Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
15.3K subscribers
14.7K photos
78 videos
156 files
1.71K links
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።
Download Telegram
ዐጤ ኃይለ ሥላሴም ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ በኋላ በ6 ኪሎ ለሰማዕታቱ ሐውልት ቆመ መጀመሪያ የተሠራው አነስተኛ በመሆኑ ኋላ አሁን ያለው ትልቅ ተደርጎ ተሠርቷል፡፡ ቀኑ እንዳይረሳም ቤተ ሳይዳ ተብሎ ይጠራ የነበረው የካቲት 12 ሆስፒታል ተባለ፡፡ ከ8 ዓመት በኋላም የሰማዕታቱንም ዐፅም ሰብሰብሰበውና አፍልሰው በ4ኪሎ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በክብር እንዲያርፍና መቃብር ቤት እንዲሠራለት ተደረገ፡፡ በሐውልቱ ላይ ያለው ጽሑፍና ግጥም እንዲህ ይነበባል፤
#‹‹ዝንቱ ውእቱ ምዕራፈ አዕጽምቲሆሙ ለብዙኃን ኢትዮጵያውያን እለ ተቀትሉ በግፍዕ በእደዊሆሙ ለሕዝበ ኢጣሊያ ፋሽስታውያን አመ ፲ወ፪ ለየካቲት በ፲ወ፱፻፳ወ፱ ዓ.ም.፤ ወተቀትሎቶሙኒ ኮኑ በውግረተ አእባን ወበአብትር፥ በመክርይ ወበመስኤ፥ በመሕፄ ወበዕፀው፥ በመብረቀ ሐፂን ወበፀዓዕ፥ ወበውዕየተ እሳት ውስተ ቤቶሙ፡፡ ወበራብዕ ዓመት እምዘኮነ ዝንቱ ነገረ ግፍዕ ተመይጠ እግዚእነ  ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ እም ሀገረ ብሪታንያ በግርማ መዊዕ፤ ወአቲዎ ብሔሮሙ ሠረዎሙ ለጸላእትነ ወአቀመ ትእምርተ ግዕዛንነ፡፡ ወእምድኅረዝ አዘዞሙ ለኅሩያኒሁ ከመ ያስተጋብኡ አዕጽምቲሆሙ ለእሉ እለ ተቀትሉ በግፍዕ ወያንብርዎሙ ውስተ ዝንቱ መካን ቅዱስ ዘሕኑፅ ለዝክረ ነገር ወለዝክረ ስሙ፤ ወኮነ በዓለ ፍልሰቶሙ ወተጋብኦቶሙ ለእሙንቱ አዕጽምተ ምውታን በ፲ወ፬ ዓመተ በዓለ ንግሡ ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትየጵያ አመ ፳ወ፫ ለጥቅምት በዕለተ ኀሙስ በ፲ወ፱፻፴ወ፯ዓ.ም.፡፡››
#ራስን ካንገት ላይ ቈራርጦ እየጣለ፤
በችንካር ቸንክሮ ሰው እየገደለ፤
ሰውን ከነቤቱ አብሮ እያቃጠለ፤
ማነው እንደ ፋሽስት በሰው ግፍ የዋለ?፡፡
ሥጋችንን ገድለው ሳይቀብሩ እየጣሉ፤
ስማችንን ገድለው ሊቀብሩት ከጀሉ፡፡
በዚህ ያልነበሩ ሐሰት እንዳይሉ፤
እሊህ አስከሬኖች ይመሰክራሉ፡፡
ይህን ታላቅ ስቃይ መከራና ግፍ፤
ሲያስታውስ ይኖራል የታሪክ መጽሐፍ፡፡
አትርሱት አንርሳው ያስታውሰው ዘራችን፤
ኢጣሊያ መሆኗን መርዛም ጠላታችን፡፡
እናንት አእጽምቶች ዕድለኞች ናችሁ፤
በኃይለ ሥላሴ ትንሣኤ አገኛችሁ፡፡
5👍1
ቅድስት፤ የዐቢይ ጾም ሁለተኛው ሳምንት ቅድስት ይባላል፡፡

‹‹ሰንበትየ ቅድስት›› የሚልና ይህን የመሰለ የሰንበትን ቅድስና የሚያዘክር ምስጋና የሚቀርብበት ሳምንት ነው፡፡ በተጨማሪ ቅድስት የተባለበት ምክንያት ለ40 ቀን ጌታችን ጾም የጀመረበት ሳምንት ስለኾነም፤ ቅድስት ጾሙን ለማዘከር ቅድስት ተብሏል፡፡

