ግንቦት 16 ተዝካሩ ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
በዚህችም ቀን የወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያው ነው። በእስያና በኤፌሶን በዙሪያቸው በአሉ አገሮች ሁሉ ስለ መስበኩና ከባሕር በመስጠምም ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር እስከ መለሳቸውና የክብር ባለቤት ጌታችን በእጆቹ ላይ በሚያደርገው ተአምራት በትምህርቶቹም ከሰይጣን ወጥመድ እስከ አዳናቸው ድረስ ጣዖታትን ከሚያመልኩ ከክፉዎች ሰዎች ስለደረሰበት መከራ ነው።
በሸመገለም ጊዜ ወንጌልን ጻፈላቸው ሦስቱ ወንጌላውያን ያስቀሩትን እስከሚጽፍ መንፈስ ቅዱስ አነሳስቶታልና የወልድንም አኗኗሩንና ሰው መሆኑን ዓለም የማይወስነውንም ተአምራቱን።
ከዚህም በኋላም ወደ ሰማይ እንደ ወጣና በሰማይ የሚኖሩ የመላእክት ሠራዊት ሥርዓታቸውን አይቶ አቡቀለምሲስ የሚባለውን ጻፈ።
ለስብከቱም የበዓሉ መታሰቢያ ሊሆን ግብጻውያን ይህን ሠሩ ዳግመኛም በእስክንድርያ አገር ውስጥ ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ቀን ነው።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።
ምንጭ - ስንክሳር
/ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

❤31🔥1
#ዜና_እረፍት
በደብራችን በጣም ለረጅም ዓመታት በተለያዩ አገልግሎቶች በቅንነት ሲያገለግሉ የነበሩት አባታችን አባ ገብር ሚካኤል ከዚህ አለም ድካም አረፉ ::
ስርዓተ ቀብራቸዉም ግንቦት 16/2018 ከቅዳሴ በኋላ በደብራችን ይፈፀማል።
"እግዚኦ አዕርፍ ነፍሰ መምህርነ ገብረ ሚካኤል"

😢63❤19🙏8
እንኳን ለታላላቆቹ አባቶች ለአቡነ ዓቢየ እግዚእና ለአቡነ ዮሴፍ ዓመታዊ በዓል (ግንቦት 19) በሰላምና በጤና አደሳችሁ፡፡
/#በጻድቃን_ተዓምራት_ማድረግ_ለምትጠራጠሩ፤ #ጻድቃን_ከበዓለ_ዕረፍታቸው_በኋላ_ዛሬም_ከማማለድም_አልፈው_በቃልኪዳናቸው_ተዓምራት_እንደሚያደርጉ_ኑና_እዩ_ተመልከቱ፡፡ ተዓምራትን ማየት ለምትፈልጉ ኹሉ ሂዳችሁ እዩ!!!!!)፡፡
ክብረ በዓላቸው (የአቡነ ዓቢየ እግዚእ በተንቤን መረታ ደብረ መድኃኒት፣ በጎንደር ከተማ ጥንታዊ በኾነው በዓቢየ እግዚእ ኪዳነምሕረት፣ በመቀሌ እንዳ ገብርኤል /እንዳ አቡነ ዓቢየ እግዚእ/፣ በአዲስ አበባ ሞጆ አካባቢ ባለው ቤ.ክ በድምት ይከበራል፡፡) እንዲሁም (የአቡነ ዮሴፍ በላስታ ላሊበላ በቅርብ ርቀት በሚገኘውና ወደ ላለበላ የሚጓዝ ኹሉ ሊያየው በሚችል በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘውና በኢትዮጵያ በከፍታ ከራስ ደጀን ተራራ ቀጥሎ በሚገኘው የዋሻ ገዳማቸው ይከበራል)፡፡
ሁለቱም ቅዱሳን አስካሁን ጊዜ ድረስ የሚታይ ባለ አስደናቂ የቃልኪዳን ተዓምራት አላቸው፤ አቡነ ዮሴፍ ከላሊበላ በቅርብ ርቀት በሚገኝ ገዳማቸው ጭላዳ እህል ጠባቂ ሳያሻው እህል እንዳይበላ ገዝተውታል፤ አቡነ ዐቢየ እግዚእ ቃል ኪዳን በተሰጣቸው ቦታ (ለምሳሌ በጎንደር ከተማ) አሁንም ድረስ ጅብ እንስሳቶችን እንዳይበላ ገዝተዋል፡፡
