Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
እንኳን አደረሳችሁ፡፡
#ግንቦት_21_ደብረ_ምጥማቅ_ማርያም_የምናከብርበት_ምክንያቱና_ሥርዐተ_ማኅሌት_ዘግንቦት_21፡፡
ግብጻውያን ክርስቲያኖች ከግንቦት 21 እስከ 25 የእመቤታችንን በዓል (አጎበር ጥለው፥ ድንኳን ተክለው፥ ድባብ ዘርግተው ያከብራሉ፤ እመቤታችንም ከቅዱሳን ጋር በመገኘት ትባርካቸዋለች፡፡) እነዚህ 5ት ቀናትም ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት 5ቱን ከተ.ቊ 25ኛ እስከ 29ኛ ያለውን ይይዛሉ፡፡ እነርሱም፤
፠25ኛ. ግንቦት 21 ቀን በግብጽ ሃገር ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቤተክርስቲያን ለተሰበሰቡት ምዕመናን በግልጽ የታየችበት ነው፡፡ 
፠26ኛ. ግንቦት 22 ቀን በግብጽ ሃገር ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቤተክርስቲያን ለተሰበሰቡት ምዕመናን በግልጽ የታየችበት ነው፡፡
፠27ኛ. ግንቦት 23 ቀን ደብረ ምጥማቅ በተባለች ቦታ የታየችበት ነው፡፡
፠28ኛ. ግንቦት 24 ተሰዳ ግብጽ የገባችበት ነው፤ /ኢሣ.1 9፥11፣ ማቴ.2፥13-15/
፠29ኛ. ግንቦት 25 ልጇ መድኀኔዓለም ክርስቶስ የደረቁ በትሮችን ተክሎ ያለመለመበት በዓል ነው፡፡
እነዚህ ከላይ ያየናቸውን የደብረ ምጥማቅ በዓላት (ከግንቦት 21-25) በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ተነሥቶ የነበረው የግብፁ ንጉሥ እንዳያከብሩ በመከልከሉ፤ ኢትዮጵያውያንም ይህንን በዓል ለማክበር ይሄዱ ነበርና አፄ ዘርዐ ያዕቆብ ለመጽናኛ እንዲሆን በሃገራችን የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያምን መሠረተ፤ እመቤታችንም ብዙ ቃል ኪዳንን ሰጠችው፤ ይኸው ቃል ኪዳኗ ሳይታጠፍ በጻድቃኔ ማርያም ዛሬ ድረስ ስፍር ቊጥር የሌለው ብዙ ተዓምራትና የምሕረት ሥራ የሚፈጸምባት ቅዱስ ቦታ ኾና ትገኛለች፡፡ እስካሁን ባለን መረጃ በሃገራችንም ግንቦት 21 የደብረ ምጥማቅ ክብረ በዓል በዋነኛነት!!! (በዋነኛነት!!!) የሚከበርባቸው ቦታዎች የሚከተሉት ናቸው፤
*1ኛ) #ደብረ_ምጥማቅ_ጻድቃኔ_ማርያም_ገዳም፡፡ /ሰሜን ሸዋ/
*2ኛ)  ሐመረ ብርሃን ደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን /ጎንደር ከተማ/
*3ኛ) ደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም /አዲስ አበባ/
(ሥርዐተ ማኅሌቱን ላልደረሰው በማድረስ ይተባበሩ፡፡)
ኦ አበው ወእማት አኃው ወአኃት ኢትርስዑነ በጸሎተክሙ (በዘጸለይክዋ በዝንቱ ሥርዐተ ማኅሌት) ለትምህርተ ቤትነ ቀ.ደ.ሰ.መድኀኔዓለም ወደ.ት.ቅ.ገብርኤል ፍኖተ ሕይወት፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
22🙏1🤝1
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማጀራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የዘንድሮ የሰንበት ት/ቤቶች ቀን የሁሉም ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤት በየአሉበት ቦታ "የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ4:3 በሚል መሪቃል እንዲከበር መልእክት አስተላለፈ።

