሰች አገር።

ባለራእዩ ዮሐንስ ስለባቢሎን እንዲኽ አለ።
  "ወድቀት ባቢሎን ዐባይ ሀገር ወኮነት ማኅደረ ለአጋንንት፤ ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች የአጋንንት ማደሪያ ሆነች"።
ሊቃውንት ይኽን ሲያብራሩ
"አገር ስትጠፋ #ደባስ የሚባል ጋኔን ያድርባታል" ብለዋል።
ሰይጣን በሰው ከማደር አልፎ አገርንም የሚቆራኝ ከኾነ፥
ምንድነው መፍትሔው?
ታስሮ ወደ ጠበል አይኼድ ነገር፥የታመመው አገር ነው።
በታመመ አገር ውስጥስ ማን ጤነኛ ኾኖ ይኖራል?

ኾኖም፥
ሰዎቿ ተግባብተው በፍቅር የሚጾሙባት የሚጸልዩባት አገር፥ ደባስን አርቃ ከአምላኳ ታርቃ መኖር ይቻላታል።
ማቴዎስ 17:21::


( ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው )

https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
https://t.me/OrthodoxAmero
ሰውየው ከሰው በር ላይ የሆነ ነገር ይሰርቃል ትንሽ ቆይቶ ግን ይጸጸታል ተጸጸቶም አልቀረ የንስሐ አባቱ ዘንድ ሄዶ አባ  ገመድ ከሰው ደጅ ሰርቄያለው ይቅር ይበሉኝ ብሎ ይናዘዛል አባም የንስሐ ኑዛዜውን ተቀብለው ቀኖና ሰተው እግዚአብሔር ይፍታህ ብለው ሸኙት።

በሌላ ጊዜ ሰውየው ተመልሶ መጣ አባ "ምነው መልሰህ በደልክ እንዴ" ሲሉ ጠየቁት ሰውዬውም እየተንተባተበ "አይ አባ የባለፈው ስርቆቴ ነው" አላቸው አባም "ላለፈውማ ቀኖና ሰጥቼ ንስሐ ገብተሃል እግዚአብሔርም ምሮሃል ሂድ" ብለው መለሱት ሰውየውም ቅር እየተሰኘ ሄደ። ነገር ግን ሄዶ አልቀረም ተመልሦ ለሦስተኛ ጊዜ መጣ። አባም ግራ ተጋብተው "አሁንስ ለምን ተመልሰህ መጣህ" ሲሉ ጠየቁት   ሰውየውም በፍርሃት ድምጽ "የ...የባለፈው ገመድ" አላቸው ያኔ አባ አንድ ነገር አስቡና ቀና ብለው በፈገግታ ከተመለከቱት በኋላ "ልጄ ከገመዱ ጫፍ ላይ ምን ታስሮ ነበር?" ብለው ጠየቁት ሰውየውም አንገቱን አቀርቅሮ በቀስታ "በ...በ...በሬ" አላቸው።

እኛስ! ስንቶቻችን በሬ የሚያክል ኃጢያት ሰርተን የገመድ ንሰሐ ገብተን ይሆን? መልሱን ልቦናችን ያውቀዋል።

https://t.me/fire_hymanot