ዕርገተ እግዚእ
እንኳን ለጌታችን በዓለ ዕርገት አደረሳችሁ፥ አደረሰን፤ በዓሉን የሚመለከት ጽሑፍና ሥርዐተ ማኅሌቱን እንደተለመደው አቅርበንላችኋል፡፡ መልካም ንባብ፤ መልካም የምሥጋና ማኅሌት፡፡
‹‹አልቦ ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ ወልደ ዕጓለመሕያው፤ ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡›› ዮሐ.3፥13
ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡ እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው፡፡ ይህ ኃይለ ቃል ክብር ምስጋና ይግባውና ስለጌታችን፣ አምላካችን፣ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሰማየ ሰማያት መውረድ ከድንግል ማርያም መወለድ እና የሰውነቱን ሥራ ጨርሶ በክብር ወደ ሰማይ ማረጉን የሚገልጽ ነው፡፡ እንደሚታወቀው አምላካችን ስለሁለት ዐቢይ ጉዳዮች ሰው ሆኗል፡፡
1. *ለቤዛነት /ዓለምን ለማዳን/
2. *ለአርአያነት /ምሳሌነት/
የሰውን ልጅ በመውደዱ ልዑል ባሕርዩን ዝቅ አድርጎ ከሰማይ ወረደ ሥጋ ለበሰ በምድር ላይ ተመላለሰ፤ ምድርን በኪደተ እግሩ ቀደሰ፤ ድውያንን ፈወሰ፤ ፍጹም ሰው እንደ መሆኑ ተራበ ፍጹም አምላክ መሆኑንም ያስረዳ ዘንድ አምስት ገበያ ሕዝብ በአምስት እንጀራ በሁለት ዓሣ አጠገበ ማቴ.14፥19 ለእኛ አርአያና ምሳሌ ለመሆን ዝቅ ብሎ የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ ዮሐ.13፥14 እኛም ፍለጋውን እንከተል ዘንድ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ ለቢጽክሙ እናንተም ለባልንጀሮቻችሁ እንዲሁ አድርጉ ብሎ አዘዘ፡፡ መምሕረ ትሕትና ነውና በዚህ ዓይነት መልኩ ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር በዚህ ዓለም ኖረ ለሐዋርያት ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ወንጌልን አስተማራቸው ትምህርት በሚገባ ከተረዳለት በኋላ ለድኅነተ ዓለም በማዕከለ ምድር በቀራንዮ ተሰቀለ፡፡
#ወገብረ_መድኀኒተ_በማዕከለ_ምድር_እንዲል_በምድር_መካከል_መድኀኒትን_አደረገ_መዝ.73፥12
‹‹እስመ ኢይደልዎ ለነቢይ መዊት በአፍአ ዘእንበለ በኢየሩሳሌም፤ ነቢይ በኢየሩሳሌም ነው እንጂ በውጭ ሊሞት አይገባውም፡፡›› ብሎ እንደተናገረ፡፡ ሉቃ.13፥33 በሞቱ ዓለምን አድኖ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር አድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ብርሃነ መለኮቱን ገልጾ ተነሣ፡፡ ነቢያት እንደተናገሩ ‹‹እግዚአብሔር ይነሣል ጠላቶቹም ይበተናሉ››� መዝ.67፥1 ‹‹እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁ እግዚአብሔርም አስነሥቶኛልና ተነሣሁ፡፡›› መዝ.3፥5 ‹‹እግዚአብሔር አሁን እነሣለሁ ይላል መድኀኒትንም አደርጋለሁ በዕለቱም እገለጣለሁ››� መዝ.11፥5፡፡
‹‹ሥጋየ ደግሞ በተስፋ /በትንሣኤ/ ታድራለች ነፍሴን በሲዖል /በመቃብር/ አትተዋትምና/ እነሣለሁ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም፡፡›› መዝ.15፥9 ‹‹አቤቱ ንቃ ለምንስ ትተኛለህ ተነሥ ለዘወትርም አትጣለን›› መዝ.43፥23 ‹‹እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ›› መዝ.77፥65 ተብሎ የተተነበየውን ትንቢት ፈጽሞ ተነሣ፡፡ በሞቱ ሞታችንን ሻረልን፤ በመቀበሩም ሙስና መቃብርን አጠፋልን፡፡ ‹‹በሞቱ ሞትን አጠፋው›› እንዲል መጽሐፈ ኪዳን፡፡ ሕንፃ መነኮሳት ‹እርሱ በሁሉ ምሉዕ ሲሆን በመቃብር ለመቀበር ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ገንዘውት