‹‹የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ፡፡›› ዘዳ 20፥8 ይህን ቃል እግዚአብሔር በሊቀ ነቢያት ሙሴ ላይ አድሮ ተናግሮታል፡፡ ‹‹ዕረፍባት›› ያለው እግዚአብሔር የፍጥረቱን አቅም ስለሚያውቅ ነው፡፡ ስናከብር ለነፍስ ዕረፍትና ፍስሐን፤ ለሥጋ በረከት ሊያሰጡ የሚችሉ ሃይማኖታዊ ተግባራትን በመፈጸም የሚከበር ነው፡፡ በቤተክርስቲያን በመሰባሰብ ቃለ እግዚአብሔርን በመስማት /በመማር/፣ ንሰሐ ገብቶ ቅዱስ ቁርባን በመቀበል፣ የተጣላ በማስታረቅ፣ ያዘነ የተከዘ በማረጋጋት በማጽናናት የታሰረን በመጠየቅ፣ በችግር የወደቁትን በመጎብኘት በአጠቃላይ በማቴ 25፥35-37 ላይ የተጠቀሱትን ምግባራት በመፈጸም ከተከበረ ከእግዚአብሔር ዘንድ የማያልቅ ዘላለማዊ በረከትን ያስገኛል፡፡ ኢሳ 56፡4-8 ይህችን ዕለት የናቁ ሰዎች በሞት ተቀጥተዋል፡፡ ዘኁ 15፡32-36፡፡

ሰንበትን እንደምናከብረው ኹሉ በየ49 ዓመታት ደግሞ እንኳን ሰው መሬትም ከሚያርሱባት እንድታርፍ ኢዮቤልዩ አድርጎ ሰጥቶናል፤ መሬትን ያለ እረፍት ከዘራንባት ፍሬ አትሰጥምና፡፡
በተጨማሪም በዚህ ሳምንት ቅዱስ ኾኖ ቅዱሳን ኹኑ ብሎ ያስተማረው የጌታችን ትምህርት የሚታሰብበት ሳምንትም ነው፡፡

፨ የዕለተ ሰንበት ክብር፤
በብሉይ ኪዳን፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ፈጥሮ ከስራው ኹሉ አርፎበታል፡፡ ዘፍ 2፥3፣ ዘጸ. 20፥8
በሐዲስ ኪዳን፤ ጌታችን የተጸነሰባት፣ ትንሣኤውን የገለጠባት፣ ለሐዋርያት ጸጋ መንፈስ ቅድስ የሰጠባት፣ ዳግመኛ ለፍርድ የሚመጣባት....ወዘተ ናት፡፡ በአጠቃላይ ታላላቅ ሥራዎችን የሰራበት በመሆኗ ከሌሎች ቀናት ለይተን እናከብራታለን፡፡
ከምጽአት በኋላ ሌሎች ቀናት ሲያልፉ ዕለተ ሰንበት ባለማለፏ ለዘለዓለም ጸንታ በመኖሯ ነው፡፡ /ድርሳነ ሰንበት/ ምዕ 18፥3-7 በዕለተ ምጽዓት ከማያልፉ ነገሮች መካከል ቃሉ፣ ዕለተ ሰንበት፣ የሰው ልጅ ናቸው፡፡

  ዛሬ ዛሬ የኀጢአት ሥራ ኹሉ ቀን ተለይቶ የሚፈጸመው (ዝሙት፣ ሴሰኝነቱ፣ መዳራቱ፣ ዘፈኑ) ወዘተ በዚች ቅድስት ዕለት ነው፡፡ ‹‹ይህን ኀጢአት ቅድስት በምትኾን በእለተ ሰንበት፣ በሰሞነ ሕማማት፣ የሚፈታም ወዮለት›› ይላል፡፡ /መጽሐፈ ፍትሐ ነገሥት/፤ የባልና ሚስት ሩካቤ ኃጢአት ባይሆንም በማይገባ ወቅት ይልቁንም በዕለተ ስንበት በሰሞነ ሕማማት በረቡዕና ዐርብ ከተፈጸመ ኃጢአት ነው፡፡

