ፍሬ ሀይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት (mana dilbata firee amentaa)
176 subscribers
239 photos
10 videos
23 files
44 links
በዚህ መንፈሳዊ ቻናል የኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሐይማኖታችንን እንድናውቅ የሚረዱ :-

፨ ከተለያዩ መንፈሳዊ ቻናሎች የምናገኛቸውን መረጃዎች አናጋራቹሃለን።

፨ ጥያቄ አና መልስ አንጠያየቃለን።


፨ መንፈሳዊ መፃህፍትን በ አማርኛ ፣ Afaan oromoo አና English language እናካፍላቹሃለን።

ሐሳብ አስተያየት ካላቹ @ye_gebriel ላይ አሳውቁን።
Download Telegram
ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስምህ፡-

“ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! መንፈሳዊ ምስጋና ሁሉ ለአንተ ይገባል፡፡ ዋጋው የማይታወቅ ነጋዴ ገንዘቡን ሁሉ ሰጥቶ የተወዳጀው እውነተኛ ዕንቁ ደንጊያ አንተ ነህ፡፡ ይህንን የዕንቁ ደንጊያ በሰውነታችን ውስጥ ያበራ ዘንድ ደግሞ ዛሬ ለእኛ አድርግልን፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! የተቀደሰው ስምህ የልባችን ደስታ የሰውነታችን ሽልማት ጌጥ ነው፡፡

አቤቱ ምድርንና ዓለሙን ሁሉ ዞርሁ ያለ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በቀር ጣፋጭ ስምን አላገኘሁም፡፡ በምድር ላይ የሚደረግ ረድኤትና ኃይል ሁሉ ያለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በቀር አይሆንም፡፡ እግዚአብሔርን ያገለገሉ የሰው ወገኖች ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኵል ነው፡፡ የከበረና የተመረጠውን እጅ መንሻ ሁሉ ያለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አልተቀበልንም፡፡ ሰማይና ምድር ያለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከሁከት አልጸኑም፡፡

የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከማር ከወለላና ከሦከር ይጥማል፡፡ ማርና ሦከር በሚበሉበት ጊዜ ይጠገባሉ፤ የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ግን አይጠገብም፡፡ የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በምጠራ ጊዜ ከንፈሮቼ ማርን ያንጠባጥባሉ፡፡ ማር፣  ስኳርና እንጀራ ቢሆኑም እንደ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእኔ ዘንድ ጣዕም የላቸውም፡፡ የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይሻለኛልና ከሰማይ በታች ካለ ፍጥረት ሁሉም ይበልጣልና፡፡

ቸርነትህ ብዙ ነው፤ አይነገርምም፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! በሚያምንብህና በሚወድህ አፍ ሁሉ ስምህ የታወቀ ነው፡፡ በሕግ ከታወቁ ምስጋናዎች ሁሉ ከውስጣቸው የሚመስልህ የለም፡፡ የዓይኖቼ ብርሃንና የሥጋዬ ብርታት ከከበረው ስምህ ወገን ነው፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! እስከ ሕይወቴ መጨረሻ የከበረ ስምህን በአንደበቴ ዘወትር የተሾመ አድርገው፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትያን ሰውነት ሁሉ የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ  ስም በአንድነት ያከብራሉ፤ ያመሰግናሉ፡፡

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ከኃጢአት ወገን የሚሆን የክፋት መንፈስን ሁሉ ከእኔ አስወግድ፡፡ መዳኛችን በሚሆን በዚህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ክርስቲያኖች ሁላችሁም ፈጽሞ ደስ ይበላችሁ፡፡

የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም ጣፋጭ ነው፤ በገነት ካለ ፍሬም ይልቅ ይጣፍጣል፡፡ አባታችን ዳዊት በአመሰገነበት በከበረ መዝሙር የጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ስም ፈጽሞ እናመሰግናለን፤ እናከብራለን፡፡

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ብዙ የሆነ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ በእኔ ላይ አሳድር፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! አንተን ደስ የማያሰኝህን ሓሳብ ሁሉ ከእኔ ታርቅ ዘንድ ወዳንተ እለምናለሁ፤ ከአንተም እሻለሁ፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! በጌትነትህ ከእኔ ጋር ቸርነትህን አድርግ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እንሰግድልሃለን! ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እንሰግድልሃለን! መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ሰማያዊ ከሚሆን ከቸር አባትህ ጋራ ማኅየዊ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንሰግድልሃለን፡፡ አሜን!”

(ምንጭ፡ ግብረ ሕማማት)
“መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡” ምሳ. 31፡29

ክርስቶስን ያከበሩ፤ መንገዱን የተከተሉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ እውነትን የመሰከሩ፤ ስለ ቃሉ የኖሩ ብዙ ሴቶች አሉ፤ መስዋዕትነትን የከፈሉ በሰማዕትነት ያለፉ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ታላላቅ የምድር ነገስታትን፤ ታላላቅ ነቢያትን የወለዱ ብዙ ሴቶች አሉ፤ ከነዚህ ሁሉ ግን አንቺ ትበልጫለሽ፡፡

ቅድስት ድንግል ሆይ አንቺ እኮ፡- ሰማይ ዙፋኑ ምድር መረገጫው የሆነ፤ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የሰላም አለቃ፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ ከሆነውም አንዳችም እንኳን ያለርሱ ያልሆነ፤ ዓለምን ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የመለሰ፤ መንበሩን የሚሸከሙ ኪሩቤልና ሱራፌል የሚንቀጠቀጡለት፤ የሁሉ ፈጣሪ፤ የሁሉ አምላክ እናት ነሽ፡፡ በፊትም አሁንም ወደፊትም ካንቺ በቀር ፈጣሪዋን ልጄ ብላ የምትጠራ ሴት አልነበረችም፤ የለችም፤ አትኖርምም ክርስቶስም እናቴ ብሎ የሚጠራት ብቸኛዋ ሴት አንቺ ነሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡

እናት ስትሆኝ ድንግል፤ ድንግል ስትሆኝ እናት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ ትውልድ ሁሉ ብጽዕት ብሎ የሚጠራሽ ብቸኛዋ ሴት በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ እግዚአብሔር መርጦና ጠብቆ ያስቀረሽ ዘር በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡ ለዓለም ሁሉ ድህነት ምልክት የሆንሽ በእውነት ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡

