Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
16.3K subscribers
15.5K photos
79 videos
172 files
1.8K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
በኢትዮጵያና በአሜሪካ የሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት፤ የፎቶ ስብስብ 7፤
1. ✤ላፍቶ ሌንቃ መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን፤
2. ✤መድኃኔዓለም ቤ.ክ፤ ደብረ ሊባኖስ አጠገብ
3. ✤የቲሊሊ ደብረ ገነት መድኃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን
4. ✤ሚዛን ተፈሪ መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን
5. ✤ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም
6. ✤ኒውዮርክ መድኀኔ ዓለም
❤3
፨፨ ሌሎች በሃገራችን የሚገኙ የመድኀኔ ዓለም አብያተ ክርስቲያናት፤ (ፎቶ ያላችሁ ላኩልን፡፡)
✤መቅደላ መድኀኔዓለም
✤ባሕር ዳር ድባንቄ መድኄኔዓለም
✤አዴት መድኃኔዓለም
✤አዲስ አምባ መድኃኔዓለም ከ1600 ዓመት በላይ ዕድሜ ያለው በግብፃዊው ጻድቅ አቡነ ሙሴ የተፈለፈለ የዋሻ ገዳም
✤በቅሎ አግት / ዝንጀሮ አስጨብጭብ/ ጨጨሆ መድኃኔዓለም ገዳም
✤ወንጪት መድኃኔዓለም በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግስት ተመስርቶ እስካሁን ድረስ ነብር በቤተ መቅደሱ እየኖረ በሚጠብቀው በታላቁ ወይን እንጨት ቅዱስ ሚካኤል ገዳም ውስጥ የተሰራ
✤መቀሌ መድኃኔዓለም
✤አድግራት መድኃኔዓለም ወቅድስት ሥላሴ ወቅዱስ ቂርቆስ ገዳም ብዙ ድንቅ ታሪክ ያለው
✤ደባርቅ መድኃኔዓለም
✤የሽረት መድኃኔዓለም እጅግ ተደንቀውና ተደምመው ምስጋናዎ ኢምንት ሆናብዎት የሚመለሱበት
✤ኮሶ በር መድኃኔዓለም
✤ሐረር መድኃኔዓለም
✤ምስካበ ቅዱሳን ጻድቃኔ ዋሻ መድኃኔዓለም ገዳም
✤እመኪና መድኃኔዓለም ገዳም በመናኔው ጻድቅ ንጉሥ በአጼ ካሌብ ልጅ በጻድቁ ንጉሥ በአጼ ገብረ መስቀል በ6ኛው መ.ክ.ዘ. የተመሰረተ ታሪካዊ ገዳም
✤በሬ አገር መድኃኔዓለም ገዳም 1000 ሜትር ፍልፍል ዋሻ ገዳም
✤ተከዜ መድኃኔዓለም ገዳም በ11ኛው መ.ክ.ዘ. የላስታ ንጉሥ ቅዱስ ገብረ ማርያም /ታላቁ ሐርቤይ/ ደቀመዝሙር እንደነ ነቢዩ ኤልያስና ወንጌላዊው ቅ.ዮሐንስም ሞትን ሳያይ እስከ ምጽዓተ ሐሳዊ መሲህ /ዳግም ምጽአተ ክርስቶስ ዋዜማ/ ድረስ የተሰወረው ጻድቁ አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ ታቦተ ኪዳነ ምሕረትን ከሰማይ ተቀብሎ የመሰረተው ንዑድ ክቡር የሆነ መካነ ጸሎት ወአርምሞ ወትኅርምት
✤ሬማ መድኃኔዓለም አንድነት ገዳም፦ በ1414 በአባ ኖብ የተመሰረተና የብዙ ቅዱሳን መካነ ጸሎት የነበረ በዘመነ ሱስንዮስ ሰማእትነትን የተቀበለቺው ጻድቅት ወሰማእት ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ አጽሟ ያለበትና የከበረና የማይሻር ቃልኪዳኑን ከአምላከ ቅዱሳን የተቀበለችበት እፁብ ድንቅ ሥፍራ ሲሆን የሰማእቷን ጨምሮ በርካታ ቅዱሳን አጽማቸው የሚገኝበት ጥንታዊ ገዳም
✤ደብረ ታቦር መድኃኔ ዓለም
✤ናዝሬት መድኃኔዓለም
❤8
እንኳን ለመድኀኔዓለም ክብረ በዓል (ለመጋቢት 27 ጥንተ ስቅለት ልዋጭ በዓል)ና ለአቡነ መብዓ ጽዮን ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡
✤፨✤ አቡነ መብዓ ጽዮን
አቡነ መብዓ ጽዮን ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል (ጥቅምት 27 ቀን) ጋር አብረው የሚታሰቡ ታላቅ የተጋድሎ አባት ናቸው፡፡ የፃድቁ አቡነ መብዓ ጽዮን መታሰቢያቸው ከመድኃኔዓለም በዓል ጋር ስለሆነ በዚህ ጽሁፍ ሥር ታሪካቸውን ይዘን ቀርበናል፡፡ መልካም ንባብ!
አቡነ መብዓ ጽዮን የተገኙት እግዚአብሔርን እያስደሰቱ ያለነቀፋ ከሚኖሩ ቅዱሳን ነው፡፡ በክህነታቱ፣ በየዋህነቱ ከሰዎች የተስማማው አባታቸው ሀብተጽዮን፣ በደግነቷና በቸርነቷ የምትታወቀው እናታቸው ጽዮንትኩና በሕግ በንፅህና በጋብቻ ተወስነው ሲኖሩ የተባረከ ልጅ ይሰጣቸው ዘንድ ወደ ጌታ ይለምኑ ነበር፡፡ የለመኑትን የማይነሳ መድኃኔዓለም ክርስቶስም መብዓ ጽዮን የተባለ ደግ ልጅ ሰጣቸው፡፡
መብዓ ጽዮን ከልጅነቱ ጀምሮ ማስተዋል እና የእግዚአብሔር ፍቅር ያደረበት ሰው እንደነበር ገድሉ ይናገራል፡፡ ይኸውም በአንዲት ቀን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብሎ ከቤተክርስቲያን ወጥቶ ይሄድ የነበረ ሰው እግሩን እንቅፋት ተመቶ ደሙ ከመሬት ሲፈስስ በአየ ጊዜ እውቀት በልጅነቱ የሞላ መብዓ ጽዮን የደማው ጣቱ እስኪደርቅ ድረስ ጠባው፡፡ በመሬት የፈሰሰ ደሙን ከአፈሩ ጋር በላ፡፡ ይህ ሥራው ከልጅነቱ የመስቀሉ ፍቅር በልቡ የቸነከረ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
#ያገባ ሰው ሚስቱን ደስ የሚያሰኝበትን ሥራ ያስባል፡፡ ያላገባ ግን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ሥራ ያስባል$ የሚለው የመጽሀፍ ቃል ያፀናው ወጣቱ መብዓ ጽዮን ከቤተሰቡ የመጣለትን የጋብቻ ጥያቄ አልተቀበለውም፡፡ ኃጢአትን ከመጨመር ውጭ ምን እጠቀማለሁ እያለ የዚህችን ዓለም ጣዕም ናቃት፡፡ በዚህም ቤተሰቦቹ ተውት፣ እርሱም ራሱን ይበልጥ ለእግዚአብሔር አስገዛ፡፡

