Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
✞   የሰሙነ ፋሲካ የመጀመርያው    #ረቡዕ#አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡
ከሞተና ከተቀበረ አራት ቀን በኋላ ከመቃብር ጠርቶ ላሥነሣው፣ አላዓዛር መታሰቢያ የእርሱንም ተነሥቶ በማየት በጌታችን ብዙ ሕዝብ ስለአመነበት ቀኒቱ «አላዓዛር» ተብላ ትታሰባለች፡፡ ዮሐ. 11-38-46

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
35
የሰሙነ ፋሲካ የመጀመርያው  #ሐሙስ#አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡ የአዳም ተስፋው ተፈጽሞለት ከነልጅ ልጆቹ ወደቀደመ የገነት ክብሩ ለመግባቱ መታሰቢያ ሆና «የአዳም ሐሙስ» ተብላ ይኸው ትከበራለች፡፡ ሉቃ. 24-25-49

በአዲስ አበባ የሚነግሥበት ብቸኛው በስሙ የተሰየመ የአቡነ አዳም ወሔዋን ቤተ ክርስቲያን

፨> ለቡ መርጡለ አርሴማ ወአቡነ አዳም ቤ/ክ
አድራሻ፦ ከፒያሳ - ሜክሲኮ - ለቡ ጋርመንት መብራት ኀይል


/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
27
✞  የሰሙነ ፋሲካ የመጀመርያው #ዓርብ#ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በክርስቶስ ደም ተዋጅታ በተመሠረተችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታላቅ መታሰቢያ በመሆኗ በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ዓርብ «ቤተ ክርስቲያን» ተብላ ትጠራለች፡፡  ማቴ. 26 ÷ 26-29 ሐዋ 20-28

በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
32
✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡
በሰሙነ ፋሲካው ያለችው ቀዳሚት ሕዝቡ ከአንዳንዱ በስተቀር ገበያ እንኳን ስለማይገበይባት «የቁራ ገበያ» የገበያ ጥፊያ ስትባል በቤተ ክርስቲያን ግን በዘመነ ሥጋዌው በገንዘባቸውና ጉልበታቸው ለአገለገሉት በስቅለቱ ዋይ ዋይ እያሉ እስከ ቀራንዮ ለተከተሉት፣ የትንሣኤው ዕለት ገና ከሌሊቱ ወደ መቃብሩ ሽቱና አበባ ይዘው በመገሥገሣቸው ትንሣኤው ከሁሉ ቀድሞ ለተገለጸላቸው ቅዱሳት አእንስት መልካም መታሰቢያ ሆና «አእንስት» ተብላ ትጠራለች፡፡ ሉቃ. 23-27-33፣ 24-1-01፣ ማቴ. 25-1-11

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
34
✞ እሑድ- ዳግማይ ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ዳግም ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

+ + + መልካም በዓል!!! + + +

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
39👏2🙏2🥱1
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
Photo
መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓዱ አምላክ አሜን!

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ፤ ብፁዕ ኣቡነ ዲዮስቆሮስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ  የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን ኣበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፣ በአጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተገኛችሁ በሙሉ፦
ማሕየዊት በምትሆን ሞቱ ሰማያውያንና ምድራውያንን ያስታረቀ፣ በቅድስት ትንሣኤውም የሙታንን ሕይወት በተስፋ ያለመለመ ጌታችን፣ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እንኳን ለዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አደረሰን አደረሳችሁ!
“እስመ ተዋለጠ እግዚአብሔር ዓለመ በክርስቶስ ኣናኅስዮ ኃጢኣቶሙ ወኢነጺሮ ጌጋዮሙ፤ ወረሰየ ላዕሌነ ቃለ ሥምረቱ፤ ወወሃበነ መልእክተ ሣህሉ፡- እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውን ኣይቈጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል ኣኖረ” (2ቆሮ. 5፥19)።
የእግዚአብሔርም ልጅ፣ የሰውም ልጅ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም በሰብእነት ሲገለጽ ግልጽ የሆነ ዓላማና ግብ እንደነበረው ቅዱስ መጽሓፍ ይነግረናል፤ እሱም በሰማይም፣ በምድርም ያሉትን በሙሉ ማስታረቅ፣ ማገናኘትና ኣንድ ማድረግ ነበረ፤
ጌታችን ይህንን ሲያደርግ ሰማያውያኑንና ምድራውያኑን የለያየው ምክንያት በማስወገድ ነው፤ የመለያየቱ ምክንያት ክፉ ኅሊና ኣምጦ የወለደው በደልና እሱን ተከትሎ የተከሠተው ኃጢኣት ነበረ፤ በኃጢኣት ምክንያት የገባው ሞት ደግሞ የቅጣቱ ማሳያ ፍርድ ነበረ።
የመጀመሪያዎቹ ሰዎች በፈጸሙት ስሕተት መነሻነት ምድርንና ምድራውያንን ለከባድ ቅጣትና መርገም የዳረገው ይህ መለያየት ለሰማያውያኑም ተርፎኣል፤
ምክንያቱም መለያየቱ በእግዚአብሔርና በሰው፣ በመላእክትና በሰው፣ በሰውና በሰው፣ በነፍስና በሥጋ ጭምር የጥል ግድግዳን ገንብቶ እስከ ክርስቶስ ዕለተ ስቅለት መዝለቁን በቅዱስ መጽሓፍ የምናውቀው ስለሆነ ማለት ነው።
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት!