ታየ፡፡ ከመሬት ውስጥ በመቀበሩም ሙስና መቃብርን አጠፋ፤ ከሥሩም ነቀለው ከተነሣ በኋላ ትንሣኤውን መጀመሪያ ለማርያም መግደላዊት ገለጸ ማር.16፥9፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ትንሣኤው ሲመሰክር ‹‹ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፤ ተቀበረም፤ መጽሐፍ እንደሚል፤ በሦስተኛው ቀን ተነሣ፡፡ ለኬፋም ታየ በኋላም ለአሥራ ሁለቱ ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፡፡ ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ኋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ›› 1ቆሮ.15፥3-8 ብሎ ክርስቶስ ትንሣኤውን ለተከታዮቹ በሙሉ የገለጠ መሆኑን መስክሯል፡፡ የሚያምኑ ፈሪሳውያንም ‹‹ትንሣኤው ምትሐት ነው›› እንዳይሉ እየታየ እያስተማረ እስከ 40 ቀን ድረስ መቆየቱን ይገልጽልና፡፡ በዚህም የአርባ ቀን ከትንሣኤ በኋላ ቆይታው ሦስት ቀን ጉባኤ አድርጎ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ ቅዱስ ወንጌል ይነግረናል፡፡ ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥላቸው ይህ ሦስተኛ ጊዜ ነበረ እንዲል ዮሐ.21፥14 ይህንም ሊቃውንት አባቶቻችን፡-
1. *የትንሣኤ
2. *የአግብኦተ ግብር /ዳግም ትንሣኤ/
3. *የጥብርያዶስ ነው ብለው አስቀምጠውታል በዚህ 40 ቀን ቆይታ መጽሐፈ ኪዳንን ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሯል፡፡
ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስም ዕርገቱን ለመናገር ከሰማየ ሰማያት መውረዱን አስቀድሞ ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ማንም ወደ ሰማይ የወጣ የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው ብሎ ከዕርገቱ በኋላ በየማነ አብ፤ በዘባነ ኪሩብ በአምላክነት ሥልጣን ለመኖር ወደሰማይ የወጣ ከእርሱ በቀር ሌላ እንደሌለ አስረግጦ ነገረን፡፡ ሲጀምር ከሰማይ መውረዱን ማስቀደሙ ወረደ ብሎ ዐረገ ለማለት ይመቻል፡፡ ተጸነሰ ተወለደ ለማለት ጥንቱ ከሰማያት ወረደ ማለት እንደሆነ ሁሉ፤ ‹‹ተሰቀለ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤ ተነሣ'››ለማለት ‹‹ጥንቱ:- ተጸነሰ፤ ተወለደ፤ አደገ ተመላለሰ ሠላሳ ዓመት ኖረ›› የሚለው ነው፡፡ ስለሆነም ቅዱስ ዮሐንስ ጠርዝና ጠርዙን ይዞ ተናገረ፡፡ ‹‹ወረደ ዐረገ›› የሚሉት ሁለት ቃላት የዓለም ድኅነት መነሻና መድረሻ ናቸው፤ እነዚህን ሁለት ቃላት ስናይ በሁለቱ መካከል የተፈጸሙትን የአምላክ ሥራዎች ልብ ማለት ይገባል፡፡ ቤት በመሠረት ይጀመራል በጣሪያ ይፈጸማል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ይህን የቤዛነት ሥራ ሲያስረዳ በዮሐ.1፥14 ‹‹ቃል ሥጋ ኮነ፤� ቃል ሥጋ ሆነ›› ብሎ ጀምሯል ይህንም ቃል ‹‹ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም›› በማለት ሰው መሆኑን ብቻ ሳይሆን በአርያም የሚኖር መሆኑን አስተማረን፡፡ እንግዲህ ጌታችን ዕርገት እንዲሁ እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ አለመሆኑን ቀድሞ በነቢያት የተነገረ ኋላም በሐዋርያት የተመሰከረ መሆኑን ማወቅ ያስፈለጋል፡፡
#የክርስቶስ_ዕርገት_በትንቢተ_ነቢያት
‹‹ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም ጨለማ /ዲያብሎስ/ ከእግሩ በታች ነበር በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ በነፍሳትም ክንፍ በረረ››� መዝ.17፥9 ‹‹አምላክ በእልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ መዝ.46፥5 ወደላይ ዐረግህ፥ ምርኮን ማረክህ ፥ስጦታንም ለሰዎች ሰጠህ›› መዝ.67፥18፡፡