እናቴ ሆይ እንግዲህ እኔ ምን ልናገር? ሺህ ቃላትን ብደረድር ያንቺን ክብር ልገልፀውስ እንደምን እችላለው? አዎ አሁንም እላለሁ “መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ፡፡” ምሳ. 31፡29
የቅድስት ድንግል ማርያም በረከቷ በሁላችን ላይ ይደር፤ ምልጃ ቃል ኪዳኗ ይጠብቀን፡፡ አሜን!!!👉🙏🙏

ለማንኛዉም አስተያየትዎ @menfesawimekerbot ይፆፋልኝ ይደርሰኛል::
@menfesawimeker
@menfesawimeker
ቅዱሳን መላእክት ለሰዉ ልጆች ድኅነት እጅግ የሚጓጉ
ከእግዚአብሔር የተሰጡ ጠባቂዎቻችን ናቸዉ። እርግጥ ነዉ፤ በመጀመሪያ እኛም እንደ መላእክት
ክብሩን ለመዉረስ ስሙን ለመቀደስ የተፈጠርን ነበርን
ግንኙነታችንም እነርሱ ከእኛ ቀድመዉ በመፈጠራቸዉ
ታላላቅ ወንድሞቻችን ናቸዉ። ከሰዉ ልጅ ዉድቀት
በኋላ ግን ነገሮች ተለወጡ። በእኛ የባህርይ መጎስቆል
ምክንያት ታላቅ ወንድም የታመመ ታናሹን እንደሚጠብቅ ጠባቂዎቻችን ሆኑ።

ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እንዳለዉ፦ የሰዉ ልጅ
ከመላእክት ጋር ክቡር ሆኖ ሲፈጠር፤ ጠባቂን
አይሻም ነበር፤ ሰዉ በኃጢአት ከወደቀ በኋላ ግን
እግዚአብሔር መላእክትን ጠባቂ አደረገለት።
ምክንያቱም ዲያብሎስ ሰዉን ለማጥፋት ሁል ጊዜ
ምክንያቶችን ስለሚፈልግ ነዉ።

እነዚህ መላእክት ከጠባቂነታቸዉ ባሻገር ለሰዉ ልጅ
መዳን እጅግ የሚጓጉ ሰዉን ወዳጆች ናቸዉ። አምላክ
ሰዉ ሆኖ በተወለደበት በዚያች ምሽት ሲዘምሩ
ያደሩት በአምላክ ሰዉ መሆን የሚያገኙት ጥቅም ኖሮ
ሳይሆን ለሰዉ ልጅ መዳን ካላቸዉ ፍላጎትና ፍቅር
የተነሳ ነዉ። በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን
በምድርም ሰላም የሚለዉ ዝማሬያቸዉ የእኛ ሰላም
ለእነርሱ ምስጋና ምክንያት መሆን የሚያሳይ ምስጋና
ነበር። ሉቃ 2:14

የማያገቡትና የማይጋቡት እነዚህ መላእክት በሰማይ
የሰርግ ያህል ደስ የሚሰኙት በምድር አንድ ኃጢአተኛ
ንሰሓ ሲገባ መሆኑ ምን ያህል የእኛ ወዳጆች
መሆናቸዉን ያሳያል ሉቃስ15;10።

ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ የተላኩ ስላላቸዉ ለማገዝ
የሚላኩ መናፍስት አይደሉምን?

ምንጭ ኢትዮጵያዊዉ ጃንደረባ በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ'
+ ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል +

ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታምሞ ተኝቶአል:: ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጠይቀው መጣ:: ሆኖም እንደ ልማዱ እግዚአብሔር ይማርህ አላለውም:: ለጆሮ የሚከብድ ቃል ጥሎበት ወጣ:: "ትሞታለህና ቤትህን አስተካክል!"

ነቢዩ ይህንን ብሎት ከወጣ በኁላ ሕዝቅያስ ወደ ግድግዳው ዞሮ ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ:: አምላኩ በንግግር ብዛት የሚሰማ አምላክ አይደለምና ፊቱን ወደ መቅደሱ አቅጣጫ አዙሮ አለቀሰ::

ከጥቂት ደቂቃ በኁዋላ ነቢዩ ኢሳይያስ ሌላ መልእክት ይዞ ተመለሰ:: እግዚአብሔር እንዲህ ይላል :- ጸሎትህን ሰምቻለሁ ዕንባህን አይቻለሁ በዕድሜህ ላይ ዐሥራ አምስት ዓመት እጨምራለሁ" (ኢሳ 38:5)

ሕዝቅያስ ቤትህን አስተካክል ከተባለ በኁዋላ ፊቱን አዙሮ ከማልቀስ በቀር ምንም አላደረገም:: ሕዝቅያስ ሆይ ከአልጋህ ሳትወርድ ያስተካከልከው ቤት ምን ዓይነት ቤት ነው? ለባሪያዎችህ መመሪያ ሳትሠጥ የምታስተካክለው ቤትስ እንዴት ያለ ነው? በደቂቃዎች ውስጥ ትሞታለህ ከተባልክ በኁዋላ ዐሥራ አምስት ዓመት ያስጨመረልህ ምን ዓይነት ማስተካከያ አድርገህ ነው? ለእኛም ንገረንና ዕድሜ እናስጨምር::

ሕዝቅያስ ከአልጋው ሳይነሣ ያስተካከለው ቤቱ ልቡ ነበር::
ልብህን ካስተካከልህ ቤትህ ይስተካከላል:: እግዚአብሔር እንደሆን ትሞታለህ ቢልህም መሞትህን አይፈልግም:: እርሱ ከኃጢአትህ እንጂ ካንተ ጋር ጸብ የለውም::

"በውኑ ኃጢአተኛ ይሞት ዘንድ እፈቅዳለሁን? ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዱስ ይመለስና በሕይወት ይኖር ዘንድ አይደለምን?" ይላል መሐሪው (ሕዝ 18:23)