ቀዳማዊና ዘላለማዊ የሆነው ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሰብእናችንን ተዋሕዶ በዚህ ዓለም የተገለጸው ሰማያውያንንና ምድራውያንን የለያየው  የጥል ግድግዳን ለማፈራረስ ነው፤
ለመለያየት ምክንያት የሆነችውን ኃጢኣት በሰውነቱ በመቅጣት የሕግን ትእዛዝ ከፈጸመ በኋላ የዕርቁን ተግባር በወሳኝ መልኩ ኣከናውኖታል፤
በክርስቶስ ቤዛነት የሆነው ይህ ዕርቅ በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የተወደደ ነበረና እሱ ራሱ በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ኣስታረቀ፤
ለዚህም ነው ተበዳይ እሱ፣ ቤዛዊ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበው እሱ፣ ኣስታራቂ እሱ፣ ታራቂ እሱ ሆኖ የምናገኘው፤ ለሱ የሚሳነው ነገር የለምና ለኛ ግር የሚል ቢመስልም ለሱ ቀላል ነበረ።
በዚህ የዕርቅ ተግባር ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሰውና ሰው፣ ነፍስና ሥጋ ታርቀው በይፋ ተገናኙ፤ በኅብረትና በኣንድነትም መኖር ቻሉ፤ በቀኙ ለተሰቀለው ሽፍታ “ዛሬውኑ ከኔ ጋር በገነት ትኖራለህ” የሚለው ቃለ ምሕረትና “ኣባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ ኣደራ እሰጣለሁ” የሚለው ቃለ አማሕፅኖ የዕርቁ፣ የግንኙነቱና የኣንድነቱ ማሳያ ኣስረጅ ናቸው።
ስቅለተ ክርስቶስ ነፍሶቻችን ወደ ግዞት ቤት ሳይሆን ወደ ገነት እንዲገቡ፣ የሚቀበላቸውም ራሱ እግዚአብሔር እንዲሆን ያስቻለ ታላቅ መለኮታዊ ፍጻሜ ነው፤
እኛ “ክርስቶስ መድኃኒታችን ነው፤ አድኖናል” ብለን በልበ ሙሉነት የምንመሰክረው፣ እሱም “ሰላሜን ሰጠኋችሁ” ብሎ የሚያረጋጋን በመሰቀሉ ይህንን ውጤት ስላስገኘልን ነው።
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት!
የድኅነታችንና የሰላማችን መሠረት የሆኑትን የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ለዓለም ማኅበረ ሰብ የማብሰርና የማሥረጽ ተግባር የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቍጥር አንድ ተልእኮ ነው፤