#አቡነ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋቱ (በወሎ ላስታ ሰውንና ዝንጀሮን በቃልኪዳን ያስተሳሰሩ #እስከዛሬ_ድረስ_ዝንጀሮ_እህል_እንዳይበላ_የገዘቱ፤ እመቤታችን ዕጣን እየሰጠቻቸው፤ ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ያጠኑ (እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባና አቡነ ዘርዓ ቡሩክ) ናቸው፤ ገዳማቸው በላሊበላ በቅርበት አቡነ ዮሴፍ ተራራ ተብሎ በሚጠራ ተራራ ቦታ ላይ የዋሻ ቤ.ክ አላቸው፡፡
#አባ_ዓቢየ_እግዚእ_፤
አባ ዓቢየ እግዚእ የተወለዱት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ትግራይ ተንቤን (መረታ) ውስጥ ነው:: የተባረኩ ወላጆቻቸው ያፍቅረነ እግዚእ እና ጽርሐ ቅድሳት ይባላሉ:: አጥምቀው 'ዓቢየ እግዚእ' ሲሉ ስም ያወጡላቸው የወቅቱ ዻዻስ ሰላማ መተርጕመ መጻሕፍት ናቸው:: ትርጉሙም "በጌታ ዘንድ ታላቅ ሰው" ማለት ነው::
ዓቢየ እግዚእ በሕጻንነታቸው ሌሊት ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ አድረው ቀን ቀን እየተማሩ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቁ:: ገና በወጣትነታቸው ወደ ታላቁ መነኮስ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ደብረ በንኮል ሔደው መንኵሰዋል:: በገዳሙ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ከኖሩ በኋላ ወደ ዋልድባ ሔደው የተሰወረች ቤተ ክርስቲያን አግኝተዋል:: በጊዜው በ40 ቀን አንዲት ቅጠል ብቻ ለቁመተ ሥጋ ይበሉ ነበር::
ከዚያም ወደ ሃገራቸው ተንቤን ተመልሰው ዛሬም ድረስ ድንቅ ሆኖ የሚታየውን ገዳም መሥርተው ብዙ መናንያንን አፍርተዋል:: ዓቢየ እግዚእ ገዳማዊና ጻድቅ ብቻ ሳይሆን ሐዋርያዊ አባትም ነበሩ:: ከትግራይ እስከ ደንቢያ ሃገረ ስብከታቸው ነው::
አንድ ጊዜ ደቀ መዛሙርትን አስከትለው ለስብከት ሲንቀሳቀሱ ተከዜ ወንዝ አካባቢ ደረሱ:: ቀኑ ነሐሴ 10 ነውና ተከዜ እስከ ገደፉ ሞልቶ ለ3 ቀናት ባለመጉደሉ ከ1,000 በላይ ሰዎች ሲያለቅሱ ደረሱ:: ጻድቁ ባካባቢው የነበሩት ኢ-አማንያን (አሕዛብ) ቢሆኑም ራርተዋልና "አምላከ ሙሴ" ብለው ጸልየው ወደ ጥልቁ ውስጥ ገቡ::
ቅዱስ ሚካኤል አብሯቸው ነበርና ተከዜ ግራና ቀኝ ተከፍሎ መሃሉ የብስ ሆነ:: ይሕን ድንቅ ያዩ ከ1,000 በላይ አሕዛብም አምነው በጻድቁ እጅ ተጠምቀዋል:: ይህም ዘወትር ነሐሴ 10 ቀን በቤተ ክርስቲያናቸው (ጐንደር) ይከበራል::
ከዚያም እያስተማሩ ጐንደር ደረሱ:: ያኔ ጐንደር በቀሃና አንገረብ ወንዞች የታጠረች አንዲት መንደር ነበረች:: ጻድቁ ቀን ቀን እየሰበኩ ማታ ዛሬ ቤተ ክርስቲያናቸው የታነጸበት ሥፍራ ላይ ሲጸልዩ ያድሩ ነበር:: በዚያ ዘመን ጐንደር ውስጥ ጅብ: እባብና መሰል አራዊት ገብተው ሕዝቡን ጨረሱት:: ይህንን የተመለከቱት አባ ዓቢየ እግዚእ ወደ እግዚአብሔር አለቀሱ:: በፍጹም ልባቸውም ስለ ሕዝቡ ለመኑ::