እርሱ ትሞታለህ የሚልህ መኖርህን ፈልጎ ነው:: አንዴ ብያለሁ ብሎ አይጨክንብህም:: በንስሓ ተመለስ እንጂ ምሬሃለሁ ለማለት ይቸኩላል:: አሁን ትሞታለህ ብዬው አሁን ትድናለህ ብለው ይንቀኛል ሳይል ተመልሶ ይምርሃል:: ኃጢአትህንም ወደ ጥልቁ ይጥለዋል:: በጎ እንድትሠራም ዕድሜ ይጨምርልሃል:: አንተ ብቻ ተመለስና አሁኑኑ ንስሓ ግባ::

ከበደል አልጋ ጋር ያጣበቀህን ፈተናም ድል መንሻው ጊዜ አሁን ነው:: ሕዝቅያስ በደቂቃ ዕንባ ምሕረት አግኝቶ ዕድሜ ካስጨመረ በዐቢይ ጾም ሙሉ የሚያለቅስ ምን ያህል ዕድሜ ያገኝ ይሆን?

ወዳጄ አንተም ተነሣና በዚህ ወር ቤትህን አስተካክል::
እንደ ሕዝቅያስ ፈጣሪህ ይጠብቅሃል:: የተቀየምከውን ይቅር በል የበደልከውን ካስ የሚበቀልህን የማይተኛ ጠላትህን ዲያቢሎስ ተበቀለው::

ጾም ዲያቢሎስ ድል የተደረገበት የጦር ዐውድማ ነው:: በዚህ ወራት ድል ያላደረግነውን ፈተና በሌላ ጊዜ አናደርገውም:: ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል እንደሚባለው በጾም የተኛ ክርስቲያን መቼም አይነቃም:: በጾም ያልተገራ አንደበት መቼም አይገራም:: በጾም ያልተፈወሰ ቂም መቼም አይፈወስም::

ጌታችን በወንጌል አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥል ጋኔን ያለበትን ልጅ ሲፈውስ "ይህ ዓይነቱ ጋኔን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም" ብሎ ነበር:: ሀገራችንን አንዴ ወደ እሳት አንዴ ወደ ውኃ የሚጥላት የጥላቻ ጋኔንም ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም::

ወዳጄ ከቁስልህ የምትፈወስበት ወር እንደደረሰ ዕወቅ:: አንተስ ብትሆን ልትላቀቀው እየፈለግህ ያቃተህ ክፉ ልማድ የለብህም:: እንደ ቅዱስ ጳውሎስ "የምፈልገውን መልካም ነገር አላደርግም የማልፈልገውን ክፉ ነገር ግን አደርጋለሁ:: ምንኛ ጎስቋላ ለዚህ ለሞት ከተሠጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" ብለህ ምርር እንድትል ያደረገህ ኃጢአት የለም? እንግዲያውስ እወቀው:: ይህ ዓይነቱ ወገን ያለ ጾምና ጸሎት አይወጣም:: ይህ ጾም ቁስል የሚሽርበት ጾም ነው:: ይህ ጾም ሸክም ማራገፊያ ጾም ነው:: እንደ ሕዝቅያስ በዚህ ወር ቤትህን በንስሓ አስተካክል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
#ቅዱስ_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ (ሐምሌ 5)

ሐምሌ አምስት በዚች ቀን የክቡራንና የዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት #የቅዱስ_ጴጥሮስ እና #የቅዱስ_ጳውሎስ የሰማዕትነታቸው መታሰቢያ ነው።

#ቅዱስ_ጴጥሮስ

ጴጥሮስ ማለት ዓለት ማለት ነው፡፡ ማቴ. 16፥18 በዕብራይስጥ ኬፋ ይለዋል፡፡ የመጀመሪያ ስሙ ስምዖን ነው፤ ትውልዱም ከነገደ ሮቤል ነው፡፡ አባቱ ዮና ይባላል፡፡ የተወለደው በገሊላ አውራጃ በቤተ ሳይዳ ነው፡፡ ጴርቴዋ የምትባል ሚስት ነበረችው የሚተዳደረው ዓሣ በማጥመድ ነበር፡፡ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር ዓሣ ከሚያጠምድበት ተጠርቶ ሐዋርያ ሆኗል፡፡ ማቴ. 4፥19

ጴጥሮስ የዋህ፣ ፈጣን ቁጡ ነበር፡፡ የዋህነቱ ጌታ በባሕር ላይ ሲሄድ አይቶ ጌታ አንተስ ከሆንክ ወደ አንተ እንድመጣ አሰናብተኝ ብሎ በባሕር ላይ ሲሄድ በመሞከሩ ማቴ. 6፥45፣ ፈጣንነቱ ጌታ ደቀመዛሙርቱን በቂሣርያ ሰዎች ማን ይሉኛል ብሎ ጠይቋቸው ሙሴ ነው፣ ኤልያስ ነው ይሉሃል ባሉትና እርሱም መልሶ እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ ጴጥሮስ ፈጥኖ አንተ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ  ክርስቶስ ነህ ብሎ በመመለሱ ማቴ. 16፥16 ቁጡነቱም አይሁድ ጌታን በያዙት ጊዜ ተቶጥቶ የማልኮስን ጆሮ በሰይፍ በመቁረጡ ዮሐ. 18፥10 ላይ ያስረዳል፡፡ መዋዕለ ስብከቱ 50 ዓመት ነው፡፡ /ገድ ሐዋ፣ ዜና ሐዋ/