እንደሚታወቀው ላለፋት አስርት ዓመታት በቅዱስ ሲኖዶስ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ ደንብ ከጸደቀበት እና በረከታቸው ይደርብን እና በብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፖትርያርክ የበዓለ ጰራቅሊጦስ ቀን የሰንበት ት/ቤቶች ቀን እንዲሆን በሰጡት አባታዊ መመሪያ ያ መሠረት በየዓመቱ በዓለ ጰራቅሊጦስን ቀን መሠረት አድርጎ የመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የሁሉም አህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተገኙበት የሁለት ቀን ጠቅላላ ጉባኤውን እና የጉባኤው ማጠቃለያ ቀን በበዓለ ጰራቅሊጦስ ዕለት ከአህጉረ ስብከት ሰንበት ት/ቤት ተወካዮች በተጨማሪ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አመራሮች እና ልብሰ ስብሐት የለበሱ የሰንበት ት/ቤት አባላት በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ የሰንበት ት/ቤቶች ቀንን በጋራ ሲያከብር መቆየቱ ይታወሳል።

ይሁን እና በዚህ ዓመት በዓሉ የዋለበት ቀን ከ7ተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ዋዜማ ላይ በመሆኑ የየአህጉረ ስብከት ተወካዮች ለመገኘት ባለመቻላቸው ጠቅላላ ጉባኤው የተዘዋወረ በመሆኑ ሁለም ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤት ቀንን "የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ4:3 በሚል መሪ ቃል እንዲከበር በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መልእክት አስተላልፏል።

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በዕለቱ ሁላችንም በየአጥቢያችን በሚኖር የሰንበት ት/ቤት ጉባኤ የሰንበት ት/ቤቶች ቀንን መሪ ቃሉን መሠረት በማድረግ ከአባላቶቻችን ጋር እንድናከብር ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

በመርሐ ግብሮቹም መሪ ቃሉን መሠረት ያደረገ ቃለ እግዚአብሔር እና በዝማሬ እንድናከብር እያልን በድጋሚ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ለሁሉም የሰንበት ትቤት አባላት እና አመራሮች እንኳን ለሰንበት ት/ቤቶች ቀን እና ለበዓለ ጰራቅሊጦስ አደረሳችሁ እያለ ሰንበት ት/ቤቶች በዕለቱ በዓሉን አክብረው እንዲውሉ እና የሰንበት ት/ቤት አመራሮችም እንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታችሁን ለመላው አባላቶቻችሁ እንድታስተላልፋ ከወዲሁ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
15
በዓለ ጰራቅሊጦስ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ቀን መሪ ቃል:-
"የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ" ኤፌ ፬;፫

