የአርሲ ሰማእታት እና የጋምቤላ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን አስመልክቶ ወቅታዊ መልእክት።
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ፤በአርሲ በሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ላይ ሊገታ ያልቻለ እና ከልካይ የሌለው ተከታታይ ግድያ ምክንያት እጅግ አዝነናል ። በዚህም ለኦርቶዶክሳውያን ይልቁንም ለሰማእታት ቤተሰቦች መጽናናትን እንመኛለን።
የአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ሞት ፣ መፈናቀልና ስደት ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍቶ ይገኛል።
በቀቢፀ ተስፋ ውስጥ የወደቁትን፤ የሚታደጋቸው ሸተው በጭንቀት ያሉትን ቤት ይቁጠራቸው። ሃይማኖታቸው ምክንያት ሆኖ ግድያ ፣ ጥቃት ፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያ የሚደርሰባቸው ወገኖቻችን ጩኸት ተበራክቷል።
ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋግሞ እየተፈጸመ ያለውን የኦርቶዶክሳዊያን ሞት ፣ ስደት እና የአቢያተ ክርስቲያናት ቃጠሎን አስመልክቶ የወግዘትና የሐዘን መግለጫ ቢያወጣም መከራውን አልቆመውም ። ተጨባጭ መፍትሔ ማምጣትም አልተቻለም።
በመሆኑም የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ
ይኸን ተከታታይ ማቆሚያ የሌለው ዕልቂት አስመልክቶ ዘላቂ መፍትሔ ለማምጣት ሊቃውንት ፣ ምዕመናን እና ወጣቶች ያሳተፈ የምክክር ጉባኤ በመሰየም በአርሲና በሌሎችም አካባቢዎች የተፈጸሙትን ኢሰብዓዊና ሰይጣናዊ ድርጊቶችን በጥናት በመለየት ፤ ምክንያታቸውን በመተንተን የአደጋ መከላከልና የተጎዱትን የማበርታት ሥራ እንዲሁም የአንድን ዜጋ በነጻነት የመኖር እና የማምለክ ህገ መንግሥታዊ መብቱን ባላስጠበቁ የመንግስት አካላት ላይ ተገቢው እርምጃ እንዲወሰድ መንግስትን በመጠየቅ እና ኃላፊነትን ባለመወጣት ተጠያቂነት እንዲሰፍን በማድረግ መንፈሳዊ ግዴታውን እንዲወጣ በትህትና በልጅነት መንፈስ እናሳስባለን ።
ከዚህም በተጨማሪ ብፁዕ አቡነ ሩፉኤልን የሚመሩት ኢህጉረ ስብከት አስመልከቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉበኤ
ጥቅምት 16 እና 17 ቀን 2019 ዓ.ም በሰፊው መወያየቱንና በርካታ ማስራጃዎችን ጉባኤው ማዳመጡን ተረድተናል። በብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ተፈጸሙ የተባሉ የቀኖናና የአስተዳደር ጥሰቶች ለመስማት የሚዘገንኑ እንኳን አማንያኑን ኢአማንያንን የሚያስደነግጡ ፤ አንገትን የሚያሰደፉ እኩይ ተግባራት መሆናቸውን በሚገባ ተገንዝበናል ።
የተፈጸመውን አስተዳደራዊ እና ቀኖናዊ ጉዳዮች ጥሰት አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉበኤ ያለ ልዩነት ሕገ ቤተ ክርስቲያን የማስጠበቅ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል። ጥቂት የሀሳብ ልዩነቶች መፈጠራቸውን ታዝበናል። ይኸ የሀሳብ ልዩነት ቀኖና እና ህገ ቤተክርስትያንን ከመጠበቅ አንጻር የቀረበ እንዳይደለ ተረድተናል ። በተፈጸሙ አሳፉሪ ድርጊት አንገታችንን የደፋነው ሳያንሰን የአደባባይ ምስጢር በሆነው ጉዳይ ላይ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ያለ ልዩነት አልመወሰን ራሱን የቻለ የቀኖና ጥሰት ነው ። ይህን ጉዳይ በሕገ ቤተክርስትያን መሠረት አድርጎ አለመወሰን ለነገም የሲኖዶስን ልዕልና ያሳጣል ሥርዓት አልበኝነትን ያነግሳል ። ስለሆነም ምልዐተ ጉባዔው ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የማስጠበቅ ፍጹም የማይሽራረፍ መንፈሳዊ ግዴታውን በምልዐት እንዲውጣ በትህትና እናሳስባለን ።
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

❤24👍6🤔3🤝2
ቀጥታ ስርጭት /ነገረ ማርያም /በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን
https://www.youtube.com/live/cfeKcqzS-UU?si=pc29zwHWh8EIHcbJ