ንጉሡ ኔሮን ቄሣር መምለኬ ጣዖት ነበረና በሃይማኖት ምክንያት አስሮት ነበር፡፡ አካይያ ዘምቶ ጠላቱን ድል ነሥቶ ሲመለስ ለጣዖት ስገድ ቢለው አልሰግድም አለ፡፡ በችንካር ተቸንክሮ በመስቀል ተሰቅሎ ይሙት ብሎ ፈረደበት ከዚህ በፊት አሕዛብ ሊጣሉት ሲነሱ ወደ ጌታ ሲያመለክት እሳት ከሰማይ ወርዳ ታጠፋለት ነበር አሁንም እሳት ከሰማይ ወርዳ ትብላቸው ብሎ ወደ ጌታ ቢያመለክት ጌታ በመስቀል ተሰቅሎ ታየው ዳግመኛ በሮም ሰቀሉህን? አለ አንተ ብትፈራ እንጂ ነዋ አለው፡፡ ፈቃድህስ ከሆነ ብሎ እንደ ጌታዬ አቁማችሁ ሳይሆን ቁልቁል ዘቅዝቃችሁ ስቀሉኝ አላቸው በራሱ ዘቅዝቀው ሰቅለውታል፡፡ ዕረፍቱ በዚህች ሐምሌ 5 ቀን ይታሰባል፡፡ ሥጋውንም ደቀመዝሙሩ መርቄሎስ ከመስቀሉ አውርዶ በወተት በወይን አጥቦ ሽቶ ቀብቶ በነጭ ሐር ገንዞ እንዳይፈርስ በማር በተመላ ሣጥን አድርጎ ቀብሮታል፡፡

#ቅዱስ_ጳውሎስ

ጳውሎስ ማለት ንዋይ ኅሩይ (የተመረጠ ዕቃ) ማለት ነው፡፡ ሐዋ.9፥15 አንድም ብርሃን ማለት ነው፡፡ አንድም መድቅሕ ማለት ነው፡፡ ደንጊያ በመዶሻ ተጠርቦ ለሕንፃ ሥራ እንዲውል አሕዛብም በእርሱ ትምህርት ታንፀው ለገቢረ ጽድቅ ይበቃሉና የመጀመሪያ ስሙ ሳውል ነው፤ ሳውልም ማለት ጸጋ እግዚአብሔር ማለት ነው፡፡ ትውልዱ ከነገደ ብንያም ማለት ነው፡፡ ፊል. 3፥5 አባቱ ዮስአል ይባላል፡፡ የተወለደው ጌታ በተወለደ በ5 ዓመት በጠርሴስ ነው፡፡ ከ15 ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም ከመምህር ገማልያል ሕገ ኦሪትን መጻሕፍተ ነቢያትን ሲማር አድጓል፡፡ ሐዋ. 22፥3 ለሕገ ኦሪት ቀናዒ ከመሆኑ የተነሣ ክርስቶስን ዕሩቅ ብእሲ ወንጌልን ዲቃላ ሕግ እያለ ሐዋርያትን ይቃወም ምእመናንን ያሳድድ ነበር፡፡ በወንጌል ያመነው ጌታ በዐረገ በ8ኛ ዓመት ነው፡፡ ምዕመናንን ለማሳደድ ከሊቀ ካህናት የሹመት ደብዳቤ ተቀብሎ ወደ ደማስቆ ሲሄድ መብረቅ ጣለበት፤ ደንግጦ ወደቀ ወዲያውም ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ የሚል ድምጽ ሰማ፡፡ አንተ ማነህ አለ ምእመናንን ከዋሉበት አላሳድር ካደሩበት አላውል የምትልብኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ፣ ሰይፍ ቢረግጡት የረገጠው ሰው እንጂ ሰይፉ ይጎዳልን፣ አንተስ እኔን ብትክድ ምእመናንን ብታሳድድ አንተ እንጂ እኔ እጎዳለሁን አለው፡፡ አሁን ምን ላድርግ አለው ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባ የምታደርገውን ይነግሩሃል አለው፡፡ ከእርሱ ጋር የነበሩም ድምጹን ይሰማሉ መልኩን ግን አላዩም፤ ከወደቀበት ተነሥቶ ዓይኑ ጠፍቷልና ሰዎች እየመሩት ቤተ ይሁዳ አደረሱት እኅል ውኃ ሳይቀምስ 3 ቀን ውሎ አድሯል፡፡ ሐናንያ በደማስቆ ይኖር ነበርና ጌታ በራዕይ ታይቶት ጳውሎስን አጠመቀው፡፡ ሐዋ. 9፥1-19

በ69 ዓ.ም ሮም ገብቶ ሲያስተምር ንጉሡ ኔሮን ቄሣር አሥሮት ነበርና አካይያ ዘምቶ ጠላት ድል ነሥቶ ሲመለስ ጥሩት አለ፤ መስቀሉን በእጁ ይዞ ቀረበ፤ ተቆጥቶ በሰይፍ ቅጡት አለ፤ እንደ በግ እየነዱ ሲወስዱት የንጉሡ ልጅ አገኘቻቸው፤ አምና ነበርና መጎናጸፊያሽን ስጪኝ አላት ሰጠችው በዚያ ሸፋፍነው ሰይፈውታል፡፡ ደሙም ሰማየ ሰማያት ወጥቶ ቀተሉኒ በዓመጻ እያለ ተካሷቸዋል፡፡ እሱን ገድለው ሲመለሱ የንጉሥ ልጅ አገኘቻቸው ጳውሎስስ? አለቻቸው፡፡ በልብስሽ ሸፋፍነን በሰይፍ ገደልነው አሏት፡፡ ልብሴን መልሶልኝ ከጴጥሮስ ጋር አሁን በዚህ ሲያልፍ እያየሁት ገደልነው ትሉኛላችሁን አለቻቸው ልብሷን አይተው አምነዋል፡፡ ተቆርጦ የወደቀ ራሱንም ከአንገቱ ቢያጋጥሙት እንደ ቀድሞው ሆኖላቸው ቀብረውታል፡፡ ዕረፍቱ በዚች ሐምሌ 5 ይታሰባል፡፡

የቅዱሳን አባቶች ጸሎታቸው በረከታቸው በሁላችን ላይ ይደር፡፡

👇👇
ለመቀላቀል
     @Mezmure_tewahdo
     @Mezmure_tewahdo
  
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊
#ሐምሌ_7 እንኳን አደረሳችሁ ✝️🙏

#ቅድስት_ሥላሴ

ሐምሌ ሰባት በዚች ቀን ሥሉስ ቅዱስ በአብርሃም ቤት የተገለጡበት ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም በአካል በግብር ሦስትነት በባሕርይ በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ተገኙ፣ በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና፡፡ ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት ‹‹ቅድስት ሥላሴ›› እንላቸዋለን፡፡ የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም፡፡ የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል፣ በቤቱም መጥተው ያድራሉ፡፡ ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም፡፡ አባታችን ቅዱስ አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል፡፡

አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኳናቸው አስተናገዱ፡፡ አብርሃም እግራቸውን አጠበ፡፡ በጀርባውም አዘላቸው፡፡ ምሳቸውንም አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም እንደሚበሉ ሆኑለት፡፡ በዚያው ዕለትም የይስሃቅን መወለድ አበሠሩት፡፡ አብርሃም ከደግነቱና እንግዳ ከመውደዱ የተነሣ በተመሳቀለ ጎዳና ላይ ድንኳን ሠርቶ የወጣ የመረደውን፣ የመጣ የሄደውን ሁሉ እየተቀበለ እግዚአብሔርን እያገለገለ የሚኖር ጻድቅ ነበር፡፡ ለዚህም ነው አብርሃም በወይራ ግራር (በመምሬ) ዛፍ ሥር ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር አንድነቱን ሦስትነቱን የገለጠለት፡፡ ዘፍ 18፡1-25፣ ሮሜ 4፡-3፡፡ ቀትር ሰዓት ላይ በድንኳኑ ደጅ ተቀምጦ እንግዳ ሲጠብቅ እግዚአብሔር ታየው ተነጋገረው፡፡ አንገቱን ቀና አድርጎ ዐይኑን አራምዶ በተመለከተ ጊዜ እነሆ ሦስት ሰዎች ከበላዩ ባለ ተራራ ላይ ቆመው አያቸው፣ ወደ እርሱም ሲወርዱ አይቶ ፈጥኖ ሄዶ ከሰግደላቸው በኋላ ‹‹አቤቱ በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ፤ ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ…›› እያለ በትሕትና በመጋበዝ ወደ ድንኳኑ አስገብቶ በሚገባ ጋበዛቸው፡፡ ‹‹በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ›› ብሎ አንድነታቸውን፣ ‹‹ጥቂት ውኃ ይምጣላችሁ እግራችሁን ታጠቡ›› ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡

ያች ሥላሴ የገቡባት የአብርሃም ድንኳን የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡፡ ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ሁሉ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም አብ ለአጽንዖ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋዋን ለመዋሐድ የማደራቸው ምሳሌ በመሆኑ አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ናት፡፡ ሉቃ 1፡35፡፡

እግዚአብሔርም አብርሃምን የዛሬ ዓመት ልጅ እንደሚወልድ ነግሮት በዓመቱ ይስሐቅን ወልዷል፡፡ ሁለቱ ሰዎች ከአብርሃም ድንኳን ወጥተው ወደ ሰዶም ወደ ገሞራ ሄዱ፣ አብርሃምም ይሸኛቸው ዘንድ አብሯቸው ሄደ፡፡ የሄዱትም ሁለቱ ሰዎች አብና መንፈስ ቅዱስ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዱ ወልድ በአብርሃም ቤት ቀርቷል ይኸውም ከቤተ አብርሃም ሰው እንደሚሆን ለማጠየቅ ነው፡፡ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ፡፡ እግዚአብሔርም የሚሠራውን ሁሉ ከአብርሃም አይሠውርም ነበርና የሰዶምን የገሞራን ጥፋት ነገረው፡፡ አብርሃምም ይቅር እንዲላቸው አብዝቶ ለመነላቸው፡፡ ሥሉስ ቅዱስን የአብርሃሙ ሥላሴን በምግባር በሃይማኖት ሆነን እናገለግል ዘንድ የቅዱሳኑ ጸሎት አይለየን
#ሰውን_የሚጥለው_መመካቱ_ነው

#ወንድሜ ሆይ በሥራህ ሁሉ የታመንህ ሁን አገልጋይ ባልንጅሮችህን ውደዳቸው። ንጹሑን አረጋዊ መቼም መች አክብረው።

#ወንድሜ ሆይ በታላላቆች መሃል አትቀመጥ። ተቀመጥ እስኪሉህ ድረስ ቁም እንጅ በሽማግሌዎች መካከል አትቀመጥ፤ በዝቀተኛው ማዕርግ ተቀመጥ እንጅ።

#ወንድሜ ሆይ ቁጡ ወይም አንጎራጓሪ አትሁን፤ በጸሎት ጊዜ ሐኬተኛ አትሁን፤ በጸሎት ጊዜ ምንም ተግባር ለመፈጸም ወዲያና ወዲህ አትናወጽ። እንዳትዋረድ በሊቅ በአዋቂ መሃል አትናገር።

#ልጄ ሆይ በጽድቅህ አትመካ፤ ራስህን አታመስግን፤ ሰይጣን ትምክሕትን እንዳያመጣብህ ራስህን በፈቃድህ አዋርድ እንጅ። በትዕቢትና ትምክሕት ሰዶምና ገሞራ ወደቁ። ከእግዚአብሔር መንገድም ተሰናከሉ። ትምክሕተኛውን መነኩሴ ፈተና ያገኘዋል፤ መንፈስ ቅዱስም ይለየዋል፤ የዲያብሎስ መንፈስም ያድርበታል። በሥራችሁ ሁሉ አትመኩ፤ ሁሉም ሰው እግዚአብሔር የሰጠውን ይሠራል እንጅ ከራሱ የሆነ ምንም የለምና። ነቢይ የተናገረውን አልሰማችሁምን? ፈጽማችሁ አትመኩ ታላላቅ ነገርንም አትናገሩ፤ ክፉ ነገርም ከአንደበታችሁ አይውጣ።

 ፍሬ ሀይማኖት
አዎን አቤቱ የሁሉ አምላክ ነህ፤
አዎን አቤቱ የሁሉ ንጉሥ ነህ፤
አዎን አቤቱ ሁሉን የያዝክ ነህ፤
አዎን አቤቱ ሁሉን የምትገዛ ነህ፤
አዎን አቤቱ ሁሉን የምታድን ነህ፤
አዎን አቤቱ በእውነት የሁሉ ገዢ ነህ፤
አዎን አቤቱ የሁሉ መድኀኒት ነህ፤
አዎን አቤቱ ሁሉን የምትጠብቅ ነህ፤
አዎን አቤቱ ሁሉን የምትመግብ ነህ።

