Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ከ10 በላይ ኦርቶዶክሳውያን ሲገደሉ
የ101 ዓመት እድሜ ያለው የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወድሟል።

የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይም ዘረፋ የተካሄደ ሲሆን ምእመናን ጽላቱን ይዘው ተሰደዋል፤ መኖሪያ ቤታቸውም ተቃጥሏል።

EOTCMK TV ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም

እንደ ወትሮው ሁሉ ዛሬም በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ምድር ላይ ታላቅ ሃዘን ላይ ይገኛል። ማቅ የለበሱ እናቶች፣ እንባቸው ያላለቀ ሕፃናት እና ማደሪያ ያጡ አረጋውያን ጩኸት ሰሚ አጥቷል።

ከግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት፣ አሰኮ ወረዳ፣ ጠላታ ጨፋ ቀበሌ እና ካራ ኩፍቴና በሚባሉ አካባቢዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ ያነጣጠረ አሰቃቂ ግድያ ተፈጽሟል።

ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸውን የማንጠቅሰው የአይን እማኝ እና መረጃ ሰጭያችን እንደገለጹልን ከሆነ፣ ጥቃቱ እጅግ አሳዛኝና አረመኔያዊ እንደነበር ይናገራሉ።

በአሰኮ ወረዳ ጠላታ ጨፋ ቀበሌ ብቻ በታጣቂ ኃይሎች በተፈጸመ ሰብአዊነት በጎደለው ጥቃት ከ10 በላይ ንጹሃን ኦርቶዶክሳውያን ተገድለዋል።

ይህ አሰቃቂ ጥቃት በሰዎች ሕይወት ላይ ብቻ አላበቃም የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም የሚፈተትበትን መቅደስም ጭምር ኢላማ ያደረገ ነበር። በአካባቢው 101 ዓመታትን ዕድሜ ያስቆጠረው፣ ታላቁ የዕድሜ ባለጸጋ የጠላታ ጨፋ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ በእሳት ወውደሙን መረጃ ሰጭያችን ገልጸውናል።

በተመሳሳይ ጥቃት በካራ ኩፍቴና መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት የተሰነዘረ ሲሆን፣ የቤተክርስቲያኑ ንብረት የሆኑ ቤቶች በመቃጠላቸው ምእመናን የመድኃኔዓለምን ቅዱስ ጽላት ይዘው በእግራቸው ወደሌላ አካባቢ መሸሻቸው ታውቋል።

ኦርቶዶክሳውያኑ ተወልደው ካደጉበት፣ ወልደው ከሳሙበት ቀያቸው በሃይማኖታቸው ብቻ ቤታቸው እየተለየ ተቃጥሏል፤ ንብረታቸውና ከብቶቻቸው ተዘርፈዋል። ከጥቃቱ የተረፉት ነዋሪዎችም ይዘውት የሸሹት እምነታቸውንና ማንነታቸውን ብቻ በመሆኑ አሁን ላይ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ ሲሉ ነበር በሃዘን ተውጠው የነገሩን።

በተያያዘ ዜና

በዚሁ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በሺርካ ወረዳ በሁለት ወጣት ኦርቶዶክሳውያን ላይ ዘግናኝ ግድያ መፈጸሙ ተሰምቷል።

ድርጊቱ የተፈጸመው ሚታና ዋጂ ቀበሌ ሲሆን፣ ታጣቂዎች ግንቦት 23 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ወጣቶቹ መኖሪያ ቤት በመግባት በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸውና በመቀጠልም ወጣቶቹን ወደ ሚታና ጋዶ ቀበሌ በመውሰድ፣ አንደኛውን በስለት አርደው፣ ሁለተኛውን ደግሞ በጥይት በመምታት በጭካኔ ሕይወታቸውን እንዳጠፉት ተገልጿል።

ሕይወታቸውን ያጡት የእነዚህ ወጣቶች ሥርዓተ ቀብር ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በጋዶ ማሕደረ ስብሐት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን፣ ምዕመናንና በቤተሰብ በተገኘበት በአንድ መቃብር ተፈጽሟል።