YouTube
👉ቀጥታ ስርጭት /ነገረ ማርያም /በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን
finote hiwot sunday school
❤33
https://youtu.be/fnu9lOguY00?si=46N96oZ6EoeYEGhF
ወአንቲኒ ደብረ ሰላም | የመድኃኔዓለም መዝሙራት ስብስብ | በዩቱዩብ ቻናላችን ይመልከቱት
ወአንቲኒ ደብረ ሰላም | የመድኃኔዓለም መዝሙራት ስብስብ | በዩቱዩብ ቻናላችን ይመልከቱት
YouTube
⚪️ ወአንቲኒ ደብረ ሰላም | የመድኃኔዓለም መዝሙራት ስብስብ 1| የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን
የቀጨኔ ደብረሰላም መድኀኔዓለም እና ደብረትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት የቤቱ ቀለም መዝሙራት ስብስብ በፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን
#Medhanealem_mezmur #Kechene_Medhanealem #Kechene #EOTC #MKtv #Mezmur

❤18🙏3
እንኳን ለመድኀኔዓለም ክብረ በዓል (ለመጋቢት 27 ጥንተ ስቅለት ልዋጭ በዓል)ና ለአቡነ መብዓ ጽዮን ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡
በሃገራችን ከሚገኙ የመድኀኔዓለም ገዳማትና አድባራት ጥቂቶቹ፤
፠ ለየብቻቸው ያሉት፤ ዋልድባ አበረንታት መድኀኔዓለም ገዳምና
ኤልሻማ ደብረ ማኅቶት መድኀኔዓለም ቤ.ክ.
፠ አንድ ላይ ያሉት፤
✤1. ዋልድባ አበረንታት መድኀኔዓለም ገዳም፤
✤2.ላሊበላ መድኀኔዓለም
✤3. ጎንደር መንበረ መንግሥት መድኀኔዓለም
✤4. መንዳባ አቡነ ያሳይ መድኀኔዓለም፤ ጣና
✤5. ሽረ እንዳሥላሴ መድኀኔዓለም ወመስቀል ክብራ
✤6. ቆላድባ መድኀኔዓለም፤ ጎንደር ከተማ አጠገብ
✤7.ቦሌ ደብረ ሳሌም መጥምቁ ዮሐንስ፤ (የመድኀኔዓለም ታቦት በድርብ አለ)
✤ 8.ድሬዳዋ መድኀኔዓለም
✤9.ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም

❤9
በሃገራችን ከሚገኙ በመድኀኔዓለም ስም የተሰየሙ አብያተ ክርስቲያናት፤ ስብስብ 2፤
ጨነቅ ዋሻ መድኀኔዓለም፤ በቅዱስ ላሊበላ በዋሻ ውስጥ እንደገና ፎቅ ተደርጎ የተፈለፈለ፤ በሰሜን ተራሮች (በራስ ደጀን) እግር ሥር የሚገኝ፤ በፓርክ ክልል ውስጥ በመኾኑ በብዙ ኢትዮጵያውያን የማይታወቅ፤ ነገር ግን ብዙ ተዓምራትን እጅጉን ፈዋሽ የኾነ ጠበል የሚገኝበት፡፡
1. ✤መናገሻ ጋራ መድኀኔዓለም፤ ግማደ መስቀሉ ያረፈበት፤ ቀድሞ የቅዳሴ ቤቱን ታላቁ አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (ቀድሞ የልደታ ቤ.ክ) በአካል በመገኘት በመስቀሉ የባረከው፤ በድርሳነ ራጕኤል ላይ የተገለጸና ቅዱስ ራጕኤል የማይለየው፤ በአረማዊው ግራኝ ወረራ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑ ካህናቱን መነኮሳቱንና ምዕመናኑን እንደያዘ በምድር ውስጥ ገብቶ የተሰወረበት በሥጋ ዕረፍተ ሞት ያልተገቱ ሥውራን ግሩማን አበው የሚኖሩበት "ዛቲ ይእቲ አምባ ማርያም መካነ ክብሮሙ ወጸሎቶሙ ለቅዱሳን ወለነገሥታተ ኢትዮጵያ በሐ በልዋ ተሳለምዋ ጊሱ ሐቤሃ ኢትርሐቁ እምኔሐ" ብለው አበው ያወደሷት የጸሎት የአርምሞና የትኅርምት ቦታ፡፡
2. ✤ገዳመ አባ ጽጌ ድንግል (መድኀኔዓለም ቤ.ክ)፤ ማኅሌተ ጽጌ የተደረሰበት ወሎ፤ ወግዲ፤ ወለቃ ወንዝ አጠገብ፤ የበረሃው ዕንቊ ገዳም፤ አባ ጽጌ ድንግል የፈለፈሉት ባለ 3 መቅደስ እጅግ ሰፊ ዋሻ ቤ.ክ፡፡
3. ✤ደብረ ቀራንዮ መድኀኔዓለም ቤ.ክ፥ አዲስ አበባ፤ በአዲስ አበባ ከተመሠረተ ከ1826 ዓ.ም ጀምሮ ፍልሰት ሳያጋጥመው በመቆየቱ፤ የመጀመሪያው የአዲስ አበባ ቤ.ክ፡፡ (ነገር ግን በመሃል ፍልሰት እያጋጠማቸው እንጂ በአዲስ አበባ ከ1600 ዓመታት በፊት ደብረ ኤረር፣ የካ ዋሻ ተክለሃይማኖትና /ኋላ የካ ሚካኤል/ በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመን፤ እንዲሁም እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት በአልአሜዳ ዘመነ መንግሥት መመሥረታቸውን ልብ ይሏል)

❤7