የምንኩስና እና ተጋድሎ ሕይወቱ
የምንኩስ እና የተጋድሎ ሕይወት የጣመ የላመ የሌለበት ፍፁም ራስን ለእግዚአብሔር ማሳለፍ ነው፡፡ ይህንን የማይወድ ጠላት ዲያብሎስ ደግሞ ፍፁም ፈተናን ያበዛል፡፡ ቅድሳንም በረድኤተ እግዚአብሔር እና በተጋድሏቸው ያልፉታል፡፡ ሠይጣንን ድል ይነሡታል፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮንም የምንኩስና ቀንበር ከተሸከመ ጊዜ ጀምሮ ከፈረስ፣ ከበቅሎ፣ ከአልጋ፣ ከምንጣፍ ላይ ሳይቀመጥና ሳይተኛ መኖሩን ገድሉ ይነግረናል፡፡ ለዚህም ተጋድሎ ሕይወቱ ያግዘው እና ይረዳው ዘንድ ክህነትን አባ ገብርኤል ከተባለ ጳጳስ ተቀብሏል፡፡ ቄስም ሆኖ የመድኃኔዓለምን ሥጋው እና ደሙን እያቀበለ ብዙ ዘመን ኖሯል፡፡ የምንኩስና ሕይወቱና ትጋቱም ታላቅ አባት እንደሆነ ያስረዳል፡፡
ትልቅ ድንጋይ በደረቱ ተሸክሞ ከምድር ከአመድ በተቀመጠም ጊዜ በራሱ ተሸክሞ፣ በሚሰግድም ጊዜ በጀርባው አዝሎ ስለ ክርስቶስ መከራ ያስባል፡፡ ራሱን ይበድላል፣ ስጋውን ያደክማል፡፡ ይኸውም ያለሰንበት እና ያለበዓላት በቀር በዚህ ተጋድሎ የምንኩስና ሕይወቱን ቀጠለ፡፡ ከዛም ወደ ደብረ ሊባኖስ በመሄድ ከአቡነ ተክለሃይማኖት መቃብር በረከትን እንደተቀበለ ገድለ መብዓ ጽዮን ይነግረናል፡፡ አቡነ መብዓ ጽዮን ራሱን ለእግዚአብሔር በሰጠ ቁጥር መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋወደሙ እየተገለፀ፤ እመቤታችንም እየታየች ትመክረው ታስተምረው ነበር፡፡