ነገረ ሞቱና ነገረ ትንሣኤው በአስተውሎት፣ በጥልቀትና በተመሥጦ ስናስተምር በውስጡ የምናገኘው የዕርቅ፣ የሰላምና የአንድነት ምስጢር ነው፤
እንደ እውነቱ ከሆነ እኛ የክርስቶስ መልእክተኞች እንደ ቃሉ ራሳችንን ክደን በሚጠበቀው መጠን ተልእኮኣችንን መወጣት ብንችል ኖሮ፣ አሁን በዓለማችን የተፈጠረው መለያየትና ግጭት ኣይኖርም ነበር፤
ችግሩን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ባንችልም በእጅጉ መቀነስና ዓቅሙን ማዳከም እንችል ነበር፤ ነገር ግን ተልእኮኣችንን በኣግባቡ ኣለመወጣት ኣንድ ነገር ሆኖ የዓለሙ መሳሪያ ሆነን መገኘታችን “በዕንቅርት ላይ…” ሆኖ ይስተዋላል።
ይሁንና ኣሁንም ሕዝቡን ወደ ኣንድነት፣ ወደ ፍቅር፣ ወደ ሰላም፣ ወደ ዘላቂ የጋራ ጥቅምና ወደ ፈሪሐ እግዚአብሔር ማምጣት የጉባኤያችን ዓቢይ ተግባር ሊሆን ይገባል፤ እነዚህ ካሉ የምናጣውም ሆነ የሚያመልጠን የለምና ነው፤ ሃገርን በኃላፊነት ተረክባችሁ በላዕላዊ፣ በማእከላዊና በታሕታዊ መዋቅር የምትገኙ፣ እንደዚሁም ኣማራጭ ሓሳብ ኣለን ብላችሁ የምትንቀሳቀሱ ልኂቃነ ሃገር ፣ ሁላችሁም እግዚአብሔርን ከሚያውቅ፣ ከሚያመልክና ከሚፈራ ሕዝብ የተገኛችሁ ናችሁና በልባችሁ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ድምፁንም ስሙ፤ የሱ ገንዘብ በሆኑ ፍጡራንም ኣትጨክኑ፤ ሰውን መያዝ የሚቻለው ኅሊናን በመርታት እንጂ በሌላ ኣይደለምና፣
የሕዝቡን ፍላጎትና የልብ ትርታ በሚገባ ኣዳምጡ፤ ሕዝቡ የሚፈልገው በኣንድነትና በእኩልነት መኖር፣ በሰላም ወጥቶ መግባት፣ ፍትሕን ማስፈን፣ ለኑሮው የሚበቃ ምጣኔ ሃብትን ማግኘት፣ የእምነት ነጻነትና እኩልነት መረጋገጥ የመሳሰሉት ናቸው።
ሕዝቡ እነዚህ ከተሟሉለት ተደመጠ ማለት ነው፤ ከተደመጠ ደግሞ እሱም በበኩሉ ያደምጣል፤ ይከተላልም፤
ስለሆነም ለሁሉም ልጆቻችንና ወገኖቻችን የምናስተላልፈው ወቅታዊ ጥሪ  ሁሉንም ችግሮቻችን በሰላምና በሰላም ብቻ ለመፍታት ተባበሩ የሚል ነው፤ ከዚህ ውጭ የሚደረገው ኣማራጭ ሁሉ ለዘላቂ ሰላማችን አይበጅም እንላለን።