የልጅህን ሥጋ ከእኛ ሥጋ ጋር አንድ እንዳደረግህ፤ የአንተን መሲሕ ደምም ከእኛ ደም ጋር አንድ እንዳደረግህ እንዲሁ አንተን መፍራትን በልቡናችን፤ በጎ አምልኮትንም በሕሊናችን ጨምር።

ሥጋውያን የምንሆን እኛ ግን የሥጋን ሕግ እናስባለን፤ የሥጋንም ሥራ እንሠራለን፤ በሥጋም መንገድም እንሄዳለን። አንተ ግን የመንፈስን ሥራ አስተምረን፤ የመንፈስንም ሕግ አስረዳን፤ የመንፈስንም መንገድ ምራን።

እኛን ኃጥአንን ብትምረን ያን ጊዜ መሐሪ ትባላለህና። ጻድቃንን ግን ከሥራቸው የተነሳ ትምራቸዋለህ፤ እንደ ጽድቃቸውም ትሰጣቸዋለህ።

የቀደመ በደላችንን አታስብብን፤ አቤቱ ይቅርታህ ፈጥኖ ይደረግልን። ወደ አንተ እንጮሃለን፤ ወደ አንተ እናለቅሳለን፤ ወደ አንተ እንማልላለን ለዘለዓለሙ አሜን።

✟ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ✟

ለሌሎችም እንዲደርስ በየግሩፑ #Share አደሩጉው !

@Orthodox_sibket

  @Orthodox_sibket

@Orthodox_sibket
††† እንኳን ለታላቁ ሊቅና አፈ በረከት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ †††

††† እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ቅዱስ ኤፍሬም የተወለደው ንጽቢን በምትባል የሶርያ ግዛት ውስጥ በ298 / 306 ዓ/ም ነው:: ወላጆቹ በክርስቶስ የማያምኑ አላውያን ነበሩ:: (ምንም አንዳንድ ምንጮች ክርስቲያኖች ነበሩ ቢሉም)

ቅዱሱ ተወልዶ ባደገባት ንጽቢን ጵጵስናን የተሾመ ቅዱስ ያዕቆብ የሚባል ታላቅ ሰው ነበር:: የሰማዕትነት: የሐዋርያነት: የጻድቅነትና የሊቅነት ግብር ያለው አባት ነው:: ታዲያ ቅዱስ ኤፍሬም ይሔ አባት ሁሌ ሲያስተምር ይሰማው ነበርና በስብከቱ ተማርኮ ደቀ መዝሙሩ ለመሆን በቃ::

ቅዱስ ኤፍሬም በቅዱስ ያዕቆብ እጅ ከተጠመቀ በኋላ ሙሉ የወጣትነት ጊዜውን ያሳለፈው በትምሕርት ነው:: የሚገርመው መምሕሩ ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን እመቤታችን ድንግል ማርያምን በፍጹም ልቡ የሚወድና ጠርቷት የማይጠግብ አባት ነውና ለልጁ ለቅዱስ ኤፍሬም ይሕንኑ አጥብቆ አስተምሮታል::

ቅዱስ ኤፍሬም ክርስትናን ሲመረምር የእመቤታችን ፍቅር ይበዛለት ጀመር:: ምክንያቱም እመ ብርሃንን ሳይወዱ ክርስትና የለምና:: እንደ እርሱ የሚወዳት የለም እስኪባል ድረስ ያገለግላት: ይገዛላትም ገባ::

እንዲህ እንደ ዛሬ የድንግል ማርያም ምስጋና በአንደበት እንጂ በመጽሐፍ አይገኝም ነበር:: እርሱ ግን ከወንጌለ ሉቃስ በስድስተኛው ወርን (ይዌድስዋን) እና ጸሎተ ማርያምን(ታዐብዮን) አውጥቶ በየዕለቱ በዕድሜዋ ልክ ስልሳ አራት ስልሳ አራት ጊዜ ያመሰግናት ነበር::

በእንዲህ ያለ ግብር እያለ አርዮስ በመካዱ እርሱን ለማውገዝና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ለማጽናት በ317 (325) ዓ.ም ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ሊቃውንት በኒቅያ ሲሰበሰቡ አንዱ መምሕረ ኤፍሬም ቅዱስ ያዕቆብ ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱስ ኤፍሬም ከሊቃውንቱ ትምሕርትና በረከትን አግኝቷል::

ከጉባዔ መልስ መንገድ ላይ በራዕይ የብርሃን ምሰሶ አይቶ "ጌታ ሆይ! ምንድን ነው?" ብሎ ቢጠይቅ "ይሕማ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ነው::" አለው:: እርሱም መምሕሩን ቅዱስ ያዕቆብን ተሰናብቶ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ (ቂሣርያ) ወረደ:: ተገናኝተውም በአንድ ሌሊት ቋንቋ ተገልጦላቸው ሲጨዋወቱ አድረዋል::

በቦታው ብዙ ተአምራት ተደርጓል:: ቅዱስ ኤፍሬም ከታላቁ ባስልዮስ ከተማረ በኋላ ሃገረ ስብከት ተሰጥቶት ያስተምር ጀመር:: ሁል ጊዜ ታዲያ ጸሎቱ ይሔው ነበር:: "እመቤቴ ሆይ! ምስጋናሽ እንደ ሰማይ ከዋክብት: እንደ ባሕር አሽዋ በዝቶልኝ: እንደ እንጀራ ተመግቤው: እንደ ውኃ ጠጥቼው: እንደ ልብስም ተጐናጽፌው" እያለ ይመኝ ነበር::

አፍጣኒተ ረድኤት: ፈጻሚተ ፈቃድ እመ ብርሃንም በገሃድ ተገልጻ የልቡን ፈቃድ ፈጸመችለት:: ዛሬ ጸጋ በረከት የምናገኝበትን ውዳሴ ማርያምን ደረሰላት:: ሲደርስላትም እርሷ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላ ወርዳ: በፊቱም ተቀምጣ ሲሆን እርሱ ደግሞ ባጭር ታጥቆ: በፊቷ ቆሞ: በመንፈስ ቅዱስም ተቃኝቶ ነው::