   ኢሳ 58፥13-14 ‹‹ፈቃድህን በተቀደሰው ቀን ከማድረግ እግርህን በሰንበት ብትመልስ፣ የሰንበትንም ደስታ እግዚአብሔር የቀደሰው ክቡር ብትለው፣ የገዛ መንገድህን ከማግኘት ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፣ በዚህ ጊዜ በእግዚአብሔር አፍ ተናግሯልና››
  ሮሜ 14፡16 ‹‹ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል›› በማክበራችን ከእግዚአብሔር የምንቀበለው ዘላለማዊ ዋጋ ክብር አለና፡፡ ባለ ማክበራችን ደግሞ ቅጣት ጉዳት አለና ነው፡፡ ሰንበትን በሚገባ ለማክበር ቸሩ አምላክ ይርዳን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
19👍2
እንኳን ለእመቤታችን ኪዳነ ምሕረት ዓመታዊ ክብረ በዓል (ቃል ኪዳን ለተቀበለችበት) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፡፡
ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ፤
ፈለገ እሳት ወደይን እምአስጠመ ኵሎ፡፡
(ድንግል ሆይ ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የሲኦል እሳት ባሰጠመን ነበር፡፡)
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሲዖልን ካየች በኋላ ስለኃጥአን እጅግ እያዘነች ኖረች የካቲት አሥራ ስድስት ቀንም በጎልጎታ ቦታ ቆማ ወደ ልጇ እንዲህ ብላ ለመነች፡፡

ጸሎትና ልመናዬን ስማኝ ቃሌንም አድምጥ እኔ እናትህ አገልጋይህ የምለምንህን ይህ ነው፡፡ መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ፣ አብያተ ክርስቲያኔን ለሚሠሩ፣ ወይም ለታረዙ ለሚያለብሱ፣ ለተራቡ ለሚያጠግቡ፣ የተጠማውንም የሚያጠጡ(በስሜ ለድሆችና ለችግረኞች ቀዝቃዛ ውኃ ለሚሰጡ) ፣ የታመመውንም የሚጎበኝ፣ ያዘነውንም የሚያረጋጉ፣ የተከዘውንም ደስ የሚያሰኙ ወይም ምስጋናዬን ለሚጽፉ፣ ልጆቹንም በስሜ ለሚሰይም፣ በበዓሌም ቀን በማኅሌት ለሚያመሰግን አቤቱ በዓይን ያልታየውን በጆሮ ያልተሰማውን በጎ ዋጋ ስጣቸው፡፡ በአማላጅነቴም የሚተማመኑትን ሁሉ ከሲዖል ነፃ አድርጋቸው ከአንተ ጋር የደረሰብኝን ረሃብና ጥማቱን መከራውን ሁሉ አስብ አለችው፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዳልሽው ይሁንልሽ የሰጠሁሽን ቃልኪዳን እንዳይታበይ በራሴ በባሕርይ አባቴ በአብ በባሕርይ ሕይወቴ በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣት፡፡

#ሥርዐተ_ማኅሌት_ዘየካቲት_16#በዓለ_ኪዳነ_ምሕረት፡፡
በሃገራችን በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የሚቆመው፤ የ3ት ዐበይት አድባራት አብነት ነው፡፡ እነዚህም፤
1ኛ) የላይ ቤት፤ የደብረ መድኀኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት
2ኛ) የታች ቤት አብነት፤ የደብረ ኃይል ወደብረ ጥበብ በዓታ
3ኛ) የደፈጫ ኪዳነ ምሕረት አብነት ናቸው፡፡
እኛም ከላይ ከተጠቀሱት ውስጥ የዐቢየ እግዚእንና የበዓታን ይትበሃል አንድ ላይ በቅደም ተከተል አድረገን አዘጋጅተንላችኋል፤ የደፈጫ ከላይ ከተጠቀሱት ከ2ቱ በጥቂት ቀለም ብቻ የሚለይ በመኾኑ አላካተትነውም፡፡ ስለዚህ እንደ የደብራችሁ ይተበሃል የላይ ቤት ከኾነ ‹‹ዘዐቢየ እግዚእ›› የሚለውን፤ የታች ቤት ከኾነ ‹‹ዘበዓታ) የሚለውን እንድትጠቀሙ እናሳስባልን፡፡
መልካም ማኅሌት፡፡

/በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/

• Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool
• Telegram 👉 t.me/finotehiwott

• Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot 
• YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958
16👍2