‹‹ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ፤ በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ›› መዝ.67፥33፡፡
#የክርስቶስ_ዕርገት_በትምህርተ_ሐዋርያት
ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ፡፡ ማር.16፥19 ‹‹እስከ ቢታንያ አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ፡፡››� ሉቃ.24፥50 ‹‹ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ ደመናም ከዐይናቸው ሰውራ ተቀበለችው፤ እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ እነሆ ነጫጭ ልብስ ለብሰው ሁለት ሰዎች /መላእክት/ በአጠገባቸው ቆሙ ደግሞም ‹‹የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት ዳግመኛ ይመጣል፡፡›› አሏቸው››� ሐዋ.1፥9-12 በማለት ሐዋርያት የክርስቶስን ዕርገት ከመላእክት ጋር ሆነው

❤21🤝1
እንደተመለከቱ ደስታውን እንደተካፈሉ ቅዱስ ሉቃስ ጽፎልናል፡፡ በትንሣኤው ነጭ ልብስ ለብሰው የታዩ መላእክት የደስታ ዘመን ነው ሲሉ በእርገቱም ነጭ ልብስ ለብሰው የዕርገቱን የምሥራች ለሐዋርያት አብስረዋል፡፡
/ምንጭ፤ የቃል ትምህርትና በመምህር ምሥጢረ ሥሳሴ ማናየ/
የአምላካችን ቸርነቱ ረድኤቱ አይለየን፡፡፠ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፠
/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/
• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott
• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

❤11🙏2👍1
ግንቦት 16 ተዝካሩ ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
በዚህችም ቀን የወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያው ነው። በእስያና በኤፌሶን በዙሪያቸው በአሉ አገሮች ሁሉ ስለ መስበኩና ከባሕር በመስጠምም ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር እስከ መለሳቸውና የክብር ባለቤት ጌታችን በእጆቹ ላይ በሚያደርገው ተአምራት በትምህርቶቹም ከሰይጣን ወጥመድ እስከ አዳናቸው ድረስ ጣዖታትን ከሚያመልኩ ከክፉዎች ሰዎች ስለደረሰበት መከራ ነው።
በሸመገለም ጊዜ ወንጌልን ጻፈላቸው ሦስቱ ወንጌላውያን ያስቀሩትን እስከሚጽፍ መንፈስ ቅዱስ አነሳስቶታልና የወልድንም አኗኗሩንና ሰው መሆኑን ዓለም የማይወስነውንም ተአምራቱን።
ከዚህም በኋላም ወደ ሰማይ እንደ ወጣና በሰማይ የሚኖሩ የመላእክት ሠራዊት ሥርዓታቸውን አይቶ አቡቀለምሲስ የሚባለውን ጻፈ።
ለስብከቱም የበዓሉ መታሰቢያ ሊሆን ግብጻውያን ይህን ሠሩ ዳግመኛም በእስክንድርያ አገር ውስጥ ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ቀን ነው።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።
ምንጭ - ስንክሳር
/ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል።/

❤31🔥1
#ዜና_እረፍት
በደብራችን በጣም ለረጅም ዓመታት በተለያዩ አገልግሎቶች በቅንነት ሲያገለግሉ የነበሩት አባታችን አባ ገብር ሚካኤል ከዚህ አለም ድካም አረፉ ::
ስርዓተ ቀብራቸዉም ግንቦት 16/2018 ከቅዳሴ በኋላ በደብራችን ይፈፀማል።
"እግዚኦ አዕርፍ ነፍሰ መምህርነ ገብረ ሚካኤል"

😢63❤19🙏8