ውዳሴዋን በሰባት ቀናት ከደረሰላት በኋላ በብርሃን መስቀል ባርካው: ሊቀ ሊቃውንትም እንዲሆን ምሥጢር ገልጣለት ዐረገች:: ከዚህ በኋላ በምሥጢር ባሕር ውስጥ ዋኝቶ አሥራ አራት ሺህ ድርሰቶችንም ደርሷል:: ዛሬ ሶርያ ውስጥ የምንሰማውን ዜማም የደረሰው ይህ ቅዱስ ነው::

እንዲያውም አንድ ቀን የምሥጢር ማዕበል ቢያማታው "አሃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ" ብሎ ጸልዩዋል:: (የጸጋህን ማዕበል ያዝልኝ) እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በመጨረሻ ሕይወቱ ተክሪት በምትባል ሃገር ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ ተሹሟል::

በጣፋጭ ስብከቱ ብዙዎችን ካለማመን መልሷል:: የምዕመናንንም ሕይወት አጣፍጧል:: ለመናፍቃንና ለአርዮሳውያን ግን የማይጋፉት ግድግዳ ሆኖባቸው ኑሯል:: በዘመኑም ብዙ ተጋድሎ አፍርቷል:: ተአምራትንም ሠርቷል:: በተወለደ በስልሳ ሰባት ዓመቱ በ365 (373) ዓ.ም ዐርፎ ተቀብሯል::

††† ቅዱሱ ለሶርያ ብቻ ሳይሆን እመቤታችንን ለምንወድ የዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ ሞገሳችን ሆኗል:: ስለዚህም እንዲህ እያልን እንጠራዋለን:-
1.ቅዱስ ኤፍሬም
2.ማሪ ኤፍሬም
3.አፈ በረከት ኤፍሬም
4.ሊቀ ሊቃውንት ኤፍሬም
5.ጥዑመ ልሳን ኤፍሬም
6.አበ ምዕመናን ኤፍሬም
7.ርቱዐ ሃይማኖት ኤፍሬም . . . አባታችን አንተ ነህ::

††† ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ለቅዱስ ኤፍሬም የሰጠሽውን ጸጋውን: ክብሩን: አእምሮውን: ለብዎውን በልቡናችን ሳይብን: አሳድሪብን . . . አሜን::

††† ጴጥሮስ ወጳውሎስ †††

††† ዳግመኛ በዚህ ቀን ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ይታሠባሉ::

ቅዱሳኑ ሶርያ አካባቢ ውስጥ ወደምትገኝ አንዲት ሃገር ገብተው ሕዝቡን ከንጉሣቸው ጰራግሞስ ጋር አሳምነው አጥምቀዋል:: ነገር ግን እነርሱ ሲወጡ ሰይጣን አስቶት አጥፊ ሰው ወደ መሆን ተመልሶ ንጉሡ ሐዋርያትን አሰቃይቷቸዋል::

ስለ ቅዱሳኑ ግን ፈረሶቹ ሰግደው: በሰው አንደበት ቅድስናቸውን መስክረዋል:: በመጨረሻም ንጉሡን ከነ ሕዝቡና ሠራዊቱ በዓየር ላይ ሰቅለው ንስሐ ሰጥተውታል:: በእነዚህ ተአምራትም ሁሉም አምነው ለከተማዋና ለሕዝቡ ድኅነት ተደርጓል::

††† ከአባቶቻችን አበው ሐዋርያት በረከት ይክፈለን::

††† ሐምሌ 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
2.ብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ
3.አባ ሓርዮንና ደቀ መዛሙርቱ (ሰማዕታት)
4.አባ ፍሬምናጦስ መስተጋድል

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
2.ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) ሰማዕት
3.ቅድስት እንባ መሪና
4.ቅድስት ክርስጢና

††† "ለምኑ ይሰጣችሁማል:: ፈልጉ ታገኙማላችሁ:: መዝጊያ አንኳኩ ይከፈትላችሁማል:: የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና:: የሚፈልገውም ያገኛል:: መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል::" †††
(ማቴ. ፯፥፯)

††† "የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም::" †††
(መዝ. ፴፯፥፴)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
​​#ቅዱስ_ገብርኤል

እንኳን ለታላቁ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!!

በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል ነው፡፡ ይህ ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት እየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከሞት አደጋ እንደታደገበት የሚታሰብበት ዕለት ነው። የሐምሌ 19 ስንክሳርና የሐምሌ ወር ድርሳነ ገብርኤል እንዲህ ተርከውታል፡፡

በዘመነ ሰማእታት ከሐድያን ነገሥታትና መኳንንት በክርስቲያኖች ላይ መከራ አጽንተውባቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙዎች ሰማእትነትን ሲቀበሉ የተቀሩት አገር ጥለው ተሰደዱ። እየሉጣም የሦስት ዓመት ህፃን የነበረውን ቅዱስ ቂርቆስን ይዛ ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኮንን አገኘችው ሰዎችም ነገር አሰሩባት ወደእርሱ አስቀረባት እና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ህፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እሱን ጠይቅ አለችው፡፡

ህፃኑም ወዳለበት ጭፍራውን ልኮ ወደእርሱ አስመጣው ህፃኑም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ህፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው፡፡ ህፃኑም መልሶ አዎ ለኔ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ሐዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፡፡ መጻሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏል እና አለው፡፡ እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስካስደነገጣቸው ድረስ ንጉሱን መኳንንቱንና ጣኦታቱን ረገማቸው፡፡ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ፡፡

መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በያይነቱ በሆነ ስቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው እናቱንም ከእርሱ ጋር አሰቃያት፡፡ እግዚአብሔርም ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር፡፡ ብዙዎች አህዛብም ይኸንን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማእትነት አረፉ፡፡ የሰማእትነትንም አክሊል ተቀበሉ፡፡ በህፃኑም ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት፡፡ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው፡፡