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

👉  Website
13
#በዓለ_ጰራቅሊጦስ

ሥርዐተ ማኅሌቱ በዓለ ጳራቅሊጦስ ከ፱ኙ ዐበይት በዓላተ እግዚእ አንዱ እንደመኾኑ በኹሉም ገዳማትና አድባራት ይከበራል፤ ነገር ግን ታቦተ ሕጉ ወጥቶ በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በሐዋርያትና በመንፈስ ቅዱስ ስም በተሰየሙ አብያ ክርስቲያናት ይከበራል፤ ይልቁንም በአዲስ አበባ ብቸኛ በኾነው #በጽርሐ_ጽዮን_ሐዋርያት_መንፈስ_ቅዱስና_/ኋላ/#ጎላ_ሚካኤል_ (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አገብ) ቤተ ክርስቲያን ይከበራል፡፡
ጰራቅሊጦስ ማለት መንጽሒ (የሚያነጻ)፥ መጽንዒ (የሚያጸና)፥ መስተፈሥሒ (ደስታን የሚሰጥ)፣ መስተሥርይ (ኀጢአትን ይቅር የሚል)፣ ናዛዚ (የሚያረጋጋ)፣ ከሣቲ (ምሥጢርን የሚገልጥ) የሚል ትርጕምን ይሰጣል (መጻሕፍተ ሠለስቱ ሐዲሳት፣ ገጽ ፪፻፹፫)፡፡ ይኸውም መንፈስ ቅዱስ በኀጢአት ጭቃ የወደቁትንና የሚወድቁትን እንደሚያነጻቸው፤ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ላሉት ኹሉ በፈተናቸውና በመከራቸው ኹሉ እንደሚያበረታቸው (እንደሚያጸናቸው)፤ የሚነዋወፁትን እንደሚያረጋጋቸው፤ ያዘኑትን እንደሚያጽናናቸው፤ የሚደክሙትን እንደሚያበረታቸው፤ የተከዙትንም ሐሴትን እንደሚሰጣቸው የሚያስገነዝብ ነው፡፡ ጻድቃንን ወደ ተጋድሎ፤ ሰማዕታትን ወደ ደም፣ መነኰሳትን ወደ ገዳም፣ ማኅበረ ክርስቶስንም ወደ ቤተ ክርስቲያን ልቡናቸውን የሚያነሣሣና የሚመራ እርሱ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ /ዮሐ.፲፮፥፲፪/፡፡ 
#በዓለ_ሃምሳ_በብሉይ
እስራኤል ዘሥጋ በዓለ ኃምሳን የሚያከብሩት ስለ ብዙ ምክንያት ነው፡፡
  ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያኽልም፤
፩ኛ) ከምድረ ግብጽ ከወጡ በኋላ ምድረ ከነዓን ገብተው ለመዠመርያ ጊዜ እሸት የበሉበትን የሚዘክሩበት ነው፡፡ ዳግመኛም በበረኻ ሳሉ እግዚአብሔር ከሰማያት ኅብስተ መናን አውርዶ፥ ከጭንጫ ውኃን አመንጭቶ እንደመገባቸው ይዘክሩበታል፡፡ በመኾኑም በዚኽ በዓል ቀዳምያት፥ ዐሥራትና በኵራት እያወጡ፣ በየዓመቱ ከሚዘሩት እኽል እሸት (በብዛት ስንዴ) እየበሉ እግዚአብሔርን ስለ ምድር ፍሬ የሚያመሰግኑበት በዓል ነው፡፡
፪ኛ) እግዚአብሔር ከግብጽ ባርነት ካወጣቸው በኋላ በሃምሳኛው ቀን በደብረ ሲና ሕገ ኦሪትን ስለተቀበሉበት ይኽን ያስቡበታል፡፡
፫ኛ) እግዚአብሔር ከምድረ ግብጽ በታላላቅ ገቢረ ተአምራት ስላወጣቸው ይኽን ያስቡበታል፡፡
  ከላይ ለመግለጥ እንደተሞከረው ይኽ በዓል እኽል በሚታጨድበት በመከር ወቅት የሚከበር በዓል ነው፡፡ መከር ሲገባ መጀመርያ ከሚሰበስቡት እኽል ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንዲያቀርቡ ታዝዘው ነበር /ዘጸ. ፳፫፡፲፮/፡፡ በመኾኑም ከበዓለ ፋሲካ ጀምረው ሰባት ሳምንታት (፵፱ ቀናት) በየዕለቱ አንድ መስፈርያ እኽል ይሰጡ ነበር፡፡ በ፶ኛው ቀን ደግሞ ሊቀ ካህኑ ከተሰበሰበው እኽል በትልቅ መስፈርያ አድርጎ ካቀረበ በኋላ መሥዋዕተ በግ ይሠዋ ስለነበር ታላቅ በዓል ኾኖ ይከበር ነበር /ዘሌ. ፳፫፥፲-፲፯፣ ዘዳ. ፲፪፥፭-፯/፡፡
***አማናዊ ትርጓሜ - በሐዲስ
ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ድኅነተ ዓለምን በፈጸመበት ዓመት ግን፥ እስራኤል ዘሥጋ ከላይ በገለጥነው መንገድ ከያሉበት ተሰባስበው በዓሉን በኢየሩሳሌም ሲያከበሩ፤ ለእሥራኤል ዘሥጋና ለእሥራኤል ዘነፍስ ብርሃን እንዲኾኑ የመረጣቸው ሐዋርያትም ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነገራቸውን ተስፋ እየተጠባበቁ በደብረ ጽዮን በቅዱስ ማርቆስ እናት በማርያም ቤት ተሰባስበው ነበር /ሉቃ. ፳፬፡፵፱/፡፡       በዓለ ሃምሳ የተባለው ቀን በደረሰ ጊዜም ከወደ ሰማይ እንደ ዓውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ድምፅ ነጕዶ ተሰማ፤ መንፈስ ቅዱስ ነበር፡፡ በዚኽም ብሉይና ሐዲስ ተገናኙ፤ ተተካኩ፡፡