           በመጨረሻም፦
በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያ አምስተኛው ቀን የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት የተጀመረ መሆኑን ለሕዝበ ክርስቲያኑና ለመላው ኢትዮጵያውያን እናበስራለን!!!
እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክ!

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
አሜን!!!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤

ሚያዝያ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ ኣበባ - ኢትዮጵያ
35
ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ

ማርቆስ የሚለው ስም ሦስት ፍቺዎች አሉት ንብ፣ አንበሳና ካህን::
*ንብ የሚለው ፍቺ የተሰጠው ንብ አበባ ካለው ተክል ሁሉ ቀስማ ማር እንድትሠራ እርሱም ቀድሞ ከጌታ ኋላም ከጌታ የተማርኩት ይበቃኛል ሳይል ከሐዋርያት ተምሮ ደገኛይቱን ወንጌልን በማስተማሩና በመጻፉ ነው፤
*አንበሳ መባሉ አንበሳ እንስሳት አራዊትን በክርኑ እንዲሰብር፤ በግብጽ ይመለኩ የነበሩ በእንስሳ አምሳል የተሠሩ ጣዖታትን በወንጌል ቃል ኃይልነት በማጥፋቱ ነው፡፡
*ካህን የሚለው ትርጉም ደግሞ በሐዋ. 14፥13 “ወአምጽኡ ማሬ ዘድዮስ” ተብሎ ከተመዘገበው መጽሐፍ ቅዱሳዊ አሳብ የተወረሰ ነው::
ማርቆስ ከመባሉ በፊት ዮሐንስ ይባል የነበረ ሲሆን ቁጥሩ ከ72ቱ አርድዕት ነው፤ ሐዋ. 12፥12፡፡ አባቱ አርስጦቦሎስ እናቱ ማርያም ይባላሉ:: እናቱ ማርያም በጌታ ትምህርት አምነው ሲከተሉትና ሲያገለግሉት ከነበሩት ደጋግ ሴቶች አንዷ ስትሆን ከጌታ ትንሣኤ በኋላ ቤቷን ለወንጌል አገልግሎት ሰጥታ ሐዋርያት በዚያ ተሰብስበው ለጸሎት ይተጉ ነበር፥ ጌታ ባረገ በ10ኛው ቀን (በተነሣ በ50ኛው ቀን) ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር በአንድነት ሳሉ መንፈስ ቅዱስን የተቀበሉትም በዚሁ በማርቆስ እናት በማርያም ቤት ውስጥ ነው፡፡ ሐዋ. 2፥1 ፤ 12፥12፡፡
የራሱን ሀገረ ስብከት ይዞ ማስተማር ከመጀመሩ በፊት ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያትን እየተከተለ ይማር ፥ በተልእኮም ይራዳቸው ነበር:: ከቅዱስ ጳውሎስ መጠራት በኋላ ጳውሎስንና አጎቱ በርናባስን ተከትሎ በአንጾኪያ ፤ ቅዱስ ጴጥሮስን ተከትሎ በሮም አስተምሯል፤ እነርሱም በመልእክቶቻቸው “ማርቆስ ሰላም ይላችኋል” እያሉ አንስተውታል:: ሐዋ. 12፥25፣ ቈላ. 4፥10፣ 1ኛ ጴጥ. 5፥13
በሮም ተልእኮው ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ሳለ ቅዱስ ጴጥሮስ ከፍጹምነት መድረሱን ዐውቆ ጵጵስና ሾሞ ከሀገረ ስብከቱ ግብጽን ከፍሎ አስተምር ብሎ ሰጠው:: እርሱም ሊያስተምር ሄዶ ወደከተማ ሊገባ ሲቃረብ የጫማው ጠፍር ተበጥሶበት አንያኖስ ወደሚባል ጫማ ሰፊ ሄደና ስፋልኝ ብሎ ሰጠው። አንያኖስ ጫማውን ተቀብሎ ሲሰፋ መስፊያው እጁን ወግቶት “ኢስ ታኦስ” ብሎ ጮኸ “አሐዱ እግዚአብሔር” ማለት ነው፤ የጠራኸውን ታውቀዋለህን? አለው፥ ሲሉ ሰምቼ እንጂ ያስተማረኝስ የለም አለው:: ቅዱስ ማርቆስም ፈቃደኛነቱን አይቶ አስተማረው አንያኖስም ከነቤተሰቦቹ አምኖ ተጠመቀ::