መስፍኑም በውስጡ ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ የዶሮ ማር፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨምራችሁ ታላቅ የብረት ጋን አንጡልኝ ብሎ ጭፍሮቹን አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮቹም እንዳዘዛቸው ካአደረጉ በኋላ ያዘዝከንን ሁሉ ፈጽመን እሳቱ ነዶ ፈልቷል፡፡ ድምፁ እንደነጐድጓድ ይጮኸል ወላፈኑም እንደጸሐይ ነጸብራቅ በሩቁ ይጋረፋል፡፡ የፍላቱም ኃይል በ14 ክንድ ያኽል ከፍታ ወደ ላይ ይዘላል፡፡ እንግዲህ በውስጡ የሚጣሉትን እዘዝ አሉት በዚህ ጊዜ ህፃን ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ በክርስቶስ ስም ስለሚያምኑ አስረዋቸው ነበርና ከፍላቱ ሊጨምሯቸው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡

በዚያም ፍላቱ ወደላይ በሚዘል ብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው የነዚህን ቅዱሳን አሟሟት ያዩ ዘንድ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ቅድስት እየሉጣ የፍላቱን ጩኸት በሰማችና ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተዘጋጅቶላት ከነበረው ክብር ልታፈገፍግ ሞከረች፡፡ ልጇ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናት ሆይ ከዚህ የብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ ድንጋጼም አይደርብሽ አናንያንና አዛርያን ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከእቶነ እሳት እንዳወጣቸው ሁሉ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ሊያወጣን ችሎታ ያለው መሆኑን አትጠራጠሪ፡፡

እናት ሆ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ጭንቅና መከራ ለመዳን ስትይ በማያልፈው ዘላለማዊ እሳት ለመቀጣት ትመርጫለሽን ይኽስ አይሆንም ይቅርብሽ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡ እናት ሆይ ሶስናን ከእደ ረበናት /መምህራነ አይሁድ/ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት ያዳነ እርሱ እኛንም ከጋን ፍላት ያወጣናል፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር በዚህ የብረት ጋን ውስጥ ግዳጃችንን ልንፈጽም ፈቅዶ ከሆነ ኢዮብ ንብረቱንና ገንዘቡን ልጆቹንና ሚስቱን በመጨረሻም የተፈጥሮ አካሉን ባሳጣው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ እግዚአብሐር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ እግዚአብሔርም እንደወደደ አደረገ ከማለት በስተቀር ምንም የተናገረው ነገር እንደሌለ ሁሉ እኛም የሱን ዓላማ በመከተል ይኽንን መከራ ልንታገስ ይገባናል፡፡

ነገር ግን እናቱ በዚህ ምክር ልትጽናና ባለመቻሏ ቅዱስ ቂርቆስ ዐይኑን ወደ ሰማይ አቅንቶ አቤቱ አምላክ ሆይ ይችን ባሪያህን ከርስትህ የምትለያት ከሆነ ከባለሟልነትህ መጽሐፍ ፋቀኝ፤ አቤቱ አዝመራውን አቃጥለ ፍሬውን ልትባርክ ትወዳለህን ይኽን እንዳታደር ግን ቸርነትህ ትከለክልኸለች አቤቱ እንጨቱን ቆርጣችሁ አንድዱት ቅጠሉን ግን ጠብቁት ብለኽ ልታዝ መለኮታዊ ባሕሪህ አይደለም፡፡ ነገር ግን እንጨቱንም ቅጠሉንም በአንድ ጠብቁት ብለኽ ታዝዛለኽ እንጂ፡፡ እንግዲህ በዚህ ምክንያት ይኽንን ያየ ሁሉ ማዳን የሚችል አምላክ ቢኖራቸውስ ኖሮ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ አይጠራጠር፡፡

አቤቱ ዲያብሎስም ከባለስልጣኑ ይልቅ እኔ በረታሁ ቅዱሳኖቹንም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማው በማለት እንዳይደነፋ ለእናቴ ጽኑ የሆነ ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ስጣት ብሎ በጸለየ ጊዜ ዲያብሎስ ከእየሉጣ አጠገብ ብን ብሎ ጠፋ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ በሰማያዊ መንግሥት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታኽ ኃይልን ሰጥቶኛልና የሚጠብቀንን ገድላችንን ፈጽመን ድል እናድርግ እነሆ በብረት ጋን ውስጥ የሚነደውን እሳት በማይበት ጊዜ በለምለም /በምንጭ/ ላይ እንደሚወርድ ጠል ሆኖ አይቸዋለሁና አለች።
“… ያችኛይቱ ሔዋን ከአዳም ተገኝታ የተሠራችና አዳም ወደ እርስዋ እያየ ‘ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ ናት’ የሚላት ናት፡፡

ይህችኛይቱ ሔዋን ድንግል ማርያም ግን ከአዳም የተገኘች ሳትሆን አዳምዋ ክርስቶስ ሥጋው በጅራፍ ግርፋት ሲቆስልና አጥንቶቹ ሲቆጠሩ በጭንቀት እያየች ‘ይህ አጥንት ከአጥንቴ ነው ፤ ይህ ሥጋም ከሥጋዬ ነው’ የምትል ሔዋን ናት፡፡

የቀደመችዋ ሔዋን አዳምዋ በእርስዋ ምክንያት ጠፍቶ ‘አዳም ሆይ ወዴት ነህ?’ ተብሎ ሲፈለግ በዛፎች መካከል ሆኖ ከአባቱ ከእግዚአብሔር ‘ፈርቼ ተሸሸግሁ’ የሚል አዳም ነበረ::

ሁለተኛይቱ ሔዋን ድንግል ግን አዳምዋን ፍለጋ የምትጨነቅና ወዴት ነህ? ስትለው አዳምዋ ‘በአባቴ ቤት እኖር ዘንድ እንዲገባኝ አታውቁምን’ ብሎ የሚመልስላት ከአባቱ እቅፍ ያልተለየ አዳም እናት ናት፡፡

ለድንግል ማርያም ክርስቶስ ከእርስዋ የተገኘ አዳምዋ ብቻ ሳይሆን በቀናተኞቹ ቃየኖች አይሁድ በግፍ የተገደለባት አቤልዋም ጭምር ነው፡፡ ልዩነቱ የአቤል ደም ወንድሙን የሚከስስ ደም ሲሆን የእርስዋ ልጅ የክርስቶስ ደም ግን ‘ከአቤል ደም ይልቅ የሚሻለውን የሚናገር’ ‘ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻ ደም’ ነው"

(የብርሃን እናት ገጽ  100 Deacon Henok Haile)