የነቢያት ትንቢታቸው፥ የሐዋርያትም ስብከታቸው የኾነው ጌታችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነቢያትንና ሐዋርያትን በደብረ ታቦር ተራራ እንዳገናኛቸው፥ በዚያም ክብረ መንግሥቱን፥ ብርሃነ መለኮቱን እንደገለጸላቸው የሚታወስ ነው /ማቴ. ፲፮፡፩-፯/፡፡ በምሴተ ኀሙስም በቤተ አልዓኣዛር የብሉይ ፋሲካን እንዳዘጋጁና እርሱም መሥዋዕተ ብሉይን በመሥዋዕተ ሐዲስ እንደተካው የተጻፈ ነው /ማቴ. ፳፮፡፲፯-፳፱/፡፡ በበዓለ ኃምሳ የኾነውም ልክ እንደዚኹ ነው /ሐዋ. ፪/፡፡ ይኽ ኹሉ በኢየሩሳሌም፣ በመዠመርያዪቱ ቤተ ክርስቲያን በተሰየመች በቤተ ማርያም (የማርቆስ እናት) ተፈጸመ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለፊተኞችም ለኋለኞችም እናታቸው እንደኾነችም ታወቀ፤ ተረዳ፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያት በዲድስቅልያ ፴፩ ላይ፡- “ከዕርገቱ ቀን በኋላ ታላቅ በዓል ይደረግ፤ በዚኽች ቀን በሦስተኛው ሰዓት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጰራቅሊጦስን ልኮልናልና እኛም በርሱ ስጦታዎች ተሞላን፤ አዳዲስ ቋንቋም ተናገርን” በማለት በዓሉን በቤተ ክርስቲያን ልናከብረው እንዲገባ ሥርዐት ሐዋርያት የሠሩልንም ስለዚኹ ነው፡፡ በነቢያትና በሐዋርያት መሠረት የታነጸችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንም ይኽንኑ በዓል ከጌታችን ዘጠኝ ዐበይት በዓላት አንዱ በማድረግ በድምቀት ታከብረዋለች፡፡
#ርደተ_መንፈስ_ቅዱስ 
   ጌታችን እንደነገራቸው መቶ ሃያው ቤተ ሰብእ በቤተ ማርያም ኀይልን ከአርያም እስኪለብሱ ድረስ ተሰብስበው ነበር፡፡ በትዕግሥት ከመጠበቅ ውጪ መንፈስ ቅዱስ መቼ እንደሚወርድም አያውቁም ነበር /ሐዋ. ፪፥፪/፡፡ ጌታችን ባረገ በዐሥረኛው ቀን ግን እኔና እናንተ እንደምንሰማው ዓይነት ያይደለ፥ ነገር ግን ከወደ ሰማይ እንደ ዓውሎ ነፋስ ድምፅ ያለ ድምፅ ነጕዶ ተሰማ፡፡ ያሉበትን ቤት ሞላው፡፡ ላንቃ ላንቃ ያለው እሳት ኾኖ ታያቸው፡፡ በበደልን ጊዜ ከእኛ ርቆ ነበርና አኹን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ስለታረቅን በኹሉም አደረባቸው:  /ማቴ. ፫፡፲፩/፡፡ ኀይል የሚኾናቸው
ሀብትን፣ ሀብት የሚኾናቸው ዕውቀትን ገንዘብ አደረጉ፡፡
#መንፈስ_ቅዱስ
መንፈስ ቅዱስ ከሦስቱ አካላተ ሥላሴ አንዱ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ጋር የሚሠለስ የሚቀደስ የባሕርይ አምላክ ነው፡፡ እንደ አብና ወልድ ፍጹም ገጽ፥ ፍጹም መልክዕ፥ ፍጹም አካል አለው፡፡ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ እንጂ ሕጹጽ (ብትን፣ ዝርው) አይደለም፡፡ በተለየ ግብሩም መሥረፅ (መውጣት) ነው፤ መሥረጹም ከአብ ብቻ እንጂ አንዳንዶች (ካቶሊኮችና መካነ ኢየሱሶች) እንደሚሉት ከወልድም ጭምር አይደለም /ዮሐ.፲፭፡፳፮/፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቢሠርፅ እንጂ አያሠርጽም፤ አይወልድም፤ አይወለድም፡፡
በባሕርይ፥ በመለኮት፥ በሥልጣን፥ በሕልውና፥ በአገዛዝ፥ ዓለማትን በመፍጠርና በማሳለፍ ከአብና ከወልድ ጋራ የተካከለ ነው  /ጸሎተ ሃይማኖት/፡፡ ቀዳሚነትም ኾነ ተቀዳሚነት የሌለው ይልቁንም ከአብና ከወልድ ጋር የተካከለ (ዕሩይ) ነው፡፡ ከአብና ከወልድ ጋር ዓለም ሳይፈጠር ፥ ዘመን ሳይቈጠር ይህ ነው በማይበል ዘመን የነበረ ቀዳማዊ፤ ከአብና ከወልድ ጋር አሁንም ያለ ማዕከላዊ፤ ከአብና ከወልድ ጋር አብሮ ተካክሎ ይህ ነው ለማይባል ዘመን ወደፊት የሚኖር ደኃራዊ ነው፡፡

ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በአዲስ_አበባ_የሚከብርበት_ #፫_ብቸኛው_ደብር፡፡
፩ኛ). #ጽርሐ_ጽዮን_ሐዋርያትና_ጎላ_ቅዱስ_ሚካኤል_ቤ/ክ፤
አድራሻው፤ ልደታ ክፍለ ከተማ፥ ኢምግሬሽን አጠገብ፥ ጎላ፤

፪ኛ). #ብርሃናተ_ዓለም_ጴጥሮስ_ወጳውሎስ_ቤ/ክ፤
አድራሻው፤ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ፥ ዊንጌት ት/ቤት፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ አራዳ → ዊንጌት (አስኮ በሚለው ታክሲ)፤
፫ኛ). #መንበረ_ልዑል_ቅዱስ_ማርቆስ_ቤ/ክ
አድራሻው፤ ጉለሌ ክፍለ ከተማ፥ 6 ኪሎ፤
17
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
#በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፩ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩ኛ). #ደብረ_ሕይወት_ማይዳዕሮ_ጰራቅሊጦስ_ገዳም፤ (እመቤታችን በስደቷ ወቅት ያረፈችበት፤ ጃንደረባው ባኮስ አድራሻው፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ ዓዲ አቡን (ኤርትራ ጠረፍ)፤

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
10👍1
#ግንቦት_24_በዓተ_ግብጽ_፤ እመቤታችን እመ አምላክ ድንግል ማርያም ከልጇና ከአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ጋር ለ3 ዓመት ከ6 ወር ከተሰደዱ በኋላ ወደ ግብጽ ሃገር ገብታ በሰላም ያረፈችበት ቀን ነው፡፡
ዖፍኒ ረከበት ላቲ ቤተ፤ ወፍም ቤቷን ሰራች፡፡ መዝ. ፹፫፥፫
*በአዲስ አበባ ታቦተ ሕጉ የሚነግሥባቸው ቦታዎች፤
፠እንጦጦ መንበረ ንግሥት ቅድስት ቊስቋም ማርያም፡፡ (365ት ቀናት ሙሉ ዝክር በማኅበረ መድኀኔ ዓለም አዳራሽ የሚዘከርባት ቤ/ክ)
፠ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን፡፡ (የቤ/ክርስቲያኑ ዐጸድ እጅጉን ልብን የሚገዛና የሚማርክ)
40🙏2