ከዚህ በኋላ አንያኖስን አስከትሎ በከተማ እየተዘዋወረ ያስተምር ጀመረ፤ ሕዝቡም ትምህርቱን ሰምተው ፥ ተአምራቱን አይተው አመኑ ተጠመቁ፤ አብያተ ጣዖታቱንም አፈራርሰው አብያተ ክርስቲያናትን ሠሩ። በዚህ ጊዜ የጣዖታቱ አገልጋዮች የለመዱት ቢቀርባቸው በጠላትነት ተነሡበት:: ምእመናኑ ተሰብስበው አባታችን እንድትለየን አንሻም፤ ነገር ግን ገነውተ ጣዖታቱ በጠላትነት ተነሥተውብሀልና ቁጣቸው እስኪበርድ ጥቂት ጊዜ ወደ ሌላ ሥፍራ ሄደህ ቆይ አሉት:: አንያኖስን ኤጲስቆጶስ ልጆቹን ቄስና ዲያቆን አድርጎ ሾሞላቸው፤ በባርቃና በሌሎች 5 አውራጃዎች እየሰበከ ቅዱስ ጴጥሮስን ለመጠየቅ ወደሮም ሄደ፤ በዚያ ሆኖ በስብከቱ ያመኑ የእስክንድርያ ምእመናን የተማሩትን እንዳይዘነጉ የማርቆስ ወንጌል ተብሎ የሚታወቀውን ወንጌል በሮማይስጥ ቋንቋ ጽፎ ልኮላቸዋል:: ዘመኑ ጌታ ካረገ 11ኛው ሲፈጸም 12ኛው ሲጀመር ፥ ቀላውዴዎስ ቄሳር በነገሠ በ4ኛው ዓመት /45-46ዓ.ም. ባለው ጊዜ/ ነው::
ከጥቂት ዓመታት ቆይታ በኋላ ወደ ግብጽ ተመለሰ፥ ምእመናኑ በቊጥር በዝተው፥ በእምነት ጐልምሰው አግኝቷተቸው ደስ ብሎት እያስተማራቸው አብሯቸው ጥቂት ጊዜ ቆየ:: በዓለ ትንሣኤን በሚያከብሩበት ቀን አምልኮ ጣዖት ከስሞ አምልኮተ እግዚአብሔር በመስፋፋቱ ምቀኝነት ያደረባቸው ጣዖታውያን ሊጣሉት መጡ፤ ምእመናኑ አባታችን ሽሽ አሉት፤ እንግዲህስ በጌታዬና በአምላኬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ወንጌል ክብር መከራ ልቀበል እንጂ ልሸሽ አይገባኝም አልሸሽም አለ:: እንደ ላም በአንገቱ ገመድ አስረው በረሀ ለበረሀ ሲጐትቱት ዋሉ ፥ ሥጋው በእሾህ በጋሬጣ ተቀረደደ:: ወደጌታ ቢያመለክት ስለተቀበልኸው መከራ ክብርህን ከ12ቱ ደቀመዛሙርቴ ክብር አንድ አድርጌልሀለሁ፤ በስምህ የተማፀነኝንም እምርልሀለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገብቶለት ነፍሱን በቃለ አቅርንት፥ በይባቤ መላእክት አሳርጓታል:: በሞቱ ያልረኩት ጣዖታውያኑ ከሞተም በኋላ ሥጋውን ለማቃጠል ሽተው እንጨት ሰበሰቡ የሚያቀጣጥልላቸውን ዝፍትም በከመሩት እንጨት ላይ አርከፈከፉ፤ ጌታ ግን ይህን እንዲያደርጉ ዕድል አልሰጣቸውም ድንገት ታላቅ ነጐድጓድ ሆነ ፥ የተከማቹበት ሥፍራ ተናወጸ፥ የፀሐይም ብርሃን ተሠወረባቸው፤ በዚህ ጊዜ ምን መጣብን ብለው ማቃጠሉን ትተው ሸሽተዋል:: ኋላ ግን ምእመናን በመብረቅ ጸዳል ተከብቦ አግኝተው በክብር ሥጋውን በአሌክሳንድርያ ቀብረውታል::
በዚህ ቦታ ተቀብሮ ለብዙ ዘመን ከቆየ በኋላ በ820 ዓ.ም ሁለት የቬኑስ ነጋድያን አጽሙን በድብቅ ከተቀበረበት አስወጥተው ወደ ቬነስ ነጋድያን አጽሙን በድብቃ ከተቀበረበት አስወጥተው ወደ ቬነስ ወሰዱት በዚህ ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን አኑረውት ቦታው የበላይ ቅዱስ ሆኖ በክብር ይኖር ነበር። ስለሆነም የግብጽ ቤተ ክርስቲያን እንዲሰጣት በየጊዜው ከመጠየቅ አልቦዘነችም ነበር። ግርማዊ ንጉሠ ነገሥታት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴም የሮማው ርዕሠ ሌቀ ጳጳስ ጳውሎስ 6ኛ ስለፈቀዱ በሞተ በ1900 በተወሰደ 1140 ዓመት ወደ ጥንተ ቦታው ለመመለስ በቃ። አጽሙም ሰኔ 17 ቀን 1960 ዓ.ም ተመለሰ ሲመለስም ጃንሆይም በስፍራው ተገኝተዋል፡፡