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በአገልጋዮችና ምእመናን ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት እንደሚፈጸምበት ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ለዓመታት መረጃ እያደረሰ ቢሆንም ዛሬም ድረስ ዘላቂ መፍትሔ አልተገኘም።
😢327
"ታሪክን ለትውልድ የማሻገር ተራው የኔ ነው ""
ከ ግንቦት 28-30 ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ 
አለም አቀፍ ገቢ ማሰባሰብያ ቀጥታ ስርጭት ላይ ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲረባረብ  ጥሪ ቀረበ
መናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን(አራዳ ጊዮርጊስ )
  በሁሉም ባንኮች 1423
15👏2
እንኳን ለአምላካችንና ፈጣሪያችን ቅዱስ አማኑኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሰን ፥ አደረሳችሁ፡፡
ክብረ በዓሉ ከሚከበርባቸው ገዳማትና አድባራት ዐበይቶቹ (እናንተም የምታውቋቸውንና በአቅራቢያችሁ ያሉትንከነፎቷቸው ጨምሩበት)
፠ ኦፍና አማኑኤል፤ መርሐ ቤቴ፥ አለም ከተማ፤ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የተመሠረተ ጥንታዊ ቤ.ክ.
፠ ኤነር አማኑኤል፤ ምድረ ጕራጌ፤ እጅግ በጣም ጥንታዊ ገዳም
፠ ደብረ መንክራት በጎል ሰከበ ሚጣቅ ቅዱስ አማኑኤል፤ ከደብረ ብርሃንና አንኮበር መሃል ላይ የሚገኝ፤ በንጉሥ ሣህለ ሥላሴ የተመሠረተ፤ እጅጉን በጣም ፈዋሽ የኾነ ጠበል የሚገኝበትና የቅዱሳን መናኸሪያ የኾነ፡፡
፠ ጫገል ቅዱስ አማኑኤል /በደብረ ሊባኖስ ገዳም ከሚተዳደሩ አብያተ ክርስቲያናት አንዱ/
፠ ደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል፣ አዲስ አበባ፤ መርካቶ መሳለሚያ
፠ ባሶ ወረዳ ጣፎ ደብረ ሰላም ቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን፤ ከጢያ ከተማ ወደ አጠገብ የሚገኝ፡፡
15
ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ተገኝተው የተጎዱ ወገኖችን የሚያጽናኑ በፁዐን አባቶችን መደበ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ተገኝተው ጉዳት የደረሰባቸውን ኦርቶዶክሳዊያን የሚያጽናኑ ብፁዓን አባቶችን መደበ።

የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሺርካ፣ በሆንቆሎ ዋቤ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በዛሬው ዕለት ባካሔደው መደበኛ ስብሰባው በችግሩ ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግ፣በብፁዓን አባቶች የሚመራ የቤተ ክርስቲያናችን ልዑካን ቡድን ችግሩ ወደ ተፈጠረበት ቦታ በመሄድ ተጎጂዎችን እንዲጎበኝ፣ እንዲያጽናና እና አስፈላጊውን ጊዜያዊ ድጋፍ አንዲያደርግ ወስኗል።

ቋሚ ሲኖዶስ በጠቅላይ ቤተክህነት በኩል በሚቋቋም
ኮሚቴ አስተባባሪነትም በተፈጠረው ችግር ምከንያት የመቃጠል አደጋ የደረሰበት ጥንታዊው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያንን እንዲያሰራ፣ከቀያቸው የተፈናቀሉ ወገኖች በቋሚነት ወደ መኖሪያቸው እንዲመለሱ የሚዲያደርግ፣ በሀገረ ስብከቱ ዳግመኛ መሰል ችግሮች እንዳይፈጠርሩ ጥናት አካሒዶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር የሚያቀርብ ዐቢይ ኮሚቴ ተሰይሞ በአስቸኳይ ወደ ሥራ እንዲገባ ወስኗል።

በትላንትናው ዕለት በምሥራቅ አርሲ አንዳንድ ወረዳዎች የተከሰተውን ችግር ተከትሎ ፦
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
ብፁ አቡነ ዲዮስቆሮስ
ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ
ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ
ብፁዕ አቡነ ማርቆስ
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ
ብፁዕ አቡነ ገብርኤል
ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ከፌዴራል ሰላም ሚኒስቴርና ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በተከሰተው ችግር ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።
21🤬20
የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት/ቤት የ4ኛየ8ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች በዕለተ እሁድ 30/09/2018
የሀገረ ስብከቱን ሞዴል ፈተና ሲፈተኑ።
39👍3