ቅዱሳንን ማክበር በዓላቸውን መዘከር እንዲገባ ከምንማርባቸው ታሪኮች አንድ የአቡነ መብዓ ጽዮን ታሪክ ነው፡፡ የመድኃኔዓለምን እና የእናቱን የቅድስት ድንግል ማርያምን በዓል አብዝቶ ያከብር ነበር፡፡ በዚህም መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ እና ከቅድሳን ጋር መጥቶ ባርኮታል፡፡ የመለኮት ምሥጢርም ሥርዓትም በአካባቢው ላሉ ሠዎችም ተሠጥቷቸዋል፡፡ መናፍቃን በዓል ማክበር አይገባም ቢሉ የበዓል ማክበር ውጤቱ እዚህ ድረስ መሆኑን እናያለን፡፡

በፀሎቱም #ኦ እግዚኦ አንተ ትብለኒ ሰአል ኩሎ ዘፈቀድከ ወአነ እሁበከ፣ ጌታ ሆይ አንተ የወደድከውን ሁሉ ለምን እኔ እሠጥሃለሁ አልከኝ፡፡ አሁንም የለመንኩን ግለጽልኝ$ በማለት የቀራንዮን መስቀል መከራውን ያሳየው ዘንድ ሁልጊዜ ይለምን ነበር፡፡ የለመኑትን የማይነሳ መድኃኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስም ቅዱሳን የሆኑ እጆቹን በመስቀሉ እንዲዘረጋ፣ እግሮቹም እንዲቸነከሩ፣ የሾህ አክሊልም በራሱ ተሸክሞ የጥቅምት 27 ቀን ታየው፡፡ ለሙሴ ሊታያቸው እንዳልቻለ አባ መብዓ ጽዮን ከመሬት ወደቀ፡፡ እንደ ሞተም ሆነ፡፡ ማንም የመስቀሉን መከራ ሕማሙን ማየት እንደማይችል ነገረው፣ በቸርነቱም አነሳው፡፡ የሞቱ ገናንነት የሚያስፈራ እና የሚያስደነግጥ መሆኑን አሳውቀው፡፡ መከራው ታላቅ በሰው አእምሮ አይታሰብምና ነው፡፡
ኃጢአትን ያልሠራ ሐሰትም በአፉ ያልተገኘበት ስለሠው ኃጢአት ስለሞተው ስለመድኃኔዓለም ክርስቶስ የሞቱ መታሰቢያ በምትሆን በዕለተዓርብ ታላቅ ተጋድሎን በማድረጉ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የስቅለት በዓል በሚታሰብበት በ27 በመድኃኔዓለም ዕለት የአቡነ መብዓ ጽዮን መታሰቢያ ተደረገ፡፡ ይኸውም ጥቅምት 27 ነው፡፡
/ከቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ሰሌዳ መጽሔት የተወሰደ/
የጻድቁ የአባታችን የአቡነ መብዓ ጽዮን በረከት ከእኛ ጋር ትሁን!!!
የመስቀሉ ፍቅር በልባችን ይኑር አሜን!!!

• Facebook 👉 https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool

• Telegram 👉 https://t.me/finotehiwott

• YouTube 👉 https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
❤14🙏4