ቅዱስ ማርቆስ በሰማዕትነት ሲያርፍ የ70 ዓመት አረጋዊ ነበረ:: ከ30 ዓመታት በላይ በዘለቀ መዋዕለ ስብከቱ ለዓለም ሁሉ የምስራች የሚሆን የወንጌልን ቃል ከመጻፉ ባሻገር ከሐዋርያዊ ተልዕኳቸው የተነሣ ብርሃናተ ዓለም ከተባሉ ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር በብዙ አህጉረ ስብከት ተዘዋውሮ በማስተማሩና ይልቁንም የጥንት ግሪክ ሥልጣኔ ተስፋፍቶባትና የሮማ ሥርወመንግሥት ቁልፍ የፓለቲካና የንግድ መዲና በነበረችው እስክንድርያ በሰማዕትነት እስካረፈባት ቅጽበት ድረስ በአንደበቱም በሕይወቱም በክብሩና በመከራው ሁሉ በማስተማር አይሁድን ከይሁዲነት ወደ ክርስቲያንነት ፥ አረማውያንን ከአምልኮ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የመለሰ እንዲሁም በጸሎታቸው የሚጠብቁ፥ በትሩፋታቸው የጽድቅን ዋጋ የሚያሰጡ የባሕታውያን አባት አባ ጳውሊን፣ የመነኰሳት አባት አባ እንጦንስን፣ አባ ጳኩሚስ እና አባ ሰራብዮንን፤ መናፍቃንን ተከራክረው የረቱ ሃይማኖትን ያቀኑ ቅዱስ እለእስክንድሮስን ፥ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊን ፥ ቅዱስ ቄርሎስን፥ ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪትና ቅዱስ ዲዮስቆሮስን የመሳሰሉ ኦሮቶዶክሳውያን ሊቃውንትንና እስከ ዛሬም መከራ ሳይበግራቸው፥ ሞትና ግርፋታቸውን እንደ ክብር ቈጥረው፥ በሃይማኖታቸው ፀንተው የሚኖሩ የጸኑ ምእመናንን ያፈራች አንፀባራቂ ስም ያላት ኦርቶዶክሳዊትና ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን ያቋቋመ ሐዋርያ በመሆኑ ዳግመኛም ከአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን /4ኛ ክ/ዘ/ እስከ አቡነ ቄርሎስ /20ኛ ክ/ዘ/ ድረስ የኢትዮጵያን ቤተክርስቲያን በክህነት የመገቡ 111 ጳጳሳት ቅዱስ ማርቆስ ወንጌላዊ ያቋቋማት የዚህችው ቤተክርስቲያን ፍሬዎች በመሆናቸውና ትምህርታችን ከትምህርታቸው ሥርዐታችን ከሥርዓታቸው
11👍1
የተስማማ ፥ የተግባባ በመሆኑ “ማርቆስ አባታችን ፥ እስክንድርያ እናታችን” ማለት በኢትዮጵያውያን ምእመናን ዘንድ የተለመደ ነበር፥ ታሪክ ነውና ዛሬም ቢሆን ቤተክርስቲያናችን ሙሉ በሙሉ ከግብጽ ቤተክርስቲያን ጥገኝነት ተላቃ በኢትዮጵያውያን ጳጳሳት ብትመራም ይህ እውነታ የሚዘነጋ አይደለም::
ምንጭ፤ በመምህር ኅሩይ ኤርምያስ ለለቩርዝቡርግ ቅዱስ ማርቆስ ሰ/ት/ቤት ዓመታዊ በዓል የተዘጋጀ ታኅሣስ ፳፻ወ፬ ዓ.ም.
“የአጤ ኃይለ ሥላሴ ታሪክ” ከሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 1132 ላይ
/የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት፡፡/
የምትመለከቷቸው ቤተ ክርስቲያናት፤
ሰላ ድንጋይ ቅዱስ ማርቆስ፤ በአፄ ምኒልክና የተሠራና የአቡነ ማቴዎስ መንበረ ጵጵስና የነበረ፤ በልዩ አሠራር በ42 ቆመ ብእሲ (ዐምድ) የታነጸ፡፡
መናገሻ ቅዱስ ማርቆስ፤ በአቡነ ማቴዎስ የተሠራና መንበረ ጵጵስና የነበረ፤ ውጭው ክብ ውስጡ ግን ልዩና ድንቅ በሆነ አሠራርና ሥዕላት የተሞላ፡፡
ጎጃም ደብረ ማርቆስ፤
መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ፤ በአፄ ኀይለ ሥላሴ ከቤተ መንግሥታቸው ላይ ቦታ ቀንሰው ያነጹት ቤ.ክ.

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
10😢1