❤77👏7🙏7🥱1🤝1
በምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ እንዳቶ ቀበሌ ከተገደሉት መካከል እስካሁን የ34 ኦርቶዶክሳውያን አስክሬን መገኘቱ ተሰማ።
ከምእመናን በተጨማሪ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም የሚፈጸመውን ጥቃት ለማስቆም ወደ አካባቢው እየሄዱ የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ አካላት የጥቃት ሰለባ መሆናቸው ታውቋል።
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሮቤ ወረዳ እንዳቶ ቀበሌ የምእመናን ግድያ የጀመረው ከጥር 21ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን ዛሬም በከፍተኛ ስጋት ውስጥ ያሉ ምእመናን የዛሬውን ግድያ ከቀድሞው ጋር ወደ ኋላ መለስ ብለው ያስታውሳሉ።
ሮቤ ወረዳ እንደቶ ቀበሌ ከሸርካ ወረዳ ጋር አዋሳኝ ስሆን ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም በሸርካ ወረዳ እንደተፈጸመው አሰቃቂ ጥቃት ሁሉ ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም በእንዳቶ ቀበሌ ከማለዳው 11 ሰዓት ጀምሮ ጥቃት መፈጸሙን ምእመናን ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቭዥን መረጃ አድርሰዋል።
እንደመረጃ ሰጭዎቻችን ታጣቂዎች በፈጸሙት በዚህ ድንገተኛ ጥቃት ይህንን ዜና እስከምንዘግብበት ጊዜ ድረስ ከሟቾች መካከል የ34 ኦርቶዶክሳውያን አስክሬን በእንደቶ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መሰብሰቡን አሳውቀዋል።
የሟቾች ቆጥርም እንደሚያሻቅብ ተጠቁሟል።
ጥቅምት 26ቀን 2019 ዓ.ም የሚፈጸመውን ጥቃት ለማስቆም ወደ አካባቢው እየሄዱ የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ አካላት የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ምእመናን ገልጸዋል።
ጥቃቱን ተከትሎም በርካቶች ጉዳት ደርሶባቸው በመንገድ መዘጋት ምክንያት እስካሁን በቂ የሕክምና እርዳታ እንዳላገኙ የገለጹት የአይን እማኞች የንግድ ተቋማትም መውደማቸውን አንስተዋል።
በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት መፈጠሩን ለማወቅ ተችሏል።
ባለፉት ዓመታት በምሥራቅ አርሲ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በሚገኙ ንጹሐን ላይ በተደጋጋሚ ሲፈጸሙ የቆዩት መሰል ጥቃቶች አሁን ላይም አሳሳቢ መልክይዘው መቀጠላቸውን ለመረዳት ችለናል።
ምንጭ :- mahibere kidusan - ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

😢23❤19👍2🥱1
ጥቅምት 27/2019 በዓለ መድኃኔዓለም ፎቶ ማስታወሻ 2