የለመኑትን የማይነሳ ጌታ ወደ ጻድቁ ቀርቦ "በስምሕ የተማጸኑ: በቃል ኪዳንህ ያመኑ: በምድር አራዊት አይሠለጥኑባቸውም:: በሰማይም እሳትን አያዩም:: ጐንደርንም አራዊት ገብተው ሰውን አይጐዱም::" ብሏቸው አርጉዋል:: ጻድቁም የወንጌል አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደ ገዳማቸው ተንቤን ተመልሰዋል::
አባ ዓቢየ እግዚእ በገዳማቸው ተንቤን ለብዙ ዘመናት በቅድስና ኑረው፥ 3 ሙታንን አስነስተው፥ ብዙ ድውያንን ፈውሰው፥ ብሔረ ብጹዓንን ጎብኝተው፥ የድኅነት ቃል ኪዳንም ተቀብለው፥ በ140 ዓመታቸው ግንቦት 19 ቀን አርፈዋል:: የጻድቁ ክብር ለሁሉ ነውና እባካችሁ እናስባቸው::
** አምላካችን በወዳጆቹ ምልጃ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይሠውርልን::
ሥርዐተ ማኅሌቱን ላልደረሰው በማድረስ ይተባበሩ፡፡
#ግንቦትት ፲፱፤ #በዓለ_ዐቢየ_እግዚዕ፡፡
#በመላው_ዓለም_የአቡነ_ዐቢየ_እግዚእ_በዓለ_ዕረፍት_ክብረ_በዓል_የሚከበርባቸው_፬ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
#በአዲስ_አበባ_የሚከበርባቸው_ #፪ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል (ብሥራተ ገብርኤል)፤
አድራሻው፤ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ፥ ብሥራተ ገብርኤል፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ(መርካቶ) → ሜክሲኮ → ብሥራተ ገብርኤል፤
፪. ኤረር ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ፤
(የአቡነ ዐቢየ እግዚእ ክብረ በዓልና የኤረር ጎሮ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ቅዳሴ ቤቱ)
አድራሻ፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ፥ ጎሮ፤
ታክሲ፤ ከፒያሳ (መገናኛ) → ጎሮ፡፡
#በኢትዮጵያና_በዓለም_አቀፍ_ደረጃ_የሚከበርባቸው_ #፪ #ገዳማትና_አድባራት፡፡
፩. ጎንደር ደብረ መድኃኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ፡፡
አድራሻ፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ጎንደር ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር ከተማ → አራዳ (ቀበሌ 16)፡፡
፪. ተንቤን መረታ ዐቢየ እግዚእ ገዳም፤
አድራሻ፤ ትግራይ ሀገረ ስብከት፥ ተንቤን፥ መረታ፤
ታክሲ፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → መቀለ → ተንቤን፡፡
ወይም፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → በአዲዓርቃይ (በዳንሻ ሁመራ) → ሽረ → አኵስም → ተንቤን፡፡
ኦ አበው ወእማት አኃው ወአኃት ኢትርስዑነ በጸሎተክሙ (በዘጸለይክዋ በዝንቱ ሥርዐተ ማኅሌት) ለትምህርተ ቤትነ ፍኖተ ሕይወት፡፡
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.
❤16🙏2